cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group https://t.me/Mezmur_Zedawit

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
235
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 1 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ ናትናኤል +"+ +በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: +ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: +ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ): አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: +በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: +ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል:: +ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: +ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ ክርስቶስ) መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: +የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል:: ❖እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከበረከቱም አይለየን:: =>ግንቦት 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ (ቀናተኛው ስምዖን) 2.ቅዱስ ሚናስ ባሕታዊ 3.ቅዱስ ቀርጢኖስ ሰማዕት 4."400" ቅዱሳን ሰማዕታት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ 2.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት) 3.ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ 4.ቅድስት እንባ መሪና 5.ቅድስት ክርስጢና =>+"+ ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልዾስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ' አለው:: +"+ (ዮሐ. 1:48-51) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Hammasini ko'rsatish...
††† እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ኤርምያስ ††† ††† ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በስድስት መቶ አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካህናተ እስራኤል አንዱ ነበር:: እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕፃንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማኅጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: (ኤር. 1:5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከሰባ ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል:: ዘመኑ ዘመነ-ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው:: የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ በ722 አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው:: በኋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ:: ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ በ586 ባቢሎን አወረዳቸው:: ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብጽ ወረዱ እንጂ አልተማረከም:: በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት : ነቢይ : መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ : ሕዝቡን ከሰባ ዓመታት በኋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል:: ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው:: በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት : ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል ሰባ ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት:: ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ሃምሳ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ : በመጽሐፈ ባሮክ : በገድለ ኤርምያስ : በዜና ብጹዐን : በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል:: ††† ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ††† ግንቦት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ (ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 2.ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ 3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ 5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ ††† "ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል : ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር : ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና : በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም::" (ማቴ. ፳፫፥፴፯-፴፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/mezmur_Zedawitt
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

👍 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌷እንኳን ለዳግማ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !        ✨እሑድ ሰንበት ➡️በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹በኋላ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ልትመሰክሩ፤ ልታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ➡️ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ ➡️እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ መልካም በዓል ዕለተ ሰንበት 😍
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ❤️ እንዲህ ያስተምረናል +++ ለራስህ ነው +++ 👉አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ 👉 ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ 👉ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ 👉 ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ 👉ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡ 👉ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ 👉 ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ 👉እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡ https://t.me/mezmur_Zedawitt
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

1
✨ግንቦት ልደታ✨ 🌿🌿🌿🌿🌿በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🌿🌿🌿🌿🌿 🕊እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት አደረሳችሁ አደረሰን🕊 ❤❤❤❤❤❤"ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም"❤❤❤❤❤❤❤ " የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው። " " ዳግመኛም የአንበሶች ልጅ ነሽ እልሻለኍ ፤ የልደትሽ ዜና እንደ አንበሳ ጩኸት እንደ ሴት አንበሳ ድምፅ ነውና ፤ ይሁዳን አባቱ ያዕቆብ የአንበሳ ግልገል ብሎታልና [ዘፍ ፵፱፱] ፤ ስለዚኽም የአናብስት ልጅ አልኹሽ ሰሎሞን እንዲኽ ሲል እንደተናገረ ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ ከአንበሶች ጕድጓድ ወጥተሽ ነዪ [ማሕ.፬፥፲] ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው።]🙏🙏🙏 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ➥ በቀደመው ዘመን በዘመነ ብሉይ “የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል” ይከበር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡ ይህ በዓል እስከ ጌታችን ዘመንም ይከበር ነበር፡፡ /ዮሐ 10፥22/ ➥ በሐዲስ ኪዳን “የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት /መዝ 111፥7/ በተአምረ ማርያም ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሠላሳ ሦስት በዓላት አሏት፡፡ ከእነዚህ በዓላት ሁሉ አስበልጣ የምትወደው በዓለ ልደቷን እንደሆነ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ከዐረብኛ ወደ ግእዝ በተተረጎመው እመቤታችን በተለያዩ ሀገራት ያደረገቻችዉን ገቢረ ተአምራት በኢትዮጵያ ከተፈጸሙት ጋር አካቶ የያዘው ተአምረ ማርያም በዝርዝር ያስረዳል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተቱና ምሉዕነት የሌላቸው ታሪኮች በአዋልደ መጻሕፍት እንደሚሟሉ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ዳዊት የሚናገረው መጽሐፈ ዜና መዋዕል “የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክ እንዲሁም በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ላይ ተጽፏል” /1ኛ ዜና 29፥29/ ◉ የእመቤታችን ታሪክ የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ “ሃና” እና ኢያቄም /ዮአኪን በሚለው ስም የሚጠሩ ሲሆን ሃና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረውን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሃና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ አርጋብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡🙏 ስለ ሃና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደው መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸው በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከውና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረው ታሪክ ተመሳሳይ ነው፡፡ እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሀሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሀሳቦች የሚያነሱ ሲሆን አንደኛው “ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች” የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ “ከሦስተኛው ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀው ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሃና የክሩሲድ ቤተ ክርስቲያን በታች ነዉ የተወለደችው” የሚል ነው፡፡ የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ በናዝሬት ነው ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸው ተጠብቀው የቆዩ ከመሆናቸው አንጻር ተአማኒነታቸው የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፍንቄ በስተ ምስራቅ ይገኛል፡፡ “ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ” የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምስጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ /መኃ 4፥7/ እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነው፡፡ በ 6ኛውና 7ኛው መቶ/ክ/ዘመን ነው የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደውና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነው ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸውን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸው የሚከበረውም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ነው፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀውልት በማቆም ዐሥር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡ ◉ የድንግል ማርያም ልደት ለምን ይከበራል? ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” በማለት ተነግሯል /ሉቃ.1፥14/ ምክንያቱም ቅደስ ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን፡፡ ስለሆነም ከጌታችን ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነው፡፡ የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል “ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” ብሏል፡ ፡ እመቤታችን ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፡ በቅድመ አያቶቿ በነቴክታና ጰጥሪቃ ህልም እንደታየችው በሌሊት የምታበራ ጨረቃ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጅ ሁሉ ደስታ ነው፡፡ ✝✝✝✝✝ ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት : 🌹“መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸው” 🌹“ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል” 🌹 “ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ” ብለው ተናገሩላት ቅድስት ድንግል ማርያም ልደቷ የትንቢታቸው ፍፃሜ ነውና ታላቅ ደስታቸው ነው፡፡ /መዝ86፥1፤ ኢሳ 11፥1
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
እንኳንለብርሃን እናት ለእመቤታችን የልደት በዓለ ክብር አደረሳችሁ። "የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው። በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።" የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን https://t.me/mezmur_Zedawitt
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከጌታችን ትንሣኤ በኋላ ያሉት ዕለታት ስያሜ ሐሙስ ፦ አዳም፦ አዳም የመጀመሪያ ሰውና የሰው ሁሉ አባት ነው፤ በ፮ኛው ቀን የተፈጠረ የሰው ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የሰው ዘር ሁሉ ከእርሱ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው የተስፋ ቃል ስለመፈጸሙ፤ ዘፍ. ፫÷፲ አዳም ከነልጆቹ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻ ስለመውጣቱ ይታሰብበታል፡፡ ክርስቶስ በተነሳበት በአምስተኛው ቀን ሐሙስ አዳም ይባላል፤ ጌታችን አዳምን ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ቃል ገብቶለት እንደነበር በቀሌምንጦስ ተጽፏል፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ትእዛዙን በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት አስወጣቸው። ኩፋ.፬፥፲፮፤ዘፍ.፫፥፳፫ "ብዙ ተባዙ" ያለው ቃል እንዳይቀር በምድር ላይ ወርደው ልጆችን ወለዱ ይላል፡፡ የተወለዱትም ልጆችም በቁጥር ፷ እንደሆኑ ፩መቃ ፳፰፥፮ የተወለዱት ልጆች ደጎችና ክፉዎች እንደ ነበሩ በአቤልና በቃየል ታውቋል። ዘፍ. ፬፥፰ አዳም በዚህ ዓለም ፱፻፴ ዓመት ኑሮ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፵፻፭፻፸ ሚያዚያ ፮ ዐርፏል፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ከትንሣኤ በኋላ ያለው ሐሙስ “አዳም ሐሙስ” ይባላል፡፡ በዚህ ዕለት ክብር ይግባውና በገነት ዛፎች መካከል “አዳም አዳም”እያለ ይመላለስ የነበረው “የእግዚአብሔር ቃል”ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው"በማለት የገባውን ቃል ኪዳን መፈጸሙንና አዳምና ልጆቹም በጌታችን ትንሣኤ ነጻ መውጣታቸውን እናስባለን፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ ህግንና ነቢያትን ለመሻር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ”እንዳለ ማቴ ፭፥፲፯ “እንደ እግዚአብሔርም መልካምና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ”ስለማይፈልግ ነው የሚለውን የዲያቢሎስን የማታለያ ቃል ሰምተው አምላክነትን ሽተው የሳቱትን አዳምንና ልጆቹን ዘፍ ፫፥፭ ሊያድን ቃል በገባላቸው ቃል መሠረት ከእነርሱ ንጹህ ዘር ሆና ከቀረች ኢሳ፩፥፱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው ሆኖ አድኖታል፡፡ በሞት ባርነት ተይዞ ለነበረ የሰው ልጅም ሰው ሆኖ በሞቱ ሞትን ድል በመንሣት በትንሣኤው ይህንን የሰውን ትንሣኤ በማረጋገጥ የገባለትን ኪዳን ፈጽሟል፡፡ ውድ ክርስቲያኖች!!! የክርስቶስ ትንሣኤ ለአዳም የተገባለት ቃል ኪዳን የተፈጸመበት ብቻ ሳይሆን የነቢያት ትንቢትና የሐዋርያት ትምህርት እንዲሁም የእምነታችንም አማናዊነት የተረጋገጠበት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- “ክርስቶስ ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት”ማለቱ ለዚህ ነው፡፡ ፩ቆሮ ፲፭፥፲፫ በትንሣኤው ወደ ሕይወት የመራን አምላካችን ስሙ ይመስገን!!! አርብ፦       ይቆየን https://t.me/mezmur_Zedawitt
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

👍 1
እንኳን ለእናታችን ለልደታ ማርያም በዐለ ልደቷ አደረሰን ዘመናችንን ህይወት መንገዳችንን የደስታ ከክፉ ነገሮች የምናመልጥበት ታድርግልን ሀገር ሀይማኖታችንን ከሚሰማው ከሚታየው ሁሉ ትጠብቅልን። https://t.me/mezmur_Zedawitt
Hammasini ko'rsatish...
መዝሙር ዘዳዊት

የዚህ ቻናል አላማ አርቶዶክሳዊ ምክሮችን መመካከር እኔ ስለእምነቴ ይመለከተኛል ሃላፊነትም አለብኝ የሚል ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ላይ ግንዛቤ መፍጠር የዳዊት መዝሙራት ይለቀቁበታል ቢያንስ በቀን አንድ መዝሙር እናነባለን አንብበንም ወደ ሕይወታችን እንቀይራለን ይሄ ቻናልይጠቅማቸዋል ብላችሁ የምታስቧቸውን ወዳጆቻችሁን ጋብዙልን!!! Tele group

https://t.me/Mezmur_Zedawit

✝✝✝ እንኳን አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ቅዱስ አልዓዛር "*+ =>ከትንሳኤው ሳምንት ይህች ዕለተ ረቡዕ "አልዓዛር" ትባላለች:: ጌታችን ከሙታን ስላስነሳው ዕለቷ የሐዋርያው መታሰቢያ ሆናለች:: +ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: +በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ:: +ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው:: +ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ. 11) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: +"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ:: +ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው) +ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል:: =>የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን:: =>+"+ ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Hammasini ko'rsatish...
✝✝✝ እንኳን አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ቅዱስ አልዓዛር "*+ =>ከትንሳኤው ሳምንት ይህች ዕለተ ረቡዕ "አልዓዛር" ትባላለች:: ጌታችን ከሙታን ስላስነሳው ዕለቷ የሐዋርያው መታሰቢያ ሆናለች:: +ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: +በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ:: +ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው:: +ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ. 11) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: +"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ:: +ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት::
Hammasini ko'rsatish...