cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Mohammedamin Kassaw

ይህ የሙሐመድአሚን ካሳው ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው :: አላማዬ አላህ ባገራልኝ ልክ በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላትና ችግሮችን በመፍታት ረገድ የራሴን አስተዋፅዖ ማበርከት ነው :: ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በቅንነት @MOHAMMADAMMINM አጋሩኝ ::

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
777
Obunachilar
+124 soatlar
+177 kunlar
+8830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

"አላህን ያላመፅክበት ቀን ሁሉ ዒድ ነው" - ሀሰነል በስሪ @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
👍 5💯 1
ከኢድ መልስ ነው:: "ሰላማላ!" በሚል ማስክ ስር ተደብቀው የሚያወረገርጉ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በየመንገዱ ዳር ይታያሉ:: ወንዶቹን ሴቶቹ ቀለበት ቅርፅ ሰርተው ከበዋቸዋል:: ከሴቶቹ ጭብጨባ ከወንዶቹ ፉጨት የጭፈራው ማጀቢያ ነው:: ግን ለምን? ሌላው ይሁን እንበልና "ሶለላህአላ!" የሚለውን ቃል ቢያስወጡት ምን ችግር አለው? "ጀማሉልአለም!" የሚል ቃል ጀማልም ሆነ ጀሚላ በሌሉበት መነሳት ነበረበትን? ፉጨት ጭብጨባ አለፍ ሲልም ቅኝቱ የታወቀም ሆነ ያልታወቀ ማውረግረግ ከዲናችን የለም:: የሸይጧን ነው ተብሎ ተከትቧል:: ወጣቶች እናስብበት:: በስሜት ፈረስ ከመነዳት በመቆጠብ ኒዟሙን በጠበቀ መልኩ ኢዳችንን እናክብር:: @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
🔥 4👍 3💯 3
"ቸግሮኝ ነው እርዱኝ!" የሚል ሰው ለቁጥር በሚታክት መልኩ ኢዱን አስታኮ ስታዲዬሙን በዙር መንገዱን በመስመር ሞልተውት ነበር:: ከመሐከላቸው እጅ የሌለው: እግር የሌለው: በደረቱም እየተሳበ በጎዳና የሚጓዝ አለ:: ሳግ እየያዛቸው እንባም እየተናነቃቸው የሚበላ አጣን ለሚበላ የሚሆን ልመናቸው ነበር::  በዚህ መሐል የሚበላው ተርፎት የሚኖርበት ሰፍቶት ሌላን የቅንጦት ህይዎት የሚፈልግ ሰው የተሰጠውን ዘንግቶ ጎደለኝ ያለውን እያብሰለሰለ በእነዚህ ሰዎች አጠገብ ያልፋል::   ይህ በዘንድሮው ኢድ ላይ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ኢዶችም ላይ ያለፍነበት ነው:: ይህ በዘንድሮው ኢድ ላይ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት በሚኖሩት ኢዶች ላይም እንደምናዬው እርግጠኛ የምንሆንበት ነው:: በየአመቱ ሀብታም ተብዬው 10 ብር ለመቶ ሰው ይሰጣል:: ለማኙም የተሰጠችውን ብር ጨርሶ በአመቱ ከዚያው ሜዳ ይገኛል:: ያምናው ለማኝ ዘንድሮም አለ:: ያምናው 10 ብር ዘንድሮም ይሰጠዋል:: ዳግም ታልቃለች:: ዳግም ይወጣል::    "ለምን?" ብሎ መጠየቅና ሁልጊዜ ወደ ጎዳና የሚወጡ ሰዎችን ከቤት አስቀርቶ በቋሚነት እንዲሰሩ የሚደረግበት መንገድ መፈለግ ግድ ነው:: ዘንድሮ በደንብ ሰጥቶ ለከርሞ ሰጭ ማድረግ:: ልመናን ማስቀረት:: የስራን ባህል ማስለመድ ማለት ነው:: @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
የዕለቱ ማስታዎሻ - 150 ۞ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ ከእርሷ (ከምድር) ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ [20:55] @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1👌 1
‟ኢስላም በፍጹም ግልጽነትና ተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው። የሚሰብከውም በፍፁማዊ አንድነቱ ሦስትነት የሌለበት፣ በመለኮታዊነቱ ሰብአዊነት የማይንፀባረቅበት፣ በሕያውነቱ ላይ ሞት የማይከተለው፣ በጠባቂነቱ ለአፍታም ስንኳ ቢሆን የማይተኛውንና የማያንገላጀውን እውነተኛ አምላክ አላህን ነው።» — ኡስታዝ አቡ ሐይደር @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
👍 10
"ዛሬ ወደ መስጅድ ያልወሰዱ እግሮችህ ነገ ወደ ጀነት አይወስዱህም።"
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
09:04
Video unavailableShow in Telegram
የድሬ ዳዋ ከንቲባ ኦቦ ከዲር ጁሃር ከኢድ ሶላት በፊት ያስተላለፉት መልዕክት ነው:: ድሬዎች ኢድ ሙባረክ😍
Hammasini ko'rsatish...
19.37 MB
7
ብዙም አስተያየት አልሰጥም! ቪድዮውን ተመልከቱት:: በባለፈው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከሙስሊሞች በኩል የሃይማኖት አባት ብሎ ከመድረክ ያወጣቸው አባት ናቸው:: ከየኔታ ቲቪ ጋር ያደረጉት የኢድ ቆይታ ነው:: ብዙውን ነገር ትተን ተዋዱዕ ግድ ነበር:: ብቻ የሃይማኖት አባት እንደ ማዕረግ ወይም መገለጫ ሆኖ አንድ ሰው ይጠራበት ዘንድ የራሱ የሆነ መስፈርት ግድ ይለዋል:: እነሱ ለእኛ እየመረጡልንና አባቶቻችንን ገሸሽ አድርገው ፕሮግራሞቻቸውን እንደፈለጉ የሚያካሂዱ ከሆነ አንዛለቅም:: አንዘልቅምም::
Hammasini ko'rsatish...
15.13 MB
😭 2😡 1
እኔና አባቴ ለመጨረሻ ቤተሰብ ጋር የሄድኩ ግዜ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ረዥም ሰአት አወጋን። ያመው ስለነበር ትንሽ ሰውነቱ ቀንሷል። ቀን ሲከፋ ግዜ ከእድሜ ቀድሞ ያስረጅ የለ እርሱም ላይ የእርጅና ምልክቶቹ መታየት ጀምረው ነበር። ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሯችንን ደግመን ደጋግመን እየቃኘን ብዙ ተጫወትን። አልፎ አልፎ ሁለታችንም በዝምታ በሀሳብ ባህር ውስጥ እንነጉዳለን። የቀዶ ህክምና ት/ቴን እና ውጭ ሀገር ህክምና ለማጥናት ፈቃድ የሚያስገኝልኝን ፈተና (USMLE) እኩል እያስኬድኳቸው እንደሆነና ሁሉም ጥሩ እየሄዱ እንደሆነ ነገርኩት። "አንተ እያመለጥክ ነው። ህይወት አምርራ ብትታገልህም እያሸነፍካት ነው"አለኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሌም የሚለኝ ነገር "ተማር ልጄ" ነበር። "ተማር ልጄ ወገን ዘመድ የለኝ ሀብት የለኝም ከጄ "የሚለውን ይወደዋል ... ታዳ ዛሬም ድረስ ድምፁ ይሰማኛል። እኔም "አንድ ቀን ሁሉም መልካም ይሆናል። ህይወት መስመር እየያዘችልኝ ይመስለኛል" ብየው ትንሽ ዘወርወር ማለት ስለፈለኩ ወጣ ብየ ልምጣና ኋላ እናወራለን ብየው ተነሳሁ። "በቀጣይ ስትመጣ አንዲት መኪና ይዘህ መትህ አብረን ደግሞ እንዞራለን" አለኝ። ውስጤን ደስ አለው። እሱ በኔ ተስፋ ሲኖረው የኔ ደግሞ የጋራ ህልማችንን የማሳካት ፍላጎቴ ይጨምራል። መኖርህስ ትርጉም የሚኖረው የምትኖርለት አላማ የምታስደስተው ሰው ሲኖርህ አይደል። ከቤት ወጥቼ ከቅዳሜ ገበያ ት/ቤት እስከ ፒያሳ በእግሬ አዘገምኩ።ፒያሳ ከሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ ብቻየን ገብቼ በረንዳ ላይ ቁጭ ብየ ማኪያቶ እየጠጣሁ በሀሳብ ከወጭ ወራጁ ጋር እየተመምኩ እኔም አንድ ቀን ከሱ ጋር ከላይ ከታች እንደምል በህሊናየ እያሰላሰልኩ አምሽቼ ምሽቱ አይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ከለታት በአንዱ ቀን በደረሰብኝ የመኪና አደጋ ከአርቲፊሻል መተንፈሻ መሳሪያው ተላቅቄ ትንሽ ማገገም ስጀምር ዘመድ አዝማድ በተሰበሰቡበት እንዳረፈ ነገሩኝ። ስለ ሁኔታው ጠየኳቸው እኔ አድስ አበባ ሆስፒታል ስገባ እርሱ በተመሳሳይ ቀን  ደሴ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ነገሩኝ፤ ስለ እኔ ሰምቶ ነበር አልኳቸው? "እኛ መናገር አልፈለግንም ነበር። መጀመሪያ የሰማው ሊጠይቁት ከሚመጡት ሰወች ነበር።" አሉኝ "እና እሱ ጋር ማን ነበር። ሁላችሁም እኔ ጋር አድስ አበባ ከነበራችሁ?" "አንተን እንጅ እርሱ ይቀድማል ብሎ ያሰበ ሰው ማንም አልነበረም። ቢሆንም ግን ግማሻችን አንተ ጋ ግማሻችን ደግሞ  እሱ ጋር ነበርን አሉኝ። "ምን አለ መጎዳቴን ሲሰማ?"ብየ ስጠይቅ ብዙ አያወራም ነበር። አልፎ አልፎ ብቻ "ልጄ ምንም አይሆንም። እርሱ ገና ልጅ ነው ፤ እኔ ለሱ ፊዳ እሆናለሁ ፣እኔ የርሱን ሞት እሞትለታለሁ" ይል ነበር አሉኝ። በዛ በክረምት እኔም ቀን ሊወጣልኝ ነው ስል ሌላ ጨለማ ውስጥ ዳግም የገባሁበት አባቴም ከዚች አስከፊ የህይወት ውጣ ውረድ ለዘላለሙ ያረፈበት ክረምት ሆኖ አለፈ። የለፋሁበት የደከምክምበት ድንገት እንደ ማለዳ ጤዛ በኖ ሲጠፋ በህልሜ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ሲቸለስበት፣ ጉልበት ሲከዳኝና አቅም ሳጣ፣ ፍራቻና ጭንቀት ቤታቸውን ሊሰሩብኝ ዱብዱብ ሲሉ በሰወች መሀል ተከበቤ ብቸኝነት ሲሰማኝ የመናር ትርጉሙ ሲጠፋብኝና የመኖር ጉጉት ሲለየኝ፣ በሀዘንና በደስታየ በከፍታና በዝቅታየ፣ ፍራቻየንና ጭንቀቴን የማዋየው ሰው ድንገት ሲለየኝ ስሜቱን መግለፅ ከባድ የነበረ ቢሆንም  ከወደኩበት የጨለማ ዋሻ ወጥቼ ድጋሜ እንደ ንስር ለመብረር "ህይወትን ብቻህን ሁነህ ለመጋፈጥ እንዳትፈራ፣ ለራስህ ከራስህ በላይ ማንም የለህም፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ከምንም በላይ ወደ አላህ ራስህን አስጠጋ"  ብሎ የመከረኝ ምክር ለመከራ ግዜ ስንቄ፣ የድካም ግዜ ምርኩዜ፣ የጨለማ ግዜ መብራቴ ከመሆኑም በላይ ነገሮችን ቀለል አድርጌ እንዳይ፣ መንፈሰ ጠንካራና የማይሰበር ማንነት እንዲኖረኝ በአለማዊም በመንፈሳዊም ህይወት ላለኝ የዛሬ ማንነት ትልቅ አሻራውን ጥሎ ያለፈ ለጀግና አባቴ ስል ምንም እንዳልተፈጠረ ነገሮችን ተቀብየ ጉዞየን ቀጥየ ዛሬ ላይ ደርሻለሁ... ስለ ነገ ነገ ራሱ ያውቃል እያልኩ በልቤ ውስጥ ህያው የሆነውን አባቴን ዛሬ በአደባባይ ላመሰግነው ወደድኩ! እንዲሁም ለመላው የእስልምና ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Dr. Nuru Ahmed: MD, Surgeon © Hakim @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
Seid Social

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

👍 8🥰 3
ለራሱ የበላውን ክትፎ ለወንድሙ ያላበላ ኢዱን አከበረ ሊባል ነውን? አይመስለኝም:: በሉ የበላችሁ ያልበሉትን ጋብዙ:: @MohammadamminKassaw
Hammasini ko'rsatish...
😁 8