Dilachin General Secondary School Stakeholders
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
3 206
Obunachilar
-224 soatlar
-157 kun
-1330 kun
Postlar arxiv
27/02/2019 ዓ.ም
✍🗣📄 ለ11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በሙሉ።
📌 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ ተቀርፆ በወረደው የውጤት ማላቅ ስትራቴጂ መሰረት ተማሪዎችን ለማትሪክ ፈተና ለማዘጋጀት ዘወትር ቅዳሜ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተመረጡ መምህራን የተለየ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም ሁሉም የ11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቅዳሜው ትምህርት ላይ በሁለቱም የትምህርት ተቋማት በተመደቡት መሰረት (በአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ እና እዚው የተመደቡ ደግሞ በድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት) መገኘት ይኖርባቸዋል።
📌 በተመሳሳይ የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችም የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ በመሆኑ ይገኛሉ።
✅ በመሆኑም ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች በማጠናከሪያ ትምህርቱ ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተማሪዎችን መረጃ እና አቴንዳንስ እየተያዘ እንዲሁም ቀሪ ተማሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ቁጥር 150/2016 ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት ስር የተጠቀሰውን ትምህርት ቤቱ ባላወቀው ወይም አሳማኝ ባልሆነ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት መቅረት ፤ በሚለው መመሪያ መሰረት ከአንድ አመት ባላነሰ ሊያስቀጣ የሚችል እና ተጠያቂ የሚያደርግ በመሆኑ እሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ እየለየን ስለሆነ ተማሪዎቹ ባለመምጣታቸው ለሚፈጠረው ክፍተትና ተጠያቂነት ት/ቤቱ ኋላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ።
**ት/ቤቱ
ቀን 26/02:2019
ለ11 እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች በሙሉ
የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ጠዋት ከ1:00 እስከ 2:30 ዘወትር ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የ11 እና 12ኛ ክፍል ሁሉም ተማሪ መገኘት ይኖርባችኃል።
👉 ስለሆነም በማጠናከሪያ ትምህርቱ እየተሳተፉ ያሉ ተማሪዎች መረጃ እየተያዘ እና ፈተናም እየፈተንን ስለሆነ ባለመምጣታችሁ ለሚፈጠረው ክፍተትና ተጠያቂነት ት/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ።
Tutorial Program for week 8 Day 3,
🌞🌅 Morning Tutorial
📌 Biology (for Natural) ✅
📌 Mathematics (for Social) ✅
ቀን 25/02/2019 ዓ.ም
ድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የሒሳብ ትምህርት የ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር በዛሬው እለት የተካሔደ ሲሆን ይሄው መሰል የጥያቄና መልስ ውድድር በእንግሊዝኛ ትምህርትና በሌሎችም የትምህርት ክፍሎች በሁሉም የክፍል ደረጃ የሚቀጥል ይሆናል።
ት/ቤቱ
24/02/2019
🗣ማስታወቂያ
ለ11-12ኛ ክፍል ተማሪዎች
📌 የ12ኛ ክፍል ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ አካል የሆነው የሰኞ ረቡዕ እና አርብ የጠዋት ማጠናከሪያ ትምህርት ነገ ረቡእ ጥቅምት 25/2019 ስለሚቀጥል 1:00 ላይ በሰአቱ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።
📌ለወላጆች፡-
የተከበራችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን በተገለፀው ስዓት መሰረት ዘወትር ሰኞ ፣ ዕሮብ እና አርብ ጠዋት ከ1፡00 እስከ 2፡15 ድረስ መደበኛ መማር ማስተማር ከመጀመሩ በፊት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን አውቃችሁ ልጆቻችሁን በስዓት እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ :-
ጥብቅ ስም ቁጥጥር ይደረጋል
Tutorial Program for Week 8 Day 2, Morning tutorial
English (for Natural),
Geography (for social)
22/02/2019
🗣ማስታወቂያ
ለ11-12ኛ ክፍል ተማሪዎች
📌 የ12ኛ ክፍል ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ አካል የሆነው የሰኞ ረቡዕ እና አርብ የጠዋት ማጠናከሪያ ትምህርት ነገ ረቡእ ጥቅምት 25/2019 ስለሚቀጥል 1:00 ላይ በሰአቱ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።
📌ለወላጆች፡-
የተከበራችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን በተገለፀው ስዓት መሰረት ዘወትር ሰኞ ፣ ዕሮብ እና አርብ ጠዋት ከ1፡00 እስከ 2፡15 ድረስ መደበኛ መማር ማስተማር ከመጀመሩ በፊት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን አውቃችሁ ልጆቻችሁን በስዓት እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ :-
ጥብቅ ስም ቁጥጥር ይደረጋል
Tutorial Program for Week 8 Day 2, Morning tutorial
English (for Natural),
Geography (for social)
ቀን 24/02/2019
የተማሪ መማክርት ክበብ በዛሬው እለት ምስረታ ማካሄድ ችሏል።
📌 የስራ ክፍፍል ማድረግና ውጤታማ ስራ ወደፊት ለመስራት በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ከስምምነት ደርሰዋል።
ት/ቤቱ
ቀን 24/02/2019
የተማሪ መማክርት ክበብ በዛሬው እለት ምስረታ በማካሄድ ችሏል።
📌 የስራ ክፍፍል ማድረግና ውጤታማ ስራ ወደፊት ለመስራት በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ከስምምነት ደርሰዋል።
ት/ቤቱ
ቀን 24/02/2019 ዓ.ም
✍📄Dilachin General Secondary school Students After Class Program
📌 የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ አንዱ አካል የሆነው የማክሰኞና ሐሙስ የተማሪዎች የከሰአት የጥናት መርሃግብር ያለምንም መቆራረጥ እየተካሄደ ይገኛል።
ት/ቤቱ
ቀን 24/02/2019 ዓ.ም
✍📄Dilachin General Secondary school Students After Class Program
📌 የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ አንዱ አካል የሆነው የማክሰኞና ሐሙስ የተማሪዎች የከሰአት የጥናት መርሃግብር ያለምንም መቆራረጥ እየተካሄደ ይገኛል።
ት/ቤቱ
22/02/2019
🗣ማስታወቂያ
ለ11-12ኛ ክፍል ተማሪዎች
📌 የ12ኛ ክፍል ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂ አካል የሆነው የሰኞ ረቡዕ እና አርብ የጠዋት ማጠናከሪያ ትምህርት ነገ ሰኞ ጥቅምት 23/2019 ስለሚቀጥል 1:00 ላይ በሰአቱ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።
📌ለወላጆች፡-
የተከበራችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን በተገለፀው ስዓት መሰረት ዘወትር ሰኞ ፣ ዕሮብ እና አርብ ጠዋት ከ1፡00 እስከ 2፡15 ድረስ መደበኛ መማር ማስተማር ከመጀመሩ በፊት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን አውቃችሁ ልጆቻችሁን በስዓት እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ :-
ጥብቅ ስም ቁጥጥር ይደረጋል
Tutorial Program for Week 8 Day 1, Morning tutorial
Chemistry(for Natural),
History (for social)
ቀን 20/02/2019
🗣📄ማስታወቂያ ለት/ቤቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ።
📌 እንደሚታወቀው በአዲስ መልክ የወረደውን የስራ ተግባር ትምህርት መነሻ በማድረግ ት/ቤቱ በአካባቢው ካሉ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር የኮሌጆቹንም ባለሙያዎችን ት/ቤታችን ድረስ በመጋበዝ በሙያ ትምህርቶች ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እና ግንዛቤ ለተማሪዎቻችን እንዲሰጥ በማድረግ እንዲሁም ፀጋዎቻችንን በመለየት አብዛኛው ተማሪዎቻችን ባሳለፍነው ሳምንት ምርጫቸውን አከናውነዋል።
📌 ት/ቤቱም የተማሪዎችን ውጤት መነሻ በማድረግ ያለንን የሰው ኋይልና ግብአት መሠረት በማድረግ በሁለቱም ዲፓርትመንቶች አራት አራት የሙያ ትምህርቶች በ2019 ዓ.ም እንዲሰጡ ወስኗል።
በዚህም መሠረት:-
✅ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ላሉ ተማሪዎች
1. Wood work
2. Building Electrical Inastalation
3. Web Design
4. Community Health Service
✅ በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ላሉ ተማሪዎች
1. Journalism
2. Accounting and Finance
3. Marketing and sales management
4. Hotel Operation
👉 በዚህ መሠረት ተማሪዎች ተቋሙ ለመስጠት በወሰነው የስራና ተግባር ትምህርቶች አብዛኛው ተማሪ በመመዝገብና ምርጫውን በማስተካከል ትምህርት የጀመረ ቢሆንም እጅግ ጥቂት ተማሪዎች በራሳቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታ በመቅረትና በተለያየ ምክንያት ምዝገባ አለማከናወናቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
በመሆኑም በነገው እለት ቅዳሜ ጥቅምት 21/02/2019 ዓ.ም ከማላቂያ ትምህርት ጎን ለጎን ትምህርታችሁን እየተማራችሁ (አዲስ ከተማ የምትሄዱም እዚሁ ድላችን ት/ቤት) የማጠናከሪያ ትምህርቱን እየተማራችሁ ከላይ ከተገለፁት የትምህርት አይነት አንዱን ብቻ እየመረጣችሁ ር/መ/ራን ጋር በመመጣት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
❌ ማሳሰቢያ ከነገ ቡኋላ ምንም አይነት ምዝገባ የማናካሂድ በመሆኑ በእለቱ ባለመምረጣችሁና ባለመመዝገባችሁ ከዚህ ቡኋላ ት/ቤቱ ኋላፊነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን።
***ት/ቤቱ
20/02/2019 ዓ.ም
ለነገ 21/2/2019 ዓ ም ልዩ ትኩረት
ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች❗️❗️
የተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በተቀየሰው ስትራቴጂ መሠረት እየተተገበረ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ነገ 21/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ ስለሆነ በተመደባችሁበት መማሪያ ክፍል ቀድማችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
በድጋሜ ጥብቅ ማሳሰቢያ ለወላጆች፡-
የተከበራችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን በተገለፀው ስዓት መሰረት ዘወትር ቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱን አውቃችሁ ልጆቻችሁን በሰዓቱ እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
እስከ አሁን ድረስ በተቀመጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ስትራቴጂ ፕሮግራም መሰረት ያልተሳተፋችሁ ተማሪዎች የትምህርት ብክነት እያስከተላችሁ ስለሆነ በአቴንዳንስ ቁጥጥር መሰረት ተጠያቂነት የሚኖር መሆኑን እንገልፃለን።
ድላችን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
