cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

📚 አሲያ ወ መርየም የሱናህ ቻናል

"ሱናህ የኑህ መርከብ ናት! የተሳፈረባት ይድናል ወደ ኋላ የቀረ ይሰጥማል" ◆ ኢማሙ ማሊክ رحمه الله ◆ 📚 📖 📚 📖 📚 📖 📚 📖📚 💡በአሏህ ፍቃድ በዚህ ቻናል በቻልነው አቅም የትክክለኛውን (የሰለፎች) ትምህርት የምንለቅበት ይሆናል። ተቀላቀሉን እንዲሁም ለሌሎች ሼር ሼር አድርጉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
602
Obunachilar
+224 soatlar
+57 kunlar
+1730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

02:40
Video unavailableShow in Telegram
ስለ ሩቃ አደምጡ 👆👆👆👆✅ በስዳት ለይ የለቹ ሩቃ የምደራግለቹ ወደፍትም ለማድራግ የሰበቹ ሴቶች ይቅርበቹ ሐጋራቹ ገብታቹ አድርጉ ወይም ከገኛቹ በሴቶች አድርጉ !︎! የለዘ ብራ ቹን ብቻ ማጫረስ እንጅ አይጣቅማቹም ቡዙ ማስፋርት ይጎለዋል!!!❌ https://t.me/Aumu_Salihat https://t.me/Aumu_Salihat
Hammasini ko'rsatish...
19.57 MB
02:40
Video unavailableShow in Telegram
ስለ ሩቃ አደምጡ 👆👆👆👆✅ በስዳት ለይ የለቹ ሩቃ የምደራግለቹ ወደፍትም ለማድራግ የሰበቹ ሴቶች ይቅርበቹ ሐጋራቹ ገብታቹ አድርጉ ወይም ከገኛቹ በሴቶች አድርጉ !︎! የለዘ ብራ ቹን ብቻ ማጫረስ እንጅ አይጣቅማቹም ቡዙ ማስፋርት ይጎለዋል!!!❌ https://t.me/Aumu_Salihat https://t.me/Aumu_Salihat
Hammasini ko'rsatish...
19.57 MB
ኢንተራንስ/ማትሪክ ❗️ ✅ውድ ለኢንተራንስ ወደ ግቢ ለምትገቡ እህትና ወንድሞቼ እነዚህ ከታች ማስቀምጥላችሁ ለጥንቃቄ ያህ ይጠቅማቹሃልና እዩት ❗️ 1⃣, በመጀመሪያ እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ ማንኛው ሚወሩ ወሬዎች ትታችሁ አላማችሁ ለፈተናው ብቻና ብቻ ይሁን ። 2⃣, ወደ ግቢ ስትገቡ ደረቅ ምግቦችን ይዛችሁ ግቡ በጭራሽ እንዳትረሱ ። 3⃣,አሪፍ ጓደኛ ምረጡ ሙስሊም ሁና/ሁኖ ስነምግባሯ/ሩ ያማረ የሆነች/የሆነ በተለይ ለእህቶች ይህንን መልዕክት ። 4⃣, በምትችይው ያህል ከዶርም ለምግብ እና ለፈተና ካልሆነ በስተቀረ እንዳትወጪ እህቴ። 5⃣, ግቢ ሲገቡ ልክ ታስሮ የተፈታ ውሻ ይመስል ከፈለጉት ጋር እንደፈለጉ የሚሆኑ አሉ እነሱም አሏህ ይመልሳቸው ከንደዚህ አይነቶቹ  ተጠንቀቂ። 6⃣, በየትኛው አጋጣሚ እና ሁኔታ ላይ ሁነሽ ብቻሽን እንዳትሆኚ ብዙ ማይታወቂ ስለ ማንነታው የሚሰበሰቡበት ቦታ ነውና በቻልሽው መጠን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሻል። 7⃣,ወንዶች ወደ ሚሰበሰቡበትም ይሁን ወደነሱ ክልል መሄድ የለብሽም ። 8⃣, ሂጃብሽን በደንብ ጠብቂ መከበሪያሽ ነውና  ። 9⃣, በተለይ ግቢ ስትገቡ መስልጠን መስሏችሁ ወደ መሰይጠን ምትገቡ በሱሪ የምትሆኑ ፀጉራችሁንም እንደፈለጋችሁ የምትለቁ እህቶች እንዲሁም በየቦታው ጥንድ ጥንድ ሁናችሁ የምትቀመጡ ጌታችሁ አሏህን ፍሩት እርሱ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካችና በነገራቶች ሁሉ አዋቂ ነውና ቅጣቱም እጅግ በጣም ብርቱ እና አሳማሚ ነው እንጠንቀቀው። 1⃣0⃣, ሌላኛው በተለይ ማታ አከባቢ ውጭ ላይ ጫዋታም እንበለው ምንም ተሰብስበው ሴትና ወንድ እንደፈለጉ ሚጨፍሩበት አለና አደራሽ አደራሽ ወደዛ ክልል እንዳትገቢ እህቴ አንተም ወንድሜ አሏህን እንፍራው ። 1⃣1⃣, አሏህ ከሸሮች ሁሉ እንዲጠብቃችሁ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማችሁ ዚክሮችን አብዙ ዱዓእም በደንብ አድርጉ ዱዓእ ጋሻችሁ/ችን ነውና። 1⃣2⃣,ሌላው ፈተናችሁን ተረጋግታችሁ ስሩ አብሽሩ እንዳትጨናነቁ አሏህ የወሰነው አይቀርም አሏህ ከናንተ ይበልጥ ለእናንተ ያውቃል የተሻለውም ከናንተ ይልቅ እርሱ ለናንተ ይመርጥላቹል እናም በርሱ ብቻና ብቻ ተመኩ ። 👌ሌላኛ ወንሞቼ እህቶቻችሁን ጠብቁ በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ ❗️❗️ والله أعلم وأحكم ✍ከወንድማችሁ ኑርአዲስ ሠልማን Https://t.me/Nuradis53
Hammasini ko'rsatish...
Nuradis🌿(ኑርአዲስ)🌿منهج السلف

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአን ፣ከሀዲስ ፣[በሰለፎች አረዳድ] ከታማኝ ኡለማዎችና፣ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል አላማዬ ሶሻል ሚዲያው ላይ ኡማውን ለማገልገል ነው! ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Rebi_zidni_Elma_Nur53 ላይ አስፍሩልኝ። ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ ጀዛኩሙል`ሏሁ ኸይራ

🎓ለኬጂ ምርቃት ሳምንትና ከዚያ በላይ መዘጋጀት❗️ 🚨 ከከሃዲያን ጋር መመሳሰሉ እንዳለ ሆኖ ቅጥ ያጣ ድግሱ ደግሞ በጣም ያስገርማል። 📮 ነገሩ እየከረረ መምጣቱን የምታውቀው አቅም የሌላቸው ሰዎች እራሱ ይህን ድግስ ለመደገስ የተለያየ ብድር ውስጥ እና ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ስትሰማ ነው። 💥 ይህ ስንል "እነሱማ  አክራሪ አጥባቂዎች ናቸው  ዲን ገር ነው"  እያላችሁ ለማሸማቀቅ እንደምትሞክሩ እናውቃለን ግን  ልክ አይደላችሁም ቢያንስ ቢያንስ  ምትመከሩትን ለመስማት ሞክሩ... ☄ የካፊሮች ወግና ባህል በልጆቻችሁ ልቦች ውስጥ ከታችሁ አሳድጋችሁ ነገ እስልምናን ተረከብ የማለት ሞራል አይኖራችሁም። ዛሬ ምትመሳሰሏቸው አካላቶች ምታልቋቸውና ዘመናዊ ናቸው ብላችሁ የምትከተሏቸው ሰዎች እነሱ ናቸው ሙስሊም ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን ያለ ምንም ርህራሄ እየጨፈጨፉ ያሉት። 💫 ላንተም ይሁን ላንቺ ለአጠቃላይ ሙስሊሞች የዝንብን ያህል ቦታ የላቸውም እኛ ግን አነገስናቸው አላቅናቸው...ሁሉ ነገራችን እነሱን ካልመሰለ አልን። 🔘 የከበረ ለዓለም ብርሃን የሚሆን እምነት ይዘን ተዋርደን መኖርን መረጥን ነብዩ ትክክል ብለዋል፦ « وجُعِلَتِ الذِّلَّةُ والصَّغَارُ على مَن خالفَ أمري » « ትእዛዜን  ለተቃረነ በሙሉ ውርደትና ማነስ ተደረገለት ❮ተገባው❯ » 🤝 የበላይነትን ከፈለክ በማንነትክ ተማመን ከፍ ያለ ነገር ይዘክ ዝቅ አትበል... 🚨 ፈረንጆቹ ምን ያማረ ሕይወት ብትኖር የተከበረ ወግና ባህል እንዲሁም ሀብት ቢኖርክ ማንነትክን እንድትረሳ ይህም ብቻ አይደለም እንድትጠላም ጭምር ያደርጉካል። ✅ ያንተን ወርቅ ድንጋይ ነው ይሉካል ያሳምኑካል የነሱን ደንጋይ ወርቅ ነው ብለው ይሰጡሃል❗️ 🤌 እናስብ እናስተንትን የበፊቶቹን የበላይ ያደረገው ነገር ብቻና ብቻ ነው...እኛንም የበላይ ሊያደርገን ሚችለው። منقول @Nuradis53
Hammasini ko'rsatish...
👉 የሙሐረም ወርና ሙስሊሞች የሙሐረም ወር ከሂጅሪያ ወሮች የመጀመሪያውና አላህ ለይቶ ካላቃቸው አራቱ ወራቶች አንዱ ነው ። ይህ ወር የሂጅሪያ ወር መጀመሪያ ቢሆንም ሙስሊሞች የዘመን መለወጫ ብለው በዚህ ወር መግቢያ ላይ የተለየ የሚሰሩት ነገር የለም ። ይልቁንም ሙስሊሞቸው ህይወታቸው የሰከንዶች ሽርፍራፊ ጥርቅም መሆኑንና እየአንዳንዱ ሽርፍራፊ በተቀነሰ ቁጥር ከእድሜያቸው እየተቀነሰና ወደ ቀብር እየተጠጉ መሆናቸውን ነው የሚያውቁት ። በመሆኑም በየትኛውም ዘመን ፣ አመት ፣ ወር ፣ ሳምንት ፣ ሳአት ፣ ደቂቃና ሰከንድ ለሚቀጥለው ዐለም መዘጋጀት እንዳለባቸው ያውቃሉ ። ከዚህ ዝግጅታቸው አንዱ ምንዳና ቱሩፋት አለባቸው በተባሉ ቦታና ጊዜያቶች የታዘዙትን መልካም ስራዎች መስራት ነው ። በመሆኑም በሙሐረም ወር ውስጥ የታዘዙ የአምልኮ አይነቶችን ይፈፅማሉ ምንዳውንም ከጌታቸው ይጠብቃሉ ። የሙሐረም ወር ከአራቱ የተከበሩ ወራቶች ለመሆኑ በመልእክተኛው ሐዲስ የተረጋገጠ ሲሆን ከ12ቱ አራቱ የተከበሩ መሆናቸው ደግሞ አላህ በተከበረው ቃሉ በተውባ ምእራፍ 36ው አንቀፅ እንዲ ብሎ ይነግረናል : – « إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ وَقَاتِلُوا الْمُشْرِكِينَ كَافَّةً كَمَا يُقَاتِلُونَكُمْ كَافَّةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ » " የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው ፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው ፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው ፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው ፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ ፡፡" የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – የተከበሩት ወራት የተኞቹ እንደሆኑ በሚከተለው በሐዲሳቸው ነገረውናል : – عن أَبي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أنه قَالَ :  " إنَّ الزَّمَانَ قَدْ اسْتَدَارَ كَهَيْئَتِهِ يَوْمَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ " متفق عليه አቡ በክረተ የተባለ ሶሐብይ እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : – " ዘመን አላህ ሰማይና ምድር ሲፈጥር ወደ ነበረበት ተመልሷል ። ( የሐጅ ወር አላህ በዙል ሒጃ አድርጎታል ። መሀይማኖች የቀየሩት ውድቅ ሆኖ ወደዛው ተመልሷልና ይህን ያዙ ) ። አመት አስራ ሁለት ወር ነው ። ከእነሱ ውስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው ። ሶስቱ ተከታታዮች ናቸው ። ዙል ቀዕዳ ፣ ዙል ሒጃ ፣ ሙሐረም , ረጀብ ደግሞ በጁማደ ሳኒና በሻዕባን መካከል ነው ። " ከእነዚህ ከአራቱ ደግሞ ሙሐረም ይበልጥ የተከበረ ወር መሆኑን ሲነግሩን የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ : – عن أبي ذر رضي الله عنه قال :  سألت النبي – صلى الله عليه وسلم – : أي الليل خير وأي الأشهر أفضل؟ فقال : " خير الليل جوفه وأفضل الأشهر شهر الله الذي تدعونه المحرم " አቡ ዘር የተባለ ሶሐብይ – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛን የትኛው ለይል ይበልጣል ? የትኛውስ ወር በላጭ ነው ብዬ ጠየቋቸው ። እሳቸውም እንዲ አሉ : – " ከለሊቱ ውስጥ በላጩ ድቅድቁ ( ከመካከለኛው በኋላ) ያለው ነው ። ከወሮች ደግሞ እናንተ ሙሐረም ብላችሁ የምትጠሩት ነው ። " በዚህ ወር ውስጥ ተወዳጅ የሆው መልካም ስራ ደግሞ ፆም ነው ። ይህንንም መልእክተኛው እንዲህ በማለት ይነግሩናል : –  عن أبي هريرة أن النبي صلى الله عليه وسلم قال :  " أفضل الصيام بعد شهر رمضان شهر الله الذي تدعونه المحرم وأفضل الصلاة بعد الفريضة قيام الليل " . رواه مسلم አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል : – " ከፆሞች ሁሉ በላጩ ከረመዳን ወር በኋላ ሙሐረም ብላችሁ የምትጠሩት ወር ( መፆም ነው) ከሶላት ሁሉ በላጩ ከፈርድ ሶላት በኋላ የለይል ሶላት ነው ። " የአላህ መልእክተኛ በሙሐረም ወር መፆም ( የቻሉትን ማለት ነው) ከረመዳን ወር ፆም ቀጥሎ የተወደደ መሆኑን እየነገሩን ነው ። በመሆኑም አንድ ሰው በሙሐረም ወር ውስጥ የቻለውን ያክል ቢፆም በጣም ተወዳጅ ነው ። እዚህ ጋር መታወቅ ያለበት ከረመዳን ውጪ ወሩን ሙሉ መፆም እንደማይቻል ነው ። በዚህ በሙሐረም ወር የዐስረኛውን ቀን መፆም ያለፈውን አመት ወንጀል የሚያስምር መሆኑን መልእክተኛው በሚቀጥለው ሐዲሳቸው ነግረውናል ። عن أبي قَتادة رضي الله تعالى عنه ، عن الرّسول - صلّى الله عليه وسلّم - قال : " صوم عاشوراء يكفِّر السّنة الماضية " رواه النسائي አቡ ቀታዳ የተባለ ሶሐብይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : – " የዓሹራእ ቀንን መፆም ያለፈው አመት ወንጀል ያስምራል ። " ከእነዚህ መረጃዎች በመነሳት ሙስሊሞች በሙሐረም ወር ከፆም የበለጠ የተወደደ ስራ አለመኖሩን ያውቃሉ ። በቻሉት አቅም በፆም ወደ አላህ ይቃረባሉ ከዚህ ውጪ አላስፈላጊ አመለካከትና እምነት ከኢስላም አንፃር ቦታ የለውም ። አላህ ከተጠቃሚዮች ያድረገን ። https://t.me/bahruteka
Hammasini ko'rsatish...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

02:29
Video unavailableShow in Telegram
🔴 الإنشغال في قيل و قال  . 🔹الشيخ عبد السلام الشويعر  حفظه الله.
Hammasini ko'rsatish...
18.55 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ሸይኽ ሷሊል አልፈውዛን አሏህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ:- "ሀያዕ (ሀፍረት) የሰው ልጅ መጥፎ ነገርን እንዳይሰራ ይከለክለዋል። ሀያዕ የሌለው ሰውመጥፎን ነገር አይፀየፍም፣ ምንም መስሎ አይታየውም።" 📑 تعليقات على الجواب الكافي صـ(224). https://t.me/UmuHassanet_UmuSekina •––––––••📖••––––––•
Hammasini ko'rsatish...
አመተ ምህረትም አመተ ልደትም ሳይሆን አመተ እርገት ነው      የሀገራችን ኢትዮጲያ ብዙ ክፍል ማህበረሰብ ኢትዮጲያ ውጪውን አለም ያልተከተለችበት ብዙ አይነት መገለጫዎች አሏት ብለው ያምናሉ። ከነዛ መካከል የራሷ የሆነ አመታት አቆጣጠር እንዳላት ያምናሉ። ይህም አቆጣጠር በሰላሳ የሚቆጠሩ የፀሀይ ቀናቶች ያሏቸው 12 ወራቶች አሉት። የወራቶቹ ስምም የተለየ እና የራሷ ነው። ሌሎች በፀሀይ መውጣት እና መግባት የሚቆጥሩ ሀገራቶች ወራቶቻቸው አንዳን ግዜ 31 ቀን እንደሚኖረው ይነገራል። የኢትዮጲያ ቆጣሪዎች ደግሞ አንዳንዴ የሚመጣውን ትርፉ አንድ ቀን ሰብሰብ አድርገው ጳጉሜ የሚባል አንዳንዶች 13ኛው ወር የሚሉት ቀሪ 5 – 6 ቀናቶች ያተራርፋሉ። ከዛ ቡሀላ ነው እንዳዲስ የቀናቶች እና የወራቶች ቆጠራ የሚጀመረው። በጣም የሚገርመው እስካሁን ያለፉት ትርፍ የጳጉሜ ቀናቶች ሲሰሉ ሰላሳ አመት ሁነው ይገኛሉ። እነሱ እንደሚሉት አመታቱን መቁጠር የጀመሩት ኢስላም ባይቀበለውም (እነሱ እንደሚሉት) ዒሳ (እየሱስ) ከተሰቀለ ግዜ ጀምሮ ነው ይላሉ። ይህ የእየሱስ መሰቀል የምህረት ፍፁም ታላቅ ክስተት ነው ብለው ያምናሉ። ለዛም ነው አቆጣጠሩን አመተ ምህረት ብለው ይጠሩታል። ግን ደግሞ ኢስላም በክስተቱም በአቆጣጠሩም ላይ የተለየ አመለካከት አለው። ክስተቱን በተመለከተ ዒሳ በፍፁም በጭራስ አልተሰቀሉም የሚል እምነት አለው። የተሰቀለው ግን ከሀዋሪያት መሀከል የሆነ ጀነትን ትገባለህ እኔን እንድትመስል ትደረጋለህ በሚል ትእዛዝ ከዒሳ በስተኩል የታዘዘ አንድ ግለሰብ ነው። ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ አይ ሰውዬው ዒሳን ለመግደል ከሚሯሯጡት መሀከል አንዱ ነው አላህ እሳቸውን እንዲያርጉ ካደረገ ቡሀላ የሳቸውን ምስል ለሱ አለበሰውና እሱን ሰቀሉት ይላሉ። ይህም ይሁን ያ ዒሳ ዐለይሒ ሰላም አልተሰቀሉም። በዚህም ክስተት ምክንያት የተማረ ማንም ሰው የለም። ስለዚህ ኢስላም አቆጣጠሩን በተመልከተ ግልፅ የሆነ ተቃውሞ አለው። አንደኛ ኢስላም የራሱ የሆነ በዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የተጀመራ ከዛም ቡሀላ ሙስሊም ሊቃውንቶች ሁሉ የተስማሞበት የሒጅራ አቆጣጠር ስላለው ነው። በመቀጠልም ደግሞ ክስተቱ የምህረት ነው ብሎ ስለማያምን። ከዚህም በመነሳት ብዙ የኢስላም እምነት ተከታዩች ይህን የአቆጣጠር ስያሜ በመቃወም ወደ አመተ ልደት ቀይረው ይጠቀማሉ። አመተ ምህረት የሚለው ከእምነታቸው ጋር ስለማይሔድ። በመሰረቱ በራሳቸው በኢስላም የሒጅራ እና የጨረቃ አቆጣጠርን መጠቀሙ ያዋጣቸዋል። ከተለያዩ የአምልኮው ስነስርአት ጋር የሚሔድላቸው ይህ ነው። የሀገሩን አቆጣጠር ከሀገሩ ብዙ ነዋሪዎች ጋር ለመግባባት ብቻ ቢጠቀሙት ችግር የለውም። ብቻ ግን አመተ ምህረት የሚለውን እንደማይስማሙበት ለመግለፅ አመተ ልደት ይላሉ። እኔ ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ አምናለው። የሀገራን አቆጣጠር ከሀገሩ ብዙ ነዋሪዎች ጋር ለመግባባት ብቻ ብንጠቀምበት ችግር የለውም። ግን ደግሞ አመተ ምህረት የሚለውን ለመቃወም የምንጠቀመው አመተ ልደት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም አቆጣጠሩ የጀመረበት ግዜ እና ስያሜያችን አይገጣጠሙም። ለምን ከተባለ አቆጣጠሩ የጀመረው እንደከሀዲያን ዒሳ ከተሰቀሉበት እንደ ኢስላም ደግሞ ዒሳ ካረጉበት እንጂ ከልዳታቸው ማለትም ከተወለዱበት አይደለም። ከልደታቸው ብለን ስንሰይም ገና ከ2016 ላይ 33 አመት መጨመር ግድ ይለናል። ምክንያቱ መቁጠር የተጀመረው ከተወለዱ ከ 33 አመታት ቡሀላ ነው። ስለዚህ ለዚህ መፍትሄ የሚሆን አንድ ሀሳብ አለኝ። ለመቃረንም በደንብ የጎላ ኢስላም ያፀደቀውን መቃረን በቀጥታ የሚገልፅ እንዲሁም ቆጠራውም ጋር የማይጋጭ የሆነ ስያሜ አለኝ እሱም አመተ እርገት የሚል ነው። ይህ ስያሜ እነሱ የሚያምኑበትን ስቅለት በቀጥታ የሚቃረን ሲሆን አቆጣጠሩም የጀመረበት ጊዜን ይገጥማል። ስለዚህ ይህን የሀገራችን አቆጣጠር ስንጠቀም አመተ እርገት ወይም በአጭሩ ደግሞ (አ እ) የሚለውን ብንጠቀም የተሻለ ነው። ✍ ወንድማችሁ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ https://t.me/abuzekeryamuhamed 📝Comment @Abu_Umer4 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.