cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
237
Obunachilar
+124 soatlar
+27 kunlar
+2230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

@ ስለ ቅዳሴ 06 @ .......#ክብረ #ቅደሴ........ ሀሌ ሉያ ማለት ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማለት ነው። አንድም ሀሌ ሉያ ማለት ስብሐት ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል ማለት ነው።በቅዳሴ በማኅሌት ብዙ ጊዜ የምንሰማው ቃል ስለሆነ ብናውቀው መልካም ነው ብየ አስባለሁ።አንድ ባሕታዊ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከምስጋናሽ ሁሉ ማንን ትወጃለሽ ብሎ ጠየቃት።እርሷም ልጄ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረ ዳዊትንና አቡነ ዘበሰማያትን የሚደግምን  ሰው በጣም እንደሚወደው ሁሉ እኔም ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን የሚጸልይ ሰውን እወደዋለሁ ከልጄ ከወዳጄ ከኢየሱስ ክርስቶስ አማልጄም ጸጋ በረከት ረድኤት አሰጠዋለሁ ብለዋለች።                          ። ቅዳሴ የሚቀድስ ሰው እግዚአብሔርን የሚቀድስ አይምሰለው ራሱ ይቀደሳል እንጂ እንዲል።እግዚአብሔርን ብናመሰግን ለእግዚአብሔር የሚጨመርለት ምንም ነገር የለም። እኛ ግን በማመስገናችን የምናገኘው ታላቅ ጥቅም አለን። ምስጋናን ወይም ቅዳሴን ሊቃውንቱ የመላእክት ምግብ ይሉታል።ወኅብስተ መላእክቲሁ በልኡ እጓለ እመሕያው የሚለውንም።የመላእክትን እንጀራ ምስጋና ሰዎች ስቡሕ ውዱስ እያሉ አመሰገኑ ማለት ነው። ሁልጊዜም ቢሆን ንሥሓ እየገባን እያስቀደስን ልንቆርብ ይገባናል።በቅዳሴ ጊዜ ማውራት ውርውር ማለት እና እንደጠቅላላው ቤተክርስቲያን ውስጥ አለማዊ ነገር ልንነጋገር አይገባንም።በቅዳሴ መካከል ይጫወቱ የነበሩ ሕጻናትን እንኳ መልአክ እንደቀሰፋቸው መንፈሳውያት መዛግብት ያስረዳሉ። ስለዚህ ሕጻናትንም ሥርዓት እንዲማሩ እንዲያውቁ ልናስተምራቸው ይገባል።                           ። በነገራችን ላይ ከዚህ የተወሰነውን ነገር ነው የጻፍኩት ዝርዝር ጉዳዮችን እና ዋና ዋና ጉዳዮችን ለማየት የ14ቱ ቅዳሴያት መጽሐፍ አንድምታ የሚለውን መጽሐፍ ገዝታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።ከዚህ እንዳው ለማስተዋወቅ ያህል ነው እስከ ክፍል 6 የጻፍኩት እንጂ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገሮቹን ለማግኘት ሙሉውን መጽሐፍ እንድታነቡት እጋብዛለሁ። ። አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል። #በመምህር_በትረ_ማርያም 👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

@ ስለ ቅዳሴ 05 @ ©41 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ© በቅዳሴ ጊዜ እግዚኦታ 41 ጊዜ ነው። ይህ 41 የሆነበትም የራሱ ምሳሌ አለው።አዳም እጸ በለስን በልቶ ከገነት በተባረረ ጊዜ እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ እንዲምረኝ ብሎ ሱባኤ ገባ። ነገር ግን ሰይጣን ገብርኤልን ሳይሆን ገብርኤል ነኝ ብሎ ሱባኤ ይዘው ሳለ በ35ኛው ቀን ሱባኤውን ለማፍረስ መጣ። እግዚአብሔር ምሯችኋል ውጡ ብሎ የውሸት ስብከት ሰበካቸው።እነርሱም የእርሱን ቃል ሰምተው ከባሕር ወጡ።ከዚያ ብዙ መንገድ ከሄዱ በኋላ አወቃችሁኝ ወይ አላቸው። ገብርኤል ነኝ አላልከንም ወይ አሉት። አይደለሁም እኔ ሰይጣን ነኝ።አስቀድማችሁ የፈጣሪን ትእዛዝ ሻራችሁ ዛሬ ደግሞ ሱባኤ አቋረጣችሁ እንግዲህ እግዚአብሔር አይምራችሁም ብሎ ተስፋ አስቆራጭ ነገር ተናግሮ ድንጋይ አንስቶ ወረወረባቸው። ወተደብተረት ይእቲ እብን ይላል።ያች ድንጋይ ድንኳን ሆናቸው 3 ቀን ተቀመጡ።ከዚያ ከድንኳኗ ወጥቶ ሳለ አዳምን ሰይጣን በሞትና በሕይወት መካከል አድርጎ ደብድቦት ሄዷል።በዚያ አዳም 3 ቀን ተቀምጧል። ከላይ 3 ከዚህ 3 ስድስት ይሆናል።6 እና 35 ሲደመር 41 ይሆናል። ከዚያ አዳም ደሙን ለውሶ መሥዋእት አቀረበ። እግዚአብሔርም አዳም ሆይ በእሩቅ ብእሲ ደም አትድንም ከአሁን በኋላ ደምህን መሥዋእት እንዳታደርግ ብሎ ነግሮ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ተስፋ ሰጥቶታል። 41 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ የዚህ ምሳሌ ነው። ። ድርገት ሲወርድ መስገድ እጅ መንሳት ይገባል። ይኽውም በትንሳኤ ጊዜ ቅዱሳት አንስት ለክርስቶስ የመስገዳቸው ምሳሌ ነው።ከቁርባኑ በኋላ ዲያቆኑ አንድ ጊዜ ዞሮ ይገባል።ይኽውም ሐዋርያት ይህችን ዓለም ዞረው የማስተማራቸው ምሳሌ ነው።ቅዳሴው እንዳለቀ ካህኑ ሕዝቡን ካህናቱን በእጁ ይባርካቸዋል።ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕርገት ጊዜ ሐዋርያትን በአንብሮተ እድ የመሾሙ ምሳሌ ነው። ፍትሐት ዘወልድን እና ጸሎተ ንሥሓን ሲጸለይ (ሲደገም) መስገድ ይገባል። ። ምስባክ ዲያቆኑ 2 ጊዜ ሕዝቡ 3 ጊዜ ይላሉ።በአጠቃላይ 5 ይሆናል። ይህ አዳም የተፈረደበት የ5500 ዘመን ምሳሌ ነው።በስድስተኛው ካህኑ ወንጌል ይላል።ይህም በስድስተኛው ሺህ እግዚአብሔር አዳምን የማዳኑ ምሳሌ ነው።ወንጌል ማለት የምስራች ማለት ነው።በቅዳሴ ጊዜ መብራት ይብራ።ይልቁንም ወንጌል በሚባልበት ጊዜ አብዝተው ሊያበሩ ይገባል።መብራት መበራቱም ክርስቶስ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ያለው ቃል ምሳሌ ነው። በነገራችን ላይ ኪርያላይሶን በግእዝ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት ሲሆን በአማርኛ አቤቱ ይቅር በለን ማለት ነው። ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

@ ስለ ቅዳሴ 04 @ .......ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን....... ንኡሰ ክርስቲያን የሚላቸው የሃይማኖት እና የምግባር ተብለው ይከፈላሉ።የሃይማኖት የተባሉት ሳይጠመቁ እድሜያቸው ትልቅ የሆኑ ሰዎች ወደ ትክክለኛዋ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሲመጡ አዕማደ ቤተክርስቲያንን እየተማሩ እስከ 3 ዓመት ይቆያሉ። በዚህ በሦስት ዓመት ውስጥ ቅዳሴ እስከ ፍሬ ቅዳሴ ድረስ ይቆዩና ፍሬ ቅዳሴ ሲጀመር ንኡሰ ክርስቲያን የሆናችሁ ውጡ ይባሉና ይወጣሉ። ይኽውም በዚሁ በሦስቱ ዓመት ውስጥ ነው እንጂ ከተጠመቁ በኋላ አይደለም።ከፍሬ ቅዳሴ በፊትስ ለምን ይቆያሉ ቢሉ ከዚያ በፊት ያለው የቅዳሴ ክፍል በስፋት ትምህርት ያለበት ነው።እንዲማሩ ነው።ከፍሬ ቅዳሴ በኋላ ግን የተጠመቁት ብቻ የሚቀበሉት ቁርባን የሚፈተትበት ስለሆነ ሙሉ በሙሉ አምነው ተጠምቀው እስኪመጡ ድረስ አይቆዩም።                           ። ሁለተኛው ንኡሰ ክርስቲያን የሚባሉ የምግባር ናቸው።የተጠመቁት ምእመናን ኃጢኣታቸውን ለመምህረ ንሥሓቸው ነግረው ንሥሓ አባታቸው በቀኖና እስከዚህ ቀን ድረስ በበረሀ ሁናችሁ እስከዚህ ቀን ድረስ በአጸደ ቤተክርስቲያን ሆናችሁ እያስቀደሳችሁ ስትጨርሱ ከቤተክርስቲያን ገብታችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚባሉት ናቸው። በበደሉት በደል ምክንያት ለተወሰኑ እለታት በቀኖና ቤተክርስቲያን  እንዳይገቡ የሚከለከሉ ንኡሰ ክርስቲያን ይባላሉ።                               ። መጋረጃ ወይም መንጦላእት የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው። የቤተክርስቲያን ሦስቱ በሮች የሦስቱ ሥላሴ ምሳሌ ናቸው። ደጀ ሰላም የምትባለው በምዕራብ አቅጣጫ ከመግቢያ በር ላይ የምትገኝ ቤት ናት።ምሳሌነቷ የገነት ነው። ቀሳውስት ደጀሰላም ትንሽ ቆይተው ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ ቅዱሳንም እስከ እለተ ምጽአት ድረስ በገነት ቆይተው በኋላ በክብር ወደምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት የመግባታቸው ምሳሌ ነው።ሌላው በቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ የሚደረገው የሰጎን እንቁላል የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው።ምሳሌነቱም እንዲህ ነው።ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈሉ ድረስ አትለያቸውም። ምግቧን ለመፈለግ ስትሄድ እንኳ ባሏን ተክታ ነው። ለአንድ አፍታ ከእይታ ውጭ ካደረገቻቸው ግን እንቁላሉ ይበላሻል።ሰጎን የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው። እንቁላሎቹ የምእመናን ምሳሌ ናቸው። መንፈስ ቅዱስ እኛን ሁልጊዜም እንደሚጠብቀን ያስረዳናል። ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል..👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

👍 1
@ ስለ ቅዳሴ 03 @ .....ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ..... ዲያቆኑ በቅዳሴ መካከል ከሚላቸው አንዱ ነው። ምሥራቅ የማኅደረ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው።አንድም የጌታችንን ነገረ ምጽአቱን አስቡ ሲል ነው።በቅዳሴ ጊዜ ሌላ ዓለማዊ ሀሳብ ልናስብ አይገባም።ከመላእክቱ ጋር እግዚአብሔርን እያመሰገንን መሆኑን መዘንጋት የለብንም።በሥጋ ከቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነን በሀሳብ ግን ሌላ ቦታ ልንሆን አይገባም።ነገራተ እግዚአብሔርን በቅዳሴው ሰዓት የሚነበቡ የወንጌል እና የሐዲሳት እንዲሁም የመልእክተ ጳውሎስ ክፍላትን እንዲሁም አጠቃላይ ካህኑ ዲያቆኑ የሚለውን እኛም የምንመልሰውን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን። ለተመስጦ እንዲረዳን ግእዝ ቋንቋውን እንወቀው። እያንዳንዱ የሚደረገው ድርጊት ምሳሌ እና ምሥጢር ስላለው ያንን ጠይቀን ተምረን እንወቀው።                           ። ከቅዳሴ በፊት መሥዋእቱ የሚዘጋጅባት ቤት ቤተልሔም ትባላለች። ቤተልሔም ከዋናው ሕንጻ ቤተክርስቲያን በስተምሥራቅ የምትገኝ ስትሆን ምሳሌነቷ ክርስቶስ ለተወለደባት ቤተልሔም ነው። ከዚያ ከቤተልሔም ወደ መቅደስ ይሄዳል። መቅደስ የቀራንዮ ምሳሌ ነው። የቤተክርስቲያን ውስጠኛዋ ክፍል #መቅደስ ትባላለች። በቀራንዮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም እንደፈሰሰ ሁሉ። በዚች መቅደስም የክርስቶስ ሥጋ እና ደም የሚፈተትባት ናትና። ከዚያ ቀጥላ ያለችዋ መካከለኛዋ ክፍል እና ሥጋ ወደሙ የምንቀበልባት ደግሞ #ቅድስት ትባላለች። ሊቃውንት ማኅሌት የሚቆሙባት እና መጀመሪያ እንደገባን የምናገኛት ክፍል ደግሞ #ቅኔ_ማኅሌት ትባላለች።                               ። ከቅዳሴ በፊት ልዑካኑ እንዲሰበሰቡ የሚደወለው የተጋብኦ ደወል ክርስቶስ ይወርዳል ይወለዳል እያሉ ያስተማሩ የቅዱሳን ነቢያት ምሳሌ ነው።ኖኅ በቀን ሦስት ጊዜ ደወል ይደውል ነበር።ይኽውም ጠዋት ለጸሎት ተነሱ ለማለት፣ ከሰዓት ደግሞ የምሳ ሰዓት ደረሰ ለማለትና በሠርክ ደግሞ መሥዋእት ለማሳረግ ነበር። #የግብር ደወል ማለትም ገና ቅዳሴ ሲጀመር የሚደወለው ሲሆን የብሥራተ ገብርኤል ምሳሌ ነው። #የወንጌል ደወል የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት ምሳሌ ነው። #የእግዚኦታ ደወል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ምሳሌ ነው። #የድርገት ደወል የሐዋርያት የ፸፪ቱ አርድእት ስብከት ምሳሌ ነው።ምሳሌነቱ እያሰብን ልናስቀድስ ይገባናል።                            ። ጻኡ ንኡሰ ክርስቲያን የሚለው በምጽአት ጊዜ ጌታችን ኃጥዓንን ሑሩ እምኔየ የሚላቸው የመዓቱ ምሳሌ ነው።ወንጌል ከተነበበ በኋላ መጋረጃው (መንጦላእቱ) ይዘጋል። ይኽውም ከምጽአት ፍርድ በኋላ ምንም ዓይነት ምሕረት እንደሌለ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።ጌታችን በቸርነቱ በቀኙ ከሚቆሙት ጋር ያቆመን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን። ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

©ስለ ቅዳሴ ክፍል 2  © _ሰላም ለኩልክሙ_ 14ቱ ቅዳሴያት የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው።        1 ቅዳሴ እግዚእ(ኢየሱስ )        2 ቅዳሴ ማርያም        3 ቅዳሴ ፫ቱ ምእት        4 ቅዳሴ ዮሐንስ ወ/ነጎድጓድ(ወንጌላዊው)        5 ቅዳሴ ሐዋርያት        6 ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ        7 ቅዳሴ ባስልዮስ        8 ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ        9 ቅዳሴ አትናቴዎስ        10 ቅዳሴ ቄርሎስ        11 ቅዳሴ ጎርጎርዮስ        12 ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ        13 ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ        14 ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ በእነዚህ ቅዳሴያት ውስጥ አምስቱ አዕማደ ምሥጢር እና ሌሎች የሥነ ምግባር ትምህርቶች በሰፊው ያሉበት ስለሆነ የሚቀደሰው ቅዳሴ ምን እንደሆነ ለማወቅ እና የሚነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ምን እንደሚሆን አስቀድመን ማየት እንድንችል የሚረዳን መጽሐፍ "#መጽሐፈ_ግጻዌ" ይባላል።እነዚህን 14ቱን ቅዳሴያት የያዘው መጽሐፍ ደግሞ "#መጽሐፈ_ቅዳሴ" ይባላል። ገዝተን ልናነበው እንችላለን። መደቡ ከመጽሐፈ ሊቃውንት ውስጥ ነው።                           ። ቅዳሴ ስናስቀድስ ዜማው የሚባለው ወይም የሚዜመው በግእዝ ቋንቋ ስለሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ግእዝ ቋንቋን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት። አለበለዚያ የሚባለውን ሳያውቅ ዝም ብሎ መቆም ብቻ ይሆንና ተመስጦ ሳይኖረው በድካም በመሰልቸት ይጨርሳልና ነው። በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በየመካከሉ የሚለው "#ተንስኡ_ለጸሎት" ለጸሎት ተነሱ ማለት ሲሆን ምስጢሩ አዳምን ጌታ ከ5500 ዘመን በኋላ አድንሀለሁ ብሎት ስለነበር ያንን  በተስፋ ይጠብቅ ስለነበር ቀኑ ሲደርስ በእለተ ስቅለት አርብ ቀን አዳም ልጆቹን ተንስኡ ለጸሎት አላቸው። እነርሱም "#እግዚኦ_ተሣሀለነ" አቤቱ ይቅር በለን።ብለው እግዚአብሔርን ይማጸናሉ።በመካከል ጌታ በአካለ ነፍስ ወርዶ "ሰላም ለኩልክሙ" ሰላም ለሁላችሁ ይሁን አላቸው።                           ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

1
@ ስለ ቅዳሴ ክፍል ፩ @ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። ። አሜን ለታሪክ ሲሆን እውነት፣ አሜን ለሃይማኖት ሲሆን አዎ፣ አሜን ለምረቃ ሲሆን ይደረግልኝ ማለት ነው። ። ቅዳሴ ማለት ልዩ ምሥጋና ማለት ነው።የሰው ልጅ የተፈጠረው ፈጣሪን እያመሰገነ በደስታ ይኖር ዘንድ ነው። በቅዳሴ ጊዜ ተሠጥዎ ለመመለስ ብቻ ካልሆነ በቀር ድምጽ ማሰማት አይገባም። አዳም ከተፈጠረ በኋላ በገነት መካነ ጸሎት ለይቶ ይጸልይ ያመሰግን ነበር። ጸሎት ማለትም ምሥጋና ያለበት ልመና ማለት ነው።በሰይጣን ተንኮል አዳም ከገነት በተባረረ ጊዜ እንዲሁ በደብር ቅዱስ የጸሎት ቦታ ለይቶ መሥዋእት ያቀርብና ይጸልይ ነበር። አዳም ከሞተ በኋላ አጽሙን እንደታቦት አድርገው በዚያ መሥዋእት ሲሰው ጸሎት ሲጸልዩ ይኖሩ ነበር።ይህ ሲያያዝ ከኖኅ ደረሰ። ኖኅም ዓለም በማየ አይኅ ስትጠፋ የአዳምን አጽም ወደ መርከብ ይዞት ገብቷል።ከመርከቡ ሲወጣም የአዳምን አጽም እንደ ታቦት አድርጎ መሥዋእት ሰዋ።ከዚያ የኖኅ ልጅ ሴም አጽመ አዳምን ለካህኑ ለመልከጼዴቅ አስጠብቆታል። ። ከዚህ በኋላ የተነሱት አበው እነ አብርሃም እነ ይስሐቅ እነ ያዕቆብ ሁሉ ቦታ ሳይለዩ በፈለጉት ቦታ መሥዋእት ያሳርጉና ይጸልዩ ነበር። ይህ እስከ ሙሴ ድረስ ዘልቋል። በሙሴ ጊዜ እግዚአብሔር የደብተራ ኦሪትን አሠራር እና የመሥዋእት አቀራረብ እንዲሁም የሚያቀርቡት ካህናት ሌዋውያን አሿሿም ለሙሴ ገለጠለት። ስለዚህም መሥዋእትም በተለየች ደብተራ ኦሪት (ድንኳን) መደረግ ተጀመረ።ከዚያ በፊት ማንኛውም ሰው መሥዋእት ያሳርግ ነበር።በኦሪት ግን መሥዋእት የሚያቀርቡ ካህናት በተለየ ተመረጡ።በንጉሥ ሰሎሞን ጊዜ ደግሞ ታላቁ ቤተመቅደስ ተሠራ በዚህን ጊዜም ከደብተራ ኦሪቱ የተለየ አልነበረም።ይህ ሲያያዝ እስከ ክርስቶስ ድረስ ቀጥሏል። ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት በየደረሱበት ቦታ እየቀደሱ ያቆርቡ ነበር። ከዚያ በፊልጵስዩስ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን ተሠራች። ጌታም ሐዋርያትን አቆረባቸው።እርሱም ወይእዜኒ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ ብሏቸዋል።ከዚያ በኋላ እነርሱም በቤተክርስቲያን እየቀደሱ ማቁረብ ጀመሩ።ያ ሥርዓት እስካሁን ጸንቶ አሁንም መሥዋእት የሚሰዋባት ቅዳሴ የሚቀደስባት ቤተክርስቲያን ናት። በብሉይ ኪዳን መሥዋእት ሰውተው ከሥጋዊ መከራ ከእለት ችግር ይድኑ ነበር።በሐዲስ ኪዳን ላለን ለእኛ ደግሞ በቅዳሴ መሥዋእት ሲሰዋ ለፍጥረታት ሁሉ ጸሎትን አቅርበን እኛም ከነፍሳዊም ከሥጋዊም መከራ የምናመልጥበት ታላቅ ነገር ነው። ሥለ ወንዞች፣ ስለ ዝናማት፣ ስለ ዓለም፣ ስለ አዕዋፋት፣ ስለ እንስሳት ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸው ዘንድ ጸሎት የሚቀርብበት ነው ቅዳሴ። ከምንም በላይ ሥጋየን ብሉ ደሜን ጠጡ ባለን መሰረት ደሙ ሥጋው የሚፈተትበት ለእኛም ጸጋን የሚያድልበት ስለሆነ ቅዳሴ በቻልንባቸው ጊዜያት እና አጋጣሚዎች ሁሉ ልናስቀድስ ይገባል። አጠቃላይ ሥለ ሥርዓተ ቅዳሴ እና ሌሎች በቅዳሴ ጊዜ ልናደርጋቸው ስለሚገቡ ነገሮች በቀጣይ ክፍል በሰፊው እንጽፋለን። ። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል 👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

............የመጨረሻ ክፍል............ #ስለ #እጮኝነት/ትዳር #ክፍል 10 ፈጣሪ የፍትወት ስሜት እንደሚሰማን እያወቀ ለምን አታመንዝሩ ይለናል? የሚል ጥያቄ ይጠየቃል። ለመሆኑ የሰው ልጅ እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ የፍትወት ስሜት ይሰማዋልና ይህ ተፈጥሯዊ ነው ወይ? ከሆነ እግዚአብሔር ተፈጥሯዊ የሆነን ነገር ተውት ለምን ይለናል? የሚል ጥያቄ ይጠየቃል። ነገር ግን የፍትወት ስሜት ተፈጥሯዊ አይደለም። አዳም ሲፈጠር ፍትወታዊ ስሜትም አብሮ አልተፈጠረበትም። ነገር ግን ሕገ እግዚአብሔርን ሽሮ እፀ በለስን በበላ ጊዜ ፍትወታት እኩያት ሰልጥነውበታል። ስለዚህ ፍትወታዊ ስሜት ተፈጥሯዊ ሳይሆን የድቀት ውጤት ነው። ይህንን በምሳሌ ላስረዳ አንድ ሰው ጤነኛ ሆኖ ከተፈጠረ በኋላ ራሱን ወደ ገደል ቢወረውር እና አካሉ ጎደሎ ቢሆን ይህ አካለ ጎዶሎነቱ በመውደቁ ምክንያት የመጣ እንጂ ተፈጥሯዊ አይደለም። የፍትወት ስሜትም እንዲሁ ነው። ተፈጥሯዊ አይደለም። በአዳም ድቀት ምክንያት የደረሰብን ጉዳት ነው። ይህ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ባወቀ ፍትወታዊ ስሜት ቢሰማን እንኳ ከተፈቀደልን ሰው ጋር ግንኙነት እንድናደርግ የትዳርን መስመር ፈቅዶልናል። ስለዚህም ባል ከሚስቱ ሚስት ከባሏ የሚያደርጉት ግንኙነት ፍትወት አይባልም። ሕጋዊ ግንኙነት ይባላል እንጂ። ለዚያ ነው ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ። አላ በሩካቤ ዘበሕግ" ይላል። ድንግል ማርያም ሆይ በኃጢኣት ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም። ሐናና ኢያቄም በሕግ ተጋብተው ባደረጉት ግንኙነት ተጸነስሽ እንጂ ይላል። ስለዚህ ሁለቱን ሕጎች ለመጠበቅ ይረዳን ዘንድ ስለ እጮ ኝነትና ስለትዳር በ10 ክፍል ተማምረናል። የቀረውን ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ መምህራንን በመጠየቅ ማስፋት ትችላላችሁ። መቼም እግዚአብሔር ያዘዘን ትእዛዛት ሁሉ እኛን የሚጠብቁ ብንጠብቃቸው እኛን የሚጠቅሙን እንጂ ጨቋኝ ሕጎች አይደሉም። ሕጻንን ልጅ እናቱ ካልበላህ እያለች ስትቆጣው እሱን ልትጠቅመው ነው እንጂ ልትጎዳው እንዳይደለ ማለት ነው። ከአሥሩ ሕግ ደግሞ አንዱ ዘጸ.20፣14 አታመንዝር የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከስድስቱ ቃላተ ወንጌል አንዱ ማቴ.5፣31 "ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እርሱ ራሱ አመንዝራ ያደርጋታል የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል" የሚለው ነው። ከዚህ ላይ ያለዝሙት ምክንያት ሰነፈች መከነች ወዘተ ብሎ ሚስቱን የሚፈታ ሰው ትልቅ በደለኛ ነው። በዚህ ምክንያት ሚስቱን የፈታን ሰው መልሰው ሊያስታርቁት ይገባል። 1ኛ ቆሮ.7፣10 "ሚስት ከባሏ አትፋታ ከተፋታችም ብቻዋን ትኑር። ያለዚያ ከባሏ ጋር ትታረቅ። ባልም ሚስቱን አይፍታ"። እምቢ አልታረቅም ካለ/ካለች ግን ሊያገቡት/ሊያገቧት አይገባም። አታመንዝር ያለን ሕግም እርሱ ባወቀ እኛን የሚጠብቀን ሕግ ነው። የእኛ ካልሆነች ሴት/ወንድ የሌላ ከሆነች/ከሆነ  ሰው ጋር ግንኙነት ለምን እናደርጋለን!? ይህስ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ያፈነገጠ ስለሆነ በነፍስ በሥጋ የሚጎዳን ስለሆነ ልናደርገው አይገባንም። 1ኛ ቆሮ.7፣2 "ነገር ግን እንዳትሴስኑ ሰው ሁሉ በሚስቱ ይወሰን። ሴትም ሁላ በባሏ ትወሰን። ለሚስትም ባሏ የሚገባትን ያድርግላት። እንዲሁ ሚስትም ለባልዋ የሚገባውን ታድርግለት"። ከተጽእኖ ነጻ የሆነ ትዳር ያስፈልጋል። ይህም ማለት ወንዱ የሴቲቱን እሷነቷን ሳይወድ ገንዘቧን ወይም የታላቅ ሰው ዘር ስለተባለች ብቻ ወይም በሌላ ምክንያት ሊያገባት አይገባም። ሴቲቱም የወንዱን እሱነቱን ሳትወድ በሌላ ተጽእኖ (ምሳሌ እድሜየ ሄደ፣ ቤተሰብ አግቢ እያሉ ጨቀጨቁኝ... ወዘተ በማለት) የማትወደውን ሰው ማግባት የለባትም። ሌላው ከተጋቡ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ወይም ከሴቲቱ ችግር ወይም ከወንዱ ችግር መውለድ የማይችሉ ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህ ምክንያት ግን ትዳርን መፍታት እግዚአብሔርን እንደመስደብ ይቆጠራል። ልጅን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነውና። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ልጅ ባላቸው መቅናትም እርስ በእርስ መጋጨትም አይገባም። ከሕግ ውጭ ግንኙነት ያደረጉ ሰዎች ተቀጥተዋል። ስለዚህ እኛም ከሕግ ውጭ የሆነ ግንኙነት አድርገን ዘላለማዊ ቅጣትን እንዳንቀበል እንጠንቀቅ። ከዚህ ቀደም በማወቅም ባለማወቅም አጥፍተንም ከሆነ ንሥሓ ገብተን ካሁን በኋላ ላለው ሕይወታችን እንጠንቀቅ። ሮሜ.7፣2 "ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና። ባሏ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈታለች"። ስለሚል ከሚስት/ከባል አንዱ ቢሞት 10 ወር ቆይቶ ሌላ ማግባት ይፈቀዳል።1ኛ ቆሮ.7፣8 "ነገር ግን ያላገቡትንና አግብተው የፈቱትን እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ ይሻላቸዋል እላለሁ። መታገሥ ባይችሉ ግን ያግቡ በፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና" ይላልና።                        ። አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል። ይቆየን 🙏 #በመምህር_በትረ_ማርያም በሌላ ተከታታይ ትምህርት እስክንገናኝ ለሌሎች ክርስቲያኖች አጋሩ 👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

#ስለ #እጮኝነት/ትዳር #ክፍል 9 ባል ከሚስቴ ጋር ብገናኝ ብሎ ወይም ሚስት ከባሌ ጋር ብገናኝ ምን ችግር አለው ብለው በአደባባይ በሰው መካከል ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም። በአደባባይ ግንኙነት ቢደረግ ያንን ያየ ሰው በልቡ እንዲመኝ እና አታመንዝር ያለውን ሕግ እንዲሽር ስለሚያደርገው በዚህም ምክንያት እንዳይኮነንብን ነው። ባልና ሚስት የባልና የሚስት ወሬዎችን ማውራት ካለባቸውም እንኳ ልጆቻቸውም ቤተሰቦቻቸውም ጎረቤትም ሳይሰማ መሆን አለበት። ይኽውም ለሚሰማውና ለሚያየው አካል ፈተና እንዳይሆን ነው። በየአደባባዩ #መሳሳም እና ፍትወት ቀስቃሽ ድርጊቶችን ማድረግ ግን አንደኛ ባልንጀራን መናቅ ነው። ሌላው በዚያ አካባቢ ያለ ሰው እናንተን ተመልክቶ እንደሚስት አስቡ። ሌላውን ሰው ፈተና ውስጥ የሚያስገባ ራቁትን የሚያሳይ ልብስ ወይም አካልን ጥብቅ አድርጎ በማሳየት የሰውነትን ቅርጽ የሚያሳይ ልብስ መልበስም የርካሽነት ሥራ ነው። የሰው ልጅ ክቡር ነው። ለዝሙት አልተፈጠረም። ዝሙትኮ የሚያኮራ ነገር አይደለም። እንስሳትም የሚያደርጉት ነገር ነው። ከእንስሳት ጋር የሚያመሳስለን ነገር ነው። እና ቢያንስ ከእንስሳት የተሻለ አኳኋን ይኑረን እንጂ። ወይፈንኮ ያረገዘች ላም ካየ አሽቶ ይመለሳል እንጂ አይሰቀልም። ሰው ግን ከወይፈንም አንሶ በእርግዝና ወቅት እንኳ ግንኙነት ካላደረግን ማለት አግባብ አይደለም። ሰው ከዝሙት ውጭ እንዳያስብ እያደረጉ ያሉት ደግሞ ጭፈራ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ናቸው። የትውልዱን አስተሳሰብ እያበላሹ ያሉት ደግሞ እኒህ ናቸው። ከእነዚህም በተጨማሪ አሁን አሁን በቴሌቭዥን መስኮት የሚታዩ ድራማዎች፣ ፊልሞች ትውልድ አምካኝ ጅል ትውልድ የሚያፈሩ ናቸው። የሰው ልጅ በፍትወት እንዳይናደድ ከፈለገ አግብቶ ይወሰን። ከዚያ ውጭ ከዚያም ከዚያም መድረስ የመኖርን ዓላማ ካለመገንዘብ የሚመጣ ደዌ ነው።                       ። ሌላው ትዳር ፈተና አለበት ይህንን ማወቅ ያስፈልጋል። ትዳር ሀብት ሲጠፋ ውበት ሲረግፍ የሚተውት አይደለም። አብርሃም እና ሣራ ከሀገር ሀገር ሲሰደዱ ኖረዋል። ስደት ቢመጣ፣ ሀብት ማጣት ቢመጣ፣ አካላዊ ጉዳት ቢመጣ እንኳ እስከ መጨረሻው አብሮ በፍቅር መኖር ያስፈልጋል። ሌላው ግን ምራትና አማት አይጥና ድመት ወይም ዓይንና አፈር መሆን የለባቸውም። ብዙ ጊዜ አይስማሙም ለምን እንደሆነ እኔ እንጃ። ነገር ግን ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይሆናል የተባለው ፍትወት ቢነሳበት ወንዱ ከእናቱ ሴቷ ከአባቷ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይገባትም ማለት ነው እንጂ ሚስትየዋ የባሏን እናትና አባት ትጥላ ባልዮው የሚስቱን እናትና አባት ይጥላ ማለት አይደለም። ዘጸ.20 እናትና አባትህን አክብር የተባለው እስከመጨረሻው ነው። ምራትና አማትስ መሆን ያለባቸው እንደ ኑኃሚን እና እንደ ሩት ነው። (መጽሐፈ ሩትን ከምዕራፍ አንድ ጀምራችሁ ተመልከቱትማሐ። ሩት ባሏ ሞቶ እንኳ አማቷን ኑኃሚንን አልተወቻትም። እንዲያውም "አምላክሽ አምላኬ ነው። ሀገርሽ ሀገሬ ነው" ብላ ተወልዳ ያደገችበትን ሀገር ትታ ከአማቷ ጋር ተሰዳለች። ጋብቻ መዛመድ ስለሆነ ሴቲቱ የወንዱን ወገኖች ወንዱ የሴቲቱን ወገኖች መውደድና ማክበር አለበት። ሴቲቱ የባሏን እናትና አባት ራሷን ዝቅ አድርጋ በትሕትና ልታገለግላቸው ልትታዘዛቸው ይገባል። ወንዱም ለሚስቱ አባትና እናት ክብር ሊሰጣቸው ይገባል።ባልና ሚስት አንዱ አንዱን ማስቀናት የለበትም። በፍጹም መከባበር፣ በፍጹም ፍቅር፣ በፍጹም መተማመን ሊኖሩ ይገባል። በባልና በሚስት ማንም ጣልቃ ሊገባ አይገባም። በቤተሰቦቿ/ቹ ወይም በጓደኞቿ/ቹ ተጽእኖ ሚስት ባሏን ልትፈታ ባል ሚስቱን ሊፈታ አይገባም።ባል ወይም ሚስት ልመንኩስ ቢሉ ከተፈቃቀዱ መመንኮስ ይችላሉ። ባሏ ከፈቀደላት ሚስትየዋ መመንኮስ ትችላለች። ሚስቱ ከፈቀደችለት ባልየው መመንኮስ ይችላል። ሚስት ባሏ ሳይፈቅድላት ወይም ባል ሚስቱ ሳትፈቅድለት ግን ልመንኲስ ቢል መመንኮስ አይችልም። ከዚህ ላይ አጥብቀህ ያዝልኝማ አሁን አሁን አንዳንድ ባሕታውያን ነን ባዮች ባልና ሚስትን እያፋቱ ካላመነኮስን ይላሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ያለ ባሏ ፈቃድ የመነኮሰች ሴት ካለች ከመነኮሰችበት አምጥቶ ከቤቱ ቢወስዳት ምንም ነውር የለበትም። ሚስቱ እንድትመነኩስ ከፈቀደላት በኋላ እሷም ከመነኮሰች በኋላ ሐሳቡን ቀይሮ እንደገና ምንኩስናዋን እንድትተው ቢፈልግ ግን አይቻልም። በምንኲስናዋ ትጸናለች። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

#ስለ #እጮኝነት/ትዳር #ክፍል #8 ከጋብቻ በኋላ ባልና ሚስት ሩካቤ ሥጋ በማይደረግባቸው እለታት ግንኙነት ማድረግ አይገባቸውም። ግንኙነት የማይፈቀድባቸው እለታትም፦ 1) በወር አበባዋ ወቅት 2) ከወለደች ጀምሮ እስከ ክርስትና 3) በእርግዝናዋ ወቅት። እርግዝናዋ ከታወቀበት ስአት  በኋላ ግንኙነት የሚያደርግ ወንድ ሚስቱ የጸነሰችው ወንድ ከሆነ ግብረ ሰዶም ሴት ከሆነች ከልጁ ጋር ግንኙነት እንደፈጸመ ይቆጠርበታልና ብለው ሊቃውንት በፍትሐ ነገሥት በሐተታቸው አስቀምጠዋል። ነገሩን የማይገባ መሆኑን አክፋፍቶ ለመናገር የተጠቀሙት ቃል ነው። ። 4) ከሁለት አንዳቸው ከቆረበ ከመቁረቡ በፊት ባሉት 3 ቀናት እና ከቆረበ በኋላ ባሉት 2 ቀናትም ግንኙነት ማድረግ አይገባም። ። 5) በአጽዋማትና በዐበይት በዓላት ጊዜ። ከእነዚህ እለታት ውጪ ግን ሚስት ወይም ባል ግንኙነት ማድረግ ፈልገው አንዱ እምቢ ማለት የለበትም። የእርሱ አካል የእርሷ የእርሷ አካል የእርሱ ሆኗልና። ፈቃዱን ወይም ፈቃዷን ይፈጽምላት/ ትፈጽምለት እንጂ። ሌላው ቀርቶ ንሥሓ አባት ቀኖና ቢሰጥ እንኳ ሚስት ባልን ባል ሚስትን አሳውቆ መሆን አለበት። ሚስት ወይም ባል ንሥሓ ላይ እንዳሉ ከታወቀ ግን ንሥሓሃቸውን እስኪጨርሱ ከግንኙነት ይከልከሉ። ከዚያ ውጭ ግን መከልከል የለባቸውም። ወንዱ ግንኙነት ማድረግ ፈልጎ ሴቷ እምቢ ብትለው እና ሴቷ ግንኙነት ማድረግ ፈልጋ ወንዱ እምቢ ቢላት እናም በዚህ ምክንያት ፍትወት አናዶት ወንዱ ከሌላ ሴት ሴቷ ከሌላ ወንድ ብትደርስ በደሉ የጋራ ነው። የእሱ በደል የእሷ የእሷ በደል የእርሱ ይሆናል።ባልና ሚስት ግልጽ መሆን አለባቸው። ፈቃዳቸውን በግልጽ ሊነጋገሩ ይገባል። ሚስት አካሏን ሳይቀር ለባሏ ከሰጠች ባልም አካሉን ሳይቀር ለሚስቱ ከሰጠ ከዚህ የበለጠ ምሥጢር ምን አለ? ምንም። ስለዚህ ያለመጣጣምና ያለመስማማት ነገሮች ካሉ በግልጽ ሊነጋገሩ ይገባል።ብዙ ሴቶች በሕገ ወጥነት መንገድ ከሌላ ወንድ ይጸንሱና መጽነሳቸውን ወላጆቻቸው ወይም ይህን ጉዳይ የሚፈሩት ሰው እንዳያውቅ ብለው በማሰብ ጽንሳቸውን በድብቅ ያስወርዱታል። ይህ ግን ሁለት ታላላቅ በደሎችን የያዘ ነው። አንደኛው ባሏ ካልሆነ ሰው ጋር በመገናኘቷ ከአሥሩ ትእዛዛት አንዱ የሆነውን ዘጸ.20፣14 "አታመንዝር" የሚለውን ሕግ ማፍረስ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ዘጸ.20፣13 ያለውን "አትግደል" ያለውን ሕግ መተላለፍ ነው። ስለዚህ ከሌላ ወንድ ጋር ባትገናኙ መልካም ነበረ። ነገር ግን ደግሞ ሥጋዊ ፈቃድ አሸንፏችሁ ግንኙነት አድርጋችሁ ልጅ ቢጸነስ አታስወርዱት ይወለድ። ወላጅ ሰምቶ ያዝናል ብለን እግዚአብሔርን መበደል አይገባምና። ወላጅም ይሁን ወዳጅ ለጊዜው ሊያዝን ቢችልም። ልጁ ተወልዶ አበ እመ ማለት ሲጀምር ግን ኀዘናቸው ይቀንሳል። ሌሎች ደግሞ ግንኙነቱን ፈልገው ግን እንዳይጸንሱ በማለት የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚጠቀሙ አሉ። ይህም ትልቅ ስህተት ነው። ማሕጸን የተፈጠረው ለጽንስ ነው ። ስለዚህ ግንኙነትን መርጦ ልጅ እንዳይወለድ መፈለግ ብዙ ተባዙ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ቸል ማለት ነው። ምናልባት ጸንሰን ወላጆቻችን መጽነሳችንን ሲያውቁ እንዳይቆጡን እንዳያዝኑብን ብለን አስበን ከሆነም ከእግዚአብሔር ሕግ ይልቅ የእናትና የአባትህ ቁጣ የሚያስፈራህ ጣዖት አምላኪ መሆንህን ያሳውቃል። ክልክሉ'ኮ ካላገቡት ሰው ጋር ግኑኝነት ማድረጉ ላይ ነው እንጂ መጽነሱ ላይ አይደለም። መጠበቅ ያለበት መሠረታዊው ሕግ "#አታመንዝር" የሚለው ነው። አታመንዝርን ተላልፈሽ መጽነስሽ ለምን ያሳስብሻል።  ሁለት በደል መበደል አይገባም። መጀመሪያ ካላገቡት ሰው ጋር ግንኙነት ማድረግ አይገባም። ሁለተኛ ሥጋዊ ፈቃድ አሸንፎሽ ብትሰናከዪ እንኳ የወሊድ መቆጣጠሪያ ተጠቅመሽ ሁለተኛ በደል አትበድይ። አንድ ጊዜ የፈለገ ሊቃውንት ደብረ ድማህ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሐዲሳትና የፍትሐነገሥት መምህር የነበሩት የኔታ ወልደ ኢየሱስ መቅጫ "ልጃችንን ወልደነው ምን እናበለዋለን ብላችሁ በመፍራት ገና ከጽንሱ የምታስወርዱ ሰዎች ይህንን ክፉ ሥራ አትሥሩ። ተውት ልጁን ውለዱትና እግዚአብሔር ከገደለው ይግደለው እንጂ እናንተ አታስወርዱ ያሉት ቃል ድንቅ ቃል ነው። ደግሞስ ጽንስን የምናስወርድ ለምንድን ነው? መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በኤልሳቤጥ ማሕጸን እያለ እኮ ነው ጌታን ያመሰገነው። ዮሐንስ ትዝ አይላችሁም እንዴ? ስለዚህ ጽንስን ማስወረድ አይገባም። የተጸነሰው በስርቆት ከሌላ ወንድም ቢሆን መጀመሪያ ትልቅ በደል በድላችኋል። ስለዚህ ሁለተኛ ታላቅ በደል ጽንስን በማስወረድ አትበድሉ።                         ። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

🙏 2
#ስለ #እጮኝነት/ትዳር #ክፍል 7 ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ ፍቺ የሚፈቀድባቸው ምክንያቶች፦      1) በዝሙት ምክንያት      2) በሃይማኖት ምክንያት      3) ባሏን/ሚስቱን ልታስገድለው/ሊያስገድላት በበቂ መረጃ ከተደረሰባት/ከተደረሰበት ናቸው። አንድ ወንድ ሚስቱን ከሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት እየፈጸመች ተኝታ ቢያገኛት መፍታት ይችላል። ተናዶ በእርሷ እና ከእርሷ ጋር ተኝቶ ባገኘው ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ የለበትም። በሃይማኖት ምክንያት የሚለውን ከዚህ ቀደም አይተናል። ከላይ ባሉት ሦስት ምክንያቶች ከሚስቱ የተፋታ ካህን ቢሆን ሌላ ሳያገባ ቢቀጥል ክህነቱ ይቀጥላል። ነገር ግን ሌላ ካገባ ወይም በዝሙት ምክንያት ሚስቱን ካገኛት በኋላ አብሯት የሚኖር ከሆነ ክህነቱ ይሻራል። ካህን በማንኛውም ምክንያት ሁለተኛ ካገባ ከክህነቱ ይሻራል። ክህነቱን አፍርሶ እንደገና ያገባት ሴት ብትሞትበት ግን ሦስተኛ እንዲያገባ አይፈቀድም። ካገባም እንደ አረሚ ይሁን ተብሎ ተነግሮበታል። ምእመን ሚስቱ ብትሞት ሌላ ያገባል። ያች ያገባት ብትሞትም እንደገና ቢያገባ ይፈቀድለታል። አራተኛ ግን ማግባት አይችልም። የምእመን አራተኛ የካህን ሦስተኛ እንደ አረሚ ይሁኑ ተብለዋልና። እስከዛሬ ባለማወቅ አድርገነው ከሆነ ለወደፊቱ እንጠበቅ።ከላይ ከተቀመጡት ምክንያቶች ውጪ ግን ማለትም ያለዝሙት ምክንያት፤ ሃይማኖት ሳይለውጡ፣ በማስገደል ሂደት ካልተገኙ በሌላ ምክንያት መፋታት አይቻልም። ጸባዩዋ ከፋ፣ ሰነፈች፣ ውበቷ ጠፋ፣ አረጀች፣ ወዘተ ብሎ መፍታት አይቻልም። እስከ እለተ ሞትህ ልትጠብቃት ይገባል እንጂ። ከላይ ካሉት ከሦስቱ ምክንያት ውጭ ሚስትህ ብትበድልህ እንኳ ያንን ታጋሽ ሆነህ አረጋግተህ በፍቅር ልትኖሩ ይገባል። የሚደርስብህን በደል ሁሉ ችለህ ኑር። ሴቷም ከላይ ካሉት ምክንያቶች ውጪ ከሆነ የሚደርስባትን በደል ሁሉ ታግሣ ትኑር።በሆነ አጋጣሚ ሚስት ወይም ባል የአካል ጉዳተኛ ቢሆኑ እንኳ እስከ መጨረሻው በፍቅር ሊኖሩ ይገባል እንጂ በዚህ ምክንያት መፋታት አይገባም። #በመምህር_በትረ_ማርያም ይቀጥላል ...👇👇👇 https://t.me/EOTC_teketatay https://t.me/EOTC_teketatay
Hammasini ko'rsatish...
ተከታታይ ትምህርቶች በየቀኑ🎚

ይህ ቻናል ተከታታይ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መጣጥፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው።

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.