cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25 በማድረግ ይጎብኙ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
377
Obunachilar
+824 soatlar
+247 kunlar
+5530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

✞ #የሐምሌ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞ ረቡዕ ሐምሌ 3 - አባ ሊባኖስ - ልደታቸው - በጣፎ ሃያት ገብርኤል - በእንጦጦ ኪዳነምህረት አርብ ሐምሌ 5 - የቅዱስ ጳውሎስ እና ጴጥሮስ - እረፍታቸው - በዌንጌት እና በሰዋሰው ቅዱስ ጳውሎስ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እሁድ ሐምሌ 7 - ቅድስት ሥላሴ - በአብርሃም ቤት የገቡበት ሰኞ ሐምሌ 8 - አባ ኪሮስ - ዕረፍታቸው ማክሰኞ ሐምሌ 9 - አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ -  - በቀበና መድኃኔዓለም ረቡዕ ሐምሌ 10 - ሐዋርያው ናትናኤል - በቡራዩ ፀደንያ ማርያም አርብ ሐምሌ 19 - ቅዱስ ገብርኤል እሁድ ሐምሌ 21 - እመቤታችን በአባዶ                         - ቅዱስ ዑራኤል በዓል - በካሳንችስ ዑራኤል ሰኞ ሐምሌ 22 - ቅዱስ ዑራኤል ማክሰኞ ሐምሌ 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቅዳሴ ቤቱ(በገነተ ፅጌ ፒያሳ) ሐሙስ ሐምሌ 25 - ቅዱስ መርቆሬዎስ - በጎፋ መብራት ሀይል                           - ቃሊቲ ቁስቋም ማርያም - ቅዳሴ ቤቷ አርብ ሐምሌ 26 - ቅዱስ ዮሴፍ - እረፍቱ ቅዳሜ ሐምሌ 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤቱ - በቦሌ በአራብሳ ሰኞ ሐምሌ 29 - አቡነ እጨጌ ዮሐንስ - ዕረፍታቸው - በወይራ ሰፈር ✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

1
ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ ሊያውቃቸው የሚገባ #ፍሬ_ጥቅሶች በኢትዮጲያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረት 5ቱ ሀብታት፤ 5ቱ ፍኖተ ጽድቅ ፤ 5ቱ አቀብተ ሲኦል ፤ 5ቱ ፍኖተ ኃጢአት፤ 5ቱ ሐራ ሲኦል ነገስት፤ 5ቱ ህሩያ ነገስት፤ 5ቱ አርዕስተ አበው ሲባሉ እነርሱም:- 5ቱ ሐብታት የተባሉት 1.ሐብተ ፈውስ 2.ሐብተ ክህነት 3.ሐበተ ትንቢት 4.ሐብተ መዊእ 5.ሐብተ መንግሥት ናቸው። 5ቱ ፍኖተ ጽድቅ የተባሉት 1.ፍቅር 2.ትህትና 3.ጾመ 4.ጸሎት 5.ምጽዋት ናቸው። 5ቱ አቀብተ ሲኦል የተባሉት 1.ጣዖትን ማምለክ 2.አፍቅሮ ንዋይ 3.ጠላልቶ አለመታረቅ 4.ሰው መግደል 5.እናት አባትን አለማክበር ናቸው። 5ቱ ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት 1.ትዕቢት 2. ስርቆት 3.ምቀኝነት 4.ዝሙት 5.ስስት ናቸው። 5ቱ ሐራ ሲኦል ነገስታት የተባሉት 1.ፈረኦን በኤርትራ ባሕር የሰጠመው 2.ሰናክሬም 3.አንጥያኮስ 4.ሔሮድስ 5.ዲዮቅልጥያኖስ ናቸው። 5ቱ ሕሩያነ ነገስት የተባሉት 1.ሕዝቅያስ 2.ኢዮስያስ 3.ዳዊት 4.ሰሎሞን 5.ንግሰተ ሳባ አዜብ ማክዳ ናቸው። 5ቱ አርዕስተ አበው የተባሉት 1.አዳም 2.ሄኖክ 3.ኖህ 4.አብርሃም 5.ሙሴ ናቸው። ምንጭ የኢትዮጲያ ተወዳጆች ቅዱሳን ታሪክ በሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ቤተክርስቲያን ባሕረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተ ክርስቲያን አትታስም የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተክርስተያን ሰላም እንማልዳለን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት የጻድቃን የሰማዕታት የቅዱሳን የሐዋርያት የቅዱሳን አበው መነኮሳት የቅዱሳን አንስት የደናግላን የቅዱሳን ሁሉ ምልጃ ቃልኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሐቅ የተገለፀች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔአለም ዘንድ ታመልደን አሜን አሜን አሜን ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን አሜን አሜን አሜን ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

✝ታዴዎስ ሐዋርያ ብእሲ ሔር፤ ወበዓለ ዐቢይ መንክር፤ በእንተ ዘረድኦ በፍኖት ሚካኤል ክቡር፤ ምስለ ዜና ድንግል ጻድቅት ተዝካሮ ንገብር! ✝እንኳን አደረሰን !
Hammasini ko'rsatish...
✞✞✞ ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ✝፡፡ ✞✞✞ ✞✞✞✝ እንኩዋን ለሐዋርያው #ቅዱስ_ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝ ✞✞✞ +"+✝ #ቅዱስ_ታዴዎስ_ሐዋርያ ✝+"+ =>#ቅዱሳን_ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል:: ¤እንደ #ዮሐንስ_ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ: ¤#ቅዱስ_ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን ¤እነ #ቅዱስ_ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም: ከጐልማሶችም ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው:: +ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ #ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) #ስምዖን እና #ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል:: +ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ: ¤ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ: ¤3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ: ¤በዕርገቱ ተባርኮ: ¤በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ: ¤#ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል:: +ቅዱስ ታዴዎስ አንድ ቀን ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ወደ አንዲት ሃገር ይገባሉ:: ታዲያ ለቀናት ያለ ምግብ ወንጌልን ሲሰብኩ ቆይተው ነበርና ደጐቹ ሐዋርያት ራባቸው:: ወደ ከተማዋ ሳይገቡ አንድ ሽማግሌ ሲያርስ አይተው ሰላምታን ሰጡትና "እባክህ እርቦናልና አብላን" አሉት:: እርሱም ምንም ወገኑ ከአሕዛብ ቢሆነ አሳዝነውት በሬዎቹን ሳይፈታ እየሮጠ ሄደ:: +ያን ጊዜ ቅዱስ ታዴዎስ ሊቀ ሐዋርያትን "እርሱ እስኪመጣ ለምን አናርስም" አለው:: 2ቱ ተነስተው ታዴዎስ ሞፈር: ዼጥሮስ ደግሞ ስንዴውን ያዘ:: ቅዱሳኑ እየዘሩ ያረሱት ሰውየው ምግብ ይዞ እስኪመጣ አድጐ: አፍርቶ: እሸት ሆኖ ቆየው:: +ገበሬው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ደነገጠ:: ሊያመልካቸውም ወደደ:: እነርሱ ግን "እኛ የልዑል ባሮች ነን" ብለው በክርስቶስ ማመንን አስተማሩት:: "ልከተላችሁ" ቢላቸው "የለም! ከእሸቱ ይዘህ ወደ ከተማ ግባና ራት አዘጋጅልን:: እኛ እንመጣለን" አሉት:: +እርሱ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሕዛብ ነገሩን ተረዱ:: ተሠብሥበውም "እነዚህ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሳትም ሰይፍም አይበግራቸውም" ብለው ወደ ከተማ እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ራቁቷን የሆነች ዘማ አቆሙ:: +ቅዱስ ታዴዎስ ገና ከርቀት ስላያት ቀና ብሎ #ቅዱስ_ሚካኤልን "እርዳን" አለው:: ሊቀ መላእክትም ድንገት ወርዶ ዘማዋን ሴት በጸጉሯ በዓየር ላይ ሰቀላት:: በከተማዋ ያሉ አሕዛብም ይህንና ሌሎች ተአምራትን አይተው ሁሉም በጌታችን አምነው ተጠመቁ:: ለሐዋርያቱም ሰገዱላቸው:: +አንድ ቀን ግን አንድ ጐረምሳ ባለ ጠጋ ቅዱስ ታዴዎስ "ሀብት ንብረታችሁን መጽውቱ" ሲል ሰምቶት ዘሎ የሐዋርያውን ጉሮሮ አንቆ ከሞት አድርሶት ነበር:: ያን ጊዜ "ጌታየ! ለካ ሀብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ያልክ ለዚህ ነው!" ብሏል:: ባለ ጠጋው "እንዴት ይሆናል?" ቢለው መርፌ አሠርቶ ግመሉን ከነ ባለቤቱ በሰው ሁሉ ፊት 3 ጊዜ አሳልፎታል:: +ያም ማለት ጌታችን እንዳለው "በሰው ዘንድ የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል::" (ማር. 10:23) በዚህ ምክንያትም ያ ክፉ ባለ ጸጋ ወደ ልቡናው ተመልሶ ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ሥር ወደቀ:: ሐዋርያውም አለው "ሀብትህን ለነዳያን ስጥ:: ይህንንም በትር እንካና እየዞርክ ወንጌለ መንግስትን ስበክ::" ባለ ጸጋውም የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ በክብር ዐርፏል:: +ቅዱሳኑ ታዴዎስና ዼጥሮስ ግን በሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው: ካህናትን ሹመው: ያቺን በዓየር ላይ የሰቀሏትን ዘማም የተባረከች መበለት አድርገው: በሌሎች አሕጉራት ወንጌልን ለማዳረስ ወጥተዋል:: +ቅዱስ ታዴዎስም እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም በዚህች ቀን ዐርፏል:: =>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን:: =>ሐምሌ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ =>+"+ ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን "ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል!" አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ:: ጌታ ኢየሱስም ደግሞ መልሶ "ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ #እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው! ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አላቸው:: +"+ (ማር. 10:23-28) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

Photo unavailableShow in Telegram
✝ቅድስት ቅፍሮንያ ሰማዕት ወጻድቅት✝ ††† ††† ይህቺ ቅድስት እናታችን ደግሞ ገና በአሥራ ሁለት ዓመቷ ታላቅ እህቷን ተከትላ ገዳም ትገባለች:: በሚገርም ተጋድሎ በጥቂት ጊዜ አጋንንትን አሳፍራ መነኮሳይያትንም አስገርማቸዋለች:: ትጋቷ ግሩም ነበርና ስትታዘዝ : ስትጸልይና ስትሰግድ ያለ እንቅልፍና ምግብ ቀናት ያልፉ ነበር:: በዚህ የተቆጣ ሰይጣን አረማዊ መኮንንን ይዞባት መጣ:: ሌሎች ደናግል ሲያመልጡ እርሷ ለመከራ ተዘጋጅታ ጠበቀችው:: አዕምሮ የጎደለው መኮንኑም ክርስቶስን ካልካድሽ ብሎ ጽኑዕ ጽኑዕ መከራን አመጣባት:: በተጋድሎ ባለቀ አካሏ ሁሉንም ቻለች:: በዚህች ቀን ግን አንገቷን በሰይፍ አስቆርጧታል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የወዳጆቹን ትዕግስትና ጽናት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ⛪✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ' " ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Hammasini ko'rsatish...
1
†††✝ እንኳን ለተባረከ ወር ሐምሌ እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ✝††† ††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ ††† እግዚአብሔርን ቸር የምንለው በባሕርዩ ፍጹም ቸር በመሆኑ ነው:: ይሕንን ደግሞ ለማረጋገጥ መቅመስ ይቻላል:: ይገባልም:: (መዝ. 33:7) ይሔው ደግሞ ያን ሁሉ ኃጢአታችንን ታግሶ ከወርኀ ሐምሌ አደረሰን:: ለዚሕ ቸርነቱ አምልኮ : ውዳሴና ስግደት ይገባዋል:: ለወርኀ ነሐሴ ደግሞ እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል:: ††† ✝ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሊቅ ✝††† ††† ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት ቅዱስ አግናጥዮስ ገና በልጅነቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየ : ራሱ ጌታችን ትንቢት የተናገረለት (ማቴ.18:1) እና ከጌታ ዕርገት በኋላ ሐዋርያትን የተከተለ አባት ነው:: ጌታ ሲያርግ የአምስት ዓመት ሕፃን ሲሆን ከሰላሳ ስድስት ዓመታት በላይ ሐዋርያትንና ቤተ ክርስቲያንን አገልግሏል:: ዕድሜው ወደ አርባዎቹ ሲደርስ (ኢየሩሳሌም በጠፋችበት ዓመት - በ70 ዓ/ም) እርሱ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ ተሹሟል:: አስቀድሞ ከወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ እግር ምሥጢርና ፍቅርን ጠጥቷልና የተለየ ሰው ነበር:: ቅዱስ አግናጥዮስ ከአንጾኪያ እየተነሳ ምድረ እስያንም በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሷል:: በአካል ያልደረሰባቸውን በጦማር (በክታብ) አስተምሯል:: በአካሉ እንኳ ምንም በጾም በጸሎትና በብዙ ድካም የተቀጠቀጠ ቢሆን ግርማው የሚያስፈራ ነበር:: ከነገር ሁሉ በኋላ የወቅቱ ቄሣር ጠራብሎስ ይዞ አሰቃይቶ ለአንበሳ አስበልቶታል:: በዚህ ምክንያት "ምጥው ለአንበሳ-ለአንበሳ የተሰጠ" እየተባለ ይጠራል:: ††† ✝አባ ብዮክ እና አባ ብንያሚን✝ ††† ††† እነዚህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ናቸው:: ካህን አባታቸው በሚገባ ቢያሳድጋቸው እነሱም ገና በወጣትነት የሚደነቅ የክህነት አገልግሎትን ሰጥተዋል:: ሙሉ ሌሊት ለጸሎት : ሲነጋ ለኪዳን : በሠርክ ደግሞ ለቅዳሴ ይፋጠኑ ነበር:: ሁሌም በየቤቱ እየዞሩ የደከመውን ሲያበረቱ : የታመመውን ሲፈውሱ : ያዘነውን ሲያጽናኑ ውለው ትንሽ ቂጣ ለራት ይመገባሉ:: ሰውነታቸው በፍቅር ሽቱ የታሸ ነበርና ብዙዎችን መለወጥ ቻሉ:: አንዴ ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ "አባታችሁ ሊሞት ነው" ቢሏቸው "ሰማያዊው አባት ይቀድማል" ብለው ቀድሰዋል:: አባታቸውንም ቀብረውታል:: በመጨረሻ ግን አንድ ቀን ለመስዋዕት ብለው ያዘጋጁትን የበረከት ሕብስት እባብ በልቶባቸው አገኙ:: እንደ ምንም ፈልገው እባቡን ገደሉት:: ነገር ግን ያ የተባረከ ሕብስት በሆዱ ውስጥ ነበርና ምን ያድርጉት? ጌታን ስለ ማክበር ሊበሉት ፈልገው ጌታን ቢጠይቁት መልአኩ መጥቶ "ሰማዕትነት ሆኖ ይቆጠርላቹሃል" አላቸው:: ሁለቱ ወንድማማቾች ብዮክና ብንያሚን ፈጣሪያቸውን አመስግነው በሉት:: ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ሁለቱንም እንደተቃቀፉ ዐርፈው አገኟቸው:: መልካም እረኞቻቸው ናቸውና ከታላቅ ለቅሶ ጋር ቀብረዋቸዋል:: ††† ✝ቅድስት ቅፍሮንያ ሰማዕት ወጻድቅት✝ ††† ††† ይህቺ ቅድስት እናታችን ደግሞ ገና በአሥራ ሁለት ዓመቷ ታላቅ እህቷን ተከትላ ገዳም ትገባለች:: በሚገርም ተጋድሎ በጥቂት ጊዜ አጋንንትን አሳፍራ መነኮሳይያትንም አስገርማቸዋለች:: ትጋቷ ግሩም ነበርና ስትታዘዝ : ስትጸልይና ስትሰግድ ያለ እንቅልፍና ምግብ ቀናት ያልፉ ነበር:: በዚህ የተቆጣ ሰይጣን አረማዊ መኮንንን ይዞባት መጣ:: ሌሎች ደናግል ሲያመልጡ እርሷ ለመከራ ተዘጋጅታ ጠበቀችው:: አዕምሮ የጎደለው መኮንኑም ክርስቶስን ካልካድሽ ብሎ ጽኑዕ ጽኑዕ መከራን አመጣባት:: በተጋድሎ ባለቀ አካሏ ሁሉንም ቻለች:: በዚህች ቀን ግን አንገቷን በሰይፍ አስቆርጧታል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የወዳጆቹን ትዕግስትና ጽናት ለእኛም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: ††† ✝ቅዱስ ቶማስ ✝††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ይታሰባል:: ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም ያመኑትን "ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሽሹ" ብሎ መከራቸው:: ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ መሸተኛዋ ሴት እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል ሰይፍ አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት:: እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ (መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ ቶማስ ነገሩን ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል ዝም አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና "ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን ጠብቆ ሊያነሳ ሲል እጁ ሰለለች:: ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ ግን ሕዝቡ ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን አምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል የገደልኩሽ እኔ:: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው:: እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች:: ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ††† ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን:: ††† ሐምሌ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያዊ ሰማዕት 2.አበው ቅዱሳን ብዮክና ብንያሚን 3.ቅድስት ቅፍሮንያ (ሰማዕት ወጻድቅት) 4.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 5.አቡነ ገብረ መድኅን ጻድቅ 6.አባ ክልዮስ ዘሮሜ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ 2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት 4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር ††† "በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ጌታ ኢየሱስ ቀርበው "በመንግስተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?" አሉት:: ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ:: እንዲህም አለ:- "እውነት እላቹሃለሁ:: ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ አትገቡም:: እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግስተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው::" " ††† (ማቴ. ፲፰፥፩) --------ወስብሐት ለእግዚአብሔር -----
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን ዜማ(Nahu seman zema)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

+++ የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት ++         አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ እንጅ የምፈጽም ባለመሆኔም ምክንያት በድቡሽት ላይ እንደተሠራ ቤት ሆኛለሁ። ጥልቀት በሌለው አኗኗር ላይ የተገነባው መንፈሳዊነቴ ጎርፍ በጎረፈ፣ ነፋስ ባለፈ ጊዜ የሚናወጥ ደካማ ሆኖብኛል። ዓለምን ለማሳለፍ ዳግመኛ መምጣትህን ባሰብሁ ጊዜ እደነግጣለሁ። ጻድቃን “አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና” እያሉ የምትመጣበትን ቀን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሴት በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ እኔ ግን አሁንም ለንስሐ ዕድሜ እንድትጨምርልኝ እለምናለሁ። በተራራው ስብከት ጊዜ ተገኝቼ ስታስተምር ባልሰማህም፤ በደብረ ታቦር በተገለጥህ ጊዜ ክብርህን ካዩት መካከል ባልሆንም፤ በደብረ ዘይት እጅህን ጭነህ ከሾምኻቸው ውስጥ ባልመደብም አንተ ግን ለእኔ ምሕረት ማድረግን አትሰለችም። ወደ አንተ ባልመጣ እንኳን በተኛሁበት መጥተህ “ልትድን ትወዳለህ?” ማለትህ አይቀርም። ከሰማይ የወረድህልኝ ሆይ! ኢያሱ ለእስራኤል ርስታቸውን እስኪያወርሳቸው ፀሐይን እንዳቆምህለት በምድር ላይ ያለን ኃጥአን ልጆችህ ሰማያዊት ርስትህን ሳንወርሳት ፀሐይ አትጥለቅብን፤ ዕድሜአችን አይለቅብን።  አሜን! ( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ) ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

††† ✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ ††† ††† ✝እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ✝ ††† ††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ✝ ††† =>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6) +የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: +ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: +የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: =>መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ +የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ +በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት +በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ +እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ +የጌታችንን መንገድ የጠረገ +ጌታውን ያጠመቀና +ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: +ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች:: +" አባ ጌራን ሕንዳዊ "+ =>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሕንድ ካፈራቻቸው ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ጻድቁ አባ ጌራን ይታሰባሉ:: የእኒህ ቅዱስ ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ቅዱሱ በሕንድ ተወልደው: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድገው: ገና በወጣትነታቸው መንነው: ደሴት ውስጥ ወደሚገኝ አንድ በርሃ ገብተዋል:: ከገድላቸው ጽናት: ከቅድስናቸውም ብዛት የተነሳ በሃገረ ሕንድ ሰይጣን እንዳይገባ: ጠብ ክርክር እንዲጠፋ: ሰው ሁሉ በፍቅርና በሰላም እንዲኖር ማድረግ ችለው በጣም ተወዳጅ ነበሩ:: +በዚህ የተበሳጨ ሰይጣን ግን ባልጠረጠሩት መንገድ መጣባቸው:: አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው መጥታ (የንጉሡ ልጅ ነኝ በሚል) አስጠግተዋት ነበር:: አንድ ሌሊት ላይ ግን አውሬ ያባረራት በመምሰል ሩጣ ወደ ቤታቸው ገብታ አቀፈቻቸው:: በዚያ ቅጽበት ፍጡር ደካማ ነውና ታላቁ አባ ጌራን ተሰነካከሉ:: ከአፍታ በሁዋላ የሆነውን ሲያውቁ ደም አለቀሱ:: +ልብሳቸውን ቀደው: እንባቸው እንደ ዥረት እየፈሰሰ አለቀሱ:: ራሳቸውን በትልቅ ድንጋይ እየቀጠቀጡት የጭንቅላታቸውና የደረታቸው አጥንቶች ተሰባበሩ:: እርሱ እግዚአብሔር መሐሪ ነውና ይቅር ብሎ: የቅድስና ስም ሰጥቶ በዚሕች ቀን ወደ ገነት አሳርጉዋቸዋል:: ለዚህ ነው መጽሐፉ "ጻድቅ 7 ጊዜ ይወድቃልና: ይነሣማል" ያለው:: (ምሳ. 24:16) =>አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ አባ ጌራን በረከት ይክፈለን:: =>ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ) 2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ) 3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ) 4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ) 2.አባ ሣሉሲ ክቡር 3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት 4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት =>+"+ ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው:: +"+ (ሉቃ. 1:76) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Hammasini ko'rsatish...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.