cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይገልፃሉ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 677
Obunachilar
+1524 soatlar
+447 kunlar
+12830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡ ይህን አልበላሁም ወይም ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ። ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣ ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣ በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ስማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤ ትርጉም በሌለው በባዶ የፆም ሥርአት ራስህን አታስገዛ። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Hammasini ko'rsatish...
👍 8❤‍🔥 6🤝 4
ከሀጢአት ሽሽ ወደራስህም ጠልቀህ ግባ በነፍስህ ውስጥ ወደ እግዝአብሔር መንግስት የሚያወጣውን መስላል ታገኛለህ። ቅዱስ ይስሀቅ ዘሶርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለእኛ ንስሀ ለገባነው ክቡር  የሆነ ሰማያዊ አክሊልን ታቀዳጀን ዘንድ የእሾህ አክሊልን ደፋህ። ቅዱስ በርተሎሚዎስ https://t.me/yekidusantarik1
Hammasini ko'rsatish...
🙏 10👍 6🤝 1
ንስሀ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዝአብሔር እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው።አቡነ ሺኖዳ በየጊዜው ሀጢአትን የማታስብን ና ንስሀ የማትገባ ከሆነ ያን ቀን እንደኖርካት አትቁጠር።ቅዱስ ይስሀቅ
Hammasini ko'rsatish...
ብሂለ አበው

በዚሁ ቻናል የቤተ ክርስቲያን ብሂለ አበው መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይቀርብበታል።

👍 12❤‍🔥 2🙏 1
በትምህርታቸው ትፅናና ዘንድ እየሄድክ ቅዱሳኑን ጠይቅ ከቅዱሳኑ ጋር የሚውል ሰው ቅዱስ ይሆናል። ሃይማኖት አበው ስምአት 125
Hammasini ko'rsatish...
🙏 20
የማይቆጣጠሩትን ምላስ ያህል መጥፎ ፆር የለም። እርሷ የፈተና ሁሉ እናት ናት አባ አጋቶን https://t.me/yekidusantarik1
Hammasini ko'rsatish...
👍 14🙏 6
Photo unavailableShow in Telegram
#ቅዱስ_ሚናስ ቅዱስ ሚናስ በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው። ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ህዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈ ሲሆን ሰኔ 15 ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው። በአንድ ወቅት 18 ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር  ወደ ቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዟቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ። የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። ሰውዬውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው። ከዚያ "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው። አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!
Hammasini ko'rsatish...
❤‍🔥 19🙏 12 4
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡ ("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
Hammasini ko'rsatish...
🙏 10
መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ትልቅ ትዕቢት የለም ቅዱስ ባስልዮስ
Hammasini ko'rsatish...
22👏 1
ዛሬ ሰኔ 12 የአፎምያ እረዳት ቅዱስ ሚካኤል ነዉ አፎምያን የረዳት መላእክት እኛንም ካለንበት ችግር ያዉጣን ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን
Hammasini ko'rsatish...
🙏 29 6👏 4👍 2
ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለፀጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው ሲል ጠየቀ ሰዎቹም ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ። እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ዐርባ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል አሉት። ያም ባለፀጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቆጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።
Hammasini ko'rsatish...
👍 9
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.