cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Hear me out

ምርጥ ፅሁፎችን አስተማሪ እና አዝናኝ ታሪኮች የምናጋራበት አዳማጭ የሚሹ ሹክሹክታዎች የሚሰማበት..... ኢስላሚክ ቻናል። ሀላል ኮንተንቶችን በማሰራጨት ሙስሊም ነቢባን የማብዛት ህልማችንን ለወዳጆ ሼር ማረግ ድጋፎን ማሳየት አይርሱ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
199
Obunachilar
+124 soatlar
+17 kunlar
-130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ከሰኞ እስከ ሰኞ‼ ============= ✍ ተከታታይ ወርቃማ ቀናት ከፊታችን፦ √ ሰኞ: የሙሐረም 9ኛ ቀን፣ √ ማክሰኞ: የሙሐረም 10ኛ ቀን → የዐሹራእ ጾም፣ √ ረቡዕ : የዐሹራእ ቀጣይ ቀን፣ √ ሐሙስ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን፣ √ ጁሙዓህ: የአያሙልቢዽ የመጀመሪያ ቀን (ሙሐረም 13) √ ቅዳሜ: አያሙልቢዽ፣ √ እሁድ: አያሙልቢዽ፣ √ ሰኞ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን አላህ አላህ! እንኳን ተጨማሪ ሰበብ ኖሮት ሙሐረምን ሙሉውን መፆም ይወደዳል። የቻልን እንጹም፣ ሌላውንም እናመላክት። አላህ ያግራልን። ©ሙራድ ታደሰ @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሰዎች ቃል እንደ ቋጥኝ ነው በጀርባህ ከተሸክምከዉ ይሰበራሀል! ከእግርህ በታች ከሆነ ግን ግንብ ሠርተህ ታሸንፋለህ።
Hammasini ko'rsatish...
Today's fact: Isn't it strange that our ancestors had to fight off wild animals to survive, but today, intangible stresses like pressure of exams, career deadlines or less attention on social media can push someone to the brink? How far we've come, yet how fragile we've become.🧐 @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
እህቴ 🌼9 ..በረሱሉ ዘመን አንዲት እህትሽ በአዉድቅ በሽታ ትሰቃይ ነበር። ያቺ ሴትም የልብና የሰዉነት ሀኪም ወደሆኑት ወደ ረሱሉ በመምጣት ችግሯን ተናገረች። ረሱሉም ሁለት ምርጫ ሰጧት። አንድም ዱዓ አድርገዉላት ከበሽታዉ መዳን፣ አልያም በበሽታዉ ላይ ታግሳ ጀነትን ማግኘት። ሙዕሚኖች ዘንድ ከጀነት በላይ ዉድ ነገር አልነበረምና ታግሳ ጀነትን ማግኘትን መረጠች። ላኪን ሌላ ችግር አለ። እቺ እህትሽ አዉድቁ በሚጥልባት ወቅት የተወሰነ አካሏ ይገለጣል፣ ፀጉሯ የተወሰነዉ ክፍት ይሆናል። ይህ እንዲቀረፍላት ረሱሉ ዱዓ እንዲያረጉላት ጠየቀች። ረሱሉም ዱዓ አረጉላት። አይገርምም! እቺ ሴት ኮ አዉድቁ ጥሏት ሰዉነቷ ቢገለጥ እንደማትጠየቅ ታዉቃለች። ግን እቺ እህትሽ በክብሯ አትደራደርምና አዉድቅ ጥሏት እንኳን የትኛዉም የሰዉነቷ ክፍል እንዲታይ አትፈቅድም። እህቴ! አደራሽን በመሸፈኛሽ አትደራደሪ! በሂጃብሽ አትደራደሪ! ፀጉርሽን ለወንዶች ክፍት አታርጊ! አደራሽን ወንዶች በአይናቸዉ በልተዉ ሚጨርሱሽ ተራ ዕቃ እንዳትሆኚ! : እህቴ! አላህ ዘንድ ትራክሺያለሽና ራስሽን አታርክሺ! ያንን ዘመናችን ካመጣዉ ሂጃብ መሳይ ነገርም ተጠንቀቂ! ያን ከመሸፈን ይልቅ ሳቢ ሆኖ ምትጋጌጪበትን ሂጃብ ተጠንቀቂ! ያ ፀጉርሽን ሸፍኖ ሰዉነትሽን ወጥሮ ሚይዘዉ ልብስ ሂጃብ አይደለም። ሂጃብ ማለት ራስሽንም መላዉ አካላትሽንንም እኩል መሸፈን ሚችለዉ ነዉ። ያ አንገትን፣ ጭንን፣ እጅን የሚያሳየዉማ ዘመናዊ ሂጃብ እንጂ ሸሪዓዊ ሂጃብ አይደለም። ሰሀቢያት እህቶችሽ የሂጃባቸዉ ጉዳይ በጣም ያስጨንቃቸዉ ነበር። የሆነ ጊዜ ኡሙ ሰለማ የሴት ልጅ ከእግሯ በታች ልብሷን ምን ያህል ማርዘም እንዳለባት ረሱሉን ስትጠይቅ ረሱሉ አንድ ስንዝር እንደሚበቃ ነገሯት። እሷ ግን አንድ ስንዝር ሴት ልጅን ሙሉ በሙሉ መሸፈን አይችልም ብላ ተሟገተች። ረሱሉም አንድ ክርን እንዲያረጉና ከዚያ እንዳያስበልጡ ነገሯት። አጀብ! ኡሙ ሰለማ የዚህ ዘመን ወንዶች ልብስ አንድ ክርን ወደታች ረዝሞ፣ በታቃራኒዉ የሴቶቹ ደግሞ አንድ ስንዝር ወደላይ አጥሮ ብትመለከት ምንትል ይሆን? የሆነ ጊዜ ሀፍሳ ቢንት አብዱረህማን ኢብኑ አቡበክር ፊቷን የተወሰነ የሚያሳይ ስስ የፊት መሸፈኛ ልብስ ለብሳ አክስቷ አዒሻ ጋር መጣች። አዒሻም ተቆጥታ 'አላህ ሱረቱል ኑር ላይ ያወረደዉን አታዉቂም እንዴ?!' ብላ ልብሱን በጫጨቀችዉ። ኡሙና! የኛ ዘመን ሴቶችን ሂጃብ ብታዪ ምን ትዪ ይሆን! የሴት ሰሀቢያት ኮ አላህ ከነዉር ሁላ ካፀዳቸዉ ከረሱሉ ሳይቀር ይሸፋፈኑ ነበር። ከረሱሉ ከተሸፈኑማ ከሌላዉ ተራና ስሜቱን መቆጣጠር ከማይችል ከኛ ዘመን ወንድ መሸፈን ይበልጥ ዋጂብ መሆኑን ለማስረዳት ሰነድ መጥቀስ ያለብኝ አይመስለኝም። ይህ ትዉልድ አለቅጥ በሸህዋ የተፈተነ ትዉልድ ነዉ። አንቺ ቢያንስ ባለመገላለጥ ትዉልዱንም ራስሽንም ከፊትና ጠብቂ! ልክ እንደ ፋጢመቱ ዘህራዕ በህይወት እያለሽ አይደለም.. ሞተሽ እንኳን ሰዉነትሽ መገላለጡ የሚያሳስብሽ ጠንካራ ሴት ሁኚ! በአላህ እምላለሁ! ክብሯን ምትጠብቅን፣ ሂጃቧን ምታጠብቅን ሴት ማንም ተራ ወንድ አይቀርባትም። ይህ የምድር ህግ ነዉ! ዝንቦች ሁሌም ቆሻሻ ላይ ነዉ የሚያርፉት። ያቺ ብዙ ሰዉ ስለሚያወራትና ወንዶች ስለከበቧት  ዉብና እድለኛ አርጋ ራሷን የምታስብ ሴት ትገርመኛለች። እቺ ሚስኪን ሴት የአንድ ነገር ዋጋ ሲረክስ ፈላጊዉ እንደሚበዛ ዘነጋች እንዴ? በዕዉነታዉማ ዉዷም፣ ዉቧም፣ በዱንያም በአኼራም እድለኛዋ ያቺ በሂጃብ የተዋበችዉ የአላህን ትዕዛዝ የጠበቀች ሴት ናት። @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
አላህ ሆይ! ~ከትንሹ ሞት በኋላ ሕይወት ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡ተጨማሪ ወዳንተ የመመለስ ዕድል ስለሠጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡ ኖረን ኖረን መሞታችን አይቀርም፤ መመለሻችንም ወዳንተው ነው፡፡ አምላኬ ሆይ! ~ካንተ ተነጥለው የሚኖሩት ኑሮ የሰቀቀን መሆኑን አውቃለሁ፡፡ሁሌም በሀሳብም ሆነ በተግባር ካንተ ጋር ከተሳሰሩት አድርገኝ።አንተን ማውሳትን ሱሴ አድርግልኝ፣ዘወትር አመሰግንህ ዘንድ አንቃኝ፣ ጌታዬ ሆይ! ~ከሚዘናጉት፣ ከሚጃጃሉትና ጊዜያቸዉን በከንቱ ከሚያጠፉት አታድርገን፡፡ኸይርህን አትንፈገኝ፣ ሲትርህን አታንሳብኝ፣ ካነሳኸኝ በኋላ አትጣለኝ። ያ ረብ ካንተ ዉጭ የሌላ ባርያ አታድርገኝ ፡፡ • ወዳጆቼ! የጠዋት ዱዓ ጉልበት አለዉና ወደ አምላካችሁ ተንፍሱ፡፡ የጠዋት አዝካሮችን በማድረግም ቀናችሁን አስዉቡ፡፡ @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
If you have no connections, build them. If you have no money, work, save, invest. If you have no friend, be a better person. If you have no talent, practice more. If you have no idea, walk more. If you have no confidence, commit more. If you have no clarity, write more. If you have no connections, build them. If you have no money, work, save, invest. If you have no friend, be a better person. If you have no talent, practice more. If you have no idea, walk more. If you have no confidence, commit more. If you have no clarity, write more. Don't sit and blame other things for ur own decision. ur the only person responsible for all things that are happening to u!✨ @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
ዝናብ ሲመጣ ብዙ ሰው ለማሳለፊያ ጃንጥላ ይይዛል፡፡ ሲያባራ ጃንጥላ ሸክም ይሆንበታል፡፡ ይህን ጃንጥላ የት ልጣለው ይላል፡፡ ከሰዉም መካከል ችግር ሲገጥመው ባንተ የሚጠለል አለ፡፡ ወጀቡን  ለማሳለፍ። ጥቅሙን ሲጨርስ ግን ለዐይን ይጠላሃል፡፡ ሊርቅህ ይጣደፋል፡፡ Allahume estur 🤲 @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
👏 3
እህቴ 🌸⑧ የበፊት ሰዎችን ታሪክ ለማንበብ እንደምትጓጊና ታሪካቸዉን ማወቅ እንደሚያስደስትሽ አዉቃለሁ። የዛሬዉ ቀጠሯችን በእስልምና ታሪክ ዉስጥ ካለፉት እጅግ ምርጥ ከሆኑት ሴቶች መሀል የአንዷ ነዉ። ዛሬ የጀግንነት፣ የቆራጥነት ተራራ ስለሆነችዋ ሴት እናወራለን። ዛሬም በፊርዖን ቤተ መንግስት እንቆያለን። እቺ ሴት በዱንያ ላይ እንደሱ ያለ ክፉ ሰዉ አልፎ የማያዉቅ ሰዉ ሚስት ናት። የዚያ በሞኝነትና በቅጥፈት ‘እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ!’ ሲል ህዝቡ ዉስጥ ዉሸት የሚለፍፈዉ ሰዉ ሚስት ነች። ይህ ሞኝ ሰዉ እንዲያመልኩት ብሎ ሰዎችን ያስገድዳል። እምቢ ያሉትን ይገላል፣ ይቀጣል። ቤተመንግስቱ በበደል የተሞላ ነበር። እንደዚያ ከመሆኑም ጋር ግን በዚህ ቤተመንግስት ዉስጥ የሱን አምላክነትን ማይቀበሉ፣ አላህን በብቸኝነት የሚገዙ ምርጥ ባሮች ነበሩ። ከነሱ መሀል የራሱ የፊርዖን ሚስት አሲያ ቢንት መዛሂም ትገኛለች። አሲያ ኢማን በልቧ የገባዉ ገና በጠዋቱ ነበር። ግን ምን ያረጋል ባሏን ከማንም በላይ ዉሸታም፣ ከሀዲና በዳይ እንደሆነ ስለምታዉቅ ኢማኗን ደብቃ ቆየች። ነገር ግን ከጊዜ ብኋላ የተለያዩ ተዓምራትን በሙሳ እጅ ስታይ፣ ሙሳ በምን አይነት መረጃ ፊርዖንን እንደሚከራከርና የሀሩንን አንደበተ‘ርቱዕነትን ስትመለከት ኢማኗ ጨመረ። እሷ በንፁህ አዕምሮዋ ይህ የሚታመም፣ የሚደክም፣ የሚበላና የሚጠጣዉ ተራ ባሏ በፍፁም ፈጣሪ ሊሆን እንደማይችል ታዉቃለች። በሀቅ ሊገዙት የሚገባዉ ብቸኛ ፈጣሪ መኖሩን ታምናለች። ያ ፈጣሪም የሙሳና የሀሩን ጌታ ነዉ። ኢማኗን ለተወሰነ ጊዜ ከደበቀች ብኋላ ኢማኗ ከፍ ብሎ ልቧን በሙሉ መቆጣጠር ሲጀምር ፊርዖንን ፊት ለፊት አናገረችዉ። ያ የግብፅ ህዝብ ሙሉ የሚፈራዉን ጨካኝ ባሏ ፊት ቆማ ‘ፊርዖን ሆይ! (አልፈራህም!) ባንተ ክጃለዉ!’ አለችዉ። በሙሉ ራስ መተማመን ‘የሙሳና የሀሩንን አምላክ ተከትዬ ባንተ ክጃለሁ።’ አለችዉ። በዳይነቱን ፊት ለፊቱ ነገረችዉ። ፊርዖን የተዉሂድን ቃል በሚስቱ መስማቱ ለሱ ከባድ ነበር። ተቆጣ፣ ገነፈለ። እጅግ ከባድ ቅጣትን እሷን መቅጣት ጀመረ። የተለያዩ ቅጣትን ቀጣት። እሱም አልበቃ ብሎት ወታደሮቹን ወደ በረሃ ይዘዋት ወተዉ ወጥረዉ አራት ቦታ ላይ እስረዋት እንዲቀጧት አደረገ። ምግብና መጠጥንም ከለከሏት። ቀኑን ሙሉ ፀሀይ ዉስጥ አቆያት። በሁለተኛዉ ቀንም ከእምነቷ ትመለስ እንደሆነ ጠየቃት። በጭራሽ እንደማታረገዉ ስትነግረዉ አሁንም ያለምግብና መጠጥ እዚያ ፀሀይ ላይ ሲያሰቃያት ዋለ። በሶስተኛዉ ቀንም ወደ ቤቷና ወደ እምነቷ ብትመለስ እንደሚሻላት ነገራት። ቅጣቱን ልትቋቋመዉ እንደማትችል አሳወቃት። እሷ ግን ቅጣቱ ከኢማንና ከሰብር ዉጪ ሌላ ነገርን እንዳልጨመረላት ነገረችዉ። ፊርዖንም ከሷ ላይ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ ወታደሮቹ ትልቅ ቆጥኝን ከፍ አርገዉ አንስተዉ ጭንቅላቷን እንዲፈጠፍጡት አዘዛቸዉ። በዚህ ጊዜ አላህ እሱን የጠየቀችዉን የጀነት ቤቷን አሳያትና ፈገግ እንዳለች ቆጥኙ ተወረወረ። አላህም ዝንተ ዓለም በየ ሚህራቦች በሚቀራዉ ቁርዓን ዉስጥ የምርጥ ሴቶች ምርጥ ምሳሌ እንደሆነች አወሳት። ለነዚያ ላመኑት ምርጥ ሞዴል እንደሆነች ተናገረላት። ያቺ ከጀነት በፊት የአላህን ጉርብትና የፈለገችዋን እንስት አላህም መሬትና በዉስጧ ያሉትን ነገር በሙሉ እስኪወርሳት ድረስ የምትወሳ እንቁ ሴት አድርጎ አቆያት። እህቴ! እስልምናሽ ደምሽ፣ አጥንትሽ እንደሆነ እንዳትዘነጊ። ለዚህ እስልምናሽ የምትከፊዪዉ የትኛዉ ዋጋ ቀላል ነዉ። አሲያ ኮ የግብፅ ሴቶች አለቃ ነበረች። አንድን ነገር ስትፈልግ በጣቷ መጠቆም ብቻ ይበቃት ነበር። የዱንያ ጀነት በእጆቿ ላይ ናቸዉ። ነገር ግን እሷ ዱንያን ስትመለከታት ጠፊ እንደሆነችና አላህ ጋር ያለዉ በረከት ዘላለማዊ እንደሆነ አወቀች። ዘላለማዊዉን መርጣ ጠፊዉን ተወች። እህቴ ሆይ! ዲንሽን ለዱንያ ብለሽ አትሽጪ! 🌻ከአላህ የሚያርቅሽን ሀራም ምግብን አትመገቢ! 🌷ከአላህ የሚያርቅሽን የትኛዉንም ፍቅረኛ አትቅረቢ! 🌹ኸይርሽን ሟጧ የሚበላን የትኛዉንም ስብስብ አትቀላቀዪ! 🥀እነሱ ፊት አላህን መታዘዝን የምታፍሪበትን የትኛዉንም ጀመዓ ራቂ! 🍁የአላህን ዉዴታ የሚያሳጣሽን የትኛዉንም ድርጊት አትፈፅሚ! 🍂ሁሉም ሴቶች በፋሽን ተታለዉ ሂጃባቸዉን ቢተዉ እንኳን አንቺ ግን እንዳተዩዉ! 🍃ሁሉም ሴቶች ላይፍ ነዉ እያሉ ወንድ ቢጨብጡም፣ ሙዚቃ ቢያዳምጡም፣ ከወንድ ጋር ተቃቅፈዉ ቢወጡም አንቺ ግን የአላህ ዉዴታ በመሻት ፅኚ! አዉቃለሁ! ይህን ሁላ ስታረጊ ያለጓደኛ ብቻሽን ትቀሪያለሽ። ግን ኮ አንቺ የዱንያን ጀነት ለአኼራ ጀነት ብላ የተወች የአሲያ ልጅ ነሽ። አንቺስ ልክ እንደሷ ከሰዉ ፍቅርና ቀረቤታ በፊት የአላህ ፍቅርና ቀረቤታን አትፈልጊም እንዴ? እህቴ ይህን አትርሺ! ሰዉ ብቻዉን ይሞታል፣ ብቻዉን ይቀበራል፣ ብቻዉን ይነሳል፣ ብቻዉን ይገመገማል። ዘላለማዊ የሆነዉን የአላህ ቀረቤታ ጠፊ በሆነዉ በሰዎች ቀረቤታ አትቀይሪዉ! ልክ እንደእናትሽ አሲያ በአምነትሽ ጉዳይ ላይ የማንንም ወቀሳ አትፍሪ! ከሁሉም በፊት የአላህ ዉዴታ ይቀድማል!! @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
3
ከተሰበሩት(በ) የጠየኩት አንድ እድል ነበር...። ሁሉንም ነገር ለማስተካከል... የተሻለ ሰው ለመሆን... ስህተቶቼን ለማረም.... የሚቆጨኝን ነገር ለመከወን.. . አንድ እድል ብቻ ነበር የጠየኩት..። . .. ... እድሌን አገኘሁት! ሁሉንም ነገር ቀድሜ አቅጄና ተሰናድቼ ስጠብቀው ስለነበር እንደሚሳካልኝ ጥርጥር የለውም። ስፍስፍ ብዬ ተቀበልኩት።! . .. ... እድሌን ገደልኩት! ሰው የመሆኔን.. ተስፋ የመዳኔን እድል... እስንትፋሱ እስኪቋረጥ ድረስ አይኖቼ እንዳፈጠጡ እጆቼን አጣጥፌ ሞቱን ታዘብኩ።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰዎች እንደ መጽሐፍ ናቸው - • አንዳንዶቹ ግልጽ ናቸው፤ ምንም የሚደብቁት ነገር የላቸዉም፤ ርዕሳቸዉን በማየት ዉስጣቸዉን ታያለህ፡፡ • አንዳንዶች ደግሞ ሽፋናቸው ሳቢ ነው፤ ግና ዉስጣቸው ቁምነገር የሌለው ይሆናል፡፡ • አንዳንዶች ደብዛዛና ቀዝቃዛ ናቸው፤ ስትቀርባቸው ፍካታቸው ይገለጣል፣ መዓዛቸው ያዉዳል፡፡ • ሌሎች ደግሞ ቀላል ናቸው፤ በአንድ ጊዜ ንባብ ትወዳቸዋለህ፣ ትቀርባቸዋለህ፡፡ • አንዳንዶች ደግሞ ከባድ ናቸው፤ ሞክረህ ሞክረህ ትተዋቸዋለህ፡፡ • አንዳንዶች ደግሞ አይገቡህም፤ እስክትረዳቸው ድረስ ደጋግመህ ማንበብ ይኖርብሃል፡፡ አንብቡ! ማንበብ መልካም ነው፡፡ ውብ ንጋት አህባብ✨😍 @lendmeurear1
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.