cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ያሲራ(ታጋሽ ሴት)

ለሁሉም ጊዜ አለው... 🙏🙏 ፩) አጫጭር ታሪኮች ፪) ግጥሞች . . .

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
259
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kunlar
+430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 81 ......... በሙሉ ነፍሴ ማዳመጥ ጀመርኩ.. የምር ግን ተለያየን? በቃ ? መለያየት እንደዚህ ቀላል ሆነ? መልሰን ላንገናኝ ተለያየን?... ፊዮሪ ዛሬ ለሞት መድሀኒት እንኳን ብፈልጋት የማላገኛት ሴት ሆናለች ትኑር ትሙት እንኳን አላውቅም... ምናልባት ራሷን አጥፍታ ቢሆንስ? አይ! ምን አይነት የሞኝ አስተሳሰብ ነው የማስበው? መሞት ከፈለገች ምን ከሀገር አስወጣት እዚሁ ቀባሪ አላት አገሯ ላይ ነበር ራሷን የምታጠፋው... ማን ያውቃል ይሄኔ የራሷን ህይወት ጀምራ ይሆናል አግብታም ይሆናል ወይ መሀን የሆነችበትን ኬዝ ውጪ ታይታው ወልዳም ይሆናል... እንጂ እኔን ትታ ሄዳ እኔን የምትጠብቅ ሞኝ አይደለችም ብትጠብቀኝ እዚሁ ከጎኔ ሆና ነበር ወደሷ እስክመለስ የምትጠብቀኝ እንጂ አድራሻዋን የማያውቅ ሰው ይመጣል ብላ አትጠብቅም እናም አመንኩም አላመንኩም ፊዮሪ ሌላ ህይወት ጀምራለች ! መራር እውነታ ቢሆንም መቀበል አለብኝ እውነታ ደግሞ መቼም ጣፋጭ ሆኖ አያውቅም እና ዮኒ ያለው እውነት ነው እኔም የራሴን ህይወት መጀመር አለብኝ "life is portion" ብሏል ጆርጅ ልክ ሳይሆን አይቀርም ህይወት እጣፈንታ ነች እና የኔ እጣ ፈንታ ፊዮሪ ላይ ባይሆን ነው...እንጂ ከዛ ሁሉ አመት ቦሀላ መልሰን ተገናኝተን ችግሮቻችን በተፈቱ ማግስት ያውም ልክ ባልሆነ መንገድ መልሰን አንለያይም ነበር እና እጣዬ ማነው ? የት ነው? ምንድነው? እንዴትስ ነው እጣዬ ቢመጣ እንኳን የምቀበለው ? " በመሀል ዮኒ እጁን ሲያወዛውዝ ከሀሳቤ ነቃሁ " የት ሄድክ ሰውየው? " አለኝ " እዚሁ ነኝ " አልኩት " ምን እያሰብክ ነው ? " አለኝ " ምንም " አልኩት " ደሞ እዛ ከሄድክ ምን አስተማሩብኝ እኔን ነው የምትሸውደው? ምንም ይለኛል እንዴ? " እያለ አልጎመጎመ " ስለ ፊዮሪ " አልኩት " ስለሷ ምን? " አለኝ " የራሷን ህይወት ጀምራ ቢሆንስ? " አልኩት " ትጠራጠራለህ እንዴ? ሴት እኮናት " አለኝ " እንዴት እርግጠኛ ሆንክ? " አልኩት " መቼም ውጪ ሄዳ አንተን አትጠብቅም ብትጠብቅህ እዚሁ ነበር የምትጠብቅህ ብትመጣም 1 አመት ሙሉ አያስችላትም ነበር ስለዚህ ሌላ ህይወት ጀምራለች አግብታለች ምናልባትም ወልዳለች " አለኝ የራሴን ሀሳብ ሲደግምልኝ ገረመኝ "ይሆናል" አልኩት " ነው እንጂ " አለኝ ብዙም ሳንቆይ ተነስተን ወደቤት ሄድን... በዚህ ሁኔታ ድፍን 4 አመታት አለፉ በመጠበቅ ብቻ ምንም ህይወት ህይወት የሚሸት ኑሮ ሳልኖር ካጣኋት ጊዜ ጀምሮ አምስት እያልኩ አመታትን መቁጠር ጀመርኩ በቃ 5 አመት እንደዚህ ቀልድ ነው? ዮኒ እሷን ስለመርሳት ሳያነሳ መሽቶ ነግቶ አያውቅም እሱም ጉትጎታውን ሳያቆም እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ካየኋት እንደቀልድ 5 አመታት ተቆጠሩ የሆነ ቀን ከስራ ስመለስ ሰኢድ ጋር ወረድኩ ዳሱ ውስጥ ነው " ሰኢዶ" አልኩት " ወዬ " ብሎ ወጣ የተኛ መስሎኝ ነበር " ደና አመሸህ? " አልኩት " አልሃምዱሊላህ እንዴት ነህ? " አለኝ " እግዚአብሔር ይመስገን " አልኩት ወጥቶ ድንጋዩ ላይ ከጎኔ ተቀመጠ " ሰኢድ?.." አልኩት " ወዬ " አለኝ " ከ ለይላ ጋር እንዴት ናችሁ ? " አልኩት " ጠልታኛለች ባክህ " አለኝ " አወቀችህ እንዴ? " አለኝ " አላወቀችኝም ግን ሳታውቀኝም ቀልቧ አልወደደኝም " አለኝ " የሆነ ቀንማ አውቃ ውሀ ራሱ ደፍታብኝ ነበር " አለኝ ብሽቅ አልኩ " ምን? ማንነትህን ስላላወቀች እኮነው... ነገውኑ ነው ምነግራት " አልኩት " በአላህ ናኦዴ እንዳታደርገው " አለኝ " እና እስከ መቼ? " " ራሷ እስክታውቀኝ " " ጭራሽ ባታውቅህስ? " " አንድ ቀን ታውቀኛለች " " ሳታውቅህ አንድ ነገር ብትሆንስ " " ምንም አልሆንም እርግጠኛ ነኝ እጠብቃታለሁ እናም አንድ ቀን ይሆናል" አለኝ ዝም አልኩ " እና አንተስ? " አለኝ " እኔ የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር ፊዮሪ ሌላ ቦታ አግብታ ወልዳ ቢሆንስ? " " እና " አለኝ " እሷ የራሷን ህይወት እየኖረች ይሆናል ምልናልባትም ባገኛት ልረብሻት የምችለው ህይወት " አልኩት " ይሆናል እና ምን ለማድረግ አሰብክ? " አለኝ " በቃ አልፈልጋትም ከመጣች ስትመጣ ትምጣ " አልኩት " ትጠብቃታለህ? " አለኝ " እንግዲህ እስካሁን እንዳልጠብቃት የሚያደርገኝ ነገር አልተፈጠረም " አልኩት " ቢፈጠርስ? " አለኝ "አላውቅሞ ግን መጠበቄን የማቆም አይመስለኝም ፊዮሪ ማለት ከስጋዬ አልፋ ነፍሴ ላይ የተነቀሰች ብቸኛ ሴት ነች " አልኩት " ጠብቃት የምር ከወደድካት ጠብቃት አንድ ቀን ትመጣለች ያንን ቀን ካልጠበካት ታፍርበታለህ ትፀፀትበታለህ ከጠበካት ግን ትወደዋለህ የትእግስትህ ፍሬ ይሆናል " አለኝ " ሳትመለስ ብሞትስ? " አልኩት " በሙሉ ልብህ ከጠበካት ሳታያት አትሞትም " አለኝ "እሺ " ብዬው ተሰነባብተን ወደቤት ሄድኩ የዮኒ እና የሱ ሀሳብ ፍፁም ተምታታብኝ ምንም ሳላደርግ ቀጥታ ገብቼ ተኛሁ ነጋ.. ተነስቼ የዮኒ ክፍል ስሄድ ወጥቷል ተነሳስቼ ቁርስ በልቼ ወጣሁ ከቤት እየወጣሁ በማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ አነሳሁት " ሄሎ " አልኩ " ሄሎ ጤና ይስጥልኝ አቶ ናኦድ? " " አዎ ነኝ ማን ልበል? " " ከ አሜን ሆስፒታል ነው የምደውልሎት አቶ ሰኢድ እኛ ሆስፒታል ይገኛል እና የተጠሪ ስልክ የእርሶን ስልክ ሰጥቶን ነው " አለኝ ........ ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል.... @fkerofficial
Hammasini ko'rsatish...
❤‍🔥 3👍 1
የኔን ሀይማኖት በእምነት የተቀበልኩት በስጋ ለተያዘች ነፍስ ለድነት የተጠቀምኩባት ስሙንም ጠርተው ከማያምኑት ምጠብቃት ለኔ የጠቀመችኝንም ለሌሎች ላወርሳት አንድጊዜም ለተሰጠች ሀይማንት ልጋደልላት አንድጌታ አንድሀይማኖት አንዲትጥምቀት ናት ልጅነትን ማገኝባት ሃይማኖት ብዬ ማምናት ተዋህዶ ናት እኔማውቃት የማልከዳት እግዚአብሄር የገለጠውን እውነት አሜንብዬ ምቀበልባት ስጋና ደሙንም በከብር ማገኝባት ተዋህዶ ናት የግዛቤር ቤት ቅዱሴ ናት ሁሉን ተቀባይ የምህረት ቤት ናት ፍቅር ከክርስቶስ ትትናን ከማርያም የተማርንባት እናቱ እናታችን ብለን የምኮራባት ወንጊልን አመሳጥራ ሊቃውንትን አስመርምራ ታስተምራለች ልጆቿን ሁሉ ሰብስባ። ከ@ግጥም ቁምነገር
Hammasini ko'rsatish...
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 80 ...........ከ አንድ አመት ቦሀላ.... እንደቀልድ አንድ አመት ሆነኝ ከዮኒ ጋር በየቀኑ እንደዋወላለን አልፎ አልፎም ሰፈር እየወጣ ጀማልን ያገናኘኛል ካናዳ ውስጥ ከመጣሁ ጀምሮ የ "Harris" መጠጥ ቤት ቁጥር አንድ ደምበኛ ሆኛለሁ ብዙ ጊዜ ብቻዬን ነው የምጠጣው አልፎ አልፎ አንድ አንድ ፈረንጆች እየመጡ ይቀላቀሉኛል የተለመደች በሊዝ የገዛኋት የምትመስል ባንኮኒ ስር ያለች ወምበር አለችኝ ለአንድ አመት ያለማቋረጥ የማወራው ብቸኛ ነጭ ጆርጅ ነበር እድሜውን ጠይቄው አላውቅም ግን ፊቱና አቋሙ ታይቶ ከ45 እስከ 55 የሚገመት ሰው ነው እስካሁን የማይገባኝ ፈረንጆች ቶሎ የማያረጁበት ምክንያት ነው በ 27 አመቱ እንዳገባና የ 29 አመት ሴት ልጅ እና የ 20 አመት ወንድ ልጅ እንዳለው ነግሮኛል ሲታይ ግን እንደዛ አይመስልም የመጠጥቤቱ ባርቴንደር ነው... የመጣሁበትን ምክንያት ጠይቆኝ ስለ ፊዮሪ ሁሉንም ነግሬዋለሁ ሁሌ የሚለው አባባል አለ " life is portion " ህይወት እጣ ነች እንደማለት ነው የእለት ከእለት ውሎዬ ፊዮሪን ማፈላለግና አመሻሽ ላይ Harris መጠጥ ቤት መገኘት ሆነ ዛሬ ግን መጠጥቤት የተገኘሁት እንደ ስከዛሬው መጠጥ ለመጠጣት እና የፊሪን ብሶት ጆርጅ ላይ ለመተንፈስ ሳይሆን ጆርጅን ልሰናበተው ነው... ሁሉም የካናዳ ስቴቶች ውስጥ.....Alberta,British Colombia , manitoba, nova scotia ,new Brunswick.... ሌሎችም ስቴቶች ውስጥ በጋዜጣ እና በ መፅሄት ሳይቀር አፋልጉኝ አስለጠፍኩ ግን ፊዮሪን በላሁ የሚል ጅብ ጠፋ ለጠቆመኝ ሰው 10,000 ዶላር ለመክፈል ተስማምቼ ብለጥፍም አንድ አመት ሙሉ ኮሽታ ጠፋ... እናም ነገ ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደኝን አውሮፕላን ትኬት ቆርጫለሁ የአንድ አመት ጓደኛዬን ጆርጅን ተሰናብቼው ወጣሁ .... ...ኢትዮጵያ ... ተመለስኩ... ትዝታዎቼን ወዳስቀመጥኩበት ከአመት በፊት ትቼው ወደነበረው መከራ የመሰለ ህይወት... ለካስ ተስፋም ትልቅ ዋጋ አለው ይህንን ያወኩት አገኛታለሁ ብዬ ስሄድ እና አላገኛትም ብዬ ስመለስ በተሰማኝ ስሜት ነው ዮኒ ያው ነው ልክ ትቼው እንደሄድኩት ከሱ ይልቅ ሰኢድ ፀጉሮች ላይ ነጫጭ ሽበቶች መብዛት ጀምረዋል ሁለቱም ኤርፖርት ሊቀበሉኝ መተው ነበር ጥብቅ አርገው አቀፉኝ አንድ አይነት አስተቃቀፍ ወደ መኪናው እየሄድን " አንተ ምንድነው የመሰልከው? " አለኝ ዮኒ " ምነው? " አልኩት " ነጮቹን መስለህ የለ እንዴ? ምንድነው ይሄ ደግሞ? " አለኝ ያደገ ፂሜን እየነካ " ኧ... ያው እዚህ ይደርሳል ብዬ እኮነው " አልኩት... የባጥ የቆጡን ስንዘባርቅ ሰፈር ደረስን ሰኢድን ዳሱ ጋር አውርደነው ወደቤት ሄድን " ናኦድ ለሁሉም ነገር ራስክን አዘጋጅ ሁለቱም ድርጅት ጋር ስሯሯጥ ነው የቆየሁት በዚህም ምክንያት አንተ ያንተ ድርጅት ትንሽ አመታዊ ገቢው ዝቅ ብሏል ለዛ ወምበር የምትገባው ትክክለኛ ሰው አንተ ነህ ስለዚህ ከነገ ጀምሮ ትገባለህ ... ሰሞኑን የሚመጡ የውጪ ኮንትራቶች አሉ አይተሀቸው ትዋዋላለህ ብቻ ራስክን አዘጋጅ " አለኝ " እሺ " አልኩት " ስለ ፊዮሪና ምን ወሰንክ ? " አለኝ " ምንድነው መወሰን ያለብኝ? " አልኩት " ከባድ ነው ግን ስትመጣ ቢያንስ የሆነ ውሳኔ ላይ ትደርሳለህ ብዬ ነው " አለኝ " ምንም አልወሰንኩም አላገኘኋትም " አልኩት " ስለዚህ ? " አለኝ " ስለዚህ እጠብቃታለሁ " አልኩት " እጠብቃታለሁ? አንድ አመት ሙሉ አጥፍተን የፈለካት ለመጠበቅ ነው እንዴ? "አለኝ " እና ምን ላድርግ " አልኩት " እርሳት! ከባድ ቢሆንም ተዋት በቃ የራስህን ህይወት ጀምር ይሄን ብቻ ውለታ ዋልልኝ" አለኝ " ቤታችን ናፍቆኛል ለምን አንድ ሁለት ብለን አለ ንመጣም? " አልኩት " ካልደከመህ እሺ " አለኝ ተነስተን ወደተለመደው መጠጥቤታችን ሄድን... አንድ አመት! ግን መጠጥቤቱ ሳይቀር ፊዮሪ ፊዮሪ ይሸታል ከእስር ተፈትቼ እኔ ዮኒ ክርስቲ እና ፊዮሪ የጠጣንበትን ቀን አስታወሰኝ ቤቱ ለስለስ ባለ ዘፈን ደስ በሚል ድባብ ተውጧል ዛሬ የምፈልገው እንደዚህ አይነት ድባብ ነበር ከዮኒ ጋር ዝም ዝም ተባብለን መጠጣት ጀመርን በመሀል የቴዲ አፍሮ ዘፈን ተከፈተ ስሜ የተጠራ ይመስል ወደ ሙዚቃው ዞርኩ " ተለያይተን ተቀያይመን አምና ዳግም ላላይሽ ማልኩና በፍቅርሽ ጨክኜ ብርቅሽም ግን እስካሁን ልረሳሽ አልቻልኩም ..ብሩህ ቀን ባክህ ና አልኩ እንዳይሽ ፊዮሪና ......." ለራሴ የተዘፈነ እስኪመስለኝ በነፍሴ ማዳመጥ ጀመርኩ.... ይ...ቀ...ጥ ...ላ...ል..... @yoakinnn
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
💚።።።። አልፈልግም ወረት።።።💚 አልፈልግም ወረት ያንን ደረስ መለስ ሰኞ ተሞጋግሶ በእሁድ መባጠስ ጊዜያዊ ፍላጎት ጊዜያዊ ጨዋታ እኔ አይመቸኝም ለዛ የለኝ ቦታ ካንቺ ጋራ ነገን እኔ የማልመው እስከ መቃብሬ በፍቅር መጓዝ ነው በለጋው እድሜያችን በዚህ ወጣትነት ሀ ብለን ስንጀምር የአብሮነት ህይወት የለኮስነው ፍቅር ፍሞ ተቀጣጥሎ እንቅፋት ሳይገታው ሲቀጥል አይሎ ተፈትነን አልፈን ብዙን መሰናክል በጎጆአችን ስንኖር ደስታን ስንታደል ተባርከን በልጆች ይዘን መልካም ፍሬ ማርጀትን እሻለው ከአንች'ጋ አብሬ ቆዳችን ሸብሽቦ ጥርሶቻችን አልቀው ድጋፋችን ሆነው ልጆቻችን ደርሰው እንደዛ ነው ውዴ አንችን የምስልሽ ምክንያቱም አለሜ በጣም ነው ምወድሽ ይሄ ሁሉ አልፎ የአመሻሼ እለት ግንባርሽን ስሜ እንዲ እልሻለሁው እንደ ድሮው ዛሬም ከልቤ አፈቅርሻለሁ🥰🥰😍😍
Hammasini ko'rsatish...
❤‍🔥 2
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል -79 ............የአየር መንገድ መኪና መጥቶ ፊት ለፊታችን ቆመ ሁለታችንም በጉጉት ወደመኪናው አፍጥጠን ቀረን ትንሽ ቆይታ ሂጃብ ያደረገች ቆንጆ ሴት ከኋላው በር ከፍታ ወጣች ሰኢድ ከተቀመጠበት ተነሳ " ለይላ " አለ እሱን ካየሁት ቦሀላ እሷን ደግሜ አየኋት ቆንጆ ልጅ እግር የምትባል አይነት ፀይም ሴት ነች ቁንጅና በፅይምና ላይ የመጀመሪያዬ ሳትሆን አትቀርም ስለ ሁሉም ታሪካቸው ሲነግረኝ እንዴት ስለውበቷ አጋንኖ እንዳልነገረኝ ገረመኝ አሁንም ግን ሀሳቤ ከመኪናው ላይ አልተነቀለም ፊዮሪ በሌላኛው በር ብትወርድ ብዬ ተመኘሁ ታክሲውን አሰናብታ አብራት ከነበረች ቀይ ሴት ጋር ሻንጣዋን እየጎተተች ፊት ለፊት ወዳለው ቤት ገቡ... ሰኢድ ውስጥ ገብተው የውጪ በራቸው እስኪዘጋ ድረስ እንደሆነ ተአምር ነበር ቆሞ ደርቆ ሲያያቸው የነበረው ልክ በሩ ሲዘጋ ድንገት ቁጭ አለና " ለይላ.. ለይላ እኮነች ፀ...ፀይሟ " አለኝ አወራሩ የሆነ ጨለማ ውስጥ ኖሮ ድንገት ፀሀይ ያየ እንጂ አንድ ሴት ያየ አይመስልም ለነገሩ ስሜቱን አውቀዋለሁ " ያ አላ...ህ " አለ " ቆንጆ ናት " አልኩት " ምን ጥያቄ አለው ደሞኮ አምሮባታል " አለኝ " እና ምን ልታደርግ ነው? መጣች እኮ በቃ ንገራትና አንድ ላይ ሁኑ " አልኩት " ሀሀሀ ናኦድ ደግሞ ትቀልዳለህ !" አለኝ " ኧረ አልቀለድኩም " አልኩት " እኔኮ ማደሪያ የሌለኝ ተራ ሰው ነኝ ስታስበው በምን ተአምር ነው እኔ እዚህ ውስጥ የምገባው" አለኝ " ታዲያ ማደሪያ ያጣኸው እኮ እሷን ለማዳን ነው ያንን ደግሞ ትረዳለች " አልኩት " አይ አይ... አይሆንም ናኦድ ለኔ ስላላት ጥላቻ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ እዚሁ አይኗን እያየሁ የምትተነፍሰውን አየር እየተነፈስኩ በሰላም ውዬ ባድር ነው የሚሻለኝ " አለኝ " እና በቃ? " አልኩት " አዎዋ.. ድና ማየት ነበር ምኞቴ አሁን ድናለች ስትወጣ ስትገባ እንደፈለኩ አያታለሁ " አለኝ ዝም አልኩት ግን ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን የራሴን ህይወት አስረስቶኝ ነበር ወደራሴ ስመለስ ጭንቅላቴ ላይ የተደፋው ሰማይ ትዝ አለኝ እንደምንም መሸልኝ ከነገ ጀምሮ የፊዮሪን ስልክ አፈላልጋለሁ ቢያንስ ለድርጅቷ ሀላፊዎች መስጠቷ አይቀርም ከዛ አወራታለሁ የግድ እሷን መመለስ አለብኝ የግድ! ዮኒ የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ አረማመዱ ቢሮ ተቀምጦ ሳይሆን በየቤቱ ሲለምን የዋለ ነው የሚመስለው... " ናኦዴ " አለኝ " ወዬ " አልኩት " እንደዚህ ሆነህ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል " አለኝ ሰው ቀና እና ፈገግ ስላለ ብቻ ጤነኛ የሚመስለን ሞኞች " ምን ሆንኩ ? " አልኩት " ተረጋግተሀል ቢያንስ አልጠጣህም " አለኝ " ምን ስትሰራ ውለህ ነው እንደዚህ እግርህ እስኪዝል" አልኩት " ስራ አልገባሁም የፊዮሪን ስልክ እያፈላለኩ ነበር " አለኝ ጆሮውን እንደተመታ ሰው ሙሉ ሰውነቴ ቀጣይ ንግግሩን ለመስማት ሲነቃቃ ተሰማኝ " እና ? " አልኩት "ማግኘት አልቻልኩም " አለኝ " ማለት? " አልኩት " ድርጅቷን መኖሪያ ቤቷን ሳይቀር ሸጣዋለች... ገዢዎቹም ቁጥሯ የላቸውም ፌቩንም ጠይቂያት ነበር ግን ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትሰናበታት እና አንተን ከሚያስታውሷት ሰዎች ጋር ላለመገናኘት ለማንም እንደማትደውል ነግራት ነው የሄደችው...ከሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው ስልኳን ያልጠየኳቸው ሰዎች የሉም ግን ማንም ጋር የለም..." አለኝ ቀልቤ ግፍፍ አለ አንድ የቀረችኝ ቅንጣት ተስፋ ተሟጠጠች ዝም ብዬ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ድንገት አንድ ቃል ከጭንቅላቴ አልፎ ከአንደበቴ ወጣ " ካናዳ እሄዳለሁ " አልኩት " ምን? " አለኝ " አዎ እሄዳለሁ እናም እፈልጋታለሁ" አልኩት " እውነትህን ነው? " " አዎ" " አድራሻዋም ምኗም የለህም እኮ " አለኝ " አውቃለሁ " አልኩት " እና የት ትሁን የት ትረፍ የማታውቃትን ልጅ ያውም ካናዳ ውስጥ እንዴት እፈልጋታለሁ ትለኛለህ? " አለኝ " ማድረግ የምችለው እሱን ብቻ ነው የተሻለ ሀሳብ ካለህ ንገረኝ " አልኩት " ሀሳብ ባይኖረኝም... ቢያንስ የትውልድ ሀገሯ ነው ያለነው ስለሷ በደምብ ብናጣራ " አለኝ " ምንም የምናጣራው ነገር የለም ብናጣራስ ምን ይጠቅመናል? ፊዮሪ እኮ አደለም ካለፈ ህይወቷ ከዛሬ ህይወቷ እዚህ ሀገር ያስቀረችው ነገር የለም ጠቅልላ ውጪ ለመሄድ ነው የሄደችው " አልኩት " እሺ ሄድክ እንበል እስከመቼ ነው የምትፈልጋት? በምን መልኩ? " " በሌላ አማራጭ ካላገኘኋት ሁሉም የካናዳ ስቴቶች ውስጥ አፋልጉኝ አስለጥፋለሁ " አልኩት " አንተ ልጅ ልታብድ ነው እንዴ? " አለኝ እንደመሳቅ እያለ " ያው ነው እዚህ ተቀምጬ ከማብድ እዛ አጥቻት ባብድ ይሻለኛል... ለሰውም እዛ ማንም ስለማያውቀኝ ጥሩ ነው " አልኩት " እየቀለድኩ አደለም " አለኝ " ምነው አፋልጉኝ ማስለጠፍ አይቻልም? " አልኩት " ይቻላል ግን እሷን ማግኘትን በጣም ተስፋ አታድርግ " አለኝ " እሞክራለሁ " አልኩት አይመሽ የለ መሽቶ ነጋ የአየር መንገድ ጉዳዬን አስፈፀምኩ የቅርብ ጊዜ ትኬት ገዛሁ ውሎዬ ከቤት ሰኢድ ጋር ከሰኢድ ጋር ቤት ሆነ በማግስቱ አይደርስ የለ ቀኑ ደርሶልኝ በ ሰኢድ እና በ ዮኒ ሸኚነት ኢትዮጵያን ለቅቄ ወጣሁ ለማውቃት ሴት ወደማላውቃት ካናዳ! ከ አንድ አመት ቦሀላ......... ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል... @fkerofficial
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
#ብትኖሪ_ባትኖሪ! ለእኔ ቦታ የለው መምጣትትሽ መቅረትሽ ባለሽበት ሆነሽ ቀን በቀን ልውደድሽ ማጣት አያርቀው ማግኘት አያቀርበው የፍቅር መነሻው ሚዛኑ ልብ ነው እድሜ ቢገሰግስ በዓመታት ቢቆጠር ዘላለማዊ ነው አያረጅም ፍቅር ብትኖሪ ባትኖሪ ብትርቂ ብትቀርቢ የእኔን ናፍቆ መኖር ቀን በቀን አስቢ ጎዳናው እድሜያችን ትዝታን ጎትቶ ያመጣው የለም ወይ ከትላንት አስማምቶ ።       
Hammasini ko'rsatish...
1
#እንዲህ_ብለሽ_ጻፊ በፍቅሬ ተይዞ ስሜን እየጠራ በየጎዳናው ላይ ብቻውን ሲያወራ ወፍፎ እየሳቀ አጥቶኝ ሲንከራተት ለእኔ ፍርቅር ታምኖ ሲሸለመው እብደት እኔ እስቅ ነበረ በድል ኩራት ጥርሴ ለእርሱ ጥልቅ ፍቅር ማዘን ትታ ነፍሴ በሞቀው ከተማ በትርምስ ቀለም ወድቆ በእኔ ውበት ሲስቅበት ዓለም አብሬ ስቂያለሁ መውደቁ አስደስቶኝ ስሜን እየጠራ ሁሌም ሲከተለኝ!!! ግና ግፌ በዝቶ ሞልቶ ፈሰሳና እጣውን ቀመስኩኝ በእኔ ደረሰና እኔም በተራዬ በሌላ ሰው ፍቅር ወፍፌ እዞራለሁ በወሰድኩት ብድር እርሱ ዛሬ የለም ለእውነት ኖሮ ሞቷል ህመም ስቃዩን ግን ለራሴ ውርስ ሆኗል        
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1
❤️ ፍቅር ብቻ ❤️❤️❤️❤️❤️ ባንቺ የተነሳ በእጥፍ ጨመረ የውበት ሚዛኑ፣ የፈኩት አበቦች አፍረው ተሸፈኑ፣ ዕንቡጦች ከምንጩ ደንግጠው መከኑ ድሮስ! ይሄ ሁሉ ውበት! ለጨረቃ ሰግዶ ፣ ፀሃይን ተማፅኖ ለምኖ ሚፈካ፣ በምን ጉልበቱ ነው ካንቺ የሚለካካ? እኮ በምን ጥበብ እኮ በምን ዘዴ እንኳን የአበቦቹ፣ የፀሃይቱ ምንጭ አንቺ አይደለሽ እንዴ? 💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝 🌹━━━✦◉●••┈❀┈┈••●◉✦━━━ 🌹E.T
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 78 ..............ጆሮዬ ላይ አንድ ቃል ደጋግሞ አቃጨለብኝ " አምስት ደቂቃ! " በቆምኩበት ተደግፌ ተንሸራትቼ ተቀመጥኩ ምንም ነገር ማሰብ አቃተኝ ድጋሚ በገዛ ስህተቴ ፊዮሪን አጣኋት ከተቀመጥኩበት ቀስ ብዬ ተነስቼ ወጣሁ ወደመኪናዬ ሄድኩ ዮኒ ውስጥ ነበር ሲያየኝ በሩን ከፍቶ ወጣ... " እንደፈራነው አረፈድን? " አለኝ " 5 ደቂቃ ብቻ " ብዬው መኪናዬን አስነስቼ ወደ ቤት መንዳት ጀመርኩ ዮኒ ምንም ሳይለኝ አንዴ እኔን አንዴ መንገዱን እያየ ዝም አለ እውነት ለመናገር እኔም ማውራት የምፈልግበት ሰአት ላይ አይደለሁም በጣም ተረጋግቼ እየነዳሁ እንደሆነ ለራሴም ታውቆኛል ለምን እቸኩላለሁ? ምን አስቸኮለኝ ባዶ ቤት ለመሄድ? ፊዮሪ የሌለችበት ከተማ እና ሀገር የትስ ለመሄድ ብፈጥን ምን ትርጉም አለው? መፍጠን እንኳን ለሌላ እሷን ለማግኘትም አልጠቀመኝም የትስ ለመሄድ ብፈጥን ምን ትርጉም አለው ? ሲጀመርስ የት እሄዳለሁ? በቀስታ እንደነዳሁ ቤት ደረስን እንደገባን አንድ ሙሉ ውስኪ አወረድኩ "ትጠጣለህ? " አልኩት " በመጠኑ" አለኝ አንድ ብርጭቆ አቅርቤ ከቀዳሁለት ቦሀላ ጠርሙሱን ይዤ ተቀመጥኩ " ናኦድ ተረጋጋ " አለኝ " አልተረጋጋሁም እንዴ? " አልኩት " ተረጋግተሀል ግን መረጋጋትህ ያስፈራል " አለኝ ዝም ብዬው መጠጣቴን ቀጠልኩ " የሆነ ነገር በለኝ ዝም አትበለኝ " አለኝ " ገብተህ ተኛ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ " አልኩት " ናኦድ! " አለኝ " ዮኒ!.... ግባና ተኛ " አልኩት ተነስቶ ገባ አሁን ብጮህ በጣም ደሲለኝ ነበር ግን አልቻልኩም ብጮህ እንኳን ውስጤ " አምስት ደቂቃ " እያለ ከሚጮኸው ድምፅ አልበልጥም የፃፈችልኝን ደብዳቤ አውጥቼ እንደገና ማንበብ ጀመርኩ እምባዬ መጣ ጊዜ ለመነጋገር የነፈግኳትን አምስት ደቂቃ ነፍጎ የተበቀለኝ መሰለኝ ሌሊቱን ሙሉ ምንጣፍ ላይ ተቀምጬ ስጠጣ አደርኩ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ ሳይዞር አደርኩ ዮኒ ጠዋት ሲያየኝ ደነገጠ " ሌሊቱን ሙሉ አልተኛህም? " አለኝ ዝም አልኩት " አብሬህ እንድውል ትፈልጋለህ? " አለኝ " አይ አንተ ስራ ግባ " አልኩት " እሺ ! " ብሎኝ ወጣ ሲረፋፍድ ከቤት ወጥቼ ሰኢድ ጋር ሄድኩ የተለመደች የድንጋይ መቀመጫው ላይ ተቀመጥኩ የሸራ ቤቱ ውስጥ ነበር አላየኝም የሰፈር ሰዎች በተናጥል ወደዛ ወደዚህ ይላሉ ማንም ምንም ቢያየኝ ጉዳዬ አይደለም ትንሽ ቆይቶ ከሸራ ቤቱ ውስጥ ወጣ " እንዴ? ናኦድ? " አለኝ ዝም አልኩት " ምን ሆነህ ነው? " አለኝ " ምን ሆንኩ ? " አልኩት " የሆነ ነገርማ ሆነሀል.. ምን ተፈጠረ? " አለኝ ዝም ብዬ ከቆየሁ ቦሀላ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት " አይዞን " አለኝ አይዞን!? እውነትም አይዞን ለኔም ላንተም አይዞን አልኩ በውስጤ " ናኦድ ህይወት እንደዚህ ናት አንዳንዴ የሚሰጠንን እድል ችላ ስንል ያ እድል በጊዜ ያልፋል በአንድ ወቅት እጃችን ላይ የነበረ በቀላሉ ማግኘት እንችል የነበረውን ነገር በሌላ ጊዜ ለማግኘት ብዙ ዋጋ የሚያስከፍለን ነገር ይሆናል ምንም ነገር እጅህ ላይ እንዳለ ዋጋውን እንደማወቅና እንደመጠቀም ትልቅ ጥበብ የለም አለዚያ ይረፍዳል እንደማርፈድ አስቀያሚ ነገር የለም " አለኝ ሰኢድ አንዳንዴ ንግግሮቹ ግርም ይሉኛል ከሱ አንደበት ሳይሆን ከአንድ እድሜ ጠገብ አዛውንት ወይም የሆነ ድርሰት ላይ እንደተፃፉ ቃላቶች የተሳሉ ናቸው " እንዳለመታደል ሆኖ ከረፈደስ? " አልኩት " የሰው ልጅ እስካልሞተ ድረስ ቢረፍድም አይረፍድም መድረስ ከቻልክ አሁን የረፈደው አረፋፈድ ከ ወር ቦሀላ ከሚረፍደው አረፋፈድ የተሻለ ነው " አለኝ " ልክ ነህ እኔና እሷ መካከል መቼም አይረፍድም " አልኩት "ተስፋ አትቁረጥ " አለኝ " አልቆርጥም " አልኩት ድንገት በመሀል የአየር መንገድ ታክሲ መጥቶ ፊት ለፊታችን ቆመ......... ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል... @fkerofficial
Hammasini ko'rsatish...
❤‍🔥 3👍 1
       ❤️🩵❤️🩵❤️🩵           ማነው የተረዳኝ ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ። ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ። እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ። እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው? እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ። አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።         ‌‌‌‌‌‌  ~~~
Hammasini ko'rsatish...
🥰 3🥱 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.