cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ዝዖን ዜና

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 164
Obunachilar
-624 soatlar
-497 kunlar
-66730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

" ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈተ ህይወት ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ ነው " - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ህይወቷ አልፏል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን ሞት 'ድንገተኛ ህልፈት'  በማለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክት አሰራጭቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዋ ' #በጩቤ_ተወግታ ህይወቷ እንዳለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎችን ተመልክቷል። ይህን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯል። በጉዳዩ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራር፤ " ፖሊስ ከተማሪዋ ህልፈት ጋር በተያያዘ የጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያደረገ ይገኛል " ብለዋል። " በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተሰራጨው መረጃ ጉዳዩ ገና በፖሊስ የተያዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዋን አስክሬን ወደቤተሰቦቿ አሸኛኘት ማድረጉንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። Via @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
😢 1
10:08
Video unavailableShow in Telegram
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም ' ማለታቸው ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " ብለዋል። ከመንግስት ጋር በታንዛንያ የሰላም ንግግር ሲያደርጉ የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) ተዋጊዎችን " በድርድር ተስፋ ሳትቆርጡ ፤ መተማመንን ለመገንባት ጥረት አድርጉ " ብለዋቸዋል። አሜሪካ ይህን ያለችው ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የምትከተለውን ፖሊሲ አስመልክቶ በአምባሳደሯ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት ነው። በአዲስ አበባ ፤ መርካቶ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ የአሜሪካን ግቢ በነበረ መርሀ ግብር የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። Video Credit : US Embassy Addis Ababa / Ethiopia Insider @ZION_NEWS
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
#Tigray ከማረት ከተስረቁት 2 መኪኖች አንደኛዋ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ። ማሕበር ረድኤት ማሕበር (ማረት) በመጋቢት እና በያዝነው ግንቦት ወር አንድ ላንድክሩዘር V8 እና ላንድክሩዘር ማርክ 2 መኪናዎችን ተዘርፏል። የድርጅቱ ንብረት የሆነች በሰሌዳ ቁጥር 35 - 2723 የተመዘገበችው V8 መኪና መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ተሰርቃ ሳትገኝ የውሃ ሽታ ሆና ቀርታ ነበር። ይህች መኪና ሳትገኘ ከቀናት በፊት ላንድ ክሮዘር ማርክ 2 መኪና ተዘርፋለች።  ፓሊስ የድርጅቱ መኪኖች ያየና ያገኘ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ በያዝነው ሳምንት የተሰረቀችው ላንድክሩዘር ማርክ2 መኪና ከመቐለ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አክሱም ከተማ በፓሊስ ተይዛለች። የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ መኪናዋ ግንቦት 3/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋልዋን አሳውቋል። ፖሊስ መኪናዋን ያገኘው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል ነው። በሰዓቱ መኪናዋን የያዛት ሹፌር ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም ማክሸፉን አሳውቋል። ከነሹፌሩ በተጨማሪ " የኔ ንብረት ናት " የሚል አመልካችም በፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል። የአክሱም ከተማ ፖሊስ " መሰል ስርቆት ከጦርነቱ በኋላ መታየት የጀመረና በትግራይ ያልተለመደ ነው " ያለ ሲሆን " ማንኛውም ወንጀለኛ ከህዝብ አይንና ጀሮ መደበቅ አይችልም ብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ስለ መኪኖቹ ስርቆት ከማሕበር ረድኤት ትግራይ (ማረትረት) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።                                             @ZION_NEWS
Hammasini ko'rsatish...
ለስድስት ዓመታት ባለቤቱን ቤት ውስጥ ቀብሮ ቤተሰቦቿን አረብ ሀገር ሄዳለች ብሎ ያታለለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ ፡፡ በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ ውስጥ አቶ ደበበ ተሰማ እና ወ/ሮ ዝናሽ ባይሳ የተባሉ ጥንዶች ከ2004 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አንድ ልጅ አፍርተው በትዳር አብረው ይኖሩ እንደነበር የሸገር ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ  ከ2004 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ሚስት ወ/ሮ ዥናሽ ወደ አረብ ሀገር ሄዳ ነበር፡፡ ከአረብ ሀገር ስትመለስ አንድ ልጅ ወልደው በመኖር ላይ ሳሉ ከቆይታ በኃላ ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ.ም ነው ምሽት ላይ  ሚስት በድጋሚ ኮንትራት ስላላት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ ሀሳብ ታቀርባለች ባል ግን በዚህ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ከሀገር መውጣት  እንደማትችል እና እዚው አብረን መኖር አለብን በማለት በሀሳቧ እንደማይስማማ ያሳውቃታል፤ በሁኔታው ወደ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባሉ  ጭቅጭቁ እና አለመግባባቱም ከሮ ባል አካፋ አንስቶ የሚስቱን ጭንቅላቷን ከመታት በሓላ በህይወት ትኑር አትኑር የሚለውን ሳያረጋግጥ ቤት ውስጥ ጭቃ ለመመረግ የተቆፈረ የአፈር ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራታል፡፡ ባል ከሶስት ቀን በሓላም ወደ ቤተሰቦቿ በመሄድ ልጃቸው  ወደ አረብ ሀገር እንደሄደች ይነግራቸዋል፤ ቤተሰቦቿም እንዴት ሳትነግራቸው እንደሄደች ላቀረቡለት ጥያቄ እንዳትሄድ እናንተ ስለከለከላቿት ነው ብሎ ያሳምናቸዋል እነሱም ይቅናት በማለት ጉዳዩን እንደተውት  ተገልፆአል፡፡ በዚህ ሁኔታ ግን ለ6 ዓመት ያህል ቤተሰቦቿ ስለሷ ምንም አይነት መረጃ ባለማግኘታቸው ተጠራጥረው ባልን ይጠይቁታል ባልም እሱ ጋር እንደምትደውል እና የቤት እና የመኪና መግዣ እስኪሞላላት ወደ ሀገር አልመለስ እንዳለችው ለቤተሰብ ይናገራል፡፡ ቤተሰቦቿም በሁኔታው በድጋሚ ጥርጣሬ ውስጥ ስለገቡ ለፖሊስ ያመለክታሉ። ፖሊስም ጉዳዩን ለማጣራት  ኢምግሬሽን እና ዜግነት ምዝገባ አገልግሎት ያመለከትታል በዚህም ወ/ሮ ዝናሽ ወደ ሀገር ውስጥ መመለሷን እንጂ ከሀገር መውጣቷን የሚያመላክት መረጃ እንደሌለ ለፖሊስ መረጃው ይደርሰዋል፡፡ ፖሊስ በቀጥታ ባለቤቷን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ማጥራት ሲጀምር አቶ ደበበ ሚስቱን ለስድስት ዓመታት  ቆፍሮ መቅበሩን እና ቤተሰቧን ሲያታልል እንደነበር  ቃል ይሰጣል በዚህ መሰረትም የግለሰቧ አስክሬንም ተቆፍሮ እንዲወጣ የኦሮሚያ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ክትትል በማድረግ ለጳውሎስ ሆስፒታል ፓቶሎጂስቶች አስክሬኑን እንዲመረምሩ በመደረጉ የአስክሬም ምርመራው ለፖሊስ ይደርሰዋል፡፡ የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የገላን ከተማ ፖሊስ ባደረጉት ምርመራ ባል ጥፋተኛ መሆኑ በመረጃ በመረጋገጡ የምርመራ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ተልኳል፡፡ ዓቃቢ ህግም በአቶ ደበበ ላይ  ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ተከሳሽ ደበበ ተሰማ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን የሸገር ከተማ አስተዳደር የህፃናት እና ሴቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ረቢሱ ደቻሳ ጨምረው መናገራቸውን ብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥንን ጠቅሶ ዳጉ ጆርናል አስነብቧል፡፡ @ZION_NEWS @ZION_NEWS
Hammasini ko'rsatish...
#EARTHQUAKE " ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " - አቶ ኦይታ ኡኖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ36 ደቂቃ ላይ ነው የተከሰተው። ክስተቱ በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል " ወይጦ ድልድይ ፖሊስ ጣቢያ " አካባቢ መከሰቱን ጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ይህ መጠን (4.8) ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የሚባል እንዳልሆነና " መካከለኛ " የሚል ደረጃ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጿል። የሚያስከትለው ውድመት እና ጥፋት እንደ አካባቢው ቅርበት እንደሚወሰን ፤ ከተማ ውስጥ ቢፈጠር ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስረድቷል። " ወይጦ " የተባለው አካበቢ የሚገኝበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ ብራይሌ ታዳጊ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ኦይታ ኡኖ ትናንት ሌሊት የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙን አረጋግጠዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ ሁለት ጊዜ መከሰቱን እና ክስተቱም አስደንጋጭ እንደነበር ገልጸዋል። " ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " ብለዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ካሉት ስድስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር ውስጥ በስድስቱ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ አረጋግጧል። እስካሁም መረጃ በተገኘባቸው መዋቅሮች ጉዳት አልተመዘገበም። አሪ ዞንም የመሬት መንቀጥቀጡ መሰማቱን የዞኑ የመንግስት አሳውቋል። ጂንካን ጨምሮ በአራት ወረዳዎች እና 2 የከተማ መስተዳድሮች ክስተቱ ማጋጠሙን አረጋግጧል። በሁሉም መዋቅሮች የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ጠቁሟል። ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በወረዳ ሁሉም መዋቅሮች 3 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር። የትናንትናው የመሬት መንቀጥቀጥም እስከ ዳውሮ ድረስ መሰማቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ‼️ በዘረመል ምህንድስና የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ከህክምናው ሁለት ወራት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ። የ62 ዓመቱ ሪቻርድ "ሪክ" ስላይማን ቀዶ ህክምናውን በመጋቢት ወር ከማድረጉ በፊት በከፋ የኩላሊት ህመም ይሰቃይ ነበር። ህይወቱ ያለፈው በንቅለ ተከላው ምክንያት ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ሲል የማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል (ኤምጂኤች) እሑድ ዕለት አስታውቋል። በዘረመል ምህንድስና ከተሻሻሉ አሳማዎች የተገኙ ክፍሎችን ሌሎች የመተካት ሙከራ ቀደም ሲል አልተሳካም ነበር። የስላይማን ቀዶ ህክምና ግን ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሎ ተወድሷል። ከኩላሊት ህመም በተጨማሪ ስላይማን የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ነበረበት። እአአ በ 2018 የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢያከናውንም ከአምስት ዓመታት በኋላ መሥራት ማቆሙ ተነግሯል። የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላውን ተከትሎ፤ አዲሱ ኩላሊቱ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ በመሆኑ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) እንደማያስፈልገው ዶክተሮቹ አረጋግጠው ነበር። "ስላይማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ህሙማን የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ ይታያል። ‘የዜኖትራንስፕላንቴሽን’ መስክን ወደፊት እንዲራመድ ላሳየው እምነት እና ፍቃደኝነት በጣም እናመሰግናለን" ሲል ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ዜኖትራንስፕላንቴሽን ህይወት ያላቸው ሴሎችን ወይም የአካል ክፍሎችን ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ መተካት ነው። =================== For more upcoming news Join now and invite to others👇👇👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Hammasini ko'rsatish...
" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡ ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦ ➡️ 61  ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣ ➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣ ➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡ ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል። ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል። " የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል። #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
#AddisAbaba “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው ” - ኮማንደር ማርቆስ ኢዩኤል ታዬወርቅ የተባለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጣበት ከህንፃ ላይ በወደቀ ብረት በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ለአደጋው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፣ “ እኛ አገልግሎት አልሰጠንም ” ብለዋል። ሆኖም፣ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል። ኮማንደር በሰጡት ምላሽ፣ “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው። 4 ሰዓት ላይ ነው የሞተው በሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ” ብለዋል። “ ሟቹ ኢዩኤል የሚባል ልጅ ነው። እድሜው 23 ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እንደሆነ ነው የተነገረኝ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ አደጋው የደረሰው “የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው” ሲሉ ተናግረዋል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ሟቹ የኪነህንፃ  (Architecture) #ተመራቂ ተማሪ እነደነበር ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ አስታውቆ፣ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። “ ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር የሄደ ሲሆን፣ በማግስቱ ከታናሽ ወንድሙ ጋር እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝ ከፍተኛ ፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ  ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል ” ብሏል ዩኒቨርሲቲው። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ብሔራዊፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች በወረቀት እና በበይነ መረብ (ኦንላይን) የሚሰጠው የፈተና መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
Hammasini ko'rsatish...
🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
የተቆጣ በሬ ባለቤቱን ወግቶ መግደሉን የኮንታ ዞን ፖሊስ አስታወቀ‼️ ነገሩ እንዲህ ነዉ በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ኮንታ ገነት ቀበሌ ነዋሪ አቶ ፍቃዱ ማሞ አንድ የእርሻ በሬ አላቸዉ እሳቸዉ ሻኛዉን እያሹ ቀንበር ከጫንቃዉ በማድረግ ከሌላኛዉ በሬ ጋር ጠምደዉ ያርሱበታል።    የበሬዉና የአቶ ፍቃዱ እርሻ ካላቸዉ ጠምደዉ እያረሱ እርሻ ሳይኖር ሲቀር በሬዎቻቸዉን ጥሩ ሳር ያለበት እያሰሩ ይንከባከቧቸዋል።ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሬዉ ያለወትሮዉ ይጮኸል ጥሩ ሳር ወዳለበት ቀይሩኝ በሚል ድምፁን እየሰሙ የነበሩት አቶ ፍቃዱ የታሰረበትን ገመድ ፈተዉ ሻኛዉን ለመዳበስ ሲሞክሩ በሬ ተቆጣ ተቆጥቶም አላበቃም ግለሰቡን በቀንዱ ወጋቸዉ።    መሬት ለመሬት እያንከባለለ በእግሩ መሬቱን እየጫረ በቀንዱ እያነሳ ከመሬት ያፈርጣቸዉ ጀመር።በድንጋጤ የተዋጡት አድኑኝ ሲሉ ተጣሩ ቤተሰቡ ከያለበት ወጣ በሬዉ ቁጣዉ በረታ ደጋግሞ መዉጋቱን ቀጠለ ግለሰቡ ድምፅ አላሰሙም።  መንደርተኛዉ ተሰባስቦ በሬዉን በድንጋይ በዱላ አባረሩት ተጎጂዉ ህይታቸዉ አለፈ።    ጉዳዮ ፖሊስ ዘንድ መረጃዉ ደረሰ ፖሊስ ደርሶ ህ/ሰቡን አስተባብሮ በሬዉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ተደርጎ ከበረት እንዲዉል ተደረገ። ፖሊስ አንዳንድ ጊዜ የምናሳድጋቸዉ የቤት እንስሳት ዉሻ፣ድመት በግና በሬ የመቆጣት ባህሪ ስለሚያሳዩ ህዝቡ ሁሌም መጠንቀቆ ይኖርበታል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል መረጃዉ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ።  ፎቶ:-ከማህበራዊ ሚዲያ @ZION_NEWS
Hammasini ko'rsatish...
👍 2