cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Ethiopian Legal insight

This is a legal software for all legal practitioners

Ko'proq ko'rsatish
Efiopiya13 072Til belgilanmaganQonun6 804
Reklama postlari
237
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+87 kunlar
+2030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
ተከሳሽ ከሞተ በምን ያህል ጊዜ ነው ማመልከቻ የሚቀርበው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 49(2) ላይ እንደተመለከተው ከሳሽ ከሞተ ክሱን ለመቀጠል መብት አለን የሚሉ ወገኖች ዋናው ከሳሽ በሞተ በአንድ ዓመት ውስጥ ክሱ ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ እንደሚሆን የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን በቁጥር 50 ላይ ተከሳሽ ሲሞት መብት አለን የሚሉ ወገኖች ክሱን ለማስቀጠል በስንት ጊዜ ማመልከት እንዳለባቸው አልተመለከተም ሆኖም የድንጋጌው እንግሊዝኛ ከአማርኛው በተለየ አራት ንዑስ አንቀፃት ያሉት ሲሆን በንዑስ አንቀፅ 3 ላይ በአማርኛው ድንጋጌ የሌለ ‹‹where within one year from the death of the defendant no application is made under sub-art.(1),the suit shall abate as against the deceased.›› ተከሳሽ በሞተ በአንድ ዓመት ውስጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 50(1) መሰረት አቤቱታ ካልቀረበ ክሱ ውድቅ ይደረጋል ሲል ደንግጓል፡፡በአማርኛ ቅጂ ላይ ያለው አገላለፅ በእንግሊዘኛው ላይ ያለውን ሀሳብ በትክክል አመላስተላለፉን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡የትርጉም ልዩነት ሲኖር የአማርኛውን ትርጉም መውሰድ ተመራጭ ቢሆንም ነገር ግን የአማርኛው ድንጋጌ በእንግሊዝኛው ድንጋጌ የማይገኝ ጭራስ ንዑስ አንቀፅ የሌለው መሆኑ ሲታይ ጉዳዩ አከራከሪ ሆኖ ሲቀርብ በእንግሊዝኛው ንዑስ አንቀፅ በመጠቀም ለጉዳዩ እልባት መስጠት ይገባል፡፡ #share #lawyer #legalsupport #legaladvice www.ethiopianlegalinsight.com https://t.me/Ethiopianlegalinsight
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
00:10
Video unavailableShow in Telegram
Digital law library and legal software, developed for the first time in Ethiopia, provides quality service to judges, prosecutors, lawyers, advocates, law teachers, students, businessmen and others.
Hammasini ko'rsatish...
2.17 MB
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኪራይ ውል እና የፎርም(በፅሁፍ)መስፈርት በውል ህግ ጠቅላላ ክፍል አንቀፅ 1719(2) እንደተገለፀው ህጉ በግልፅ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ አንድ ልዩ የሆነ የሚጠበቅ አፃፃፍ(ፎርም) እንዲኖር እንደሚያስፈልግ ተደንግጓል፡፡ከእነዚህም መካከል በአንቀፅ 1723(1) ላይ እንደተገለፀው ባለሀብትነት(ownership)፣የአላባ ጥቅም(usufruct)፣መያዣ(mortgage) እና ሌላ አገልግሎት(servitude) የሚደረጉ ውሎች በፅሁፍ መደረግ ያለባቸው ሲሆን በተጨማሪም በአንቀፅ 1725 መሠረት ለብዙ ዘመን የሚቆዩ ውሎች ማለትም የዋስትና ውሎች፣የኢንሹራንስ ውሎች እና ይህ አፃፃፍ(ፎርም) በህግ ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ሌሎች ውሎች በፅሁፍ መሰራት ያለባቸው ሲሆኑ የኪራይ ውል ግን የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት አልተመለከተም፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 7 በሰ/መ/ቁ 25938 ላይ ህጉ የኪራይ ውልን በፅሁፍ እንዲሆን የሚያዝ አስገዳጅ ድንጋጌ ባላስቀመጠበትና ተዋዋዮች ውሉ በፅሁፍ እንዲሆን የተስማሙ መሆናቸው ባልተረጋገጠበት ሁኔታ እንዲሁም የኪራይ ውልን የሚመለከተው የፍ/ህ/ቁ 2893(1) የኪራይ ውል መከናወን ጀምሮ እንደሆነ የውሉን መኖር በምስክሮች ወይም በግምት አስተያየት ማስረዳት እንደሚቻል ተደንግጎ ባለበት ሁኔታ ውሉ የህጉን ፎርማሊቲ ያላሟላ ስለሆነ ፈራሽ ነው ሲል የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ #share #lawyer #legalsupport #legaladvice www.ethiopianlegalinsight.com https://t.me/Ethiopianlegalinsight
Hammasini ko'rsatish...
👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ያለንግድ ፈቃድ ደላልነት ሥራ መሥራት ይቻላል? በተለምዶ በሀገራችን በርካታ ሰዎች የደላልነት ሥራን ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲሰሩ እና መተዳደሪያቸው አድርገው የሚኖሩ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ለመሆኑ ህጋችን ስለደላልነት ምን ይላል የሚለውን ስናይ በኢፌድሪ ንግድ ህግ አንቀፅ 54(1) ደላሎች ማለት ውል የሚዋዋሉ ሰዎችን በተለይም እንደ ሽያጭ፣ኪራይ፣ኢንሹራንስ፣የማመላለሻ ውል እንደዚህ ያሉትን ውሎች የሚዋዋሉ ሰዎችን ፈልገው የሚያገናኙና የሚያዋውሉ ራሱን የቻለ የሙያ ተግባራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት የሚሰሩ ሰዎች ወይም ይህንኑ የደላልነት ሥራ የሚሠራ የንግድ የንግድ ማህበር ነው፡፡እንዲሁም በዚሁ ንግድ ህጋች አንቀፅ 5(34) ላይ የንግድ ወኪል፣የኮሚሽን ወኪል፣የንግድ ደላላ የአክሲዮን ደላላ በመሆን ስራ የሚሰሩ ማንኛውንም ዓይነት የሰዎችን የአገናኝነት ሥራ የሚሰሩ ሰዎች ነጋዴዎች እንደሆኑ ተደንግጓል፡፡ ታዲያ የደላልነት ንግድ ፈቃድ ሳይኖረው ስራውን የሠራ ሰው ክፍያ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 25 በሰ/መ/ቁ 204199 ይህንን ስራ የሚሰራው ሰው የህግ ጥበቃ ሊያገኝ የሚችለው እንደማንኛውም ሰው አግባብ ባለው ህግ በነጋዴነት ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አውጥቶ መሥራት ሲችል ነው፡፡የደላልነት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው የደላልነት ሥራ ሰርቻለው የአበል ክፍያ ይከፈልኝ ማለት አይቻልም ሲል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ #share #lawyer #legalsupport #legaladvice www.ethiopianlegalinsight.com https://t.me/Ethiopianlegalinsight
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የመኪና ሽያጭ መኖሩን በምስክር ወይስ በፅሁፍ እናረጋግጥ? የማንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በፅሁፍ መሆን እንዳለበት በፍ/ህ/ቁ 1723(1) የተደነገገ ሲሆን መኪና ደግሞ እንደሚታወቀው ተንቀሳቃሽ ንብረት ቢሆንም ልዩ ተንቀሳቃሽ እንደመሆኑ መጠን እንደማንኛውም ተንቀሳቃሽ ንብረት በምስክር ማረጋገጥ ይቻላልን?የሚለውን ስንመለከት በፍ/ህ/ቁ 1186(1) ግዙፍነት ያላቸው የተንቀሳቃሽ ንብረቶች ባለሀብትነት ንብረቱን በመግዛት ወይም በሌላ አኳኋን ያገኘው ወይም በኑዛዙ የተሰጠው ሰው ንብረቱን እጅ ባደረገው ጊዜ የተላለፈ ይሆናል ሲል የሚደነግግ ሲሆን በንዑስ አንቀፅ (2) ስር ደግሞ ልዩ የሆኑ አንዳንድ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው በማለት ለአንዳንድ ልዩ ተንቀሳቃሾች የተለየ ጥበቃ ያደርጋል መኪና ደግሞ ልዩ ተንቀሳቃሽ በመሆኑ መኪናን በሚመለከት የወጡ አዋጆች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ስለተሽከርካሪ መለያ መመርመሪያና መመዝገቢያ የወጣ አዋጅ ቁጥር 681/2002 አንቀፅ 6(3)(4) አንድ ተሽከርካሪ በቀድሞ ባለንብረት በሽያጭ ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑ ተረጋግጦ የባለሀብትንት ዝውውር ሊፈፀም የሚችለው ውሉ በፅሁፍ በተደረገ ጊዜ መሆኑን ይደነግጋል፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 14 በሰ/መ/ቁ 81406 ላይ የሀዋላ ሰነድ በማቅረብ የመኪና ሽያጭ ተደርጓል በማለት ዳኝነት መጠየቅ አግባብነት እንደሌለው እና አግባብነት ያለው ማስረጃ የሽያጭ ውሉ የተደረገበትን ሰነድ በማቅረብ እንደሆነ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ #share #lawyer #legalsupport #legaladvice www.ethiopianlegalinsight.com https://t.me/Ethiopianlegalinsight
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ(res judicata)ጉዳይ በተከራካሪ ብቻ? ወይስ በፍርድ ቤትም በራሱ አነሳሽነት ? ጭምር መነሳት ያለበት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በኮመን ሎው የህግ ሥርዓት አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዳይ(Res Judicata) በተከራካሪ እንዲቀርብ ወይም እንዲነሳ የተቀመጠ መከላከያ(Affirmative Defence) ነው፡፡ፍርድ ቤቶች ወይም ዳኞች ይህን መከላከያ በራሳቸው አነሳሽነት የማያነሱት ሲሆን ይህም የሚያሳየው ተከራካሪዎች በድጋሜ ለመከራከር ፍቃደኞች እሰከሆኑ ድረስ እና ይህን መከራከሪያ ለማንሳት የተዉ ከሆነ መንግስት ምንም አይነት ፍላጎት አይኖረውም፡፡በሌላ በኩል በአህጉረ አውሮፓ(Continental legal system) ፍርድ ቤቶች ወይም ዳኞች በራሳቸው አነሳሽነት አስቀድሞ በፍርድ ያለቀን ጉዳይ(Res Judicata) ከግምት የሚያስገቡት መከላከያ ነው፡፡የእኛስ የህግ ሥርዓት ? አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዳይ(Res Judicata) በፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ህግ አንቀፅ 244(2) ከ ሀ-ረ ከተዘረዘሩት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች አንዱ ሲሆን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 3 ላይ መቅረብ ከሚገባቸው መቃወሚያዎች ውስጥ ሳይቀርቡ የቀሩት ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የማያሰናክሉ ከሆኑ ባለጉዳዩ ራሱ ሆን ብሎ ለማቅረብ ባለመፈለጉ እንደተዋቸው ይቆጠራሉ ብሎ ህግ አውጪው የደነገገ ሲሆን የትኞቹ መቃወሚያዎች ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክሉ እንደሆኑ ሮበርት አለን ሴድለር ሲዘረዝሯቸው ከዚህ በልዩነት(exception) የሚወድቁት 4 መቃወሚያዎች ናቸው ይላሉ እነዚህም የፍርድ ቤት የስረ ነገር ሥልጣን(የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 9) ፣በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ክሶች(Pendency)(የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 8 ፣ችሎታ የሌላቸው ተከራካሪዎች፣የማይነጣጠሉ ተከራካሪ ወገኖችን አለማጣመር (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 34(2)) ናቸው፡፡ በእነዚህ 4 ጉዳዮች ላይ ፍ/ቤቶች ትክክለኛ(valid) ፍርድ ለመስጠት ስለማይችሉ ችሎቱ በራሱ አነሳሽነት መቃወሚያውን ሊያነሳው ሲችል በሌላ በኩል የፍ/ሥ/ሥ/ህቁ 5 ን ወይም አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ጉዳይ ነው የሚለውን መከራከሪያ ተከራካሪ ወገኖች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ካላነሱት እንደተዉት እንደሚቆጠር ወይም ይህ ጉዳይ ትክክለኛ ፍርድ ከመስጠት የሚያግድ አይደለም ይሉናል፡፡ነገር ግን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትበፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ንብረታቸውንእንዲካፈሉ በተሰጠ ውሳኔ ቅር የተሰኘችው የሰበር አመልካች ከዚህ በፊት በሸሪዓ ፍ/ቤት የፍቺ ውሳኔም ሆነ የንብረት ክፍፍል ጉዳይ የተቋጨ ሆኖ እያለ ሌላ ክስ መቅረቡ ያለአግባብ ነው፡፡በሸሪዓ ፍ/ቤት በተሰጠው ውሳኔ የቤት ቁሳቁስ በተመለከተ በሰፈር ሽማግሌ ይካፈሉ ሌላ ንብረት ካለ ደግሞ ከመደበኛ ፍ/ቤት ይጠይቁ በማለት የድሬደዋ የመጀመሪያ ደረጃ የሸሪዓ ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሰበር ሰሚውበህግ ስልጣን በተሰጠው የሸሪዓ ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ተከራክረውበት በፍርድ ያለቀን ጉዳይ ተጠሪ በውሳኔው ቅሬታ እንኳ ቢኖረው በዚያው በሸሪዓ ፍ/ቤት መዋቀር ቅሬታውን ለሚመለከተው የይግባኝ ወይም የቅሬታ ሰሚ ክፍል ማቅረብ ሲገባቸው እንደ አዲስ ጉዳይ በመደበኛ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5(1) መሰረት ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡ የበታች ፍ/ቤቶችም የአሁን ተጠሪ ያቀረበው ክስ በሌለበት የተሰማ ቢሆንም በሂደት ግን ጉዳዩ ቀድሞ በውሳኔ ያለቀ መሆኑን እንደተረዱ የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባቸው በቀረበው ክስ መሰረት ውሳኔ መስጠታቸው አግባብነት የሌለውና መስረታዊ የህግ ስህተት ተፈፀመበት ነው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ 58119 ቅፅ 13 https://t.me/Ethiopianlegalinsight #share
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian Legal insight

This is a legal software for all legal practitioners

👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 3
በድጋሜ ዳኝነት እና የይግባኝ መብት ፍርዱን በሰጠው ፍርድ ቤት ዳኝነት በድጋሜ ከሚታይባቸው ሶስት ሁኔታዎች አንዱ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 6 መሰረት አዲስ በተገኘ ማስረጃ አማካኝነት ፍርዱን በሰጠው ፍ/ቤት በድጋሜ ዳኝነት የሚቀርብበት ሁኔታ አንዱ ነው፡፡ሌሎቹ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 207-209 መሰረት ከሥነ-ሥርዓት ውጪ የሆነ ጉዳይ ሲቀርብ እና በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ ሲቀርብ ነው፡፡በዚህም መሰረት ዳኝነት በድጋሜ እንዲታይለት ምክንያቱን ገልፆ ማመልከቻ ያቀረበ ሰው ዳኝነቱ እንደገና ሊታይ ይገባዋል ወይም አይገባውም ሲል ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይቻል ተደንገጓል፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 9 በሰ/መ/ቁ 42871 ላይ አንድ ጉዳይ በድጋሜ ዳኝነት ሲቀርብ ዳኝነቱ በድጋሜ ሊታይ አይገባውም ወይም ይገባል ሲል ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሲሰጥ ይግባኝ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 6 (3) እና(4) ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ በግልፅ ያሳያሉ በዚህም መሰረት ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም ሆነ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሲታይ ህጋዊ ነው፡፡ የአመልካች ነገረ ፈጅ አቤቱታውን ሊያቀርብ ይገባ የነበረው ስርዓቱን ጠብቀው ለሰበር ሰሚ ችሎት እንጂ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አይደለም ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ነገር ግን ማቅረብ የሚችለው ለሰበር ሰሚው ፍ/ቤት ከሆነ በድጋሜ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርብ የሚከለክለው ህግ ይኖርን? የሚለውን ስንለመከት በድጋሜ ከማቅረብ የሚከለክለው ህግ ያለ አይመስልም ምክንያቱም በድጋሜ ዳኝነት እንዲታይለት ምክንያቱን አቅርቦ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገበት ሰው ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ማቅረቡ ለየትኛው ፍ/ቤት ማቅረብ እንዳለበት ባለማወቁ የተነሳ ሲሆን በተጨማሪም በከፊልም ቢሆን ፍርድ ቤቱ በስህተት ማከራከሩ መብቱን ማጣት የሌለበት ተከራካሪ ስልጣን ባለው የሰበር ሰሚ ፍ/ቤት መብቱን እንዲጠይቅ እድል መስጠት ለሰበር ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ ካላገደው በቀር ተገቢ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል ። @Ethiopianlegalinsight
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian Legal insight

This is a legal software for all legal practitioners

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
1
Photo unavailableShow in Telegram
ይቅርታ የጥፋተኝነትን ውሳኔ ይሽራልን? አንድ በወንጀል የተከሰሰ ሰው በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ ከተባለ በኃላ በወ/ህ/ቁ 84 መሠረት ከሳሽ ዐ/ህግ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን ካለው እንዲያቀረብ ፍ/ቤቱ የሚጠይቀው ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሠረት ዐ/ህግ ከሚያቀርባቸው የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች መካከል ደግሞ በአንቀፅ 84(1)(ሐ) መሠረት የወንጀለኛው የቀድሞ ጥፋተኝነቱ አንዱ ነው፡፡ ሆኖም አንድ ተከሳሽ(ወንጀለኛ) አስቀድሞ በሌላ ወንጀል የቅጣት ውሳኔ ከተሰጠበት በኃላ ሥልጣን በተሰጠው አካል ቅጣቱ በይቅርታ ቢቀር የቀድሞ ጥፋተኝነቱን ያስቀረዋለልን? የሚለውን ስናይ በወንጀል ህግ አንቀፅ 229(2) ይቅርታ ሲሰጥ በተቀጪው ላይ የተወሰነው ፍርድ ከሚያስከትለው ውጤት ጋር በወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ ይኖራል ሲል ይደነግጋል፡፡የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትምበቅፅ 10 በሰ/መ/ቁ 41248 ላይ በይቅርታ ከተፈታው በኃላ እንደሪከርድ ተወስዶ ቅጣቱ ከብዶ መወሰኑ አግባብነት የለውም ሲል የሰበር አመልካች ያቀረበለትን አቤቱታ ተመልከቶ ይቅርታ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዳልነበረ የሚያስቆጥር አይደለም፡፡ለአመልካች የተሰጠው ይቅርታ እንጂ ምህረት ያለመሆኑን ያላገናዘበ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በወ/ህ/ቁ 230(2) እንደተገለፀው የጥፋተኝነትን ታሪክ(ሪኮርድ) እንዳልነበር የሚያደርገው ምህረት እንጂ ይቅርታ አለመሆኑን ነው፡፡ #share www.ethiopianlegalinsight.com
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.