cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አል–ዒምራን (CMC) የቁርኣንና ኢስላማዊ ት/ት ተቋም

➡️ ይህ የአል–ዒምራን(cmc) የቁርአንና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም official ቻናል ሲሆን፣በዚህ ቻናል ➲ ስለ ተቋሙና በስሩ ስላሉ ቅርንጫፎች የተለያዩ መረጃዎች ይለቀቃሉ ➲ እለታዊና ወቅታዊ ምክሮች ➲ ሳምንታዊና ወርሓዊ የዳዕዋ ፕሮግራሞች የሚለቀቁበት ይሆናል። ቻናሉ ተደራሽነት እንዲኖረው ለሌሎች በማጋራት የበኩሎን ይወጡ። https://t.me/alimranislamic

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
5 618
Obunachilar
+724 soatlar
+787 kunlar
+29030 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የዒድ ሶላት በአል ዒምራን የቁርአን እና ኢስላማዊ ትምህርት ተቋም
Hammasini ko'rsatish...
53👍 5🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከዐረፋህ ቀን ትሩፋት       👇👇👇 عن عائشة -رضي الله عنها- أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: "ما من يوم أكثر أن يعتق الله فيه عبدا من النار من يوم عرفة،  رواه مسلم ከእናታችን ዓዒሻህ (ረዲየሏሁ ዐንሀ ) በተላለፈ ሐዲስ ነብዩ ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)  እንዲህ ብለዋል ፡ " አላህ ባርያን ከእሳት ነፃ ከሚያደርግባቸው ቀናቶች መሀከል የዐረፋን ያህል የበዛ ነፃነትን የሚለግስበት ቀን የለም " ሙስሊም ዘግበውታል
Hammasini ko'rsatish...
22👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
የዐረፋህ ቀን ትሩፋቶች **** ➡️ የዐረፋ ቀን በዒድ አል–አድሐ ዋዜማ ማለትም በዙል ሒጃህ ዘጠነኛ ቀን ላይ የሚውል ቀን ነው ። ▶️  የዐረፋ ቀን ከዓመቱ ቀናቶች ሁሉ በላጭ እንደሆነ በኢብኑ ሒባን በኹዘይማህ እና በበዛር የሐዲስ  ጥራዝ ውስጥ በሰፈረው የጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ሐዲስ ነብዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ተወስቷል ... " ما من يوم أفضل عند الله من يوم عرفه " " ከዐረፋ ቀን በተሻለ በአሏህ ዘንድ በላጭ የሆነ ቀን የለም " ➡️ የዐረፋህ ቀን ሑጃጆች ወሳኝ የሚባለውን የሐጅ መሠረት ለመፈፀም በዐረፋህ ሜዳ ላይ የሚቆሙበት ቀን ሲሆን በሐጅ ኑሱክ ላይ ያልሆነ ሰው ቀኑን በመጾም እና የተለያዩ ዒባዳዎችን በማብዛት ማሳለፍ ይወደድለታል ▶️ ሰዪዱና አቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት’ና ሙስሊም ውስጥ በተዘገበ ሐዲስ ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዐረፋ ቀን ስለመፆም ተጠይቀው ... "يكفر السنة الماضيه والسنة القابلة " " ያለፈውን እና የመጭውን ዓመት ወንጀል ያስምራል " በማለት መልሰዋል ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 21 11
ስለ ኡድሂያ ማብራርያ ( በመዝሀብ ሻፊዒይ) ሰይዳችን ﷺ ስለ እርድ እንዲህ ብለውናል :- « የአደም ልጅ የአረፋ ቀን ከማረድ የበለጠ አላህ የሚወደውን ስራ አልሰራም ፤ የታረደችዋም የቂያማ ቀን ከቀንዶቿ ከጥፍሮቿም ጭምር ትቀርባለች፤ ደሙ መሬት ላይ ከመድረሱ በፊት አላህ ጋር አጅሩ ይደርሳል፤ ተደስታቹ ስሯት » 📗 ኢብኑ ማጀ'ህ (3124) ፡================== • ኡድሂያ የተባለበት ምክንያት ወቅት ዱሀ (ረፋዱ) ሰዓት ላይ የሚታረድ በመሆኑ ነው ይላሉ ዑለማዎች። • ኡድሂያ ማረድ በዒዱ ቀናቶች ከሚያስፈልገው ነገር ተጨማሪ ማረድ የሚያስችል ሀብት ላለው ሰው  የጠበቀ ሱና ነው። ኢማሙ ቲርሚዚ'ይ በዘገቡት ሀዲስ ሰይዳችን ﷺ :- « እንዳርድ ታዝዣለው ፤ ለእናንተ ደሞ ሱና ነው »  ብለዋል ነዝር ካደረገው ግን ( ስለት ከገባ) ዋጂብ ይሆናል። • ለኡድሂያ የሚቀርቡት 1- ግመል (5 አመት የሞላው) 2- በሬ/ላም/ፍየል (2 አመት የሞላው) 3-  በግ (1 አመት የሞላው) • የሚታረደው ከብት ስጋውን ከሚቀንስ ወይም ከሚያነውር ጉድለት መጥራት አለበት ( በጣም የከሳ ፤ ያበደ ፤ እውር ውይም አንድ አይኑ የጠፋ፤ በሽታ ያለበት ፤ ጆሮው ወይ ምላሱ የተቆረጠ  ወይ ሙሉ ጥርሱ የሌለና የመሳሰሉት ነውሮች የሌለበት መሆን አለበት ) • አንድ ቤተሰብ ውስጥ አንዱ ካረደ ይበቃል። ሁሉም ከቻሉና አጅር ለማግኘት ሁሉም ቢያርዱ የተወደደ ነው። • ግመል ወይም ከብት ለሰባት ሰዎች መሻረክ ይቻላል። • የሚታረድበት ሰዓት የሚጀምረው የዒዱ ጠዋት ፀሀይ ከወጣችና አጠር ያሉ የሁለት ረክዐ ሰላትና ኹጥባ ጊዜ ካለፈ  ቡሀላ ነው። ከዛች ሰዓት ጀምሮ እስከ ሶስተኛው አያም ተሽሪቅ (13 ዙል ሂጃ) መግሪብ ድረስ ይቻላል። • ቡኻሪና ሙስሊም ከሰይዳችን ﷺ በዘገቡት ሀዲስ :-  « በዚህ ቀናችን (የአረፋ ቀን) መጀመርያ የምንጀምርበት ስራ ሰላት እንሰግዳለን ፤ ከዛ ተመልሰን እናርዳለን። ይሄን ያደረገ መንገዳችንን በእርግጥ አግኝቷል ፤ ከዛ በፊት ግን ያረደ ለቤተሰቡ እንደማንኛው ግዜ እንደሚያቀርብላቸው ስጋ ነው ከኢባዳ ( ኡድሂያ) አይቆጠርም..» • ሱና ከሆነው ኡድሂያ ትንሽም ቢሆን ሰደቃ መስጠት ግዴታ ነው። ትንሽም ቢሆን ሰደቃውን ካወጣ ሙሉ አጅሩን ያገኛል። - የበለጠው ደሞ አንድ ሶስተኛውን በልቶ ሌላውን ሰደቃ ማውጣት ነው። - ከዚህም የበለጠ ደሞ ከኡድሂያው ጉበት ትንሽ  በልቶ ስጋውን በሙሉ ሰደቃ ማውጣት ነው። - የኡድሂያን ስጋም ሆነ ቆዳ ሰደቃ መስጠት እንጂ ምንም ነገር መሸጥ ክልክል ነው። ለገፋፊውም ቢሆን ክፍያ ተደርጎ አይሰጥም። • ኡድሂያ ለማድረግ ነዝር ያደረገ ( ስለት የገባ ) ኡድሂያው ዋጂብ ይሆናል። ዋጂብ ኡድሂያን ደሞ ስጋውን በሙሉ ሰደቃ ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል። • የኡድሂያን ሙሉ አጅር ለማግኘት ከማረዱ በፊት ወይም ሲያርድ ኒያ ማድረግ ይኖርበታል ። - እራሱ የማያርድ ከሆነ ኡድሂያው ሲታረድ መመልከት ይወደድለታል። አላህ ይወፍቀን ፣ አላህ ይቀበለን ፡==================
Hammasini ko'rsatish...
23👍 17
▶️ የዙል ሒጃህ መልዕክት ****               ❤️ በአሏህ ስጦታዎች እንጠቀም! ! ➡️ የተለያዩ በጎ ስራዎች በተለየ መልኩ እጥፍ ድርብ ምንዳ የሚያገኙበት ፣ ወንጀሎች የሚሰረዩበት’ና ብዙ ስጦታዎችን ያጨቁ የተለያዩ ቀናት ፣ ሳምንታት እና ወራት መኖራቸው ከጌታችን አሏህ እዝነት እና ስጦታ መገለጫዎች መሀከል ይመደባሉ ። እኚህ ቅዱስ ወቅቶች በተለያዩ ጊዜያት እየተፈራረቁ መምጣታቸው ባሮች በጥቂት ስራ እጥፍ ድርብ ምንዳ የሚያገኙበትን እድል ከመፍጠርም ባሻገር በመልካም ተግባሮች ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት ከፍ ማድረግ ይችላሉ ። ➡️ ከሳምንቱ ቀናቶች ውስጥ በላጭ የሆችው የጁሙዐ ቀን ስትመጣ ሶሏቷ የሳምንት ወንጀልን ማስማሯ ፣ የባርያው ልመና ተቀባይነትን የማይነፈግበት ድብቅ ሰዓት መያዟ’ና ሌሎችንም መልካም ነገሮች መያዟ ባርያው ከሌሎች ቀናት በተሻለ ለዒባዳ እንዲነሳሳ ያደርገዋል ። ነገረ ግን ቀኑን ከበጎ ተግባራት ተዘናግቶ የዋለ ባሪያ የአሏህን የሳምንት ስጦታ ሳይቀበል’ና ሳይጠቀምበት እንዳሳለፈ ይቆጠራል ። ➡️ ከወራቶች ሁሉ በላጭ የሆነው የረመዳን ወር ሲመጣም ሙስሊሙ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ለዒባዳ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ አያሌ መልካም ነገሮችን እንደመያዙ’ና ከለሊቶቹ አንዱ የ 83 ዓመት ዒባዳን ማስገኘት የሚችል እንደመሆኑ የአሏህ ባሮች ከሌላው ወራት በተሻለ በበጎ ተግባራት ላይ ይበራታሉ ። ነገር ግን ይህን መልካም እድል ችላ ብሎ የተገኘ ባሪያ የአሏህን ውድ ስጣታ ሳይቀበል’ና ሳይጠቀምበት እንዳሳለፈ ይቆጠራል ። ➡️ ከዐመቱ ቀናቶች ሁሉ በላጭ የሆኑት አስሩ  የዙል ሒጃህ ቀናት ሲመጡም  መልካም ስራዎች ሁሉ (ከጁሐድም በበለጠ) ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሚሆኑበት እንደመሆኑ የአሏህ ባሮች በጾም ፣ በዚክር ፣ በቁርአን ንባብ እና በመሳሰሉት በጎ ተግባሮች በመበራታት በዐመታዊው ልዩ የአሏህ ስጦታ ተጠቃሚ ለመሆን ይሽቀዳደማሉ ፣  እኚህን ውድ ቀናቶች ችላ ያለ ግን የአሏህን ስጦታ መጠቀም ባለመቻል ትልቅ ኪሳራ ውስጥ ይወድቃል ።   በአሏህ ስጣታዎች ተጠቃሚ እንሁን ! !
Hammasini ko'rsatish...
16👍 6