Werabe university muslim students union
Kanalga Telegram’da o‘tish
This is the official telegram channel of wrumsu. Email: wrumsu12@gmail.com twitter: http://twitter.com/wrumsu Telegram: @wrumsu
Ko'proq ko'rsatish1 447
Obunachilar
+424 soatlar
+127 kun
+4530 kun
Postlar arxiv
🕌🕌السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🕌🕌
🗓በ2019 ዓ.ል አዲስ ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ል ወራቤ ዩኒቨርስቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ::
✏️በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለእዚህ እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን !!
✏️የወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን እያሳወቀ የናንተን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::
ማንኛውንም information ለማግኘት እነዚህን የተመደቡ የጀመአ አባላቶችን Contact ማድረግ ትችላላችሁ::
✅ አ/ሀሚድ ረሺድ +251955354953
✅አ/ሀኪም ሙሰማ +251919289727
✅አባስ ኢድሪስ +251972984344 (ormomifa)
የእህቶችን ስልክ በ: +251919289727 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ራሳችሁን እና ማህበረሳባችሁን የምትጠቅሙበትን እውቀት እና ልምድ ትቀስሙ ዘንድ ተመኘን::
https://t.me/wrumsu
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ለ2 ወራት የሚቆይ ልዩ ኮርስ፦
(ወጣ ያለ ሀሳብ ስለሆነ ሙሉ ብታነቡት።)
ይህ ኮርስ በአላህ ፍቃድ በተለያዩ ኢስላማዊ የዒልም ዘርፎች ላይ ያለንን እውቀት ከፍ ለማድረግ፣የንባብ ልምዳችንን ለማዳበር እና ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም አጋዥ ነው።በሂደቱ ላይ ፈተናዎች የሚኖሩ ሲሆን ተደምረው ከ300 በመያዝ ከፍተኛ ውጤት ለሚያስመዘግቡ 30 ሰዎች ተሸላሚ የሚያደርግ ይሆናል።ለሁሉም ተሳታፊዎች ደግሞ የውጤት ካርድ ይዘጋጃል።
የኮርሶቹ ይዘት እንደሚከተለው ሆኖ በአማርኛ ቋንቋ ለየብቻ በPDF ወይም በ PPT የሚቀርቡ ይሆናሉ።
1,ከዓቂዳ:ኹዝ ዐቂደተክ
2,ከፊቅሂ:ስለ ውርስ ህግጋት(መዋሪስ)
3,ከአዳብ:ሙንከራት
4,ከሲራ:ከረሱል(صلى الله عليه وسلم)ታሪክ በጥቂቱ።
ንባብ በራሳችሁ ሆኖ አንዳንዴ live ልንገናኝ እንችላለን።
ሽልማቱ የተዘጋጀው በስፖንሰር አማካኝነት ሲሆን በቅደም ተከተል፦
አንደኛ ለወጣ/ች:ኪታብ እና 60,000ብር
ሁለተኛ:ኪታብ እና 50,000ብር
ሶስተኛ:ኪታብ እና 25,000ብር
አራተኛ:ኪታብ እና 10,000ብር
አምስተኛ:ኪታብ እና 5000ብር
ስድስተኛ:ኪታብ እና 4000ብር
ሰባተኛ:ኪታብ እና 3000ብር
ስምንተኛ:ኪታብ እና 2000ብር
ዘጠነኛ:ኪታብ እና 1500ብር
አስረኛ:ኪታብ እና 1000ብር
ከ11 እስከ 30ኛ ለሚወጡ ደግሞ የኪታብ ሽልማት ይሆናል።
የመመዝገቢያ እና የሙሉ ሂደቱ ዋጋ:300 ብር ነው።
የኮርስ ግሩፑ link፦https://t.me/liyucourse
ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች እዚያው ግሩፑ ላይ ታገኛላቹ።
በዚሁ አጋጣሚ:fresh ተማሪዎች ካላችሁ የpsychology,logic & english ኮርሶች tutorial እና ppt ሊዘጋጅ ስለሚችል በ @zidni1 አሳውቁኝ።
🌺 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 🌺
🌸 ውድ እና የተከበራችሁ እህቶቻችን!
እነሆ ያላወቅነውን የምናውቅበት፣ ያልተማርነውን የምንማርበት እና የመንፈስ እርካታን የምናገኝበት ልዩ የእህቶች ለእህቶች የሙሀደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል!
‼️ መች? የት? በምን ርዕስ? አትሉም?
ባትሉም በለመድነው በታወቀው ስፍራችን ተገኝተን በአላህ ፈቃድ በሚከተሉት አስተማሪ ርዕሶች ላይ ልንተዋወስና ልንማማር ቀኑ እስኪደርስ በጉጉት እየጠበቅን ነው፦
👉 ስለ እስልምና እና ተውሂድ (ልዩ ዳዕዋ)
👉 ስለ ሴት ሰሀብያት አርአያነት ያለው ታሪክ
👉 ልዩ ልዩ አነቃቂና ማራኪ ግጥሞች
👉 እና ሌሎች በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች
📅 ቀን፦ እሁድ (01/02/2019 ዓ.ል)
⏰ ሰዓት፦ ጠዋት 3:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሰልማን አል-ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ
🌸 ለኢልም እንደሚጓዙ እግሮች ጠንካራ፣
ለኢልም እንደሚከፈቱ አእምሮዎች ብሩህ፣
ኢልምን እንደሚናፍቁ ልቦች ቅን የሉም! 🌸
✨ዉድ እህቶች በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችዋል!
@wrumsu
🌺 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ 🌺
🌸 ውድ እና የተወደዳችሁ እህቶቻችን!
እነሆ ያላወቅነውን የምናውቅበት፣ ያልተማርነውን የምንማርበት እና የመንፈስ እርካታን የምናገኝበት ልዩ የአህቶች ለእህቶች የሙሀደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል!
‼️ መች? የት? በምን ርዕስ? አትሉም?
ባትሉም በለመድነው በታወቀው ስፍራችን ተገኝተን በአላህ ፈቃድ በሚከተሉት አስተማሪ ርዕሶች ላይ ልንተዋወስና ልንማማር ቀኑ እስኪደርስ በጉጉት እየጠበቅን ነው፦
👉 ስለ እስልምና እና ተውሂድ (ልዩ ዳዕዋ)
👉 ስለ ሴት ሰሀብያት አርአያነት ያለው ታሪክ
👉 ልዩ ልዩ አነቃቂና ማራኪ ግጥሞች
👉 እና ሌሎች በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች
📅 ቀን፦ እሁድ (01/02/2019 ዓ.ል)
⏰ ሰዓት፦ ጠዋት 3:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሰልማን አል-ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ
🌸 ለኢልም እንደሚጓዙ እግሮች ጠንካራ፣
ለኢልም እንደሚከፈቱ አእምሮዎች ብሩህ፣
ኢልምን እንደሚናፍቁ ልቦች ቅን የሉም! 🌸
✨ እህቶች በሙሉ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል! እንዳያመልጥዎ!
@wrumsu
Repost from Werabe University
#ማስታወቂያ
ቀን፡-29/01/2019
1ኛ) ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ1ኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ
2) በ2018 ትምህርት ዘመን የሪሜዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አጠናቃችሁ የማለፊያ ነጥብ ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በተራ ቁጥር 1) እና 2) የተገለጻችሁ ተማሪዎች የ1ኛ አመት 1ኛ ሴሚስተር ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 16 እና 17/2019 መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሜድያል) ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ወደፊት በመገናኛ ብዙሃን የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን።
በተራ ቁጥር 1 የተገለጻችሁ ተማሪዎች:-
◆ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ክልላዊና በሔራዊ ፈተና ሰርተፍኬት እና ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና አንድ የማይመለስ ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል።
◆ ሁሉም ተማሪዎች የእስፖርት ትጥቅ፣አንሶላ፣ብርድ ልብስና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።
◆ በተለያየ ምክንያት በ1ኛ አመት 1ኛ መንፈቅ የመልሶ ቅበላ ሞልተው የወጡ የመጀመሪያ ዲግሪ የመደበኛ መርሐ ግብር ተማሪዎች ጥቅምት 19/2019 ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
◆ ጥቅምት 18/2019 የቅጣት ምዝገባና መማር ማስተማር የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
◆ ሌሎች መረጃዎችን በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽ የሚገለጹ ስለሆነ የዩኒቨርሲቲውን ፌስቡክ ገጽ ይከታተሉ።
ዕውቀት ለልህቀት!
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
🎙የዳዕዋ ፕሮግራም!
🔻በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=7b970bcacee9ec3de3
✨ ታላቅ የምስራች ለወራቤ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በሙሉ! ✨
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
👉እነሆ የ2019 ዓ.ል የቂርዓት ፕሮግራማችንን ማስጀመርያን እና ለእናንተ ለውድ ወንድምና እህቶቻችን የተዘጋጀውን ልዩ Welcome Program ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው
👉በፕሮግራማችን ላይ በተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን) የተዘጋጀ ልዩና መንፈስን የሚያድስ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል.
ከጥዑም አንደበታቸው የሚወጡ ጠቃሚ ተግሳፆችንና ምክሮችን በመቅሰም የመንፈስ ምግብ እንድንሸምት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል.
🕌ቦታ፦ ሰልማኑል ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ
🕧ቀን እና ሰዓት፦ ዛሬ ጁመአ ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ
⭐እጅግ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንዳያመልጥዎ.
ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ.
⭐الدآل عل الخير كفاعله.⭐
💐 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌼
ውድ የ WRU ሙስሊም እህቶች እንዴት ከርማችኋል?
እንኳን ወደ ግቢ በሰላም ተመለሳችሁ እያልን፤ አላህ ባገራልን ልክ ለዲናችን ጊዜ በመስጠት ለመጪው ዓለም ስንቃችንን እንያዝ! በዚህም ጀማዐው በሚያዘጋጃቸው የቂርዓት ፕሮግራሞች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ጀማዐችን ለሴት ተማሪዎቻችን የቁርኣን ቂርዓት ምዝገባ የጀመረ በመሆኑ፤ ነባርም ሆናችሁ አዲስ ተማሪዎች በተጠቀሰው ጊዜ መስጂድ በመገኘት እንድትመዘገቡ እንገልጻለን💥
📚 የሚሰጡ ትምህርቶች: ቃኢዳ እና ነዞር (በተጅዊድ)
📍 ቦታ: ሰልማን አል-ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ
📅 የምዝገባ ቀን: ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ
🚀 ቂርአት የሚጀምርበት ቀን: ሰኞ
⏰ የቂርአት ሰዓት: ከእራት በኋላ ከ 11:30 ጀምሮ
"ከእናንተ መካከል በላጩ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው።" (ሐዲስ)
✨ ዕድሉን ሳይመልጡ ፈጥነው ይመዝገቡ!
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ጀማዐ (WRUMSU)
ማስታወቂያ
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
ውድ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን በደህና መጣችሁ እያልን የሰልማነል ፋሪስ መስጂድ በኩል ጀመዓችንን ለማገዝ በተቋቋመዉ የሱቅ አገልግሎት እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናቀርባለን ።
{ባልዲ🪣፣ መዘፍዘፊያ፣,የበሶ መበጥበጪያ,መጥረጊያ,መወልወያ,ሳሙና, ደብተር📕✏️ ..ሌሎችም የሸቀጣሸቀጥ አቅርቦት አለን!!)
✍በይተልማል ስትራክቸር
11-1-2019 ዓ.ል
የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን
ወደ ዩኒቨርሲቲ ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች፦
ከላይ የተቀመጠው መረጃ የየዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎችን መረጃ የያዘ ሲሆን በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ስለ ዩኒቨርስቲዎቹ፤ ጀመዓዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች መጠየቅ ትችላላችሁ።
አላህ ለስኬት መሠረት የሆነን ቆይታ ያድላችሁ።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቀጥታ ስርጭት!
◇ ሰይድ ቁጥብ ማን ነው?
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=abaae191d35c62b5f9
ለግቢ ተማሪዎች ማስታዎሻ
እንደሚታወቀው እንደ ሀገራች ዛሬ ''የዘመን መለወጫ በአል'' ነው ተብሎ ነው ሚታሰበውና እንደ ሙስሊም ደሞ ይህ ነገር አይመለከተንም አናውቀውም,በመሆኑም በአሉን ተከትለው በሚመጡ ማነኛውን ተግባራት እንዳንገኝ መጠንቀቅ ኣለብን:
ከዎትሮ በተለየ መልኩ የሚዘጋጀውን ምግብ,የእንኳን አደረሳቹህ መልእክት,በተለየ መልኩ መቆነጃጀት.... ሌሎችንም ፈፅሞ መራቅ ኣለብን።
አቡ ፈውዛን
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
📢 አስቸኳይ ማስታወሻ
📢 ከወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የረመዳን የገቢ ማሰባሰቢያ ማስታወሻ
🕌በተከበረው የረመዳን ወር ህብረታችን ባደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ብዙ ወንድሞችና እህቶች በመሳተፍ በግላቸው እንዲሁም በዲፓርትመንት፣ በስትራክቸር እና በግሩፕ ደረጃ የተለያዩ ኒያዎችን ገብተዋል። አሁን የዩኒቨርሲቲ መመለሻ ጊዜ እየተቃረበ በመሆኑ፣ ያ የተገባው ኒያ ወደ ተግባር ሳይቀየር ጊዜው ማለቅ የለበትም ።
🔹 1. በግል ኒያ የገባችሁ
በረመዳን ወቅት በግላችሁ የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት ኒያ የገባችሁ ሁላችሁም፣ የገባችሁትን ኒያ እንዳትዘነጉ እና በተቻለ ፍጥነት እንድታስገቡ እንጠይቃለን።
ሙሉውን የገባችሁትን መጠን አሁን ማስገባት ካልቻላችሁ፣ የተቻላችሁን ያህል ክፍል አሁኑኑ በማስገባት ቀሪውን በኋላ ማሟላት ትችላላችሁ። ነገር ግን የገባችሁት ኒያ ሳይፈጸም እንዳይቆይ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ።
🔹 2. በዲፓርትመንት፣ በስትራክቸር እና በግሩፕ ደረጃ ኒያ የገባችሁ
በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ወቅት በዲፓርትመንት፣ በስትራክቸር ወይም በግሩፕ ስም የተወሰነ የገንዘብ መጠን ለማስገባት ኒያ የገባችሁም የተገባውን ቃል በመፈጸም የተሳተፋችሁበትን ስራ እንድታጠናቅቁ እንጠይቃለን።
ይህ የጋራ ኒያ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ አካል በተቻለው መጠን በመተባበር የተገባው መጠን እንዲሟላ ማድረግ ይጠበቅበታል። ስለዚህ የዲፓርትመንታችሁ፣ የስትራክቸራችሁ ወይም የግሩፓችሁ ኒያ እስካሁን ካልተሟላ፣ እባካችሁ አታዘግዩት፤ አሁን ባለው ጊዜ አስተባብራችሁ አስገቡ።
🔹 3. ኩፖን የወሰዳችሁ
በረመዳን የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ እና ለክረምት ከግቢ ስትወጡ ኩፖን የወሰዳችሁ ወንድሞችና እህቶችም ኩፖኑን ይዛችሁ የዩኒቨርሲቲ መመለሻን እንዳትጠብቁ። እስከምትመለሱ ድረስ ባለው ጊዜ ኩፖኑን በመሸጥ የተሰበሰበውን ገቢ እንድታስገቡ እንጠይቃለን።
ኩፖኑን ሁሉ ለመሸጥ የምትችሉትን ያህል ጥረት አድርጉ። ሁሉንም መሸጥ ካልቻላችሁ ግን የሸጣችሁትን ኩፖን ገቢ እንዳትይዙት እና በተቻለ ፍጥነት እንድታስገቡ እንጠይቃለን። የቀረውንም ኩፖን በተቻለ መጠን አስቀድማችሁ እንድታጠናቅቁ እንጠይቃለን።
⏰ አሁን የምንጠይቀው በቀላሉ የሚታለፍ ማስታወሻ አይደለም። የመመለሻ ጊዜ እየተቃረበ በመሆኑ፣ በግል የገባችሁትን ኒያ፣ በዲፓርትመንት/ስትራክቸር/ግሩፕ የገባችሁትን ኒያ እና ከኩፖን የተሰበሰበውን ገቢ ከዛሬ ጀምሮ በተቻለ ፍጥነት እንድታስገቡ እንጠይቃለን።
ይህንን ስራ በረመዳን ወቅት በጋራ ጀምረነዋል፤ አሁን ደግሞ በጋራ ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል። ስለዚህ የገባነውን ኒያ እንፈጽም፣ የወሰድነውን ኩፖን እንሸጥ፣ የተሰበሰበውንም ገቢ በጊዜው እናስገባ።
በአዲስ አበባ የምትገኙ ኩፖን መዉሰድ የምትፈልጉ ከስር ባለዉ ስልክ በመደወል መዉሰድ ትችላላችሁ
0903232526
📢ማሳሰብያ:-💳 ገቢውን ካስገባችሁ በኋላ፣ የክፍያውን/የማስገባቱን ማረጋገጫ Screenshot አድርጋችሁ ይዛችሁ ይሁን። ይህም ገቢው በትክክል መግባቱን ለማረጋገጥ እና የተገባውን ኒያ ከመዝገብ ላይ ለማስተካከል/ለመሰረዝ የሚያግዝ ማረጋገጫ ነው።
📌 የገቢ ማስገባቱን Screenshot ከያዛችሁ በኋላ፣ ለሚመለከተው አካል በዚህ telegram username @Jelu23 በመጫን እንድትልኩ እናሳስባለን። ማረጋገጫው ከደረሰ በኋላ የከፈላችሁት መጠን ከኒያ መዝገብ ላይ እንዲታወቅና እንዲሰረዝ ይደረጋል።
አካውንት:
1000381650018 ወራቤ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመኣ
የሱና ሰዎች ለሌሎች መመራት ይጨነቃሉ እንጂ በሌሎች መሳሳት አይደሰቱም!!
ሀቅን የያዝከው በአሏህ ፍቃድ እንጂ በራስህ ብልህነት, እውቀት, ጉልበት… አይደለም: ስለሆነም በያዝከው ሀቅ ቀጥ ትል ዘንድ ጠዋት ማታ አሏህን መለመን ግድ ነው!
እንዲሁም በሌሎች መመፃደቅ, መሳለቅና በእነሱ ላይ ፈፅሞ ዱኣ ማድረግ የለብህም በል የነሱ መንገድ መሳት ሊያሳዝንህ ሊያስከፋህ እና ብሎም ዱኣ ልታደርግላቸው ነው ሚገባው ቀደምት ሰለፎች ይታወቁ የነበረው በእዝነት በትህትና በመምከርና ለሌሎች ዱኣ በማድረግ ነበር!
ዛሬ የኛን ሁኔታ ግን ከሰለፎች አንፃር ማገናዘቡ ያባት ይሁንና…
እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ አስመልክቶ ሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ:
"የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች በዓርሽ ጉዳይ፣ ቁርኣን የአሏህ ቃል በመሆኑ እና በአሏህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ መውረድ(ኑዙል) ጉዳይ ምክንያት በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱት በደል በበረታ ጊዜ፤ ወንድማቸው ሸይኽ ሸረፉዲን ተማጽኖ በማቅረብ በእነርሱ ላይ ዱዓ ማድረግ (እንዲጠፉ) ጀመረ።"
"ሸይኽ አል-ኢስላም ግን ከለከሉትና እንዲህ አሉት፦ 'በል እንዲህ በል፦ አላህ ሆይ! ወደ እውነት የሚመሩበትን ብርሃን ስጣቸው።'"
ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ይህን ንግግር አስመልክተው እንዲህ ይላሉ:
"ለአላህ ምስጋና ይሁንና! ይህ ምንኛ ታላቅ ስነ-ምግባር ነው! ምንኛ የላቀ ባህሪ፣ የነፍስ ዝቅታ (ትህትና) እና እውነትን መፈለግ ነው! በአላህ ይሁንብኝ! ይህች (ትምህርት) ብቻዋን ረጅም ጉዞ ሊደረግላት የሚገባት ፋይዳ ናት።"
"እኛ ካለንበት ሁኔታ ጋር ይህ ምንኛ ይራራቃል! ከእኛ መካከል አንዱ በትንሹ እንኳን ሲበደል ወዲያው ቁጣና ጥላቻ ይወርረዋል፤ በጠላቱ ላይም የዱዓ አይነቶችን ሁሉ ያዘንባል። አላህ ሆይ! ለእኛም ሆነ ስለ አንተ ብሎ ለበደለን ሰው ወደ እውነት የምንመራበትን ብርሃን ስጠን።"
አቡ ፈውዛን
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
📢 ልዩ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም!
❝ሰይድ ቁጥብ ማን ነው? ለተሳሳቱ ውዳሴዎችና ማደናገሪያዎች የሚሰጥ ምላሽ❞
🎙 አቅራቢ፦ ኢብኑ ሙነወር
🗓 ቀን፦ ዛሬ ማክሰኞ
⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ
◇ የቀጥታ ስርጭት አድራሻ👇
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
