uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union

Kanalga Telegram’da o‘tish

This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.

Ko'proq ko'rsatish
4 431
Obunachilar
-124 soatlar
-147 kun
-8630 kun
Postlar arxiv
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሙሐመድ! @EHEMSU    @EHEMSU @EHEMSU

በአንድ ወቅት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የነበረው ሞሼ ዳያን ስለ ሀገሩ እቅድ ለአንድ ጋዜጣ ሲናገር አይሁዶች "ሚስጢር አወጣህ!" ብለው ተቆጡ:: እርሱም "አይዟችሁ አትስጉ! አረቦች (ሙስሊሞች) ማንበብ አይወዱም! ንባብ ሞታቸው ነው! ያልኩትንም አያነቡትም!" ሲል በንቄት መለሰ::   የኢቅረዕ ትውልድ ከዚህ ደርሷል:: ሙስሊም ሆኖ ከትምህርት ከንባብ እና ከእውቀት ህይዎቱን ሙሉ ያልተገናኘ እልፍ አዕላፍ ነው:: በዙሪያው እየተካሄዱ ስላሉት ጉዳዮች ምንም መረጃ የሌለው ሙስሊም ብዙሃኑ ነው:: እንደ አጠቃላ የንባብ ችቦ ከኢቅረዕ ትውልድ ውስጥ ጠፍቷል:: እናንብብ - ወደነበርንበት እንመለስ! ወደ ኢቅረዕ!!! @EHEMSU   @EHEMSU  @EHEMSU @EHEMSU   @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU    @EHEMSU @EHEMSU

"አሁን ባለው ተጨባጭ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለው የሙስሊም ተማሪ ቁጥር በመጀመሪያ ዲግሪ ከ14% አይበልጥም:: ሁለተኛ ዲግሪ (ማስትሬት) ከ2% አይዘልም:: ሶስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) 1% ይገመታል::" ይላል በኢትዮጵያ 2010 ዓ.ል ላይ እንደተሰራ የተጠቀሰ ጥናት::    ከእነዚህ ምሁራንስ ኢስላምን ከዱንያው በማስቀደም ስለ ኢስላም የሚታገሉ: ሙስሊሙ መብቱ ተጠብቆለት እንደ ኢትዮጵያዊ ማግኘት ያለበትን አጊኝቶ እንዲኖር የሚታገሉት ምን ያክሉ ይሆኑ? ጥቂቶቹ እንደሚሆኑ አያጠራጥርም:: ያም ሆኖ ይህ እንደ ሀገር ማግኘት ያለብንን ለማግኘት በቁጥራችን ልክ መማር: ማጥናት: መመራመርና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ብሎም ለመላው ኢትዮጵያዊ ማበርከት ያለብንን ማበርከት ግድ ነው:: ሙስሊምም ተማሪም የሆነ ትውልድ ያስፈልጋል:: @EHEMSU   @EHEMSU  @EHEMSU @EHEMSU   @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU    @EHEMSU @EHEMSU

እያንዳንዱ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ያለፈ ታሪኩን በጥሞና ቢፈትሽ ስለ መብቱ መጣስ ስለ ህልውናው መገፋት ከትምህርት ስለመራቁ መደራጀት ስለመነፈጉ ወዘተ ... በርካታ አሳዛኝና የሚቆጩ እውነታዎች ላይ ሊደርስ ይችላል::   ያ ታሪክ ሆኗል:: ዛሬ የምንሰራው በታሪክነት ለነገው ትውልድ ይተላለፋል::    የነገው ትውልድ ካለንበት ሁኔታ አንፃር ምን እንደሰራን ይገመግማል:: ከዚያ የከፋው ግን በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ዘንድ ከጥያቄ አለመራቃችን ነው:: ይህ ከመሆኑ በፊት "ካለፈው ጭቆና አንፃር ዛሬስ ቢሆን ሙስሊሙ ለተሻለ ሁኔታ እየሰራ ነውን?" ብለን እንጠይቅ:: "በንቃትና በትጋት ራሱን እየገመገመ ከተሻለ ጉዞ ላይ ነውን?" ብለንም እናጢን:: ምክንያቱም ትላንት ትምህርት ሆኖ ለዛሬ ልውጥ እርሾነት የማይውል ከሆነ ታሪኩ መወራቱ ብቻ ጥቅም አልባ ነውና:: @EHEMSU   @EHEMSU  @EHEMSU @EHEMSU   @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU    @EHEMSU @EHEMSU

የኢትዮጵያ  ከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ሙስሊም  ተማሪዎች  ህብረት  ዓላማ ! 📌 በከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ውስጥ  ያሉ  ሙስሊም  ተማሪዎች  በእምነታቸው  ፀንተው፤  አንድነታቸውን ጠብቀው  እና  አስጠብቀው  እንዲኖሩ  ማድረግ 📌 በሁሉም  ዩኒቨርስቲ  ያሉ  ሙስሊም  ተማሪዎች  በእምነታቸው  ሳቢያ  የሚመጣን  የመብት  ጥሰት  በአንድ  ላይ ሆነው  መፍትሔ  እንዲያበጁ  ማድረግ 📌 የዩኒቨርስቲ  ሙስሊም  ተማሪዎች  በማንኛውም  ጉዳይ  እራሳቸውን  እንዲችሉ  እንዲሁም  በአካባቢያቸው  ላለ ሙስሊም  ማህበረሰብ  እገዛ  እንዲያደርጉ  ማድረግ 📌 በከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ሙስሊም  ተማሪዎች  ላይ  ጫና  ሊያሳድሩ  የሚችሉ  ማናቸውንም  ህጋዊ፣ ፖሊቲካዊ፣  እንዲሁም  ቢሮክሪያሳዊ  ማነቆዎችን  ለማስወገድ  መጣር፤  እንዲሁም  የሙስሊም  ተማሪዎችን ሃይማኖታዊ  ነጻነት  ሊገድቡ  የሚችሉ  ማናቸውንም  ህጎች  እና  ደንቦች  ከሚመለከታቸው  አካላት  ጋር  በመሆን ለመፍታት  መጣር ምንጭ:- የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት መተዳደሪየ ደንብ (አንቀፅ 7) @EHEMSU  @EHEMSU @EHEMSU   @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU    @EHEMSU @EHEMSU

ይህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው:: በቻናሉ ከዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች እና የህብረቱ የዕለት ተዕለት ክዋኔዎች ይቀርባሉ:: በአላህ ፍቃድ እና እርዳታ ከዚያም ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በሚኖር መናበብና መተጋገዝ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች መብታቸው ተከብሮ ይማሩ ዘንድ እንተጋለን:: መረጃዎች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ይደርሱ ዘንድ ቻናሉን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ:: @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU