cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Gajabba sda church members

Creater: [email protected] Add friends on this group. 👇የምንሰጣቸው አገልግሎቶች👇 👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች እናስከምጣለን። 👉 መንፈሳዊ VIDEO እና እናስከምጣለን። 👉 መንፈሳዊ photo እናስከምጣለን። 👉 ሰንበት ትምህርት ቤት PDF እናስከምጣለን። @Gajabba00sdabot

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
210
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

“እግዚአብሔር ለሕጉ ፈጣን እና ከሙሉ ልብ የሆነ መታዘዝን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ሰዎች በሰይጣን ማታለያዎች ተዘናግተው ወይም ሽባ ሆነው በኤደን ገነት ውስጥ ለሔዋን ‘ሞትን አትሞቱም’ ብሎ እንዳታለለ በሚያቀርብላቸው የተንኮል አሰራሩ ይታለላሉ። አለመታዘዝ የበደለኛውን ሰው ልብና ሕሊና የሚያደነድን ብቻ ​ሳይሆን የሌሎችንም እምነት ያበላሻል። መጀመሪያ ላይ ኃጢአት መስሎ ይታይ የነበረው ስህተት ቀስ በቀስ ይህን መልክ ያጣል፣ በመጨረሻም በእርግጥ ያ ድርጊት ኃጢአት መሆኑን እስኪጠራጠሩ ድረስ ሳያውቁት ተመሳሳይ ስህተት ውስጥ ይወድቃሉ።”—Ellen G. White, Testimo- nies for the Church, vol. 4, p. 146።
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
🔰 መዝሙሮችን ለማግኘት Full Album የሚለውን ይጫኑ 🙏 ✅ የማንን መዝሙር አልበም ይፈልጋሉ❓ 👤 ገነቱ ጋጋዶ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ኢያሱ ረጋሳ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ዳታን ደምሴ 🎸     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ተሰፋዬ ሽብሩ 🎻     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ማሞ ጴጥሮስ 🎹     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 በረከት ፈለቀ 🪗     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ጌታቸው ጉታማ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ሻለቃው ፎላሞ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ተፈራ ወ / ማሪያም 🎸     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ሳምራዊት በቀለ 🎻     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ለምለም ለብሶ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ዳግማዊት ክፍሌ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆
Hammasini ko'rsatish...
🔰 መዝሙሮችን ለማግኘት Full Album የሚለውን ይጫኑ 🙏 ✅ የማንን መዝሙር አልበም ይፈልጋሉ❓ 👤 ገነቱ ጋጋዶ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ኢያሱ ረጋሳ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ዳታን ደምሴ 🎸     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ተሰፋዬ ሽብሩ 🎻     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ማሞ ጴጥሮስ 🎹     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 በረከት ፈለቀ 🪗     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ጌታቸው ጉታማ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ሻለቃው ፎላሞ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ተፈራ ወ / ማሪያም 🎸     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ሳምራዊት በቀለ 🎻     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ለምለም ለብሶ 🎺     [Full Album] ይጫኑ 👆 👤 ዳግማዊት ክፍሌ 🎷     [Full Album] ይጫኑ 👆
Hammasini ko'rsatish...
ብዙ የተቀበለ ሰው በብዙ ለብዙ ነገር ይፈለጋል.... "Gondooru noosihu barrasi agadhanno!!" New album track #7 በጥሪ ተጀምሮ በክብር የቀጠለውን እንዲሁም በፍሬ የታጀበውን አገልግሎት ምን በማለት ጀምሬ ምን በማለት መቀጠል እንዳለብኝ አላውቅም።ነገር ግን በ12/06/2015 በሐዋሳ በሹ ኮምፕሌክስ ከነበረው የመዝሙር ምረቃና የ25ዓመት የአገልግሎት ዘመን ላይ አንዲት ነገርን መዝዤ መጻፍን ወደድሁ።መቼስ ብዙ ተዓምር ያየ ምን ብሎ መቀጠል እንዳለበት አላውቅም።ያየሁትን የ25ኛ ዓመት ጉዞ ፍሬ በዛሬው ጽሁፍ ልጀምር እንኳ አልችልም፤ተደንቂያለው።ያየሁትን ክብር አለመናገር ግን እግዚአብሔር የሰራውን አለማውራት ምስክርነት መብላት ነውና ህያው ምስክር በመሆን እንደ አንዱ ቆሚያለው።እግዚአብሔር በሰጣቸው ሁለንተናዊ አገልግሎት ያልተባረከ ያልተፈወሰ ያልተጽናና እንዲሁም ያልተኮተኮተ የለም።እግዚአብሔርም ምድርን የሞላ ብዙ ፍሬ ሰጥቷቸዋል።ክብሩን ራሱ ጌታ ይውሰድ።ከማን ጋር እንደሄዱም "ate ledo ha'nanni busha dancha la'nanni" ብለው ዘምረዋል። ጸጋ በዝቶለት ያመነው እምነት እና የሚመሰክረው እውነት ውሸት ቢሆን እንኳ ከሚከስሩ ሰዎች አንዱ ነው። በአዲሱ አልበም ላይ ደግሞ qaange illonninke qaalunni...tini heesho roortanno baalunni track 2 ላይ ብለው ዘምረዋል።በብርታት ያቆማቸው አምላክ ክብሩን ይውሰድ። የኤልቶ መልካም ተጽኖ እግዚአብሔርን እንድናይ የሚያደርግ ነው፤ አይተንም የሰማዩን አምላክ አመስግነናል።በይበልጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ(on social media) ሁለንተናዊ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነኝ።የተጋባብኝ ነገር አለና፤ኮሮና ከያዘው ሰው ጋር የዋለ በኮሮና እንደሚያዝ ሁሉ ባለ ራዕይ ከሆነ ሰው ጋር የዋለ ባለራዕይ እንደሚሆን ምስክር እንደሆንኩ ለመናገር ድፍረት አለኝ።ሰዎች evangelist eliyas batiroን ኤልቶ ሲሉት እሰማለው፤አንዲት እህት ደግሞ እንዲህ ብላለች"እናት ከኤሉ(ኤልቶ) ጋር የዋለ ልጇን በመምከር ጊዜዋን አታጠፋም" ፣በመስማት በመስማት ብዙ የሚባለው የሆነውን ነውና ብዙዎች አገልጋይ ፣ዘማሪ(የሚዘምረው በሲዳምኛ እና በአማርኛ) ፣ባለራዕይ፣መሪ ፣አስተማሪ፣መልካም ተጽኖ ፈጣሪ፣ ሙዚቀኛ(በራሱ መዝሙሮች ላይ ብዙ ግሩም የሙዚቃ intro ሰርቷል) ፣ጸሀፊ ፣ሀያሲ፣artist፣የቋንቋ ምሁር(በዚሁ ድግስ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ tuuti faarso በማለት ቃሉን ፈጥሮልናል)፣ፖስተር፣አማካሪ፣አስታራቂ፣ ወንድም ፣ አባት ብዙ ብዙ የሆነውን ተናግረዋል።ስለኤልቶዓችን ሳወራ እግዚአብሔር የሰራውን እና በህይወቱ ያደረገውን መመስከሬ ነው።እርሱም የክብር ክልሉ የእግዚአብሔር ቤት እንደሆነ ሲያስተምረን አውቃለው።እርሱም እንዳለ"ትልቁ ስኬት እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር መሆኑ ነው"።በነበራቸው ጉዞ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር መኖሩን አይቻለው።hasaambe hasaambe ብለው የእግዚአብሔር ፍቅር ተወርቶ እንዳማያልቅ track 12 ምስክርነታቸው በአዲሱ አልበም በመዝሙራቸው ላይ ይገኛል።ምንም እንኳ ከምጽፈው ጋ ባይገናኝም በሁሉም በመዝሙር አልበሞቹ ውስጥ አንድም የተውሶ ቃላትን አልተጠቀመም።የመዝሙር አጻጻፉ በቅኔ የተሞላ አስደናቂ የቃላት አጠቃቀም የተለያዩ የሙዚቃ ያለበት ያለፈበትንና የኖረውን የዘመረ መዝሙሮቹም ጆሮ የሚገቡ ልብ ላይ የሚታተሙ የወደ መስቀሉ የሚያመላክቱ ናቸው ።ስለተሰጠው ጸጋ ሰጪው ይመስገን። ብዙዎች በሚያልፉበት መንገድ ሲዋጡና ተጽኖዓቸው ሲገደብ አይቻለው።ኤልቶ በሄደበትና በተጓዘበት ተጽኖ ፈጣሪ ነው፤ብዙ ተቀብሏልና የተቀበለው ጸጋ ሰውን የሚደርስ፣በመልካም ተጽኖ የሚውጥ፣አጀንዳ የሚያስለውጥ፣የጠላትን መንደር የሚያናውጥ፣ከአብ ጎን የሚያስቀምጥ፣ለጥሪ መክፈል ያለብንን ዋጋ የሚያመላክት፣መንፈሳዊ አይን የሚገልጥ ሁለንተናዊ በረከትን ዕንድንቀበል የሚያደርግ ጸጋ አለው።ባለራዕይ አርቆ ነገን የሚያይበት ዓይን አለው ከዘመናት በፊት ያየውን እኛ ደግሞ ጸጋ በዝቶልን በምረቃ ቀን አየን።እግዚአብሔር ይመስገን።በእግዚአብሔር ምሪት የተጀመረው ጉዞ በምሬት አልተቀጠለም በክብር እንጂ። በአገልግሎት ዘመኑ ውስጥ ከፍሎ ያገለገለ መጠራቱንም ጠንቅቆ ያወቀ ሰው ነው።"ክርስቶስን የህይወታችን መርህ ካደረግን ተጽኖ ፈጣሪ እንሆናልን።"ብሏል ሚስጢሩ ይህ ነው።ብዙ የተቀበለው ጸጋ ስላለው አገልግቱም ሁለንተናዊ ነው።እግዚአብሔር ይባርካቸው በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ልል እወዳለው።አከባቢ፣ ቤተክርስቲያን ፣ሀገር እንዲሁም አለም የምትቀየረው በባለራዕይ ሰዎች ብቻ ነው።ከባለራዕይ ጎን መሰለፍ ራዕይ መደገፍ ብቻ ሳይሆን ራዕይ ማግኘትም ነው። በዚህ ሰዓትና በዚህ ጊዜ በክርስቶስ ያረፈ ብቻ እንዲህ ይላል "fooliishishi'nummo!" Ephrem mesfin
Hammasini ko'rsatish...
Repost from N/a
sticker.webp0.14 KB
ዋና ርዕስ - “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን . . .” ዕብ. 12፡1-2 የዕለቱ ጥቅስ - “ናትናኤልም። ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ መጥተህ እይ አለው” ዮሐ. 1፡47 የዕለቱ ርዕስ - መጥተህ እይ!  ሰላም ሰላም የጌታ ልጆች! በጌታ ጸጋ እንደ ደመና ስለ ከበቡን ምስክሮች እያጠናን የምንገኝ ሲሆን ምንም እንኳን ገና ምስክሮቹ ያልተነኩም ቢሆን በጌታ ጸጋ በቀጥይ ጥናት ይህንን መሪ ርዕስ ደግሞ ቋጭተን ደግሞ ወደ ሌላ ርዕስ እንዞራለን። ጌታ አብዝቶ ይባረክ! ይባርካችሁም! የዛሬዎቹ ምስክሮቻችን ደግሞ ናትናኤል እና ፊሊጶስ ሲሆኑ ውይይታቸውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ይተርክልናል። “ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ። ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው። ናትናኤልም። ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ መጥተህ እይ አለው” (ዮሐ. 1:46-47)። ሃሌሉያ! የተወደዳችሁ ወገኖች በአጠቃላይ ይህ ምዕራፍ የምስክርነት ምዕራፍ ሊባል ይችላል። ዮሐንስ “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ቁ. 29) አለ ጌታ ኢየሱስም “መጥታችሁ እዩ” (ቁ. 40) አላቸው። እዚህ ላይ የፊሊጶስን እና ናትናኤልን ውይይት በተለየ መልኩ ስናጠና የተወሰኑ ሀሳቦች ላይ ልናተኩር ይገባል። “ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል” ሃሌሉያ! ፊሊጶስ ስለ ጌታ ኢየሱስ በፊት የሚያውቀው ነገር እንዳለ እንረዳለን። ስለ ጌታ የሰጠው ምስክርነት ከተገናኙ ወዲህ ያለን ጊዜ ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ይህ በግል የሚያሳየኝ ሰዎች ስለ ዘለዓለማዊው እውነት በየትኛውም የመረዳት ደረጃ ላይ ይሁኑ በቅን ልብ እና እውነትን ለማወቅ በናፈቁ መጠን የሚጠቅምን ብርሃን ጌታ ይልክላቸዋል። አዎን ምናልባት “ኢየሱስ እርሱ መሲሁ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነው።” ወደሚለው ደረጃ አልደረሱ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን እንደ ፊሊጶስ ነገ ላይ “ሙሴ በህግ . . .” የሚሉበትን እውቀት እያከማቹስ እንደሆን? ጌታ በራሱ ጊዜ እና መንገድ በነገር ሁሉ ያሳድገን? ናትናኤል “ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?” አለ። ናትናኤልም እንዲሁ ተራ ሰው አልነበረም። “ከመልካም ምንጭ መልካም ውሃ እንደሚቀዳ፣ ጥሩ ነገር እንኳ ቢገኝ እንኳን ከ . . . አካባቢ ሊገኝ ይገባል።” የሚል መርህ በህይወቱ ነበር። ናዝሬት ለናትናኤል “ቢገኝ ቢገኝ ሌባ ብቻ የሚገኝባት ፣ ቢነሱ ቢነሱ ሀሰተኛ ነቢያት ብቻ ሊፈልቁባት የሚችሉ . . .” የሚል ደረጃ (status) የተሰጣት ከተማ ነበረች። ይህ ምናልባትም ናትናኤል ለዘመናት ባደረገው ጥናት ላይ የተመሰረተ ድምዳሜ ሲሆን ይህንን የሚስማሙ በርካቶችም ይኖሩ ይሆናል። የሆነ ሆኖ ግን ናትናኤል ሊደነቅበት የሚገባ ምክንያት ቢኖር ይህንን “ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ” እንበለው አቋሙንም ቢሆን መልሶ ለመፈተሸ፣ ለመመርመር ዝግጁ ነበር። ስንቶች ናቸው ዛሬ አንዴ “ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ አይችልም!” ብለው ከያዙት አቋማቸው የተነሳ ምንም እንኳ ቃሉ እንደሚል “እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ” (ሮሜ 1:19) ቢሆንም ህይወት የሚገኝበት መንገድ ለልባቸው ከበራ በኋላም እንኳ በሞት ጎዳና ላይ የሚጓዙ? ፊሊጶስም “መጥተህ እይ አለው” ሃሌሉያ! ፊሊጶስ ስለ ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳን የተከማቸ እውቀት የነበረው ደቀ መዝሙር ብቻ ሳይሆን በጌታ ጸጋ የተካነ መስካሪ (ውጤታማ የምስክርነት አቀራረብን ያስተዋለ) ሰው ነበር። እኔ ብሆን ብዬ አስባለሁ ለናትናኤል የተለያዩ ንድፈ ሀሳቦችን እየደረደርኩ “ከዚህ ቀደም ከናዝሬት እነ እገሌስ ቢሆን አልወጡም?. . .” የሚል ሀሳብ ይዤ የምቀርብ ይመስለኛል። ፊሊጶስ ግን ወደዚህ ማብቂያ የለሽ ክርክር አልገባም። ያለው ነገር ቢኖር “መጥተህ እይ!” ነበር። የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬም የእኛ ክርክር እና ጥበብ የሚፈይደው የለም። ልብን ሊደርስ ህይወትንም ሊለውጥ የሚችለው ብቸኛው ነገር ሰው ኢየሱስን በግል ሲገናኝ /ሲያይ/ ሲለማመድ ነው። ለዚህ ነው በመዝሙር መጽሐፍ “እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም” (መዝ. 34:8) የሚለው። ሃሌሉያ! በነገራችን ላይ ስለ ሆነ ነገር መረጃ የምናገኝባቸው የተለያዩ መንገዶች ያሉ ሲሆን ለምሳሌ ስለ ስኳር ጣፋጭነት ቀምሰን ልናገኝ የምንችለውን መረጃ በማንበብ፣ በማየት፣ በማሽተት፣ በመዳሰስ . . . ልናገኝ አንችልም። በመሆኑም ይህንን ጥናት ስንቋጭ ለተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ልንል የምንሻው ነገር ቢኖር፦ “መጥተህ እይ አለው!” “መጥተሽ እይ አለው!” “እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም!” “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና . . .” ዕብ. 12:1-2 Source:Ethio Agabe Bible study
Hammasini ko'rsatish...
#ሰለ_አዉሬዉ_ምልክት_ለማወቅ_ይህን_ማንበብ_ብቻ ይህን ሰታነቡ መጻፍ ቅዱስን አይርሱ 🙏ተባረኩ🙏
Hammasini ko'rsatish...
የተሰጠ መስጠንቀቂያ Rev-13(Original)_Final.pdf3.44 MB
ከዝህ በፊት እንደ መረጣችዉ ትምህርቱን ይዘን ዛሬ መተናል። #እንደ_ምርጫቸው_48%_ሰለ_አዉሬዉ_ምልክት ሰለ_ሆነ_የምናቀርባቸው_ትምህርት_ሰለ_አዉሬዉ_ምልክት_ይሆናል። 🙏እባካችሁ 10 ዴቂቃ መሥዋዕት አድርገን እናንቢብ🙏 👇ትምህርቱ ቀጣይ post ላይ👇
Hammasini ko'rsatish...
በየዕለቱ የሚሸከምልን የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል- መዝ 68:15-19 ብርቱዎች እንጂ ደካሞች በማይፈለጉበት አለም ውስጥ ስንኖር ለደካሞች እጁን የሚዘረጋ አፍቃሪ አምላክ እንዳለና ወደ እርሱ ለመምጣትም መስፈርቱ ደካማ መሆን እንደሆነ ቃሉ የሚያስተምረንን ጠንቅቀን ልንረዳ ይገባል። ጠላታችን ዲያቢሎስ ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ በተሻለ የጽድቅ ቁመና ላይ መገኘት እንደሚያስፈልገን እንድናስብና ያ ካልሆነ ግን ወደ እርሱ መቅረብ እንደማንችል በማሰብ ወደዚህ ጌታ ሳንቅረብ እንድንቀር ለማድረግ ይፈልጋል። በእርግጥም በራሳችን ኀይል ራሳችንን ቀይረን፣ ሸክማችንን አራግፈን ወደ እርሱ እንቀርባለን ማለት ዘበት ነው። ምክንያቱም “ያለ እኔ አንዳች ማድረግ አትችሉም” ብሎናልና። ይልቁንም “እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ” የሚለውን ጥሪ ተቀብለን ወደ እርሱ ስንቀርብ እርሱ ሸክማችንን ይሸከምልንና እረፍት ይሰጠናል። 1 ሸክማችንን የሚሸከምልን የከበደን ሸክም የህሊና ክስ ቢሆን፣ “እኔም አልፈርድብሽም፣ ደግመሽ ኀጢአት አትስሪ” በማለት ከኩነኔ ሸክም ያሳርፈናል። የከበደን ሸክም ፍርሃት ቢሆን፣ “እመን እንጂ፣ አትፍራ” በማለት ባስፈራራን ወጀብ ላይ በእግሩ እየተራመደ ወደ እኛ ይመጣል። የከበደን ሸክም ተስፋ መቁረጥ ቢሆን፣ “በእኔ ብትኖሩ ብዙ ፍሬ ታፈራላችሁ” በማለት የኀይላችን ምንጭ እንደሚሆንልን ዋስትና ይሰጠናል። ሸክማችን ምንም ይሁን ምን፣ “እናንት ሸክም የከበዳችሁ ደካሞች ወደ እኔ ኑ” ወዳለን ጌታ እናምጣው። እርሱም እረፍት ይሰጠናል። እኛም እንዲህ ብለን እናመሰግነዋለን:- “ ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ።” መዝ 68:19 2 በየዕለቱ አምላካችን ሸክማችንን የሚሸከምልን ደግሞ በየዕለቱ ሲሆን ያለ አንዳች መሰለቸትና መድከም ይህንን እንደሚያደርግልን ይህ ቃል ያረጋግጥልናል። በየዕለቱ የሚሸከመን አምላክ ይህንን የሚያደርግልን ደግሞ ከማሕጸን አንስቶ እስከ ሽበትና ሽምግልና ድረስ እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ ጨምሮ ያረጋግጥልናል። ወላጆቻችን በልጅነታችን ተሸክመውናል፣ በእጅና በእግራችን ስንድህ፣ እጃችንን ይዘው መራመድን አስተምረውናል። ከዚያ ግን እኛ እየበረታን እነርሱ እየደከሙ፣ ብሎም እድሜያቸው ሲገፋ ድሮ በጀርባቸው አዝለውት በነበረው የእኛ ትከሻ እነርሱን አዝለናቸው ይሆናል። የትኛውም ሰብአዊ ወላጅ ልጁን እስከ ሽበት እስከሽምግልና ሊሸከም አይችልም። ስሙ ድንቅ መካሪ፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት” የተባለው ጌታችን ግን እርሱ በእርግጥም የዘላለም አባት ነው። ከማህጸን አንስቶ እስከ ሽበት ድረስ የሚሸከመን የዘላለም አባት! ምናልባት ሌሎች ሰዎች ሰልችተውን፣ እኛን ለመሸከም ትእግስታቸው አልቆ ሊሆን ይችላል። ምናልባት የተደገፍንባቸው ነገሮች ድንገት አንሸራተው ጥለውን ሊሆን ይችላል። ምናልባት ሽክማችን እጅግ ከመክበዱ የተነሳ ምንም አይነት ሰብአዊ እገዛ አጥተን ሊሆን ይችላል። ዛሬ ወደዚህ ወደ ዘላለማዊው አባታችን ሸክማችንን ይዘን እንቅረብ። እርሱም “እኔ እሸከምሃለሁ” ይለናል። ጭነታችንን አራግፎ፣ በእርሱ ሰላም ነፍሳችንን ያሳርፋታል። እኛም አንደበታችን በምስጋና ይሞላና እንዲህ እንላለን:- “ሸክማችንን እለት እለት የሚሸከምልን አዳኝ አምላካችን ይባረክ” መዝ 68:19 በእርግጥም ከማህጸን አንስቶ እስከ ሽበት፣ እለት እለት እኛን በመሸከም እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም! 3 ይባረክ እንግዲህ ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸምከልን አዳኝ አምላክ እንዳለን በማስተዋል በምስጋና በፊቱ ልንቀርብ ይገባል። እርሱ ከእኛ የሚፈልገው በሚያደርግልን ነገር ተደስተን፣ በምስጋና ተሞልተን ስላደረገልን ነገር እንድናመሰግነው ብቻ ነው። ጠላት ሊያስቆዝመን፣ ሊያስጨንቀን፣ ተስፋ ሊያስቆርጠን ሲጥር ሸክማችንን እለት እለት በሚሸከምልን ጌታ ላይ ጥለን በእርሱ ሁልጊዜ ደስ እያለን በሁሉ ነገር እርሱን ልናመሰግን ይገባል። አባት ሆይ፣ ያጎበጠኝን ሸክም ዛሬ በአንተ እግር ስር እንድጥልና በትከሻህ መካከል መኖሪያዬን እንዳደርግ፣ በምስጋናም ተሞልቼ “ሸክማችንን እለት እለት የሚሸከምልን አዳኝ አምላካችን ይባረክ” ማለት እንድችል በጸጋህ እርዳኝ። አሜን።
Hammasini ko'rsatish...
እንደ ተለመደው ሰንበት ትምህርት በ PDF መልክ ይዘን መተናል ። ተጠቀሙ ተባረኩ!! ሰንበት ትምህርት የሚትይዛቸዉ ነገሮች ❤ key concept (ዋና ሀሳብ ) ❤ color full ❤SDA LOGOS ❤ clear meaning words ❤others አስታይህት ካለ comment section ላይ ፀፉልን። ተበረኩ
Hammasini ko'rsatish...
Presentation(1).pptx0.61 KB