cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

እዮብ ንጉሴ

የሀሳብ ምልከታን በግጥም

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
200
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#ሰው_መሆን !!! [ገጣሚ ሄኖክ ፀጋዬ] ረቂቅ ነው ቃሉ፣ ክቡድ እና ሙሉ፣ ገነትን ቀድሞ የረገጠ፣ መላዕክትን በፍርሃት ያንቀጠቀጠ፣ ሰውነት ክቡር ነው መለኮትን ያስቀመጠ። ሰው ማለት! ሰው ማለት ሰባተኛ፣ የጥበብ ልጅ ጥበበኛ፣ ክቡር ፍጡር እውነተኛ። ሰው ክቡድ ነው ታምረኛ። ሰው መሆን ሰውነት የታረዘን ማልበስ፣ ማዘን ማስተዛዘን ለራስ ለሰው ማልቀስ፣ የሰው እንባን ማበስ፣ ሰው መሆን ክቡር ነው! ምስለ መንፈስቅዱስ። ታዲያ.... ታዲያ የኛ ግብር ሰው ያስብላል፣? የሰውነት ትርጉም በኛ ተንፀባርቋል፣? እርኩሰት ወይንስ ቅድስና ክብር ወይንስ ውርደት፣ ማፍቀር ወይንስ መጥላት መግደል ወይንስ ማንሳት፣ ማልበስ ወይንስ መግፈፍ ማመፅ ወይንስ መርዳት፣ የትኛው ነው ሕይወታችን፣? የትኛው ነው ተግባራችን፣? ጉድ ነው ሰውነታችን ቆሽሿል ተበክሏል በድፍ፣ ሰው መሆን ተረስቷል ሰው አንሷል ከጉድፍ። ሰው መሆን ክቡር ነበር፣ ከራስ አልፎ መኖር፣ በሰውነት ሰውን ማክበር፣ ምስለ ማርያም ምስለ እግዚአብሔር። እዚያ ማዶ በምትታየው ዓለም፣ ከጥቂቶች በቀር ነብሴን ያለ የለም፣ ህዝቡ ያድራል ቅዠት ሲያልም፣ በስጋ ፍላጎት እንዲሁ ሲስለመለም። የተማረ ፤ የተመራመረ የሰውነት ክብርን ያወቀ፣ ደግሞም ከንቱ ነኝ ሚል እራሱን ያላመፃደቀ፣ ጥቂት ነው በዝች ዓለም ሰውነቱን የጠበቀ፣ ሰው ሆኖ የሚኖር ከፈጣሪው የታረቀ። ግድ የለህም የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰውነትን መልበስ ያስከብርሀል በሰማይ፣ ደግሞም ከፍ ትላለህ ከፍጡራን በላይ፣ ሰውነት ወልድ ነው የአዳም ሲሳይ። ሰውነት ማለት የታረዘን ማልበስ የተራበን ማጠጣት፣ የታሰረን መጠየቅ የተጠማን ማጠጣት፣ እራስን ማሳነስ የወደቀን ማንሳት፣ ሰውነት ይሄ ነው ለሰው ክብር መስጠት።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
ተይ..... እረፌ....... ’ረመጦ ያረፈውን ልቤን አ’ቆስቁሺ ላትሞቂበት ላትደምቂበት እጎጆሽ ላይበራበት እፍ... አትበይ አታንጂ ተይ ኋሌትን አታንሺ እረፌ እረፌ... ነካክተሺው ላታሞቂ ምድጃሽን ላታበስይ የህይወት እንጀራሽን ተይው በቃ.... እጅሽ ይፁም አትነካኪው የኋሌቱን ይብረድ..... አታግሚው ይታቀፈው ናፍቆትሽን እረፌ.... ስለምን ነው ምታፍሚው መናፈቅን ስለምን ነው ምታበዢው ስቃያትን ተይ.... ትዝታን አትንኪ ኋሌትን አትለኪ ጊዜን አታምልኪ መውደድን አስነኪ ተይ.... እረፌ..... ወዳጅን አታልፌ እ ረ ፌ ! 07/3/2016 ⏱_07:52 AM ✍️_ @eyob_Nigusse @eyob_Nigusse
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
እሰይ እንኳን ደግ አረገች መጀመሪያ ያየሃት ቀን እግሯ ሲያልፍ በመንገዱ አይቆጨኝም ነግሪያለው እሷን ያዩ እንዳበዱ አልሰማህም አንድም ቃሌን ተው እያልኩህ ተከተልካት ለጭድ ቤትህ ሳትሳሳ እሳት እርሷን ተዋወካት ቀጠረችህ ዘንጠህ ሄድክ አጫወትካት ቀልዱን በገፍ ስታሻሽህ ከታፋህ ላይ ትስቃለህ ጥርስህ ይርገፍ እንዳጨብጥ ብዬህ ነበር የእጇ መዳፍ አይነካም ኧረ እንደው የምን ጉድ ነህ ምኑ በግ ነህ አንተ እከካም አትቅረባት  አሻፈረኝ አትጠጋት መልስህ እምቢ አሁን የት ነህ? ከደጇ ስር? አንተ የወንድ አሰዳቢ ጅብ ነገር ነች ትበላለች አንጀት ልብን ቀረጣጥፋ አንተ ግና እንደ መዥገር ከአጠገቧ የማጠፋ ስትስቅልህ ደስ እያለህ ማባበሏ እውነት መስሎህ የሴትነት ሚያምር ለዛ ኩራትህን ተቀብሎህ ከርሷ ጋራ እንዳልከነፍክ ሽቶ ልብሴን እየቀማህ ዛሬ ውሻ ስታደርግህ እጅ እግርህን ምን ተሰማህ? እንደ በለስ አትነካ በጥጥ አምሳል አትፈተል ተወኝ ብላህ ላይሆንልህ እንደ ጭራ ስትከተል አለቀልህ አሁንማ እሰይ እንኳን ደግ አረገች ኩራትህን አይታ አይታ ይህን ነበር የፈለገች ዛሬ ስሯ ስትነጠፍ ቁጭት በፍም ያነደደህ ከጆሮህ ላይ ስለፈልፍ ትናንትና ምን ጋረደህ? መጀመሪያ ሳትለከፍ ሳታማትር ገፀ መልኳን ተው ይቅርብህ አላልኩህም ስታጮልቅ ከርሷ ድንኳን? እሰይ እንኳን! ።።።።።።።።።።።።።።። @mikiyas_feyisa
Hammasini ko'rsatish...
👍 6🥰 1
እምፅፈው ላንቺ ነው እንዲያው..... ሲመስለኝ እንጂ ለዛ የለው አውቃለሁኝ ሀሳብ ብቻ ......መተፋተፍ የኔ አቻ ምንስ ይሆን ፍርሀት መግቻ? : መስመር አላውቅ መወላገድ ሚዛን አላውቅ መንገዳገድ አቅም አ’ቶ እራስ መዝራት ባንቺ ብሎ ህልም መስራት ባጣ ማደርገው ጥበብ መቅጣት እንዲ ነው አለሜ የኔ ቅኔ በማይጥም ልሳን ወኔ ማግተለትል ፍቅር እኔ አሁን ተረዳሁ ከጭንቅ! ከተደበቀ ፍቅር ይልቅ! የተገለጠ ዘለፋ እንደሚልቅ! ✍️_ @eyob_Nigusse @eyob_Nigusse 27/2/2016 ⏱_ 6:32 pm
Hammasini ko'rsatish...
👍 7👏 1
ሰው ምልክት ሰቶሽ ያውቃል? አረሳውም የሚል... መልክት በሌላ ቃል በቃ ለምልክት ቁጭ ብቻ እንዳጣልሽ ወቶ አቻ ቋንቋ እንደጠፋው ቃሉን መፍቻ ሰው ምልክት ሰቶሽ ያውቃል? የ ነሆለለ አቅሙ ያነሰው አንቺን.... ባየ ቁጥር ሀሴት የሚሞላው ፈገግታሽን ሲስል ፈገግታ ሚቃኘው ውበትሽን ሲስል የ’ግዜር ቃል ሚታየው እድሜ ልኩን ቢሮጥ ካንቺ ’ማይሸሸው ሰው ምልክት ሰቶሽ ያውቃል? ከልጅነት ጨልፎ መልክሽን ቀንሶ ለራሱ ያስቀረ በምናብ ተዋርሶ ሰው ምልክት ሰቶሽ ያውቃል? ✍️_ @eyob_Nigusse @eyob_Nigusse 23/2/2016 ⏱ 3:59 pm
Hammasini ko'rsatish...
9
ሰው..... ቃልን አምኖ በቃል ታምኖ ከቃል ተምሮ ...በቃል ኖሮ : ቃልን አልፎ በቃል ገርፎ ቃል ተላልፎ ከቃል ገዝፎ : ቃል ሲቀል በተቀባይ በቃል አጉዳይ ሲደበያይ ቃል ሲመርጥ ዝምታን ቃል ተናገር አንድ በለን ካፋችን ቃል የሚወጣን ሰው.... እና ቃል..... ✍_ @eyob_Nigusse @eyob_Nigusse
Hammasini ko'rsatish...
2🔥 2🤓 1
ተስፈ እያለ ተስፋ መጣል እልም እያለ ቅስም መግደል ላያስችል አይሰጥም በሚል ቢሂሉ እየኖርን አይደል አምነን በቃሉ የምን መቁረጥ ተስፋ ....ከአምላክ ምንጋፋ የምን መሻል በአልቦ .....ያለ ስሜት ተከቦ ደና ነን እያልን ምንገፋው አይኖርም አይደለሁም ብለን ገላጭ ቃል አጠቅስም በምንም ምንም ውስጥ ምንም ነገር የለም ስሜት አለባ ጉዞ ሞት በምንም ይዞ ዝም..... ጭጭ.... በድንን ..........አዞ ✍️_ @eyob_Nigusse @eyob_Nigusse
Hammasini ko'rsatish...
👍 6🔥 1😁 1
ስሚኝ ይኸውልሽ "እኔን....! አዎ አንቺን "እሺ....! እሺ አትበይ እፈራለሁ "እንዴ....! ምን ሆንሽ እገርማለሁ "አይ ምንም....! አጠምዝዢ ያፍሽን ቃል ተናገሪ በኔ ይበቃል "ወይ ጉ......ድ! አይድነቅሽ እንደዚ ነኝ ወይ ተናግሮ አይወጣልኝ ወይ ቁርጤን አላውቅ አይዋጥልኝ "እኔን....! መልስሽ ነው? "አዎ....! እንዴዴዴዴ.....! ተው አትዪ ስብከለከል አንቺም አተይ ማጀናገል ቀልብን ሰርቆ መደላደል "ኧረ...... ምን ነው? "እንደዛ ነው.....? እንደዛ ነው! እደ ቀላል ቀልቤን ሰርቀሽ በናፍቆትሽ እኔነቴን ከሸራረፍሽ በመውደድ ነውላላነቴን ካፀደቅሽ በፊትሽ መግለጫ ቃል ካሳጣሽ የፀሀይ ጮራን ለብሰሽ እድሜ ልክ ካበራሽ ኧረ አንቺስ ተአምር ነሽ ኧረ አንቺስ ተአምር ነሽ ግን... ግን... ማን ነው የላከሽ ....? እ.....! ✍️_@eyob_Nigusse @eyob_Nigusse
Hammasini ko'rsatish...
❤‍🔥 6
ከኔ ፍቅር ይዞሽ ያውቃል? አትወጂም አለብሽ ቂም? የፊትሽን ገፅታ እንጂ የአይንሽን ቃል አትደብቂም ኢኝ አትበይ ስታስጠዪ እንደ ህፃን አያድርግሽ ቢሆን እንኳን ለፍቅር እንጂ ለትወና አልፈልግሽ ወለም ዘለም አለመድኩም ነግርሻለው ቃሉን በቃል ቂን አትበይ እውነት አውሪ መውደድሽን ስልክሽ ያውቃል ሀገር መልቀቅ የፈለገ መኪና እንጂ ቤት አይገዛም ከወደድኩሽ ወደድኩ ነው ሌላ ጣጣ አላበዛም አይደበቅ መቼም እውነት ቢሸፋፈን ጊዜ ይገልጣል ከወደድኩሽ ወደድኩ ነው እምቢ እንጂ ምን ይመጣል? ብትነግሪኝ ኡኡ አልል ሀገር ምድሩን ጥዬ አልጠፋ ከአጉል ኩራት ዙሪያ ጥምጥም ወድሃለው ምን አጠፋ? ✴✴✴✴✴✴✴ @mikiyas_feyisa
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1😁 1
አሜን በይ ልመርቅሽ ካልሽ እንግዲህ አቦል ጀባ ያብብ መልክሽ እንደአበባ ያውድ ጥሩ ቴሌግራም ቤትሽ በ Hi ይሙላ Inbox ደጅሽ😅 እንዳማረው ሸክላ ጋቻ ጀንጃኝ አትጭ አግኝ አቻ😘 በይ አሜን በይ ልመርቅሽ,,,, ካርድ አትጪ ዳትሽ ይብራ😄 ላይክ አድራጊሽ ይበል ጎራ ሼር ፣ ኮሜንትሽ አያባራ😜 በይ አሜን በይ ልመርቅሽ ይሰውርሽ ከጂል ፍሬንድ ከዘረኛ የሰው እምነት ከሚሳደብ በሽተኛ በፖሰትሽው ከሚናደድ ቀናተኛ ከአዲስ ጀንጃኝ ከሆነ አዛ🙄 ማሬ ፣ ማሬ ከሚያበዛ ይጠብቅሽ ከሞዛዛ🤪 በይ አሜን በይ ልመርቅሽ ስልክ ቁጥር ላኪ ከሚል😟 ቢሰጡትም ከማይደውል😩 በባዶ አንጀት ከሚያደርቅሽ😕 ልብ ጠቢ ይጠብቅሽ🤲 በይ አሜን በይ ልመርቅሽ,,,, እንደፈላው ቆንጆ ቡና😍 የኔ አይነት ልጅ መልከ ቀና😌 ላግባሽ ብሎ ይላክልሽ ሽምግልና አቦ እፎይ በይ በቃ አግብተሽ💍 ስልክሽ አርፎ አንችም አርፈሽ ቶሎ ተኝ ዳታ አጥፍተሽ😗 በባልሽ ክንድ ብሎክ ሁነሽ😂 😁አሜን በይ 😂
Hammasini ko'rsatish...
👏 4👍 1
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.