cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ጥርኝ ጥበብ

ጥርኝ ጥበብ ማለት አንድም እንደ ሽቶ መልካም የጥበብ መዓዛን እናገኝ ዘንድ በሽቶ ከምንገለገልባት ጥርኝ ስም ሰየምናት አንድም ከሞላ የህይወት ስብጥርጥር እና ካልገቡን የህይወት መራራነት በጥርኝ ወይም ደግሞ በትንሽ ጥበብ እፎይታን እናገኝ ዘንድ በዩቱዩብ https://www.youtube.com/@2112-trgn-tbeb በቴክቶክ tiktok.com/@trgntbebhiluabiy

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
430
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kunlar
+230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አንዳንድ ቀኖች አሉ መከፋታችንን የሚያጋንኑ ጥቂት ቆዛዝመን ለመላቀቅ ስንራመድ የሚጨምሩ ክስተቶች ይበረክታሉ። ለመከፋቴ መጥጊያ ያልነው ያፈሳል ሌላ የሀዘን ዝናብ ያስመታናል።መተማመናችን ሁሉ ይጠፋል። እንዲሁ መቀጠል ይሻላል ጥቂቷን መከፋት ይዞ
Hammasini ko'rsatish...
🥰 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4 2👏 1
እውነት አላት... ክፍል አንድ (1) "አንዳንድ ቀን የማይጎረብጡ ውድቀቶች ሰላሞ የማይነሱ መንገጫገጮች የልብን ወዳጅ በሞት አጥቶ ወደአምላኩ ሄዴ ብሎ የሚሰማ እፎይታ ይሰማል"። አለችኝ ከልቧ እንደሆነ ፊቷ ላይ የሚነበበው የእፎይታ እና የሰላም ማገኘት አይነት ገፅታ ነው። በሁኔታዋ ደነገጥኩ ...አባቷ ከተቀበረ ገና ሶስት ቀን ታድያ ይሄ ጤንነት ነው? ወይስ ምን ያህል ክፉ ብትሆን ነው በአባቷ ሞት ማግስት ስለውድቀት እና ግልግል እየተፍለቀለቀች የምትነግረኝ... ከራሴ ጋር ሆኜ ላጠናት ልመረምራት አሰብኩ ሞከርኩ የቱም እውነት አልገለጥ አለኝ አላውቅማ እንደዚህ አይነት ሁናቴ አድሴ ነዋ አባቱ የሞተበት ልጅ ያዙኝ ልቀቁኝ በሞትኩ በሚልበት ማህበረሰብ ወጥቼ እንዴት ብዬ ይህንን ልቀበል። ኦንዳለችው እንኳን ወደፈጣሪ ሄደ ብላ ይሆን አይይይ ቢሆንም አያስደስትም በቃ ያስከፋል ስጋ አይደለም የለበሰችው ከአፈር አልተሰራችም እንዴት ልቧ ሸርተት አይልም?... መጠያየቄን አስተውላለችና "በማታውቀው እና ባልገባህ ጎጆ አትመራመር ትደክማለህ እንጅ ምንም አታገኝም ክፉ መስዬ ታይቼህ እንደሆነ አውቃለሁ እኔ የማውቀውን ብታውቅ ከሀቄ በተጠጋጋህ ነበር ግን አታውቅም ማወቅም የለብህም" ምንም ብትለኝ ሀቋ አልደርስህ አለኝ ምናልባት እውነት ይኖራታል ሀቅ ተሸክማለች ግን እውነት ሁሉ ትክክል ነው ሀቅ ሁሉ አግባብ ነው? እንጃ እውነቷ ሳይገባኝ ይቅር ይቀጥላል ...
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1
እናቴ ጎደለኝ የምለውን ስቆጥር ስለካ ስመትር ስለካ አንች ማለት ለእኔ ሙላቴ ነሽ ለካ በአለም ሁካታ እንዳልቆም ፈዝዤ ግራውን አለፍኩት ቀኝ እጅሽን ይዤ ሙሴ አልልሽ በትር የለም ከእጅሽ ኖህ አልልሽ መቼ መርከብ ሰራሽ ዳዊትነት እንዳልሾምሽ ወንጭፍ የለም ከመዳፍሽ ጠጠር የለም ከመሬትሽ ብቻ... በአንች መልካምነት ስንት ችግሮችን አለፍኩኝ ተከፍሎ ሳቅሁ ያለገደብ በሳቅሽ ጠጠር ጎልያድ ተጥሎ በመልካምነትሽ መርከብ ተሳፎሬ ተመስገን እያልኩኝ ደረስኩ እስከዛሬ ከቶ እንዳይነካካሽ ክፋት እና ነውር ጤና ይስጥሽና ሳመሰግን ልኑር #እናቴ የጌጥ የእኔ አምባር የእኔ እንቁ የእኔ አልማዝ ስንቴ ተጨንቀሻል በጭንቅ እንዳልያዝ የለፋሽው ልፋት ፍሬ እንዲያፈራ እናቴ የምወድሽ ደህና ሁኝ አደራ ✍ዐቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን)
Hammasini ko'rsatish...
1🔥 1
ይናፍቀኛል ... ስም አጠራሩ ጆሮየ ላይ ያቃጭላል ። ጎራዳ አፍንጫየን ለማሳደግ በእጆቹ ሲነካኝ" እረፍ አትረፍ" ንትርኩ ይናፍቀኛል። ተገናኝተን አማይገቡኝን ነገር እያወራኝ ከንፈሮቹን ብቻ እያየሁ ፈገግ ማለት ይናፍቀኛል ። ባለማመን ዉስጥ ያለች መዉደድ ያመጣት ቅናቱ ይናፍቀኛል ። ሲስቅ የድምፁ መጎርነን ከጥርሶቹ አሰዳደር ጋር ተዳምሮ ነፍሴ ላይ የሚፈጥረብኝ ደስታ ይናፍቀኛል ። እያጣሁት እየተለያየን መሆኑን ለልቤ ሹክ ባልኩት ቁጥር ይናፍቀኛል ። ደጀ ሰላሙ ስር ተንበርክኬ በእየየ ቤቱን ያራስኩት ዉሳኔን ለግሰኝ ብየ ነበር ። መቁረጥን ወይ መቀጠልን ። በትንሽ ቅናቱ ዉስጥ እምነት አልባነት ተጨምሮ ቀና መንገዱን በኔ መወላገድ ህይወቱ ሲንጋደድ ተሰምቶኝ ነበር። ከቤቱ ሙሉነት በ ሄዋን ስም ልቡ ውስጥ ገብቸ ጥርጣሬን የጫርኩ አሳቹ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ከጠራ ህይወቱ ድፍርሷን አኔን ጨምሬ በ ሀዘን ድባቅ እንዳስመታሁት ልቤ አረዳኝ ። መሳቅ አና ማዉራቴን ለዛ ነዉ የጠላሁት ። ፈገግታየ እምነቱን ሸረሸረበት ። ለሰዎች ቅርብነቴ የልቤን ሰዉ ለጥርጣሬ አጋለጠዉ። ልባምነቱ ከኔ እልህ ጋር አይወዳደርም። ግልፅ አንደበቱ ከኔ ዝምታ ጋር አይታሽም። ቀስ በቀስ ማዉራት ጀምሬ ነበር። ለማንም ካላወጣሁት እኔነቴ ጋር እያስተዋወኩት ነበር። ከረሳሁት ፍቅር ጋር ተላትሜ እሱን ስለማግባትም አልሜ ነበር ። ለተከታታይ ቀናቶች ዝምታን አርምሞን ከመረጥን በኋላ ሰላም አየተሰማዉ እንደሆነ ስሰማ ነው ልቤ የሸሸዉ ። "ለካ ማዉራታችን ነዉ ሰላም የነሳኝ" ማለቱን ለጆሮየ ሲያቀርቡት መለየቱን የመረጥኩት ። በመቅረብ ያደፈረስኩትን በመራቅ ለማጥራት።ለዚህ ነዉ ህይወቱን ላጠራ ያልተገባሁትን እኔን ለኖርኩበት ብቸኝነት ሰጥቸ ከኔ ነፃ እንዲወጣ መለየትን የመረጥኩት ። ብቸኝነቴ ዉስጥ ለማንም እማይብራራ የሱ ናፍቆት በቀናት ብዛት በዝምታ ተጀቡኖ ወደነበርኩበት እኔነቴ እንደሚመራኝ አዉቃለሁ።
Hammasini ko'rsatish...
4👏 2🔥 1🥰 1
በሚዛን ስንለካ ስራዬ መዛኝ ነው የሰውን ክብደት ስለካ እውላለሁ። ሚዛኔ ሰውነታቸውን እኔ ደግሞ ሀሳባቸውን እንመዝናለን ሰው በጠፋ ሰዓት የማዋራት ሚዛኔን ነው። ሳቄ ነው የምላት እርሷን  ማንም እየረገጣት እየደለቃት በምትሰጠኝ ሳንቲም የእኔ ሆድ ሞልቶ ስቄ ስለምውል ሳቄ ናት።ስንት አይነት እግርን ትችላለች ስንት አይነት ጫማን ትሸከማለች አንዳንድ ቀንማ ከጫማቸው ክብደት በላይ በንፅህና ጉድለት የሸተተ ጫማ ተረግጧት ትውልና ስታስነጥስ ትሰነብታለች ያን ሰሞን እንዴት ነው የምታሳዝነኝ መሰለቻሁ።አሞኛል ልረፍ አትልም ሁሌ ትረገጥልኛለች።እንዳልኳችሁ ሳቄ ሰውነት እኔ አመለካከት እና ሀሳብ እንመዝናለን። አንዳንድ ሰው አለ የሚስቱን ሞት የልጆቹን ርሀብ በትከሻው ተሸክሞ ይመጣና ሲመዘን በኪሎው ይደነግጣል አደነጋገጡ ራሱ  አምስት ኪሎ  ያስቀንሳል።ወትሮስ የቤቱን ድምቀት የጎጆውን ምሰሶ በሞት የተነጠቀ ልጆቹ የራበኝ ሰቆቃቸውን እንደ እለት ኪዳን የሚያሰሙት ወጣት መፋፋት አምሮት ኖሯል። ሳቄ ከትከሻዋ ወርዶ አምስት ብር ሲሰጠኝ አይታ አዘነችለት "አሁን ይሄኔ እኮ ምናለ ዳቦ በገዛሁበት እያለ ነው ዝንብ ያረፈበት ያህል ሳይሰማኝ ወርዶ አምስት ብር ሙሉ ይከፍላል ምስኪን " ንግግሯ አንጀቴን ይበላኝና ልመልስለት እቃጣለሁ ከዚያ የእኔስ ልጆች ከራስ በላይ ...እተወዋለሁ። ደግሞ አንዳንድ ቀን ጅምር ኮንደሚኒየም የሚያክል ሰው ይመጣል ገና ወደእኛ ሲቀርብ ሁለታችንም እንሳቀቃለን። ሳቄ በመለኪያዋ ራሷን ስትለካ አስር ኪሎ ቀንሳለች ሰማይ የተደፋባት ያህል ሲጫናት አይጥ በወጥመድ ስትገባ የምታሰማውን ሲቃ ታሰማለች።ከብዙ የመቶ እና ሁለት መቶ ብሮች መሀከል አምስት ብር አውጥቶ ይሰጠኛል።ያኔ ነው ሳቄ ሀዘኗ የሚበረታው "ለዚህ ነው ህብረሰረሰሬ እስኪቆረጥ የተሸከምኩት"እንደማልቀስ ይቃጣታል ሚዛኔ ታሳዝነኛለች ብዙ ጉዶችን ትቸከማለች።አንዳንዴ ኢትዮጵያን ትመስላለች ብዙ ቀጫጭን ለጋሶችን በተሸከመች ሀገር ጥቂት ወፋፍራም ስስታሞች ያጎብጧታል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ሰባት ሆነን ነበር ትምርት ቤት የምንሄደው አንለያይም። እናጠናለን አቅማችን ፥ ኑሯችን ፥ ጥረታችን ተመሳሳይ ነበር። ማትሪክ ደረሰ ፤ አጠናን ተፈተንን ፤ ፕሪፕ ስንገባ ምን እንደምንመርጥ እቅዳችን አውጠነጠንን ፤ ውጤት ከብዙ ጥበቃ በሆላ ወጣ ተባለ ፤ ልንቀበል ሄድን... ሁሉም አለፉ ከኔ በቀር። ከውጤት መልስ አብርያቸው ነበርኩ እንደልባቸው ድላቸውን እንዳያጣጥሙ አደረኳቸው። ጓደኞቼ ፣የሰፈሩ ሰዎች፣ የጓደኞቼ  ቤተሰቦቾ  አይዞህ አሉኝ አዘኑልኝ። ውጤቴን ለቤተሰቦቼ አሳየኋቸው እቤት እከሌስ እከሌስ እንዴት ሆነ ሲሉኝ ከኔ በቀር ሁሉም አልፈዋል አልኳቸው። ለመጀመርያ ግዜ ከቤት መውጣት ደበረኝ። አለመርባት ስሜት ተሰማኝ.. እድል የለኝም አልኩ.. ምን አለ ሞቼ ብሆን አልኩ.. ድብርት አከሳኝ። አብሮ አደጎቼ ጋ መሆን አልፈለኩም ነበር። ኋላ የምቀር መሰለኝ ....የሆንኩትን የገጠመኝን ቀላል እንደሆነ የሚያሳምነኝ አንድም አላገኘሁም። መውደቅን ፥ ማነስን ፥ ብቻዬን ተጋፈጥኩት። እናቴ ብቻ ናት የራሱ ጉዳይ አንተ ብቻ ደና ሁንልኝ ያለቺኝ ዋናው ጤና ነው የሚቀጥለው ታሻሽላለህ አለቺኝ። ደግሜ መፈተን እንደማልችል አልገባትም ነበር። . . . አጎቴ ገራዥ ነበረው እሱ ጋ መዋል ጀመርኩ። የማታ Auto mechanic መማር  ጀመርኩ። ጎበዝ ባለሙያ ሆንኩኝ። practically እወቀቱን ሳየው ስለምውል theory ቀለለኝ። ከክፍሉ አንደኛ እየወጣሁ ስራ ቦታም ጎበዝ መካንኪ ሆንኩኝ። ብቻ መቆም ለመድኩኝ ብቻ መውደቅ ምን ምን እንደሚል ጌታዬ አስተማረኝ የወደቀ ሰው እንዴት እንደሚፅናና ተማርኩኝ መውደቅ ሁሉ መውደቅ እንዳይደለ ተማርኩ ዛሬ ሃብታም ነኝ። የመኪና  'spare part' አስመጪ እና ላኪ ሆኛለሁ። ጌታ ኋላ የቀረን ግምባር ቀደም ማድረግ እንደሚችል ፤ በሁሉም ሰው  የታዘነለትን ፥ በሁሉም ዘንድ የሚያኮራበት ሰው ማድረግ እንደሚችል አይቻለሁ። ያኔ ብቻዬን ስሆን የተሰማኝ ውድቀት የወለደልኝ ጥንካሬ እና ብስለት ዛሬ ድረስ ስንቴ አሻግሮኛል...! አንዳንዴ ተለይቶ የመውደቅ መጨረሻ ድልም ሊሆን ይቻላል!!   
Hammasini ko'rsatish...
👍 5🔥 1🥰 1