cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አምደ ተዋህዶ ሚድያ

🌼በደብራችን አመታዊ ክብረ በዐላት ፣ልዩ ፕሮግራሞች፣ ምርቃት ፣ ሰርግ እንዲሁም የህብረት መርሐግብሮች ላይ የሚኖረንን ማስታወሻ፤ እንዲሁም ማስታወቂያ የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው።🌹 https://www.instagram.com/amde_tewahdo_media https://tiktok.com/@amed_tewahido በኢንስታግራም ና በ ቲክቶክ ይከተሉን🙏

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
285
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
+530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
#የአባላት ጉዞ ዋሻ ተክለ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
sami altmchgnm mnm leza new bedenb yalserahut ngerew ledani
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
† ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ † 🕊 የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ አማርኛ እንገልጠዋለን? ¤ ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው? ¤ የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ? ¤ ይልቁኑስ የርሱን ፲፬ [14] ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም:: ቅዱስ ዻውሎስ ከነገደ ብንያም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ፫ [3] ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ፵፪ [42] ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ፰ [8] ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ:: ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን [የዓለም መጨረሻ] ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ፳፭ [25] ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ:: እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ፷፯ [67] ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል:: ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው::
Hammasini ko'rsatish...
6
Photo unavailableShow in Telegram
#ሐምሌ 5 በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው። በረከታቸው ይደርብን አሜን!! ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት የዮና ልጅ ስምዖን ጴጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው። በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ አድጐ፣ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ሃምሳ ስድስት ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል። (ማቴ. ፲፮፥፲፯ ፣ ዮሐ. ፳፩፥፲፭) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሠራው ስሕተት ንስሐ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የእርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል። በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል።        #መልካም__ቀን🙏
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 2
እንኳን ለሰንበት ት/ቤታችን 20ኛ አመት የምሰረታ በዓል አደረሳችሁ🌹🌹
Hammasini ko'rsatish...
4
እነዚህም መርሀ ግብራት 🌹 ሐምሌ 14 ልዩ የአባላት ጉዞ 🌹 ከሐምሌ 19 - 21 ልዩ የአውደ ምህረት ጉባኤ 🌹 ሐምሌ 21 ጠዋት የደም ልገሳ 🌹 ሐምሌ 28 ጠዋት ልዩ የወላጆች ጉባኤና ከሰዓት ልዩ የኪነ ጥበብ መዓድ። 🌹 ከነሐሴ 5 - 12 "አንድነታችን ለቤተክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ አውደ ርዕይ 🌹 ነሐሴ 12 ትላልቅ ሰዎች የሚገኙበት የፓናል ውይይት 🌹 ነሐሴ 19 ልዩ የምስጋናና የመዝጊያ የአዳራሽ መርሃ ግብር ናቸው። 🌹እነዚህ ሁሉ የእናንት ልዩ ተሳትፎና እርዳታ ስለሚጠይቅ እንደ ባለ ልደት በንቃት እንድትሳተፉ እንጠይቃለን። 🌹ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ቤተመጽሐፋችንን አጠናቀን ለንባብ ዝግጁ ለማድረግ በምናደርገው እንቅስቃሴ የሚጎሉንን 👉 በር 👉 ጠረጴዛና 👉 ወንበር እንዲሁም ለሌሎችም ለሚያስፈልጉን ጉዳዮች በ ንግድ ባንክ (1000502871057 Abrham tamerat&Desta merga) እገዛ እንድታደርጉልን/ እንድታስደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን መልካም በዓል። የሰ/ት/ቤትና 20ኛ ዓመት ኮምቴ  ሰብሳቢ             🌹እንግዳወርቅ አየነው🌹
Hammasini ko'rsatish...
7👍 1
ውድና የተከበራችሁ የአምደ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ እንኳን ሰ/ት/ቤታችን ለተመሠረተበት 20ኛ ዓመት መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ🙏 በዛሬ ቀን በወንድማችን አብርሃም ዘውዴ መሪነት ሸራ ወጥረው እህት ወንድሞቻችን ለኛ ዛሬ መሰባሰቢያና ሕይወት ማግኛ የሆነችውን የአምደ ተዋህዶ ጎጆ የቀለሱበት ቀን ነው። ይህችን ቀን ስናስብ የኛን በተመቸ ወንበር ላይ መቀመጥ፣ በማያፈስና ተሰብስበን የማንሞለው ሰፊ አደራሽ ውስጥ መማርና ማጥናት ከማሰብ ዘወር ብለን በሸራ በተወጠረና ጎርፍ በሞለው ደሳሳ ጎጆ፣ በተጋደመ ቦለኬትና ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ሲማሩና ሲያጠኑ የነበረበትን የመፈቃቀርና የመተሳሰብ ጊዜ በማሰብ እኛ ያለን መንፈሳዊ ሕይወት 20 ዓመት ያስቆጠረና በትንሹም ቢሆን መገልገያ ንዋያት የተሟሉለትን ሰ/ት/ቤት ይመጥናል ወይ ብለን እንጠይቅ። መልሱን ለራሳችን ለማንኛውም 20 ዓመት አስቆጥረናል 20 ዓመት እንዳስቆጠረ ሰ/ት/ቤት ለመንቀሳቀስ የሚጎድሉንን መንፈሳዊ ሕይወት፣ መንፈሳዊ እውቀትና ማኅበራዊ ሕይወት ለመኖር ካሁኑ እንድንንቀሳቀስ ወንድማዊ ምክሬን እየለገስኩ የ20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ከሃምሌ 14 እስከ ነሃሴ 19 ለአንድ ወር በተዘጋጁት ልዩ ልዩ መርሃ ግብር ላይ በንቀትና በእንደራስ መንፈስ እንድትንቀሳቀሱ ለማሳሰብ ወዳለሁ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 3
አነዚህም መርሃ ግብራት 1. ሃምሌ 14 ልዩ የአባላት ጉዞ 2. ከሃምሌ 19 - 21 ልዩ የአውደ ምህረት ጉባኤ 3. ሃምሌ 21 ጠዋት የደም ልገሳ 4. ሃምሌ 28 ጠዋት ልዩ የወላጆች ጉባኤና ከሰዓት ልዩ የኪነ ጥበብ መዓድ። 5. ከነሃሴ 5 - 12 "አንድነታችን ለቤተክርስቲያናችን" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ አውደ ርዕይ 6. ነሃሴ 12 ትላልቅ ሰዎች የሚገኙበት የፓናል ውይይት 7. ነሃሴ 19 ልዩ የምስጋናና የመዝጊያ የአዳራሽ መርሃ ግብር ናቸው። እነዚህ ሁሉ የእናንት ልዩ ተሳትፎና እርዳታ ስለሚጠይቅ እንደ ባለ ልደት በንቃት እንድትሳተፉ እንጠይቃለን። ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ቤተመጽሐፋችንን አጠናቀን ለንባብ ዝግጁ ለማድረግ በምናደርገው እንቅስቃሴ የሚጎሉንን 1. በር 2. ጠረጴዛና 3. ወንበር እንዲሁም ለሌሎችም ለሚያስፈልጉን ጉዳዮች በ ንግድ ባንክ (1000502871057 Abrham tamerat&Desta merga) እገዛ እንድታደርጉልን/ እንድታስደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን መልካም በዓል። የሰ/ት/ቤትና 20ኛ ዓመት ኮምቴ  ሰብሳቢ             እንግዳወርቅ አየነው
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ በአምደ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት አባላት ጉዳይ ክፍል የተዘጋጀ መጠይቅ

ይኽ መጠይቅ በአባላት ጉዳይ ክፍል ተዘጋጅቶ የቀረበ ዓላማውም በሰ/ት/ቤቷ ያሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና ፈተናዎችን ለመቃኘት ያስችል ዘንድ የተዘጋጀ መጠይቅ ሲሆን በነጻነት መጠይቆቹን በእውነተኛነት እና መፍትሄ በሚሉት ሀሳቦች ይሙሉ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡ ለሀሳብ ነጻነት እና ፍትሀዊነት ስም መግለጽ አይጠበቅባችሁም፡፡ ስለሰጡን ገንቢ ሀሳቦች አምላከ ቅ/ገብርኤል ይ

🙏 2
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.