cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Afewerki and Afewerki Law Firm

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
201
Obunachilar
+424 soatlar
+37 kunlar
+330 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሐራጅ ሽያጭ ሥነ ሥርዓት   መግቢያ የፍርድ ባለእዳ የሆነ ሰው በፍርዱ መሰረት ሳይፈፀም ሲቀር እንደ ፍርዱ እንዲፈፅም በአፈፃፀም ሥነ ሥርዓት የሚገደድ ሲሆን አፈፃፀም ፍርድ ቤት እራሱ የሰጠውን ፍርድ ወደ ተግባር የሚለውጥበት ሥርዓት ነው፡፡ አፈፃፀም ስለፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የማስፈፀሚያ ሥርዓቱ በጥቅሉ በፍትሐብሐር ሥነ-ሥርዓት ሕጉን መሠረት ይፈፀማል፡፡ በፍርድ አፈፃፀም ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ያሉ ሲሆን እነሱም ንብረት ማስከበር፣ በተከበረ ወይም በተያዘ ንብረት ላይ ሦስተኛ ወገኖች የሚያቀርቡት መቃወሚያ አና የሐራጅ ሽያጭ ሥነ-ሥርዓት ናቸው፡፡ በዚህ ጽሁፍ የሐራጅ ሽያጭ ሥነ-ሥርዓትን የምንመለከት ይሆናል፡፡   የሐራጅ ሽያጭ ሥነ ሥርዓት ምንነት ሐራጅ "እንዲሸጥ የተወሰነ ንብረት በጨረታ ወይም ገበያ ላይ በተገኘው ዋጋ የሚሸጥበት መንገድ ነው በማለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ ጥናትና ምርምር የአማርኛ መዝገበ ቃላት(1993) ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ የሐራጅ ሽያጭ ሥነ ሥርዓትን ስንመለከት አንድ ጊዜ ንብረቱ በፍርድ ቤቱ ታግዶና በታገደው ንብረት ላይ ተቃወሞ ቀርቦ ምርመራ ከተደረገበት ከተወሰነ በኋላ ንብረቱ በሀራጅ እንዲሸጥ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ይህም የሐራጅ ሽያጭ ሥርዓት አፈፃፀም የሚጀምረው ለህዝብ ማስታወቂያ በማውጣት ይሆናል፡፡ በቀጥታ ወይም በተለዋዋጭ ገንዘብ እንዲከፈል የተሰጠ ማናቸውም ፍርድ ወይም ውሣኔ የሚፈፀመው የባለዕዳውን ንብረት በማስከበርና በማሸጥ ሲሆን፤ ማናቸውም ሀብት ወይም ንብረት የሚሸጠውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 422/3/፣ 427 እና 439 የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሐራጅ ሽያጭ በማድረግ ነው፡፡ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ተብሎ የሚሸጠውም ንብረት በቁጥር 394/2/ እና 422/1/ እንደተደነገገው ከሚፈለገው የዕዳ መጠን ጋር በተቻለ መጠን ተመጣጣኝ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡    ለፍርድ አፈፃፀም ንብረትን የመሸጥ ሥነ-ሥርዓት የመሸጥ ሥነ ሥርዓቱ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር ከ422 እስከ 449 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡ ከቁጥር 422 እስከ 431 የተደነገጉት በሁሉም የሽያጭ ዓይነቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ፣ ከቁጥር 432 እስከ 438 ያሉት በተለይ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ብቻ የሚመለከቱ እና ከቁጥር 439 እስከ 449 ያሉት በተለይ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ማንኛውም ንብረት በአፈፃፀም የሚሸጠው በሐራጅ ሽያጭ ነው፡፡ ሆኖም በፍርድ ባለመብቱና በፍርድ ባለዕዳው ፈቃድ ንብረቱ በስምምነት እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል፡፡ ንብረቱ በሐራጅ እንዲሸጠጥ ትዕዛዝ (ውሳኔ) ከተሰጠ የሽያጩ ማስታወቂያ ለሕዝብ መገለፅ ይኖርበታል፡፡   የሐራጅ ሽያጭ ሥነ ሥርዓቱ በማን ይፈፀማል? የታገደ (የተከበረ) ንብረት የሚሸጠው የሽያጩን ሥርዓት እንዲያስፈፅም ፍርድ ቤቱ በተለይ ባዘዘው ሰው ወይም በፍርድ ቤቱ ሠራተኛ አማካኝነት ነው፡፡ ፍርድን ለማስፈፀም ማናቸውንም ሀብት ወይም ንብረት እንዲሸጥ የታዘዘ ሰው በሕጉ አነጋገር ሐራጅ ባይ ተብሎ ይጠራል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 422(2))፡፡ በሌላ በኩል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በፍትሐብሔር ችሎቶች በሐራጅ እንዲሸጡ ውሳኔ የሚያሳርፍባቸው የፍርድ ባለዕዳ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብትና ንብረቶችን ፍርድ ለማስፈጸም የሐራጅ ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑ ይታወቃል፡፡   የሐራጅ ሽያጭ ሥነ ሥርዓት ሂደት የሐራጅ ሽያጭ ሥርዓት አፈፃፀም የሚጀመረው ለህዝብ ማስታወቂያ በማውጣት ይሆናል፡፡ ማስታወቂያውም ንብረቱ በሚገኝበት አቅራቢያ ወይም ግልጽ ሆኖ ሊታወቅና ሊሰማ በሚችልበት ዘዴና በማናቸውም ልማዳዊ ዓይነት በአደባባይ በመንገር ወይም በመለጠፍ ለፈፀም ይችላል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 425(1) እና 414(2))፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስታወቂያው በጋዜጣ መውጣት አለበት (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 425(2)፡፡ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423 መሰረት የሐራጅ ማስታወቂያው • የሚሸጠውን ንብረት አይነትና የዋጋ ግምት • ከንብረቱ ላይ የሚጠየቅ የዋስትና መያዣ ወይም ሌላ መብት መኖር አለመኖሩና ካለም መጠኑን • ለመሸጡ ምክንያት የሆነውን በፍርድ የተወሰነ የገንዘብ መጠን • ንብረቱ የሚሸጥበትን ሁኔታ፣ ገደብ፣ የሽያጭ ገንዘብና የሚከፈልበትን ጊዜ • ሌሎች ገዢው ከመግዛቱ በፊት ሊያውቃቸው ይገባል ብሎ ፍርድ ቤት የሚገምታቸውን ዝርዝር መረጃዎች አሟልቶ መያዝ አለበት፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 426 መሰረት የፍርድ ባለዕዳው ከዚህ አስቀድሞ እንዲሸጥ ካልተስማማ በስተቀር ማናቸውም የሚንቀሳቀስ ንብረት አንዲሸጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 ቀን፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ደግሞ 30 ቀን ድረስ ሳይቆይ በሐራጅ ሊሸጥ አይችልም፡፡ ይህም ቀን መቆጠር የሚጀምረው ማስታወቂያው ከተለጠፈ ወይም በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡ የታገደው ዕቃ ቶሎ የሚበላሽ ከሆነ ከላይ የተጠቀሰውን ጊዜ መጠበቅ ሳያስፈልግ ንብረቱ ወዲያውኑ ሊሸጥ ይችላል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 426፣ 406(2))፡፡  በመጀመሪያው ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው የዋጋ ግምት ንብረቱን የሚገዛ ገዥ ካልተገኘ ሁለተኛ ጨረታ እንዲደረግ ይታዘዛል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428)፡፡ የሐራጅ ማስታወቂያ ከመውጣቱ በፊት የፍርድ ባለዕዳው የሚፈለግበትን ዕዳ በሙሉ ከከፈለ የሐራጁ ሽያጭ ይቆማል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 427)፡፡   የሐራጅ ሽያጭ ስለሚፀናበትና ስለሚሰረዝበት ሁኔታ ሽያጩን እንዲፈርስ የሚጠይቅ ሰው በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ማመልከቻ አቅርቦ እንዲፈርስ ወይም እንዲሰረዝ ካላደረገ ሽያጩ የፀና ይሆናል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 447)፡፡ የሚንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ሲሸጥ የሽያጭ ሥርዓት በትክክል አለመፈፀሙ ሽያጩን አያፈርሰውም፡፡ ሆኖም ጉዳት የደረሰበት ወገን ከጉዳት አድራሹ ካሳ እንዲከፍለው መጠየቅ ይችላል (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 435) ፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ ሲሸጥ በአሻሻጡ ሥርዓት ላይ ግዙፍ የሆነ ጉድለት የተፈፀመ ከሆነ ግን የፍርድ ባለ ገንዘቡ ወይም መብቱ የሚገባው ሌላ ሰው ሽያጩ እንዲፈረስ ወይም እንዲታገድ መጠየቅ ይችላል፡፡ ሽያጩ የሚፈርሰው ከሥርዓት ውጪ ስለተፈፀመ ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የሆነ ጉድለት ወይም የማታለልና የማጭበርበር ሥራ ተፈፅሞ ሲገኝና ይህም በአመልካቹ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ያደረሰበት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው (የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 445)፡፡ በፍርድ ምክንያት ንብረት እንዲታላለፍ የተሰጠውን ትዕዛዝ የመቃወም ወይም የእምቢተኝነት ደርጊት ሲፈፀም ፍርድ ቤቱ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 450 እስከ 455 በተደነገገው መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይችላል፡፡    ማጠቃለያ ሐራጅ በፍርድ ባለእዳ ላይ የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ባለእዳው ንብረት ላይ ለማስፈፀም ንብረት የሚከበርበት እና የሚሸጥበት ሂደት ሲሆን የሚፈፀምበት የራሱ ሥነ ሥርአት ያለው በመሆኑ በሂደቱ የሚሳተፉ አካላት ሥነ ሥርአቱን በአግባቡ ሊረዱ ይገባል፡፡                                                     # በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Hammasini ko'rsatish...
Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu
Hammasini ko'rsatish...
5432024.pdf7.61 KB
Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu
Hammasini ko'rsatish...
209604 ዕግድ ይነሳልኝ.pdf8.19 KB
Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu
Hammasini ko'rsatish...
Binding Interpretation of Law in Ethiopia_240331_160316.pdf5.16 KB
Shared by One Read - an all-in-one file viewer: https://st.simplehealth.ltd/uAJjyu
Hammasini ko'rsatish...
223024.pdf1.07 MB
ሰበር መ/ቁ/201427 /7 ዳኛ በአብላጫ ድመጽ የተወሰነ-3/4/ -(ያልታተመ) በመሰረቱ ይርጋ መብትን እና መብት ለማስከበር የሚቀርብ ክስ/limitation of action/ ቀሪ የማድረግ ዉጤት ያለዉ የህግ ጽንሰ ሃሳብ ነዉ፡፡የይርጋ ደንብ /period of limitation/ ዓይነተኛ ዓላማ እና ዝርዝር አፈጻጸሙ የተለያየ ቢሆንም በጥቅለ ሲታይ አንድ ባለመብት በህጉ በተገለጸ ጊዜ ገደብ ዉስጥ በመብቱ ባለመስራቱ የመብት ጥያቄዉ በጊዜ ማለፍ ምክንያት ቀሪ የሚሆንበት ሲሆን በሌላ በኩል ሌላዉን ወገን ባለመብት የማድረግ ወይም ግዴታዉን ቀሪ የማድረግ ዉጤት ያለዉ ነዉ፡፡በሌላ አገላለጽ የይርጋ ደንብ ጽንሰ ሃሳብ በሶስት ተከፍል ሊታይ ይችላል፡፡አንደኛዉ ዓይነት የይርጋ ደንብ በህግ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላ የፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ (ዳኝነት) ተቀባይነት እንዳይኖረዉ የሚያደርግ (የሚከለክል) ወይም ዳኝነት ጥያቄ በጊዜዉ ባለመቅረቡ ምክንያት ብቻ ክሱ ቀሪ ነዉ /limitation of action/ የሚባለዉ ሲሆን በፍትሃብሐር ህግ ቁጥር 1845 የተደነገገዉ ዓይነት ነዉ፡፡ይህ ማለት ባለመብቱ ወይም ባለገንዘቡ በህግ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ መብቱን ባለመጠየቁ ጥያቄ የማቅረብ መብቱን የሚያሣጣዉ ሲሆን በሌላ በኩል ከባለ ግዴታዉ አንጻር ሲታይ ግዴታ አስቀሪ (liberative prescrption) ተብሎ የሚገለጸዉ ነዉ፡፡ደንቡ የሚያገለግለዉ አንድ ግዴታ ከዉል ይሁን ከዉል ዉጭ የመነጨም ቢሆን ግዴታዉ መጠየቅ ባለበት ጊዜ ዉስጥ ባለመጠየቁ ግዴታ ያለበት ወገን ዝንተ ዓለም እያሰበ እንዳይኖር የሚከለከል ነዉ፡፡ሁለተኛዉ የይርጋ ደንብ አንድ ሰዉ ያልነበረዉን መብት የሚያጎናጽፍ ወይም የሚያሥገኝ (acquisitive prescription) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ደንብ መሰረት ያለማንም ከልካይ ወይም ጠያቂ አንድን ንብረት በህግ ለተወሰነ ጊዜ ይዞታዉ ስር አድርጎ ሌሎች የህግ መስፈርቶችን እያሟላ በመጠቀም በንብረቱ ላይ የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት መብት የሚያገኝበት ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1168 ድንጋጌ ተጠቃሽ ነዉ፡፡ሶስተኛዉ ዓይነት የይርጋ ደንብ ተብሎ የሚወሰደዉ ባለ ንብረቱ በንብረቱ ለተወሰነ ጊዜ ባለመጠቀዉ ወይም ንብረቱን ይዞ ባለመገኘቱ የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት መብት የሚያሣጣ (extinictive perscription) መሆኑን የሚያመለከት ደንብ ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1192 ድንጋጌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ባጠቃላይ የይርጋ ደንብ ዓይነተኛ ዓላማ ባለመብቱ ዳተኛ እንዳይሆን ማስጠንቀቅ ሲሆን በሌላ በኩሌ ከዉል ወይም ከህግ የመነጨ ግዴታ ያለበት ወገን በህግ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በህግ እንደማይገደድ ብሎም መብት ላልነበረዉ ሰዉ መብት የሚሰጥ ተብል የሚወሰድ የህግ ጽንሰ ሀሳብ የያዘ ነዉ፡፡ በተሻሻለው የአማራ ብ/ክ/መ/ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/09 ስለ ይርጋ የሚደነግገዉ አንቀጽ 55 ላይ የገጠር መሬትን በወረራ /invasion/ ወይም በሌላ በማናቸውም ህገወጥ መንገድ /in any illegal means/ ይዞ በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን እንዲለቅ በማንኛውም ሰው ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በመቃወሚያነት ሊያነሳ እንደማይችል ይደነግጋል። በተያዘው ጉዳይም ክሱ በይርጋ እንደማይታገድ በአብላጫው ድምጽ አቋም ተይዞበታል። አነስተኛው ድምጽ የተለዩት ዳኞች በሰ/መ/ቁ 178927 ቅጽ 24 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም በገጠር መሬት ይዞታ ይገባኛል ክርክር ተከሳሽ የሆነ ወገን የይርጋ መቃወሚያ ለማንሳት መሬቱን በሕግ መሠረት በሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተፈቅዶለት በሕጋዊ መንገድ ወይም በከሳሽ ፈቃድ የያዘው ስለመሆኑ አስቀድሞ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት ተብሏል።ተከራካሪ ወገኖች መብታቸውን በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ ካልተጠቀሙ መብታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትሕ /procedural justice/ በተመሳሳይ በመሠረታዊ ሕግ እንደተመለከተው መብትና ፍትሕ /substantive justice/ መከበርና መተግበር አለበት፡፡ አንደን ከአንደ ማበላለጥ ሆነ አንደኛውን የፍትሕ ዘንግ ለማስከበር ሌላኛውን መጣስ ተገቢ አይደለም፡፡ አነስተኛው ድምጽ ይህ የህግ ትርጉም መቀየር እንዳለበት አቋም የያዘ ሲሆን አብላጫው ድምጽ ግን ትርጉሙ ይጣጣማል እንጂ አይጋጭም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። // በተጨማሪ የተነሱ ህጎችና የሰበር ውሳኔዎች የፌዴራሌ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ 59(2)፣ የፍ/ብ/ህግ/1853 ፣1854 እና 1856፣ሰበር መ/ቁ 69302//
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
ኣብ ኩለን ክልላት ተፈፃምነት ዘለዎ ረቂቅ ክራይ ገዛ ኣመልኪቱ ኣዋጅ::
Hammasini ko'rsatish...
Ethiopian Employment Law Notes, Cases and Materials.pdf2.31 MB
Law of Traders and Business Organizations.pdf2.74 MB
Principles of Ethiopian Criminal Law (Revised Edition).pdf3.59 MB
Ethiopian Constitutional Law.pdf4.37 MB
Ethiopian property law 1.pdf38.94 MB
Ethiopian Criminal Procedure Text Book.pdf38.63 MB
Eth_Draft Public Holidays Proclamation.pdf5.10 KB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.