cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

መንታ ልቦች

Feta bcha no ድብርት😂🤣🤣 1~መጀናጀን😍 2~ፍቅር መመስረት❤ 3~መሰዳደብ😡😡 4~no ድብርት 😂 5~70ሰው add ላረገ admin ይሰጠዋል 6~100 ሰው add ላረገ 50 ብር አለው add አርጉ ተሸለሙ 7~በተረፈ አውሩ ዝም አይቻልም Lmangwem tyaki @Mtg24ab @Mtg24ab

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 840
Obunachilar
+824 soatlar
+157 kunlar
+1230 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
ያልታደለች እናት 💔 ሳቋን ለገሰችው መልኳን አተመችው ሳጠግብ አጉርሳ ከዚህ አደረሰችው አደገልኝ አለች ጦሮ ሊያሳርፈኝ የልፋቴን ዋጋ ፈጣሪ ሊክሰኝ . ግና መቼ ሊሆን ከልቧ ያለመችው በእርሱ ስትሰቃይ ዕድሜዋን ፈጀችው ዕድሜዋን ፈጀችው! ውጥኗን ቀጨችው! መኖር እንዳልጓጓች ሞቷን ናፈቀችው በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr @getem @getem @getem
230Loading...
02
‍ ​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ የቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ              ክፍል ❾ promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት ምን መሰለህ ጆን...ወሬው ላንተ ምንም አይጠቅምም ስትለኝ ይጠቅማል እንጂ ማወቅ አለብኝ አልኳት እንደዛ ነው? በቃ ፍቅር ይዞኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች🤔 ዘንድሮ እኮ አልቃሽ በዝቶ ተቸገርን🤔🤔 ፍቅር የያዘው ሰው ማልቀስ ነው😆 ሚስት ያገባ ወንድ ማልቀስ ነው😅 ትዳር የያዘች ሴት ማልቀስ ነው😆 ትዳር ያጣች ሴት ማልቀስ ነው😅   አሁንማ ሰው ለደስታ ብሎ እስከ አፍንጫው ጠጥቶ ሁሉ ማልቀስ ጀምሯል🤔🤔 አንቺ በይ ወደዛ ሂጅ አትነፋረቂብኝ የወደደ ሰው መውደድ የሚችል ልብ ስላለው ደስ ማለት ነው እንጂ ያለበት  ምን የሚሉት ለቅሶ ነው? ተይ ግን አንቺ ልጅ ቀልብ ግዥ በትንሽ በትልቁ አታልቅሽ ስላት አንተ ምን አለብህ በውስጤ ያለውን እሳት እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ስትለኝ ውስጥሽ ያለው እሳት ከሆነ ያንቺን እሳት ለማጥፋት ልብሽ ውስጥ የሚገባ ማንም አይኖርም ባይሆን በእሳቱ ቦታ  ወተት ምናምን ቢኖር ከኑሮ ውድነት ሸሽቶም ቢሆን ብዙ ሰው ይገባ ነበረ ብዬ መሳቅ ቀጠልኩኝ ጥርሳም ነህ እሺ የኔ ልብ የወተት መደብር መሰለህ እንዴ ማንም ሰው ገብቶ ገዝቶ የሚወጣው እኔ ነኝ እንጂ ቁም ነገር አለህ ብዬ የልቤን ስሜት የምናግረው ስትለኝ ውይይይ መቅዲ አንቺ እና ቴሌ ደሞ ቀልድ አታውቁም      ሁሉንም ነገር መቁጠር ስትወዱ በቃ እሺ ይቅርታ ከማነው ፍቅር የያዘሽ? ከባለሱቁ ደስታ ነው አይደል አልኳት ባክህ ከእሱ አይደለም አለችኝ ምን😬😬😬 ታድያ ከማን ሊሆን ይችላል አልኳት? ከፌስቡክ ጓደኛዬ ደስታ ነዋ ስትለኝ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ😎አንቺ እሱ እኮ ደስታ አይደለም ምን እያልሽ ነው አልኳት ምን? ምን እያልክ እንደሆነ አንተ ንገረኝ እንጂ ታድያ ደስታ ካልሆነ ማነው ስትለኝ የቱ? ማን? ብዬ ድንብርብር ማለት ቀጠልኩኝ ጆን ምን ሆነካል? የፌስቡክ ጓደኛዬ ማነው ብላ በድጋሚ መጠየቅ ጀመረች እኔም መልሼ የትኛው የፌስቡክ ጓደኛሽ አልኳት🤔🤔🤔 ልጁ ጤና የለውም እንዴ ሆሆሆ በቃ እንደውም ተው ባለሱቁ ደስታ ራሱ ነው መሰለኝ ስትል መቅዲ እኔ እኮ ብዬሽ ነበረ ደስታ ማለት እኮ በቃ ሁለት ሰው ነው አልኳት የምን ሁለት ሰው ስትለኝ አይ እሱማ ያው አንድ ሰው ነው እኔ እኮ በፊትም ብዬሻለሁ ደስታ ሴት በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ሴቶች እፊት ለፊቱ ሲሆኑ ምን እንደሚያወራ ራሱ አያውቅም ችግሩ በቃ ይኼ ብቻ ነው እንጂ እሱም እኮ ይወድሻል አልኳት እርግጠኛ ነህ ጆን ስትለኝ አዎ መቅዲ አልኳት እንደዛ ከሆነ እንደምወደው እነግረዋለሁ በቃ የምን ጭንቀት ነው ስትለኝ ዋውውው መቅዲ ምርጥ ሃሳብ እንደውም ዛሬ እንሂድ አልኳት እሺ ግን አሁን አይደለም ከሰአት በኋላ እንሄዳለን አለችኝ እኔ ደስ ብሎኝ እሺ አልኳት ሰአቱ እየቀረበ ሲመጣ መቅዲን ይዤ እሄዳለሁ ባልኩት ነገር ልቤ ቅር ተሰኝቶ ነው መሰለኝ መሄድ በጣም አስጠላኝ ልብስ ምናምን ቀይር እንሂድ ጆን ስትለኝ ድብርት ድብርት አለኝ ደሞ በጣም አምሮባታል😎😍😋 እንሂድ እንዴ አልኳት እንደ አዲስ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ እንዴ ቶሎ በል እንሂድ አለችኝ ደስ ባይለኝም መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ቀጠልን..... ክፍል አስር አርብ   ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄ https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
320Loading...
03
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_21 ...🖌የመቅደስ ድንጋጤ አንደበቷን አሰረው ሰውነቷን አደነዘዘው የምትሆነው ግራ ገባት ብቻ ደጋግማ ጌዲ ጌዲ ትላለች ጌዲዮ ግን አውቆ ስለነበር መጨረሻ ላይ በሳቅ ተንፈራፈረ ወይኔ መቅዲ ብሞትም አትጮሂም ማለት ነው እያለ የማያቋርጠውን ሳቁን ይስቅ ጀመር....በድንጋጤ ብቻ ቢሞት መቅደስ ሞታ ነበር ሞቶ መመለስም እንዲህ ከሆነ መቅደስ ግማሽ መንገድ ሄዳ ነው የመጣችው...እንደምንም እራሷን አረጋግታ እውን ቀልድ መሆኑ ሲገባት ንዴት ፊቷን በርበሬ አለበሰው...እሱ ግን አሁንም ይስቅ ነበር ቀልደህ ልብህ ወልቋል አለችው ጌዲም እየሳቀ እንዲህ ልበቢስ መሆንሽን ባቅ ኖሮኮ እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀልድም ነበር ሲላት መቅደስ ቦርሳዋን አንስታ ያዘዘችውም ቁርስ ሳይመጣ ጥላው ወጣች እሱም አረ ቁርሱ ቢቀር ልልበስና አብረን እኔዳለን አላት እሷ ግን እንዳልሰማች ሆና ከንዴቷ ብዛት መሬቱን አጥብቃ እየረገጠች ጥላው ሄደች።..ከዛም ቡሀላ ደጋግሞ ብዙ ጊዜ ቢደውልላትም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም በመጨረሻም እንደተቀየመችውና እንደማታነሳው ሲገባው ወይንሸት ጋር ደወለ ወይናም ገና ከማንሳቷ አንተ ልጅቱን ምን አርገሀት ነው እንዲህ አደንዝዘህ የላካት ነው ወይስ ድንግልናዋን ዛሬ ነው የወሰድከው ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ጌድዮም ባማረው ሳቁ አጅቦ እሱንማ እኮ ቆየሁ ከተረከብኩት ባይሆን ትዝታው ይሆናል አላት ወይናም ሳቁን ተቀብላ እየሳቀች ትዝታ እንዲህ ቢያረግማ እኔ በሽተኛ እሆን ነበር አለችው እሱም ወይናዬ ባክሽ በሆነ ነገር አስቀይሚያት እኮ ነው ስልኳንም አላነሳም አለችኝ በማሪያም አገናኚኝ አላት እሷም ውይ ጌዲዬ ገና ስወጣ ነው የደወልክልኝ አሁን ደግሞ ላይብረሪ ልገባ ነው ባይሆን ብርሀንና ሰአዳ ዶርም ስላሉ አንድኛቸው ጋር ደውል አለችው እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት..... የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ አላት...መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው... ✎ ክፍል ሀያ ሁለት(22) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜
340Loading...
04
Be Fetariyachu Emenu 🙏 @marakye22
881Loading...
05
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እንዲሁም የደስታ እንዲሆን እንመኛለን። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
930Loading...
06
💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 ✎ ክፍል (9) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌 20 reaction please ❤️😘
930Loading...
07
💓❦የልቤ ትርታ❦💓 ✎ ክፍል (21) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌 20 reaction please ❤️😘
921Loading...
08
ለማታዉቀኝ 2 ገጣሚ እና አንባቢ✍ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
1080Loading...
09
‍ ​​​​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በ የፍቅር ታሪክ የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ                            ክፍል 8⃣ እሷ ግን አሁንም ማልቀስ አላቆመችም ቆይ ግን ችግሯ ምንድነው? መቅዲ በእናትሽ በጭንቀት መሞቴ ነው የሆንሽውን ነገር ንገሪኝ አልኳት ጆን በቃ ቤት እንሂድ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መኪና ውስጥ ገባች🤔🤔 እኔም ዝም ብዬ መኪና ውስጥ ገብቼ ወደ ቤት መጣን.... ቤት እንደገባች በፍጥነት ወደ ክፍሏ ገብታ በሩን ዘጋች፣ መቅዲ እንደዚህ ስትሆን የመጀመርያ ነው የሆነ አዲስ ነገር መኖሩ ግልጽ ነው፤ ግን ምን ሊሆን ይችላል? ቆይ ውሸቴን ሰምታ ይሁን? እንደሱ ቢሆን ነው እኔንም ዘግታ ብቻዋን መሆን የመረጠችው? ቆይ ቆይ እንደዛ ብሆን በዝምታ ብቻ ማለፍ ትችላለች? ኖ በፍጹም አትችልም በዝምታ ማለፍ የምትችል ቢሆንማ ዛሬውኑ እውነቱን አፍርጬ እርፍ አልልም ነበረ! ለማንኛውም ለሁሉም ነገር ጊዜ መስጠት  ያስፈልጋል ውሃ ራሱ ድፍርስ ሲል ሰአት ስሰጡት እኮ ቆሻሸው ለብቻው ንጹህ የሆነ ውሃ ደሞ ለብቻው ይሆናል፤ የሰውም ስሜት እንደዛ ሲሆን ትንሽ ጊዜ መስጠት ከምንም በላይ ጠቃሚ ነው። እዛው በር አጠገብ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ስለ መቅዲ ማሰብ ጀመርኩኝ መቅዲ ትንሽ ከቆየች በኋላ ከክፍሏ ስትወጣ እኔ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ በሃሳብ ግን ህንድ ውቅያኖስ በመርከብ በማቋረጥ ላይ ነኝ😆😃😅 ሃሳብ እኮ ግፍ አያውቅም አንድ አንድ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ በልቶ ሀገሩ በደስታ ሲዋጥ አንተም በዚያን ጊዜ ተጫዋች እንደነበርክ ሁሉ አድርገው አምጥቶ ፊትህ ላይ ድቅን ያደርገዋል😆😅😃 በዚያን ቀን ብራዚል ላይ ሃትሪክ የሠራክ ሁሉ ሊመስልክ ይችላል😛😛 ከሃሳብ መርከብ ወረድ ስትል ነው ባህር ውስጥ ሳትሆን ደረቅ መሬት ላይ እንደሆንክ የሚታውቀው፣ እኔም እኮ በዚህ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ እኔ እና መቅዲ ፍቅረኛሞች ሆነን ልጅ ምናምን ቢኖረን እያልኩ ነበረ😉😉😃 እንደውም የልጁን መልክ ራሱ የማውቀው ይመስለኛል😛😛😛 መቅዲ በበር ጭንቅላቴን ባትለው ቆይ በሃሳብ መርከብ የት ልደርስ ነበረ🤔🤔 አንቺ መቅዲ ወይኔ ጭንቅላቴ ስል እሷም ተደናግጣ አይዞህ እሺ ጆን እኔን ይምታኝ ሲጀምር ቆይ እዚህ በር ስር ምን ትሠራለህ ለዛውም መሬት ላይ፣ ደሞ እንቅልፍ ወስዶህ ነበረ እንዴ በር ስከፍት እንኳን አትነሳም እያለች ጭንቅላቴን በእጇ ማሸት ጀመረች😗😗 የሷ እጅ ጭንቅላቴ ላይ አይደል ያለው? ቆይ ምንድነው ልቤን እንደዚህ ደስ ደስ አለው😍😍 ህመሙ ትቶኛል ግን ዝም አልኩኝ እጇን ከጭንቅላቴ ላይ ታነሳዋለች ብዬ ይበልጥ እእእእ ወይኔ ጭንቅላቴ ወይኔ ጭንቅላቴ እያልኩ ጎንበስ ብዬ ቀስ አልኩና ትንሽ ምራቅ ከአፌ በእጄ አምጥቼ አይኔ ላይ ቀብቼ ማልቀስ ቀጠልኩኝ😛😛😛 የኔ ምስኪን የእውነቴን መስሏት ጆን አይዞህ ጆን ይቅርታ እያለችኝ ነው፣ አሁን ጥሩ ሃሳብ መጣልኝ ቆይ ቅድም እሷ ያለቀሰችበትን ምክንያት ለምን ይኼን አጋጣሚ ተጠቅሜ እላውቅም ብዬ መቅዲ ዞር በይ እንደውም ያንቺን እርዳታ አልፈልግም አልኳት😉 ምን እያልክ ነው ጆን ጭንቅላትህ እኮ አብጧል ቆይ ትንሽ ልሸው ስትል በቃ አልፈልግም አንቺ ምን ስለሆንሽ ነው እኔ ስጎዳ እኔን ለመርዳት የመጣሽው? ቅድም አንቺ አልቅሰሽ አይዞሽ ሲል አይደል ክፍልሽ ገብተሽ በር የዘጋሺው አልኳት ጆን እሱ እኮ ሌላ ጉዳይ ነው ይኼ ደሞ ህመም እስቲ ቆይ ስትለኝ አልፈልግም አልኩሽ እኮ በቃ ዞር በይ አልኳት እሺ እኔም የሆንኩትን እናግራለሁ ግን በመጀመርያ ጭንቅላትህን ልሸው ስትል ኖ መጀመርያ ቃል ግቢልኝ አልኳት ከአንተ ይነጥለኝ እነግርሃለሁ አለችኝ ህመሜ የውሸት እንደሆነ እንደታውቅ  ትንሽ ዝም አልኳትና መቅዲ እጅሽ እኮ መድኃኒት ነው ዳንኩኝ እኮ አልኳት😛😛 አየህ የኔ እጅ እንደዚህ ነው ስትለኝ እንኳንም የኔ ሆንሽ አሁን የቅድሙን ምስጢር አልኳት ጆን እሱ ላንተ  ምን ያደርጋል ስትለኝ Promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት ጆን ምን መሰለህ.... ክፍል ዘጠኝ ማክሰኞ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄ https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
1092Loading...
10
‍ ​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ           ክፍል 7⃣ እኔ ግን እስከአሁንም በመቅዲ የጨረቃ ምሳሌ እንደተመሰጥኩ ነው😍 ግን እኮ አንድም ቀን መቅዲ እንደዚህ አስተዋይ ናት ብዬ አስቤ አላውቅም ነበረ ሞኝ የሚመስሉ ሰዎች ልባቸው እንቁ ነው፤ ልባቸው ውስጥ ከፍቅር ከገርነት ውጭ ተንኮል ሆነ ጥላቻ አይኖርም! የዋሀ ሰዎች የፍቅር ተምሳሌት አይመስሉም? ኩራት አያውቁም ትዕቢት አያውቁም በኔ ላይ እየሳቁ ነው ብለው አይጨነቁም አንተ እነሱ ላይ ስትስቅ አብረው ይስቃሉ😍😍የዋሀ ሰዎች የፍቅር ተምሳሌት መሆናቸውን ያወኩት በመቅዲ ነው የመቅዲን ስሜት ሳጠና መቅዲ ከደስታ ጋር ስትሆን ብዙም ደስ አይላትም ቤት መጥታ በፌስቡክ ግጥም ማንበብ ስትጀምር ግን የት እንደሆነች ሁሉ አታውቅም😅😆😛 አንድ አንድ ጊዜ   ቤት ውስጥ እናቷ እና አባቷ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን እየተመለከቱ መቅዲ ፌስቡክ ውስጥ ገብታ ደስታ በእናትህ አንድ ግጥም ላክልኝ ትላለች እምቢ ማለት ችግር ስለሆነ አንድ ግጥም እልክላታለሁ መቅዲ በድንገት የስስስ የስስስ ብላ ቁጭ ካለችበት ብድግ ትልና ይቅርታ ብላ እንደገና ቁጭ ትላለች😅😆😅😛 እኔም በሆነ ነገር ምክንያት አድርጌ ሳቄን ለቅቄ እርፍ እላለሁ😛በነገራችን ላይ እኔ የመቅዲ ሹፌር ብቻ አይደለሁም ጋርድ ጭምር እንጂ😃😉 ማነው ቀጭን ሰው ጋርድ አይሆንም ያላችሁ? የትም ስትሄድ ብቻዋን መሄድ አትወድም አብረን ነው የምንሄደው፤ ደስታን ፍቅር ወጥሮ ይዞታል መሰለኝ ቀጠሮ ቀጠሮ አብዝቷል አሁንማ ቋንቋ ቻልኩ ብሎ አንተ ምንድነው ጭራሽ ፍቅረኛ መሰልክ እኮ አንድ አንድ ጊዜ ነጻነት ስጠን እንጂ እያለ በአሽሙር ላጥ እያደረገ ነው😃😛 እኛ ኢትዮጵያውያን በአሽሙር ምላጭ እኮ ነን🙁🙁 መቅዲ ደሞ ከእኔ ተለይታ መሄድ አትፈልግም አብሬ እሄድና እነሱ አብረው እንዲቀመጡ እኔ የሆነ ምክንያት ፍጥሬ ከቦታው ላሽ እላለሁ። ለምንድነው አጠገቤ ስትሆን ለመቅዲ  ምንም  ስሜት የሌለኝ ለትንሽ ሰአታት ከአጠገቤ ስትጠፋ ለአንድ ሳምንት የራቀችኝ የሚመስለኝ? ስሜታችሁ እንደ ሐምሌ ወራጅ ወንዝ ድፍርስ ሲልባችሁ ከየትኛውም ውሳኔ በፊት ለጊዜው ከቦታው መራቅ ምርጥ መፍትሔ ይመስለኛል መቅዲ ስልኬን በተደጋጋሚ መያዝ ስትጀምር እውነቱን በአንድ አጋጣሚ ልታውቅ ትችላለች ብዬ ደስታ በሚለው ስም የከፈትኩትን የፌስቡክ አካውንት ለደስታ ሰጥቼ ከስልኬ Remove አደረኩት በመጀመሪያው ቀን በጣም ደስ አለኝ😗😗😗 እንዴት ደስ ይላል ደስ እንዳላቸው ይሁኑ ግልግል ነው ግጥሙን እኔ ለደስታ እልካለሁ ብዬ ዘና አልኩኝ😗😍 በሁለተኛው ቀን ከመቅድ ይመጡ የነበሩ መልእክቶች ሁሉ ቆሙ እእእእእ ትንሽ ቅር ብሎኛል🙁🙁 በሦስተኛው ቀን ለምን ሰጠሁት ማለት ቀጠልኩኝ😅😃 በድንገት ከሌላ ሰው ሚሴጅ ሲመጣ የመቅዲ መስሎኝ በደስታ ፍንጥዝ ብዬ ውስጥ ስገባ የሌላ ሰው ይሆናል😛😉😛😉😛 ቆይ ግን ምን አይነት እብደት ነው? እሷ አጠገቤ ቁጭ ብላ እያለች የሷን ሚሴጅ መጠበቅ ምን የሚሉት ነው😅😃😛 አንድ ቀን ከት/ቤት እየመጣን እኔ መኪና ውስጥ ሙዚቃ ከፊቼ በሙዚቃው ተመስጫለሁ መቅዲ ከትከሻዬ ላይ መቼ እንቅልፍ ለጥ እንዳለች ሁሉ አላውቅም😅😃😛 ሙዚቃው አልቆ ወደ መቅዲ ዞር ስል እሷ ለራሷ ምቹ እንቅልፍ ላይ ናት😍😅😃ሰውነቷ በጣም ይሞቃል ራስ ምታት ነው መሰለኝ  ሰውነቷ በጣም እየሞቀ ነው እንቅልፍ ላይ ስለሆነች ዝም አልኩኝ ትንሽ ቦታ እንደሄደን ከእንቅልፍ ተነሳች... መቅዲ ምን ሆነሽ ነው ሰውነትሽ እኮ በጣም ይሞቃል አልኳት ምንም አልሆንኩም ጆን አለችኝ መቅዲ እሺ ቆይ ከእኔም ነገር መደበቅ ጀመርሽ አልኳት ጆን እኔ እኮ ለመደበቅ ፈልጌ አይደለም ብላ ማልቀስ ጀመረች😢😢😢 እንዴ አንቺ ምንድነው የሆንሽው ብዬ መኪናውን ወደ ጥግ አውጥቼ አቆምኩኝና እምባዋን  መጥረግ ቀጠልኩኝ... እሷ ግን አሁንም ማልቀስ አላቆመችም😢😢🤔🤔 ቆይ ችግሯ ምንድነው?🤔 ክፍል ስምንት አርብ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄ https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
1022Loading...
11
Media files
910Loading...
12
ምን ተክቼ ልርሳሽ አንቺ ሰው 😭😭 😔 # redu @marakye22
971Loading...
13
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_20 #ከሁለት_አመት_በኋላ ...🖌መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ታናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል የመቅደስና የጌዲዮ ትውውቅ ድፍን ሶስት አመት ሊሞላው አንድ ሳምንት ብቻ ነው የቀረው አሁን አመቱ አዲስ ነው የረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው መቅደስ ያራተኛ አመት ጌዲዮ ደግሞ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ነገ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ይጓዛሉ በተለይ ለጌዲዮ ይህ አመት ልዩ ነው ዛሬ ላይ እንዲቆም በትምርቱ ገፍቶ ሰው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፈጣሪ በታች መሰላል የሆነችውን የናቱን አደራ የሚወጣበት ተመርቆም ለቁም ነገር የሚበቃበት ልዩ አመት ነው እንኳን ለናቱ እንኳን እራሱ መቅደስም የዚህን አመት መጨረሻ ናፍቃለች ደወለችለት ....ሄሎ ጌዲ ወዬ ፍቅር እንዴት ነህልኝ እግዚያብሄር ይመስገን ደናነኝ አንቺ እንዴት ነሽ እማ ደናነኝ አንተ ግን እያመመህ ነዋ አለችው አረ ደናነኝ ደሞ ደናነኝ ትላለሀ ቅድም እኮ ስደውል ማዘር አንስተው እንዳመመህ ነግረኛል ውይ መቅዲ እማን አታውቂያትም እና ነው እራሴንም ስል እኮ ነው አቋረጠችው በቃ እራስ ምታት ላንተ በሽታ አይደለማ ለማንኛውም ነገ መናህሪያ እንደደረስክ ደውልልኝ አባዬ አደርሳችኋለሁ ብሎኛል ለሊት ስለምትነሳ አሁን ተኛ አለችው እሺ ደናደሪልኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ እሺ ቻው። .......በንጋታውም ልክ እንዳለችው ተያይዘው ባባቷ መኪና ተያይዘው ጅማ ገቡ አባቷም ምሳ ጋብዞ ግቢ አድርሷቸው ወደአ.አ ተመለሰ.......መቅደስና ጌዲዮ ግቢ እንደገቡ ከሁሉም ጓደኞቻቸው ጋር ተገናኙ ወይና ብርሀን ሰአዳ በለጠው ሌሎቹም ተሰባሰቡና ቡና ለመጠጣት ሻንጣዎቻቸውን አሳርፈው ወጡ....... በለጠው በጓጓው ልቡ እናንተ የተገናኛችሁበትን ሶስተኛ አመት እንዴት ነው የምታከብሩት አላቸው መቅደስም እንዳምናው ነዋ አለችው በቃ ይቀወጣል አላት ብርሀንም ሙድ ስትዪዝበት የሰውንማ ለማሞቅ አንደኛ ነህ ግን ያንተ መቼ ነው ስትለው ሁሉም ሳቁበት እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ ባንድ ሳምንት አንድ ሴት እቀይራለሁ ታዲያ እኔ ለየትኛዋ ፓርቲ ላዘጋጅ ስታዪኝ ከበርቴ ቱጃር መሰልኩሽ እንዴ ጌዲዮም ቀጠለና አንድ መያዝ ነዋ አለው ወይ አንድ ትቀልዳለህ መሰል እንደዛ ሲል ሰአዳ ወሬ ቀይር አለችው ከዛም ትንሽ እንደተዝናኑም ጌዲዮ አመመው ብዙም ሳይዝናኑ ወዲያው ወደግቢ ተመለሱ።...... ........ሶስተኛ አመት የትውውቅ ልደታቸውንም በደመቀ መልኩ እያከበሩት ሳለ ዛሬም ጌዲዮ አመመው ቢሆንም እስኪነቃ ጠብቀው ሻማቸውን አብርተው ሲደሰቱ ነው ያደሩት ቢሆንም ግን መቅደስ የፍቅረኛዋ ነገር እያሳሰባት ነው ጭራሽ እንቅልፍ አልወሰዳትም ጌዲዮ ሲነቃ እንቅልፍ አልያዛትም መቅዲ ምን ሆንሽብኝ ለምን አተኚም ሲላት እንቅልፌ ስላልመጣ ነው አንተ ተኛ አለችው ፊቷ ተቀያይሮ ስለነበር ጌዲዮ ወዲያው አወቀባት ምን እያሰብሽ ነው ስለኔ ነዋ አላት አዎ ስላንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንዲህ በሽታህን ተሸክመህ የምትኖረው መቅዲዬ እሺ ምን ላርግ ምን ላርግ አትበለኝ ይኸው ሀኪም ቤት ለመሄድ አይደል እንዴ ዛሬ ነገ እያልክ ስንት ጊዜ የሆነክ መቅዲ ብሄድም ምንም ለውጥ አይኖረውም እኮ እንዴት አወክ መቅዲዬ የኔ በሽታኮ አትጨርሰው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ልትለኝ ነዋ አዎ ደሞኮ ሰዎች ሲያወሩ እንደሰማሁት ከሆነ እጀ ሰብ ነው ይባላል አረ ጌዲ እንደተማረ አስብ ለስሙ ነው እንዴ አራት አመት ሙሉ አገር አቀፍ ውጤት አሸንፈህ የተሸለምከው ለነገሩ ጌዲ ሀሳቧን እንድትቀይር እንጂ በንደዚህ አይነት ነገር አያምንም .....መቅዲዬ ምንም አልሆንም ደሞ ፀበል እየሄድኩ አይደል ይሻለኛል ጌዲ ልታባብለኝ አትሞክር እኔ እንቅልፍህም ያስፈራኛል እንባ ባይኗ ሞልቶ ፈሰሰ ደግሞ የትኛው ፀበል ነው ሀኪም የሚከለክለው ሁሌ ይሻለኛል ትላለህ ግን እያባሰብህ ነው ጌዲ አንተን ካጣን እኔም ሆንኩ እናትህ አንድ ቀን አናድርም መቅደስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲም ሊያስቀይሳት ፈልጎ ማታ ወድቄ አሳፈርኩሻ አላት መቅደስ ባንዴ አራስ ነብር ሆነች ባለ በሌለ አቅሟም በጥፊ ሞላችለት ለመናገር ተስኗት ትንፋሿ ተቆራረጠ ጌዲዮም ጉንጩን ይዞ እየሳቀ አረ እየቀለድኩ ነው አመረርሽ እኮ ሲላት በንዴት ደረቱን እየወቀረች እኔ ጨንቆኛል አንተ ትቀልዳለክ ጌዲዩ በፍቅር የሚመቱትን ሁለት እጆቿን ግጥም አርጎ ይዞ አቀፋት መቅደስ ይበልጥ አለቀሰች የምታጣው የምታጣው እየመሰላት ነው ጌዲዮም ሁኔታዋ ግራ ገብቶት አረ በቃ አንቺ ደስ ካለሽ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እኔዳለን አላት እስኪ ማሪያምን በል አለችው በንባና በሳቅ መሀል ሆና ማሪያምን እኔዳለን ብሎ አባበላትና አቅፏት ተኙ።.......... .......መቅደስ ከጌዲዮ ቀድማ ነቃች ሻውር ወስዳ ለባብሳ ስትጨርስ ልትቀሰቅሰው ጌዲ አለችው መልስ አልሰጣትም አሁንም ተጣራች ዝም አላት አንተ ጌዲ ተነስ ሰአት እረፍዷል ግቢ ክላስ መግባት አለብን አለችው አሁንም መልስ አልሰጣትም ክው አለች ከወንበሯም ተነስታ ወዳልጋው አመራች በጆቿም እየደበደበች ብጠራውም ሊሰማት አልቻለም እንደበረዶ ቀለጠች ሰውነቷ ደነዘዘ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋ ጌዲ ጌዲ ደጋግማ እየተጣራች አቤት በለኝ አለች ጌዲዮ ግን...  ✎ ክፍል ሀያ አንድ (21) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 https://t.me/mentalebe https://t.me/mentalebe
1302Loading...
14
ይቀጥል የምትሉ 👍 በlike አሳውቁኝ
1230Loading...
15
💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2022Loading...
16
አሁን ተነስቼ ማፍቀሬን ልንገረው_ _---------___----------- _----_-_--------------- አይ አይሆንም እኔው አፍ አውጥቼ አንባቢ፡-ሲፈን የእናቷ ልጅ ጣፍጭ ታሪኮች ከsifu join share #N @marakye22 @marakye22
1412Loading...
17
✎ ክፍል (19) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌 20 reaction please ❤️😘
6264Loading...
18
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_19 ...🖌መቅደስና ጌዲዮን መናፈሻው ውስጥ ተቃቅፈው ለብዙ ሰአት አልወጡም መቅደስ የቆሰለውን ፊቱን እየደባበሰች አይን አይኑን ታየዋለች እሱ ግን የወይንሸት ነገር አሳስቦታል በርግጥ መቅደስም በውስጧ እየተመላለሰችባት ነው ቡሀላም ጌዲ አለችው እሱም ወዬ መቅዲ ሲላት ትላንት ስታገት እኮ ወይንሸትም አብራ ታግታላቸ በዛ ላይ እስካሁን አልመጣችም እኔ ፈራሁ አለችው ወይና ስልክ ደውላም እንደነገረችው ቡሀላም መረጃ አቀብላ እንዳስፈታችው ለማንም እንዳይናገር በራሷ በመቅደስ ነው ያስማለችው ....ለምን አትደውዪላትም አላት አረ ብዙ ሞክረናል ስልኳ ዝግ ነው አሁንም ሞክሪ ከፍታው ይሆናል አላት ስልኳን አውጥታ ደወለች ዝግ ነው ደግማ ደጋግማ ሞከረች ቢያንስ አስሮ ከሞከረች ቡሀላ ጠራ መቅደስ ከተቀመጠችበት ተነሳች ጌዲዮን በተስፋ ያዳምጣት ጀመር ስልኩ ተነሳ ሄሎ....ሄሎ....ሄሎ.....ወይና የት ነሽ አለቻት ወይናም በሚቆራረጠው ድምጿ ከክሊኒክ እየወጣች ቢሄንም እዚሁ ነኝ እየመጣሁ ነው አለቻት መቅደስም ግን ደናነሽ ስትላት አዎ ብላ ዋሸቻት ከ15 ደቂቃ ቡሀላም ግቢ እንደምትመጣ ነገረቻትና ስልኩን ዘጋችው ጌዲዮም ችግር አለ አላት መቅደስም ድምጿ ጥሩ አይደለም ግን ደናነኝ ብላኛለች አለችው በቃ አትፍሪ ደና ትሆናለች ዶርም ሄጄ ልብሴን ቀያይሬ እመጣለሁ ሲላት ወይና እየመጣች ስለሆነ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ አለችው ግንባሯን ስሟት ሄደ። ..........ባለቻት ደቂቃ ወይና ግቢ ገባች መቅደስ ስታያት ደነገጠች ፊቷ ድልዝ ብልዝ ብሎ አልኮን ተቀብቷል አይኗ ገብቷል ጉንጯ ደግሞ አብጧል ጭራሽ ያቺ ቀበጧን ወይንሸት አትመስልም መቅደስ አቅፋ ምን እንደሆነች ጠየቀቻት ወይና ግን መልሷ ምንም አልሆንኩም ነበረ ብዙ ለመነቻት ፍንክች ዮናስ ነው አይደል ዝም መቅደስ ተናደደች እንዴ ፊትሽ እንደዚህ ባንዲራ መስሎ የምንብምንም አልሆንኩም ነው አለቻት ወይና አይኗ ግንባ ሞላ መቅዲ ይሄ ይገባኛል እንደውም እንደኔ በደል ሲያንሰኝ ነው አለቻት መቅደስ ግራ ገብቷት የተፈጠረውን እንድትነግራት ባባቷ ስም ለመነቻት እሷም ቤተክርስቲያ ሄደው እንደምትነግራት ቃል ገብታ ይዛት ሄደች...... .......ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንደገቡ ከጥላ ስር ቁጭ አሉ ወይና ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ያረገቻትን በንባ ጎርፍ እየታጠበች ነገረቻት ይህን ሁሉ ያረገችውም አባቷን ለማሳከም እንደሆነ እናም በግዚያብሄር ስም ይቅርታ እንድታደርግላት ከግሯ ተንበርክካ ለመነቻት መቅደስ ግን የሰማችውን ማመን ስለተሳናት ቃል ሳተነፍስ ጥላት እየተጣደፈች ወጣች አጋጣሚ ሆኖ የለቱ ጉባኤ የስብከት ፕሮግራም ላይ ደርሶ ነበር የስብከቱም ቃል ይቅር እንዳልኳችሁ ይቅር ተባባሉ ነው መቅደስ ይህን ቃል ስትሰማ ቆም ብላ አሰበች ቢሆንም ስጋዊ መንፈሷ እልህ አሲዟት መንገዷን ቀጠለች ቀጥታም ዶርም ገብታ ማንንም ሳታናግር ተጠቅልላ ተኛች ወይናም ትንሽ ቆይታ ከኋላዋ መጣች ሰአዳና ብርሀን ደነገጡ አንቺ በአላህ ምን ሆነሽ ነው አለቻት ሰአዳ ብርሀንም ቀጥላ አረ ምን ጉድ ነው በማሪያም መቅደስ ነይ እያት ብላ ልትቀሰቅሳት ስትል እንደተኛ ሰው ዝም አለቻት ወይናም ምንም አልሆንኩም አታስቡ ደናነኝ ብላ እሷም ተኛች ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ሲገላበጡ አደሩ ጠዋትም........ .........መቅደስ ተነስታ ጌዲዮ ጋር ሄደች ተያይዘውም ካፌ ገቡ ምን ሄነሽ ነው ማታ ስደውል ስልክሽን ያላነሳሽው አላት እሷም ዝም አለችው ፊቷ ልክ አልነበረም መቅዲ ምን ተፈጠረ ትክክል አይደለሽም አላት እሷም አዎ አይደለሁም እንዴ ምን ሆንሽብኝ አላት እሷም የተፈጠረው ነገረችው እሱም እንዴ ታዲያ ይቅርታ ሳታረጊላት መጣሽ አላት ጌዲ ከበደኝ በሷ የተነሳ እኮ እኔና አንተም ተለያይተን ትምህርታችንንም አጥተን ነበር። አለችው ጌዲ ፈገግ ብሎ መቅዲ እውነተኛ ፍቅር ይፈተናል በርግጥ አጥፍታለች ግን እኛ ከተፃፈልን ውጪ አልኖርንም አንኖርምም አንዳንዶቻችን የሌላውን ብርሀን ስላጨለምን የኛ ይበልጥ ይበራል ብለን እናስባለን ግን ተሳስተናል ከምንም በላይ ግን ጥፋተኝነትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅ ጥበብ ነው ይቅርታንም መቀበል መሸነፍ ሳይሆን ትልቅ ብልህነት ነው ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም ፍቅራችንን ገደል ልትጨምረው ብትሞክርም ከገደሉ የመለሰችውም እሷ ነች አላት ግን ይህን የተናገረው እንዳትናገር ያለችውንም የነገረቻት መስሎት ነበር መቅደስ ቀበል አርጋ እንዴት ነው ከገደል የመለሰችው አላት እንዴ የዛቀን ማታ ስልክ ባትደውልልኝ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስበሽዋል በዛላይስ እኔን ለማስፈታት ካገቱሽ ልጆች መረጃ ለመሰብሰብ አንሶላ እስከመጋፈፍ እራሷን ለመስዋት ማቅረቧ ይቅርታን ሊያስደርግላት አይችልም መቅደስ ጭንቅላቷን ያዘች ቆይ ለምን አልነገረችኝም ስትል ጌዲ ደንግጦ አልነገረችሽም እንዴ አላት አዎ ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ ቡሀላ እንገናኛለን ብላው እየሮጠች ሄደች...... .......ዶርም ስትገባ ወይና እያለቀሰች ለመሄድ ሻንጣዋን እያዘጋጀች ነበር መቅደስም ተቆጥታ የት ልትሄጂ ነው አለቻት ወይናም አባቴ ሰው ያስፈልገዋል ልሂድለት አለቻት መቅደስም ውሸትሽን ነው ይቅርታ ስላላረኩልሽ ነዋ አለቻት ወይናን ባታረጊልኝም አልፈርድብሽም ስትላት መቅደስ ጥምጥም ብላ አቀፈቻትና ይቅርታዋን እንደተቀበለቻት ነገረቻት ወይና በደስታ ጮቤ እረገጠች ትልቅ ሸክም ቀለለላት.......... ......ከዚህ ቡሀላ ወይና ከመቅደስና ከጌዲዮ ጋር በመተባበር ዮናስን ለፍርድ የሚያበቁ መረጃዎችን ሰበሰቡ ለምሳሌ ሴቶችን ለሹገር ዳዲዬች እንደሚሸጥ አደንዛዥ እፆችን ግቢ ድረስ እንደሚያዘዋውር ሌሎችም ከዛም ከጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ተባረረ በመቀጠልም በፍርድ ቤት ሶስት አመት ተፈረደበት....... ...... ከዚህን ጊዜ በፍቅራቸው ማህል የገባና ከፍተኛ ክፍተት የፈጠረ ሰው የለም ያመቱ መጨረሻ ላይ ማለትም ትምህርት ሲዘጋ ጌዲዮ...  ✎ክፍል ሀያ (20) ይቀጥላል...ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 https://t.me/mentalebe https://t.me/mentalebe https://t.me/mentalebe
1641Loading...
19
💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
1461Loading...
20
✎ ክፍል (14) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌
1591Loading...
21
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_18 ...🖌መቅደስን ጓደኞቿ ወስደው ካስተኟት ቡሀላ በንጋታው ቢያንስ ከቀኑ ስድስ ሰአት ድረስ አልነቃችም ነበር ጓደኞቿም እጆቿንና እራሱዋን ይዘው እየጠበቋት ነው ቢሆንም አሁንም አልነቃችም ከዛም ሰአቱ ብዙ አጠንጥኖ ስምን ሰአት አካባቢ ነቃች ስትነቃ ሁሉም ነጭ ሆነባት ቀስ እያለም ጓደኞቿን አየቻቸው በስማቸውም ጠርታ እንዴት እንደመጣች ጠየቀቻቸው ስላስታወሰቻቸው በደስታ ዘለሉ የተፈጠረውን ግን ወዲያው ሊነግሯት አልፈለጉምሽ ግን እየቆየች ስትመጣ ትላንት እስከማደንዘዣው መርፌ የሄነው ትዝ አላት ባይኖቿም ፈልጋ ስታጣት ወይንሸትስ አለቻቸው እነሱም ስላላወቁ ከትላንት ጀምሮ አላየናትም አሉዋት....... መቅደስ ቁጭ ብድግ አለች ምን አርገዋት ይሆን ብላ አሰበች ባይኗ እንባ ሞላ በርግጥ አፍነው ምን አረጉኝ ብላም ተጨነቀች ይበልጥ ግን የወይንሸት ነገር አሳሰባት እነብርሀንም ምን እንደተፈጠረ ጠየቋት እሷም የምታስታውሰውን ብቻ ነገረቻቸው እነሱም ካፈኗችሁ የምታስታውሺው አለ ብለው ጠየቋት ምንም እንዳላየቻቸው ነገረቻቸው........ ......ሰአዳና ብርሀንም እርስ በርስ ተያይተው ይህን ያረገው ዮናስ መሆኑን ተረዱ......መቅደስም ፈጠን ብላ ለወይና እንድረስላት አለች ስልኳንም አንስታ ወደ ጌዲዮ ልትደውል አስባ ስልኳን ስትፈልግ አጣችው ሰአዳ ነበረች የደበቀችው መቅደስም የጠፋ መስሏት ብርሀን ስልክሽን ስጪኝ ጌዲ ጋር ልደውል አለቻት ብርሀንም ቻርጅ ዘግቷል አለቻት እሺ ሰአዳ አለች እሷም ምንም ሳንቲም የለውም አለቻት ኮልሚ ባክስ መልሳ ሰአደ በማፈር ስሜት አራቴ ስለላኩበት አይልክም አለች መቅደስ አይታባቸው የማታውቀው የመረበሽና የማይሆን ምክንያታቸው ግራ አጋባት ወዲያው በቃ ተዉት ዶርሙ እሄዳለሁ ብላ ስትነሳ ሁለቱም ጮኸው አስቀመጧት መቅደስ ይበልጥ ተንቀጠቀጠች ምን እንደተፈጠረ እንዲነግሯት ለመነቻቸው አጋጣሚም ሆኖ ስልኳን ከብርሀን ትራስ ስር አየችው.......... ከዚ በላይ ሊዋሹዋት ስላልቻሉ ከመጀመሪያ ጀምሮ እየተቀረፀ ሼር የተደረገላቸውን ቪዲዮ ተራ በተራ አሳዩዋት .......መቅደስ የወጉዋት መርፌ እንደዛ እንዳረጋት ትረዳች ግን የኔ የምትለው ዮናስ ይሄንን ማድረጉ ሰው ማመን ቀብሮ ነው የሚባለው ተረት እውነት ነው አስባላት ወዲያውም ለባብሳ ጌዲዮ ወደታሰረበት ሄዳ ሁኔታውን አስረዳች በርግጥ ፖሊሶቹ አጭበርባሪ ቢሏትም ከግቢም ቢያስወጧት ወዲያው ወይንሸት ተሸፋፍና ይህንን ሁሉ ያደረገው ዮናስ ስለመሆኑ መረጃ ይዛ መጣች ወዲያውም ፈቱላት ጌዲንም እስከዛሬ በፍቅራችሁ ጣልቃ ገብቼ ስለበጠበጥኩ ይቅርታ አለችው ጌዲዮን በጥፋቱ እስከመጨረሻ የፀና እንጂ ጥፋቱን ተረድቶ ንስሀ የገባ ክፉና ወንጀለኛ አይባልም አላት አይኗ እንባ ሲሞላ አቅፎ አባበላት ምንም ብትበጠብጪንም ዛሬ ፍቅራችንን መልሰሽልናል ትላንት ባደውዪልኝ ኖሮ መቅደስ ላይ ሊፈጠር የሚችለው አደጋ ከባድ ነበር ስለዚ በፍቅራችን ስም ላመስግንሽ አላት ወይና በደስታ እንባዋን ጠራርጋ በቃ አንተ ሂድ የዮናስ አይን ብዙ ስለሆነ ካየኝ አይለቀኝም ብላ መልሳ ተሸፋፍና ቻው ብላው ሄደች...... ፖሊሶቹም ወዲያው ወንጀለኛውን ዮናስን ፍለጋ ሀይል አሰማሩ ወይናም ወዲያው ከጌዲዮ ትንሽ እንደራቀች በመኪና አፋፍሰው ወሰዷት......... ጌዲዮ ግቢ እንደደረሰ ለመቅደስ ደወለላት እሷም ቅድም ደማምቶ በዛ ላይ በሽታውም ተነስቶበት እንደነበር አይታም ተነግሯትም ስለነበር ተይዛ እያለቀሰች ነበር ስልኳም እንደጮኸ አንስታ ስታየው ጌዲ ነው በህልሟ በሀሳቡዋም መሰላት ብቻ በደመ ነብስ አንስታ ሄሎ...ሄሎ...ስትለው ተፈቶ ግቢ መናፈሻው ጋር እየጠበቃት መሆኑን ሲነግራት ህልሟን በውን ለማየት ስልኩንም ሳትዘጋ እየከነፈች ሄደች አንገቱም ላይ ተጠምጥማ ይቅርታ አውቄ አይደለም አለችው ጌዲዮ በትንፋሹዋ ተሸሽጎ እንደተረዳት ነገራት ወዲያውም የክፍል ጓደኞቹ መጥተው እያቀፉ በመፈታቱ መደሰታቸውን ገለፁለት ብርሀንና ሰአዳም መተው አቅፈው እንኳን ደስ አለህ አሉት እሱም ስለመልካም ምኞታቸው በፈገግታ አመሰገናቸው..... ከዛም ሁለቱ ጥንዶች ተያይዘው መናፈሻው ውስጥ ገቡ .... ........ከዛም በስስትና በናፍቆት ትቅፍቅፍ ብለው ተ0ቀመጡ........ ወይንሸትን ዮናስ ጋር ወሰዷት ውይ ዮናስ ያ ውበቱ እርግፍ ብሏል ፊቱ ደረቱም ሳይቀር እዛም እዚም ታሽጓል እንዳያትም በጥፊ አጋጫት ምንም አላለችውም ደገማት የወይና ሰውነት እንደበረዶ ቀለጠ ለነገሩ መስሏት እንጂ ፖርቲው ላይ ጌዲዮ እንዲመጣ ማድረጓን እንጂ ማስፈታቷን አላወቀም ይህን ቢያውቅማ በነብስም አልተረፈች በቀጥታ መጥቶ አንገቷን አነቃት ለምን ለጌዲ እንደተናገረችም አፍጥጦ ጠየቃት እሷም የዛሬውን ማስፈታቱዋን አለማወቁ ሲገባት እኔ አይደለሁም ብላ ካደች ያሰበውን በቀል ከሷ ውጪ ማንም ስላላወቀ ክደቷ ይበልጥ አግሎት እንዳህያ እረገጣት ብዙም ከደበደባት እሷም ከዋሸች ቡሀላ እስኪ አባቴን ይንሳኝ አልተናገርኩም በይ አላርት ወይና ባባቷ በውሸት እንደማትምል ስለሚያውቅ እውነትም መማሉ ከበዳት እያለቀሰችም አዎ እኔ ነኝ አለችው ደግሞ በጥፊ ሲላት ሴትን ስለተማታህ ጀግና የምትባል መስሎክ ነው ወንድ ከሆንክ ትላንት መማታት ቢያቅትህ እንኳን እራስህን አትከላከልም ነበር ስትለው በብስጭት በቦቅስ ሲላት እስከታሰረችበት ወንበር ተዘረረች ወዲያውም ፖሊሶች በሩን በርግደውት ገቡ ያሉትንም ሁሉንም አፋፍሰው ይዘዋቸው ሄዱ... ✎ ክፍል አስራ ዘጠኝ(19) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜
1883Loading...
22
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_17 ...🖌ከዛም በተቤሉበት ሰአት ወክ ብላ ይዛት ወጣች ሰአቱ መሽቷል የወይንሸት ሳቅ የውሸት ቢሆንም እየተሳሳቁ መንገድ ጀመሩ.....መድረስ አይቀርምና ዮናስ ያላት ቦታ ደረሱ ከዛም ከየት መጡ ሳይባል በጥቁር ጨርቅ የተሸፈኑ አራት ጎረምሶች አፋፍሰው ሁለቱ ወይንሸትን ሁለቱ መቅደስን ተሸክመው በግራና በቀኝ ወሰዷቸው ሁለቱ ጓደኛሞች እየተወራጩ ተለያዩ በርግጥ ለማስመሰል እንጂ ወይንሸት ውሸቷን ነበር..... ........ከዛም ቀጥታ በጣም አስፈሪና ጨለማ የሆነ ቦታ ወሰዷት ማን ይያዛት ማን ይልቁቃት ምንም አታውቅም ወዲያው አንዱ በደንብ ያዛትና አንዱ አደንዛዥ እፅ ወጋት ከዛም ከቆይታ ቡሀላ ሁለቱ ወንዶች ጥለዋት ወጡ ከመውጣታቸውም ሶስተኛው ዮናስ ዋሻ የመሰለውን አስፈሪ ቤት መብራት አበራው........ ......በሰአቱ ሌላ ሰው ሆና ነበር ምንም አታስታውስም ዮናስንም እንዳየችው ዋው ምን አይነት ውበት ነው አለችው እየተቅበጠበጠች እሱም ታዲያ ስንቱ ያረገደለትን ውበት እንዴት እረግጠሽው ሄድሽ አላት እሷም ግራ በመጋባት እኔ አለችው ...አዎ አንቺ አላት ቀጥላም አረ ይሄን የመሰለ ገላ እንቢ ብል እራሱ ሀጢያት ይሆንብኛል ስትለው የወጓት እፅ መስራቱን ተረዳ........ .........ሊበቀላት ያሰበው በህዝብ መሀል ነበር ዛሬ ደግሞ የቀወጠ ፓርቲ አለ ለዛም ነው ይህንን ቀን የመረጠው.... ......መጨፈር ትፈልጊያለሽ አላት እሷም አዎ በደንብ አለችው እየተሻሸችው እሺ እንደዛ ከሆነ ዛሬ ፓርቲ ስላለ አብረን ሄደን እንቀውጠዋለን አላት በደስታ ዘለለች አቀፈችውም እሱ ግን ከዛ በፊት ባንድ ነገር እንስሜ አላት እሷም ምንድነው አለችው ቀጠለ ማንም ሰው ዮናስ ምንሽ ነው ቢልሽ ፍቅረኛዬ ነው ትያለሽ አሁንም መቅደስ ግራ በመጋባት ዮናስ ማነው አለችው እሱም እየውልሽ ዮናስ ማለት እኔ ነኝ ለዛሬ ማለትም ለፓርቲው ፍቅረኛሞች ሆነን ነው የምንታየው ገባሽ አላት እሷም በደስታ ተስማማች..... .....ገና ተቃቅፈውም ሲገቡ ብዙ የሚያውቋት ተማሪዎች ስለነበሩ ሰላም ሊሏት ተጠጉ እሷ ግን ማንንም ልታውቅ አልቻለችም ግራ ተጋቡ መቅደስ መንታ እህት አላት እንዴ እስከማለት ደረሱ እውነትም ታስብላለች ቅብጥብጥ ብላ ዮናስ ላይ እንደማስቲሽ ተለጥፋ ለመጣው ለሄደው ትስቃለች ምንም አላሳፈረችውም አንዴ ካንገቱ አንዴ ከወገቡ እየተጠመጠመች ትስመዋለች ለማያውቃቸው አዲስ ፍቅረኛሞች ነው የሚመስሉትግን አብዛኛዎቹ የጌዲዮ ፍቅረኛ መሆኗን ስለሚያውቁ ግራ በመጋባት ጭፈራቸውን አቁመው እነሱን ያያሉ.... .......ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ግን ዮናስ እንዳሰበው ሳይሆን ተቃራኒ ሆኖ በቀሉን ከግብ ሳያደርስ ጌዲዮ ፊቱ በርበሬ መስሎ እሳት ለብሶና ጎርሶ ከፊትለፊቱ ቆመ ዮናስ የታወቀ ተደባዳቢ ስለሆነ አልፈራውም...ከዛም ጌዲዮ መቅደስን ከቅፉ ጎትቶ አስወጣት እሷም ምንድነው ብላ ጮኸችበት ዮናስም ፈልጋ እንጂ አስገድጃት እኮ አይደለም ምን ያበሳጭሀል አለው ጌዲም የመቅደስን ጉንጮች በሁለት እጆቹ ይዞ አይናይኗን እያየ መቅዲ ምንድነው የተፈጠረው አላት እሷም ማናት መቅደስ ምንድነው የምታወራው ብላ መልሳ ከጠየቀችው ቡሀላ ወደ ዮናስ ዞራ ፍቅር ምን ፈልጎ ነው አለችው...ዮናስም መልስ ለመመለስ ሲቃጣ ሁኔታዋ ግራ ያጋባው ጌዲዮ ምን አርገሀት ነው ብሎ ከመቅፅበት በቦቅስ አፍንጫውን ሲለው ዮናስ ደም በደም ሆነ የፓርቲው ሙዚቃ ባንዴ በጩኸት ተቀየረ......... .........ዮናስ ደሙን ጠራርጎ ሊመታው ሲል እንዳልነበር አርጎ ቀጠቀጠው ከዛም የዮናስ ጓደኞችም ተጨመሩ ቢሆንም ከጌዲዮ ቦቅስ ተቋደሱ እንጂ አላስጣሉትም ምናልባት አንድ ሁለቴ እንጂ ከዛ በላይ አልተመታም ጌዲዮ በቃ ከዚያን ቡሀላ ቆሞ የሚቀርፅና የሚጮህ እንጂ አገላጋይ ጠፋ ብዙ ተደባደቡ...... ......ጌዲዮ በበሽታው ይፈራል እንጂ ከማንም ጋር ተደባባድቦም ሆነ ተሰዳድቦ አያውቅም ነበር ዛሬ ግን በዝምታው ውስጥ ወንድነት ባንገት ደፊነቱ ውስጥ ጀግንነት መያዙን አስመሰከረ ወዲያው ነበር በሼር እየተቀባበለ ያየው............ ......ብርሀንና ሰአዳም ወዲያው እንዳዩት እየበረሩ ቦታው ላይ ደረሱ ሲደርሱ ግን አካባቢው በፖሊስ ተከቦ ነበረ ወዲያውም መቅደስን ጌዲዮንና ዮናስን ጥያቄ እየጠየቁዋቸው ተመለከቱ......ፓሊሶቹም የማን እንደሆነች ሲጠይቋቸው ሁለቱም የኔ የኔ ማለትና መከራከር ጀመሩ ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ፓሊሶች ወደ መቅደስ አፍጥጠው የማን ነሽ አሏት እሷም ዮናስ እንዳላት የዮናስ ፍቅረኛ ነኝ አለች ጌዲዮ በሰላሟ እንደልሆነ ቢገባውም እንዲህ ስትል ደነገጠ ጓደኞቿም በድንጋጤ አፋቸውን ይዘው ደርቀው ቀሩ... ወዲያውም ፓሊሶቹ ጌዲዮን እስር ቤት ዮናስን ደግሞ በጣም ደም እየፈሰሰው ስለነበር ሆስፒታል ይዘዋቸው ሄዱ። መቅደስን ደግሞ እንደምንም ብለው በጌዲ መታሰር በሀዘን ተኮራምተው ግን ምንም ማድረግ ስላልቻሉ ወደ ዶርም ይዘዋት ሄዱ... ✎ ክፍል አስራ ስምንት (18) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜
1441Loading...
23
Kfil 17 post yidrg? Eski reaction?????🙏❤️😘
1400Loading...
24
ጥያቄ አለኝ🙋‍♂❓ አይኔ ሲያይሽ......ስደነብር ስታዪኝም..........ሳቀረቅር ምፍለቀለቅ........ሀይ ስትዪኝ ጎኔ ኖረሽ.........ምትናፍቂኝ ኸረ እስቲ እንደው ልጠይቅሽ መቼ ይሁን........ምትረጂኝ አፈቀርኩሽ.........አልረሳሽም ባፌ ብዬ...........ባልነግርሽም አንዴት አንቺ እስከዛሬ የኔ ስሜት.....አልገባሽም?? 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
1653Loading...
25
Btesb yikerta kefil 15 post argnal 🙏🙏🙏❤️❤️😘😘
1730Loading...
26
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_15 ...🖌ጌዲዮ እንደምንም እንባውን ጠራርጎ ታሪኩን ቀጠለላት አየሽ እኔን ማንም ከሰው ተራ ቆጥሮኝ ስላላደኩ ዛሬም ሰው እፈራለሁ ብቸኝነቴን እመርጣለሁ ዝምታዬን እወደዋለሁ ለኔ የመኖር ምክንያቴ እናቴ ናት እሷ ናት ታሪኬ እንዳባት ሞፈር ተሸክማ እንደህት መክራ እንደወንድም ጋሻ ሆናኝ ከናት በላይ ብዙ ሆና ያኖረችኝ ታሪኬ እናቴ ብቻናት አየሽ መቅደስ አንቺ እኔን ከመደገፍሽ በፊት ከናቴ በቀር ማንም ጎንበስ ብሎ አንስትትምኝ አያውቅም ለዚም ነው አንቺን እንደናቴ ያየሁሽ አላት ሳያውቀው ለሷ ያለውን ስሜት ነገራት መቅደስ እጆቿን ከጉንጩ ሰዳ እንባዉን ጠረገችለት ለብዙ ጊዜ ፍቅራቸውን እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ሲጨነቁ የነበሩት ጥንዶች ዛሬ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አንድ ሜዳ ላይ ተገናኙ በርግጥም እውነተኛ ፍቅር የቃላት ድርደራ አይፈልግም ለካ እውነተኛ ፍቅር ባይን ጥቅሻ ብቻ ያግባባል በቃ በዝምታ ተያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌዲዮ ከንፈሩን ከሴት ከንፈር አገናኘው መቅደስ ለብዙ ጊዜ የናፈቀችውን ጌዲን በቅፎቿ አስገባችው በቃ ያለምንም አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ያለማንም አጃቢ በከንፈራቸው ቃልኪዳን አሰሩ የፍቅር ድግሳቸው ትተጠነሰሰ ማንም ባይገምትም የጌዲዮና የመቅደስ ፍቅር እውን ሆነ የዛኑ ቀን ነበር ግቢው ይህን እውነት የሰማው ዮናስ ጌሙን ባደባባይ ተሸነፈ መቅደስ ከሱ ቁንጅና ይልቅ የጌዲዮ መልካምነት አሸነፋት ከዮናስ ማስመሰል የጌዲዮ ፍቅር በለጠባት የውጭ ማንነቱን ሳይሆን በውስጥ መልካም ስብእናው ባደባባይ የጌዲዮ ነኝ አለች ዮናስ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ አይነት ጌም ሲሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብና እሱ የሚያምንበትን ክብሩን አጣ የመጨረሻ እርምጃ ያለውን በቀል በውስጡ አበቀለ በክፋትም ሊጥላት አሰበ ጌዲና መቅዲ ግን ግቢውን ያስቀና ፍቅር ጀመሩ አይቶ ካይን ያውጣችሁ የማይል ምቀኛ ብቻ ነው በፍቅራቸው አልተደነኩም የሚል ካለ ውሸታም ነው... ✎ ክፍል አስራ ስድስት (16) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜     
1731Loading...
27
Ene ednante aydlhum post arkugn 🥺start belu eshi ahun
280Loading...
28
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_16 ...🖌ጌዲና መቅዲ ባሁን ሰአት ለደቂቃ እንኳን መለያየት ይከብዳቸዋል በቀን ቀን ፍቅራቸው እየጨመረ አማላይ ጥንዶች ሆነዋል ጌዲም በብዙ ነገር ተቀይሯል አሁን ከሰው ጋር ይውላል ከክፍል ጓደኞቹም ጋር ይጮታል አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል በመዘነጥም ቢሆን የግቢውን ቆንጆዎች አስንቋል ግን ለዚህ ሁሉ መሆን መቅደስ በፍቅሯ ቃል አስገብታው ነው አረ አሁንማ ከማድነቅ አልፈው ብዙ ሴቶች ለፍቅር እየተመኙት ነው ጌዲ ግን በፊቱ ፋሽን ሾ ሲሰሩ ቢውሉም ዘወር ብሎም አያያቸውም በርግጥም ትክክል ነው የፍቅር ጀግና የሚባለው መቶ ያሰለፈ ሳይሆ ከመቶዎቹ ላንዷ ብቻ መኖር ሲችል ነው መቅደስም ብትሆን ለማንም ቦታ የላትም ግን አንዳንድ ሰዎች ግርም ይሉኛል ወድቆ እያዩት አይጠቅምም ብለው ያላነሱት ነገር ሌላ ሰው አንስቶ ሲያዩ ለምን ቅጥል እርር እንደሚሉ አይገባኝም...... ጌዲዮ ካፌ ቁጭ ብሎ ሻይ እየጠጣ መቅደስ ከክፍል እስክትወጣ እየጠበቃት ነው አንዲትም ልጅ መጥታ አጠገቡ ተቀመጠች ጌዲዮም ይቅርታ የኔ እህት ወንበሩ ተይዟል አላት እሷም በተሞላቀቀ አፏ እኔ ሰው አይደለሁ ስትለው እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፍቅረኛዬን እየጠበኳት ነው ስለዚህ ቦታ ቀይሪ ብሎ ሳይጨርስ ምን መቅደስን አይደል ሶ እኔ ከሷ በላይ ፍቅርን ልሰጥህ ዝግጁ ነኝ ብላ ጠረንቤዛው ላይ ያረፉትን እጆቹን ጭብጥ አርጋ ያዘችው መቅደስም እየመጣች ስለነበረ ፊትለፊት እያየቻት ነበር ጌዲዮ እጇን ከጁ አመናጭቆ አስለቀቃት በጥፊ ሳልልሽ ተነስተሽ ከፊቴ ጥፊ ብሎ ሲጮህባት ደንግጣ እየበረረች ሄደች መቅደስ ፊቷ በደስታ ተሞልቶ በፈገግታ ታጀበ እንደደረሰችም አቅፋ ሳመችውና ተቀመጠች ........ .........ጌዲዬ ዛሬ ላይብረሪ እናጥና ድብርብር ብሎኛል አለች መቅዲ ከደበረሽ ለምን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን አንመጣም አላት መቅደስም ደስ ይለኛል ነጠላዬን ላምጣና እኔዳለን አለችው። ከግቢም ሲወጡ ዮናስ አያቸው ወዲያው ወይንሸት ጋር ደውሎ ጠራት ከዛም ይዟት ወጣ እሷም ዮኒ ምን ፈልገክ ነው እዚሁ ንገረኝ ካንድ ሰአት ቡሀላ መቅደስ አስጠናችኋለሁ ብላናለች ስትለው ዮናስ ዶማ አጠና አላጠና ያው ዶማ እኮ ነው አላት ወይንሸት ንቀቱ አናደዳት ውስጧ ገብቶ ነዘራት መልሳ ዶማ እያልከኝ ነው አለች እሱም ገብቶሻል አታድርቂኝ ሲላት አሁን ትርፍ ማውራትህን አቁመህ ምን እንደፈለክ ንገረኝ አለችው እሱም ቀለል አርጎ ወደማታ መቅደስን እኔ ጋር እንድታመጪያት ነው አላት ወይናም ዮናስ ውላችንን የጨረስን መሰለኝ የተሰጠኝን ግዳጅ ባግባቡ ተወጥቻለሁ ውርርዱን የተሸነፍከው በራስህ ድክመት ነው ታዲያ ምን ችግር አለው አዲስ ውል እንዋዋል ገንዘብም ቢሆን ከባለፈው በላይ እከፍልሻለሁ ሲላት ወይና ፊቷን አኮሳትራ ......በቃኝ ዮናስ በቃኝ አልፈልግም አለችው እሱም ምኑ ነው የበቃሽ አላት በቃ ከዚህ ቡሀላ ካንተ ጋር መስራት አልፈልግም አለችው እሱም እየቀለድሽ መሆን አለበት ዮናስ እየቀለድኩ አይደለም በሀጢያት መጨማለቅ መሮኛል አይገርምህም መቅደስን እስከዛሬ የበደልኳት እየቆጨኝ ነው ደግሜ ሌላ ስተት መስራት አልፈልግም አለችው ወይንሸት የተቀየረችበትም ምክንያት ትላንትና ተደውሎላት አባቷ በጣም እንደታመመ ሲነግሯት ስታለቅስ መቅደስ አየቻት ምን እንደሆነችም ስጠይቃት አባቷ መታመሙን ነገረቻት መቅደስም በየዋህ ልቧ አብራት እያለቀሰች እግዚአብሔር ይረዳቸዋል ደግሞ አንቺን የመሰለ መልካም ልጅ አላቸው አይደል አይዞሽ ፀልዪ እኔም እፀልይልሻለሁ ብላ ስታፅናናት በደሏ ተሰማት ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ውስጧ ሲረበሽ ነበር ለዚያም ነው ዛሬ ለዮናስ ገንዘብ አልፈልግም ያለችው ዮናስ ግን............ መቼም ጨክነሽ ባባትሽ ነብስ አትፈርጂም ሲላት ስማኝ ይኸው ካይስኩል ጀምሮ በነውር በሀጢያት በምሰበስበው ገንዘብ አሳከምኩት ግን ዳነ አልዳነም አየህ እግዚአብሔር ካላለ እኔ ስላልኩ ወይም ማንም ስላለ አባቴ አይሞትም ደግሞ ቆሽሼ ከማገኘው ገንዘብ ንፁ ፀሎቴ ይሻለኛል መቼም ከዚህ ቡሀላ ወደኋላ አትመልሰኝም መቅደስ ጥሩና ደስ የሚል ስሜት ውስጥ ነው ያለችው ደግሜ ልበጠብጣት አልፈልግም ደግሞ የማላቅ አይምሰልህ ሆን ብለክ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንዲደርሰን የጣ ድልድሉ ውስጥ እጅህን ያስገባኸው እኔ ካንተ ከማገኘው ጥቅም በላይ አንተ ከኔ የምታገኘው ጥቅም ስለሚበልጥ ነው ለፍቅር ብቀርብህም አንተ ግን ከየትም እንደተገኘ ገላ ተጫወትክብኝ መጫወትክም ሳያንስ አሳልፈህ ለሹገር ዳዲዎች ሸጥከኝ እኔ ከማገኘው መቶ ፕርሰንት ዘጠናውን አንተ እንደምትወስድ አውቃለሁ ግን አስሯ ፕርሰንት ላባቴ መኖር ምክንያት ስለመሰለችኝ የከተትከኝ ሀጢያት ውስጥ እንደተስማማኝ ሆኜ ኖርኩኝ በርግጥ የኔን ትክክለኛ ማንነት ማንም አያውቅም ግን ይሁን እስከዛሬ ያልሆንኩትን ሆኜ ብኖርም የኖርኩትም ላባቴ ቢሆንም ባርቴፊሻል ማንነቴ አባቴ ድኖ ከሚያዝንብኝ በትክክለኛው ማንነቴ የሆነውን ቢሆንም ወይና አባቷን እጅግ ከሚባለው በላይ ስለምትወደው እንባዋ እንደጎርፍ ወረደ ዮናስም እንዳመረረች ሲረዳ ኦኬ እንደዛ ከሆነ መቅደስ ላይ ያረግሽውን ሁሉ አንድም ሳይቀረኝ እነግራታለሁ ይህ ወሬ ተማሪዎች አወቁ ማለት ሳምንት እንኳን እዚህ ግቢ አትማሪም እኔን እንደሆነ አንዴ ጠልታኛለች የሆነው ቢሆን ማንም ከቁብ አይቆጥረኝም አንቺን ግን ሲላት ሰውነቷን ድንጋጤ ወረረው ዮናስ አታደርገውም አለችው ከት ብሎ ሳቀባት ዮናስ እኮ ነኝ ጭካኔዬን ያኔ ካይስኩል ጀምሮ ከማንም በላይ ታውቂዋለሽ አላት ወይንሸት ከመስማማት ውጪ አማራጭ አልነበራትም እሺ ግን እንዴት ብዬ ለፍቅር ከመጠየቅክ በላይ ደጋግመክ ጌዲዮን እንድትጠላው ለማድረግ በመሞከርክ ላይኗ እንኳን ጠልታሀለች ታዲያ የት ምን ብዬ ነው የማመጣት አለችው ለሱ አታስቢ ወክ እናርግ ብለሽ ውስጥ ውስጡን ትወስጂያታለሽ ከዛም እላይኛው ጫካ ጋር ስትደርሱ ሁለታችሁም የታፈናችሁ አስመስለን አንቺን በጎን ይወስዱሻል እሷ እጄ ትገባለች... ✎ ክፍል አስራ ሰባት (17) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜     
1692Loading...
29
Manm sw start alalem 😭 selzhi kefil 15 aylkekm✍
10Loading...
30
Kefil 15 ??????**??????
210Loading...
31
Join blachu start connect kargachulgn ktayun kefil elkwalw 🙏🙏
310Loading...
32
hamster combat ላይ አዲስ Hamster pre market card መጥቷል 🎆 🎆 ይህንን ካርድ ለመግዛት 1 ሚሊየን Coin እና 1 friend invite ማድረግ ይጠበቅባችኋል እድሉ ሳያመልጣችሁ ካርዱን ግዙ ቤተሰብ በዛውም profit per hour እንዲጨምርላችሁ ይረዳችኋል —————————— https://t.me/haMster_kombat_bot/start?startapp=kentId5544264963 https://t.me/haMster_kombat_bot/start?startapp=kentId5544264963
330Loading...
33
‍ ​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_14 ...🖌መቅደስም የመሄጃዋ ሰአት ደረሰ ወይንሸትም እንዴ መቅዲ አትቀባቢም እንዴ ዮናስ ጋር እኮ ነው የምትሄጂው ያውም እራት አለቻት ባክሽ ብዙም ደስተኛ አይደለሁ እንደውም እሱ ሆኖብኝ ነው እንጂ አልሄድም ነበረ አለቻት ወይንሸትም ቢሆንም አንዴ ተስማምተሻል ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ ስለዚ አሁን ይሄንን ልበሺ ይሄንን ተቀቢ እያለች ያለውድ በግዷ ውበቷ ጎልቶ እንዲታይ አረገቻት ከዛም ተሰናብታቸው ስትሄድ ወይንሸት ወዲያው ተከትላት ወጥታ ጌዲዮን በሌላ ተማሪ አስጠራችውና ደብዳቤ ሰጠችው። ........እሱም ከፍቶ ሲያነበው ስማ አንተ በሽተኛ ነግሬህ ነበረ መቅደስ የኔ ናት ለማንኛውም እንድታምነኝ ስል ዛሬ ምሽት የፍቅር ጥያቄ አቀርብላታለሁ ከቻልክ መጥተክ መታደም ትችላለህ ዮናስ ይላል እሱም ወሬኛ ብሎ ደብዳቤውን ቀደደና ወደዶርም ሊመለስ ሲል መቅደስን በዛ በጨለማ ንግስት መስላ ከግቢ ስትወጣ ከሩቅ አያት ጌዲዮ ማመን አቃተው ባይፈልግም ፍቅር ነውና ተከትሎ መጨረሻቸውን ሊያይ ከኋላዋ ተከተላት......... .........መቅደስ ባላት ሰአት ሆቴሉ ገባች ባይኗም ብዙ ወንበሮች ላይ ፈለገችው የለም ከዛም አንድ ወንበር ይዛ ተቀመጠች አስተናጋጅ ፊትለፊቷ መጥቶ ምን ልታዘዝ አላት እሷም ሰው እጠብቃለሁ የሚል መልስ ሰጠችው ከቆይታዎች ቡሀላ ሌላ አስተናጋጅ መጣችና መቅደስ አለቻት እሷም አዎ ነኝ ኦኬ ተከተይኝ አለቻት መቅደስም ግራ በመጋባት ወዴት ስትላት ዮናስ የተባለ ደንበኛችን ነው ይዘሻት ነይ ያለኝ አለቻት እሺ ብላ ተከተለቻት ሁለተኛ ፎቅም እንደደረሱ ስለደረስን አይንሽን ላስርሽ ነው አለቻት መቅደስ ይበልጥ ግራ በመጋባት እኮ ለምን ስትል አርጊ የተባልኩትን ነው ብላ አይኖቿን አስራ ግን ግለጭ ሳትባይ ምንም እንዳታዪ አደራ ብላት የፎቁ በረንዳ ላይ አድርሳት ተመለሰች ዮናስም ከጥቂት ደቂቃ ቡሀላ ግለጪ አላት መቅደስ የታሰረችበትን ጨርቅ ካይኖቿ ስታነሳ የምታየው ነገር ህልም መሰላት አበባ ተጎዝጉዞ ምሽቱ በሻማዎች ደምቆ አለ የተባለ መጠጥ ቀርቦ ዮናስ አንዲት ቀይ ፅጌሬዳ ይዞ ፊቷ ተንበርክኳል .......በዛ ሰአት ጌዲዮ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ህኖም እያያቸው ነበር..... መቅደስ ግራ ገባት ላንድም ቀን ዮናስን በዚህ መልኩ አስባው አታውቅም ዮናስ ምን እየሆንክ ነው አለችው እሱም ክሽን አድርጎ በሚያወራት አስመሳይ ግን ጣፋጭ በሆነ አንደበቱ መቅዲ ካየሁሽ ቀን ጀምሮ አፍቅሬሻለሁ የልቤ እመቤት አድርጌ ሾሜሻለሁ መቅዲ አንቺ ከማንም በላይ ለኔ ልዩ ነሽ እስከ ሂወቴ ፍፃሜ ያንቺ ብቻ ልሁን ፍቀጂልኝና የፍቅርሽ ባሪያ ልሁን አያለለ ዜማ ቢጨመርበት አንድ ክሊፕ የሚሰራውን ዜማውን አፈሰሰባት ከዛም መቅደስ ምን እንደምትል እንኳን ግራ ገብቷት እየውልክ ዮናስ ይሄን ላረግ አልችልም ብላ ከተንበረከከበት እጆቹን ይዛ አስነሳችው ዮናስ ደሙ ፈላ ግን ለምን አላት እየውልክ እኔ የኔ የምለው የማፈቅረው ሰው አለኝ አንተን ወንድሜ እንጂ ፍቅረኛዬ ላደርግህ አልችልም ዮኒ የእውነት በጣም አዝናለሁ እኔ ያንተ ልሆን አልችልም በቃ ውለታውን በዚ መልኩ ልትከፍለው እንደማትችል ነግራ በጣም አስተዛዝናው ተመልሳ ሄደች ልክ እሷ እንደተመለሰች ጌዲዮ ፊትለፊቱ ሄደና ስማ መቅደስን እንኳን በውንህ በህልምህም የግልክ አታደርጋትም የእውነት ግን በራሴ አፈርኩ አንተን አምኜ እዚህ ድረስ መልፋት አልነበረብኝም ይህንን ትርኪ ሚርኪህን በለመድካቸው ላይ ግን ለዚህ ሁሉ ወጪ ስንት ብር ፈጀብህ እያለ የዮናስን ንዴት በእጥፍ ጨምሮ ሄደ ዮናስ መጠጡን እየገለበጠ በፍቅር እንቢ ካልሽ የበቀል ልቡን አሳበጠው........ ...........ከዛም በንጋታው ጌዲዮና መቅደስ ተያይዘው ለጥናት ወደጫካው ሄዱ አጥንተውም እንደጨረሱ ታሪኩ እንዲነግራት አስገደደችው እሱም .....እኔ ምንም ሌላ ታሪክ የለኝም ታሪኬ አንድ ግን ብዙዋ እናቴ ናት ተወልጄ ያደኩት በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ጃማ የሚባለው ገጠራማ ስፍራ ነው አባቴን አላውቀውም በልጅነቴ ነው የሞተው ከኔ በፊት እናቴ ሶስት ልጆች ሞተውባታል እኔንም ስለት ተስላ ነው ያደኩላት ግን ባድግም የአራት አመት ልጅ እያለሁ በየቦታው ይጥለኝ ጀመር እማ በሀዘን ላይ ሀዘን ተጨመረባት አስበሽዋል ሶስት ልጆቿን ባሏን ያጣች ሴት መከራ በዛላይ እኔም በሽተኛ መሆኔ አላፊው አግዳሚው አላስቀምጥ አላት ያባቴ ዘመዶችማ ለነገሩ እሷ ስላለችኝ እንጂ እንኳን ያባቴን የራሷንም ዘመዶች አላቃቸውም ምክንያቱም የሷ ቤተሰቦች እንድታገባ ሲለምኗት አሻፈረኝ ካገባሁ ልጄ ይጎዳብኛል ስላለች እስከዛሬ ድረስ ማንም የሚፈልጋት የሚጠይቃት የለም አየሽ እናቴ ለኔ ስትል ስንት ነገር እንዳጣች አባ ሲሞት ቆንጆ ወጣት ነበረች ብታገባ ኖሮ እንደ ወንድ ሞፈርና ቀንበር አንዴ ከጓሮ አንዴ ከጓዳ ባልተንከራተተች ነበር ግን ለኔ ስትል ሁለት መልክ አወጣች መከራ ትንሽ ነው ብዙ ብዙ ነገር አየች እኔ እናቴ የማስደስታት ቀንበር ይዤ ስከተላት አልነበረም ጓሮ ሄጄ ስቆፍር እንጨት ስሰብርላት አይደለም እውነተኛው የናቴ ደስታ ደብተር እስኪቢርቶዬን አንግቤ ለትምርት ስወጣ ነው ብዙ ጊዜ ትምርት አልማርም እላታለሁ እሷ ግን ምክንያቴን ስለምታውቅ ሰምቶ እንዳልሰማ አይቶም እንዳላየ ሁን ትለኛለች እዚህ ለመድረሴ የናቴ ትልቁ ምክሯ ይህ ነበር የልጆች ጨዋታን እየተጫወትኩ ሳይሆን እያየሁ እየዘመርኩ ሳይሆን እየሰማሁ ነው ያደኩት ማንም ልጅ ከኔ መጫወት ቢፈልግ እንኳን አይችልም ምክንያቱም የትኛውም እናት አባት አይፈቅድም መቅዲ እኔኮ ከሰው ጋር ስሆን አይደለም የሚያመኝ ግን ማንም አይረዳኝም ብሎ ለብዙ ግዜ ያመቀው ቁስል ስለሆነ ዛሬ ግን ፈነዳና አመመው ሳይጨርስላት እንባው ቀደመው አስተዳደጉ በሙላ አይኑ ላይ ተስሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ መቅደስም አንጀቷን በልቶት አብራው አለቀሰች... ✎ ክፍል አስራ አምስት (15) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 https://t.me/mentalebe https://t.me/mentalebe https://t.me/mentalebe
1621Loading...
34
ያላሰብነው ነገር ሲገጥመን💔😔 ያሰብነው ነገር ሲቀርብን 🥺 ይከብዳላ😔🥺 ግን ሁሉም በምክንያት ነው ለእኛ ከእኛ በላይ የሚያስብ እና ያሰበልን አምላክ ከእኛ ጋር ስላለ ነው ሁሌም በነገሮች አንከፋ😊እሱ ከሁሉም በላይ እኛ ላይ ነውና ትኩረቱ☺️ የትም ቦታ ቢትሆኑ አምላካችሁን እያሰባችሁ በርቱልኝ❤️ @hilmegnit21
1643Loading...
35
ፍቃዱ ግርማ አንቺዬዋ ወዴ ........ ልጅ መውለድ አሁን ነው ለምን ........? ሲባል ሰምቻለሁ ......... ፍቅርና ገንፎ ትኩስ ትኩሱን ነው እድሜም ቆሞ አይጠብቅ በደቂቃ ሰዓት ወደ ሞት መንፈፏቀቅ ስለሆነ ቅሉ ....... በዋዛ ፈዛዛ እድሜን ከምንፈጀው እውነት እልሻለሁ ....... መውለድማ አሁነው እናም ....... በቅጡ አዳምጪኝ የምልሺን ስሚኝ እድል አንዲቷ ነች ካለፈች አትገኝ ስለዚህ እንውለድ ... ልጄም ቅር አይበለው በስርጌ ቀን ይገኝ ። ♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲ ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  𝑠ℎ𝑎𝑟𝑒   💡💡💡💡💡💡💡💡     ✍📝  @poem_timest      📝✍ @poem_timest   💡💡💡💡💡💡💡💡 🌹.................................🌹
1871Loading...
36
hamster combat ላይ አዲስ Hamster pre market card መጥቷል 🎆 🎆 ይህንን ካርድ ለመግዛት 1 ሚሊየን Coin እና 1 friend invite ማድረግ ይጠበቅባችኋል እድሉ ሳያመልጣችሁ ካርዱን ግዙ ቤተሰብ በዛውም profit per hour እንዲጨምርላችሁ ይረዳችኋል —————————— https://t.me/haMster_kombat_bot/start?startapp=kentId5544264963 https://t.me/haMster_kombat_bot/start?startapp=kentId5544264963
151Loading...
37
✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌
1842Loading...
38
‍ ​​​​​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ            ክፍል ❻ መፍትሄው ምን ይሁን እያልኩ ጭንቅ ውስጥ ገባሁ ዬስስስ አንድ ሃሳብ መጣልኝ... በነገራችን ላይ እንደ ውሸት ሰውን እንቅልፍ የሚነሳ ነገር የውስጥን ሰላም የሚያደፍርስ ነገር የለም! Especially የቅርብ የሆነውን ሰው ሁሌም እየዋሹ መኖር  በጣም ከባድ ነገር ነው፤ የሰው ልጅ ትልቁ ስህተት ማለት ስህተት መስራቱ ብቻ ሳይሆን የሰራውን ስህተት ለመሸፈን ሲል ሌላ ስህተቶችን ጨምሮ ጨማምሮ መስራቱ ነው።   እኔም ለስህተቴ መፍትሄ እንደ አማራጭ መጠቀም የፍለኩት ራሱን ስህተት ነው በጊዜው እውነቱን  ለመቅዲ መናገር እሷን የሚጎዳት መስሎኝ ስለነበረ ለደስታ መሆን የማይችለውን ነገር ትችላለህ ብዬ ግጥም በድብቅ በስልክ እና በተግባር ማስለመድ ቀጠልኩኝ... በዚህ አለም ላይ መሆን የማይችሉትን ነገር ለሌሎች ሁኑ ብሎ እንደማስለመድ ሆነ ለመሆን እንደመሞከር የሚከብድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመሆን ስትሞክር  ሁሉ ነገር አስቂኝ ይሆናል በራስህ እንኳን መተማመን አትችልም ሁሌም ሰው ምን ይለኝ ይሁን ትክክል ነኝ ወይስ አይደለሁም የሚል ጥያቄ ታበዛለህ የምትከተለው ሰውን ስለሆነ በራስህ እርግጠኛ መሆን አትችልም። እኔም ደስታ የማይችለውን ግጥም በግድ እንዲችል ለማድረግ መሞከር ትርፉ በራሴ ሰአት እና በደስታ ሞራል ላይ መጫወት ነው እንጂ ትክክለኛ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፤ ለጊዜው ግን ይሆናል ብዬ ነበረ ያሰብኩት እናም ጨወታው ቀጠለ....መቅዲ እንግዲህ ደስታ ለግጥም በጣም ጎበዝ እንደሆነ ነው የምታውቀው እውነታው ግን ደስታ ስለ ግጥም ምንም ስጦታ ሆነ እውቀት የላትም😅😆😃 መቅድን ሁሌም ት/ቤት ስወስዳት ደስ የሚል ስሜት ይሰማኛል ምክንያቱ ደሞ መቅዲ በቃ አሪፍ ልጅ ናት ሁሌም አዝናኝ ሳቂታ ነገር ነች የትኛውም ቦታ ላይ ይሁን በየትኛውም ሁኔታ የኔን ስሜት ለመጠበቅ የማትሆን ነገር የለም! በደስታዬ ደስ ይላታል😗😗 በሌሎች ደስታ ደስታን ማግኘት ግን ምነኛ ታድሎት ነው!? በሌላ ሰው ደስታ ደስ የሚል ሰው ውስጡ ሰላም የሆነ ውስጡ ላይ ችግር የሌላ ሰው ከቅናት ነጻ የሆነ ሰው ነው በሌሎች ደስታ ደስታን ማገኘት የሚችል ሰው ሲሆን ይህ ሰው ደሞ በህይወት ዘመኑ ሁሌም ደስተኛ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ አለም ላይ የሰዎችን ደስታ ከሚቀሙ ነገሮች አንዱ እና የመጀመሪያው ሌላ ሰዎችን እያዩ መቅናት ነው በሌላ ሰው ደስታ አብረው ደስ የሚል ሰው ከዚህ ችግር ነጻ ነው😗😗 እኔም እኮ የመቅዲን ደስታ እፈልጋለሁ መቅዲ ሁሌም ብትስቅ ደስ ይለኛል እንደውም የመቅዲን ጉዳት ማየት ስለማልፈልግ ነው ለደስታ ግጥም ማስተማር የጀመርኩት... መቅዲ ደስታን በጣም ማቅረብ ጀምራለች ደስታም ቢሆን ከበፊቱ ቋንቋም ሆነ አነጋገር ተሻሽሏል የግጥሙ ነገር ግን አሁንም ትልቁ ጭንቅ ነው🤔🤔🤔 ለደስታ ግጥም ማስተማር ለአንደኛ ክፍል ልጅ የአምስተኛ ክፍል ትምህርት ለማስረዳት እንደመሞከር ነው🤔🤔😅ቤት ውስጥ ስልኬን ልክ እንደ አይን ብሌኔ ነው የምጠብቀው ምክንያቱም እዚህ ስልክ ውስጥ ከእኔ እና ከደስታ ውጪ ሌላ ሰው የማያውቀው ሚስጥር አለ🙉🙈 እቺህ መቅድ ግን ለሁሉም ነገር ስልክህን ስልክህን ማለት አብዝታለች ስልክ ስትለኝ ልቤ በድንገት ቀጥ ይላል😛😛😛ስልክ ውስጥ ድሌት ያላደረኩት ነገር ካለ ብዬ በፍጥነት ገብቼ አይቼ ነው ስልኩን የምሰጣት ደሞ እኮ ለትንሽ ደቂቃ እኮ ስልኩ በሷ እጅ እንዲቆይ አልሰጥም ብቻ የሆነ ምክንያት ፈልጌ ከእጇ እቀባላለሁ ምናልባት ደስታ የሆነ መልእክት ቢልክ ብዬ እኮ ነው😅😆🙉🙈እንዴ ውሸታም ሰው ሁሌም ለነገሮች ምክንያት የሚፈልግ ሰው ግን ይኖር ይሁን? አንድ ቀን  እኔ እና መቅዲ ቤት ውስጥ ለብቻችን ቁጭ ብለን እያለን ጆን ጆን ቆይ አንተ ለሴት ያለህ ጥላቻ ምንድነው ስትለኝ ደንግጬ መቅዲ ምን እያልሽኝ ነው? ከምን ተነስተሽ ነው እንደዚህ አይነት ጥያቄ ለመጠየቅ የቻልሽው ብዬ ስጠይቃት..... ትንሽ ከሳቀች በኋላ ጆን ከልብህ የምትወዳት ሴት አለች ማለት ነው ባይሆን እንደዚህ አትደናግጥም ነበረ ስትለኝ ኧረ መቅዲ ቀልድ ጀመርሽ ማለት ነው በቃ? ቆይ መጀመሪያ ላንቺ ፍቅር ምንድነው አልኳት? ፍቅር ማለት ለኔ? አዎ ላንቺ አልኳት ፍቅር ማለት ለኔ... ባህር ውስጥ ገብቶ መዋኛት እንደማለት ነው ፍቅር ማለት ለኔ መሬት ላይ ሆነው ሰማይ ላይ ያለውን ጨረቃን እንደማየት ነው ፍቅር ማለት ለኔ ራዕይ ነው ስትለኝ... መቅዲ ምን አይነት ንግግር ነው ግራ ተገባሁ እኮ ምን ለማለት ነው ብዬ በሚገርም ስሜት ውስጥ ሆኜ ስጠይቃት ጆን አየህ ፍቅር ውስጥ ስትሆን ባህር ውስጥ ከመዋኛት ሁሉ አስር እጥፍ የሚከብድ ስሜት ጋር መጋፈጥ ትቀጥላለህ... ውሃ ውስጥ ስትሆን ትንፋሽ እንደሚያጥር ሁሉ ፍቅር ውስጥ ስትሆንም ልብህ ሌላ ነገር ማሰብ ያቅተዋል❤ ፍቅር ማለት መሬት ላይ ሆነህ ሰማይ ላይ እንደምታየው እንደ ጨረቃ ነው🌠🌠🌠🌕🌖 አንተ ሩቅ ላይ ነህ አንተ ጨለማ ላይ ነህ ብሎ ጨረቃ ውበቱ በፍጹም ደብዝዞ አያውቅም❤ ፍቅርም እንደዚሁ ነው አንተ ድሃም ሁን አጭር ወይንም በሽተኛ አንተ እንደዚህ ነህ ብሎ እሱ ስራውን አይተው የማንም ልብ ውስጥ ገብቶ እንደ ጨረቃ ውበት ይሰጣል🌠🌠🌠 ፍቅር ማለት ራዕይ ነው መቼም ዋሽቶ አያውቅም ራዕይ እኮ አይዋሽም ሁሌም እውነተኛ ነው አንዴ ያያከው ራዕይ ምንም ቢቆይም መሆኑ አይቀርም ለኔ በቃ ፍቅር ማለት ይኼ ነው❤ ብለ እሷ ወሬውን አውርታ ስትጨርስ እኔ ሌላ አለም ውስጥ ነበርኩኝ🙉🙈🙊 አንተ ጆን? ምነው ፍዝዝ አልክ ስትለኝ አይ ምንም አልኳት እኔ ግን በጨረቃው ምሳሌ እስከአሁንም እንደተመሰጥኩ ነው💓💓💓 መቅዲ ግን እንደዚህ አስተዋይ ናት ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም ነበር ክፍል ሰባት ረቡዕ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
2270Loading...
ያልታደለች እናት 💔 ሳቋን ለገሰችው መልኳን አተመችው ሳጠግብ አጉርሳ ከዚህ አደረሰችው አደገልኝ አለች ጦሮ ሊያሳርፈኝ የልፋቴን ዋጋ ፈጣሪ ሊክሰኝ . ግና መቼ ሊሆን ከልቧ ያለመችው በእርሱ ስትሰቃይ ዕድሜዋን ፈጀችው ዕድሜዋን ፈጀችው! ውጥኗን ቀጨችው! መኖር እንዳልጓጓች ሞቷን ናፈቀችው በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
‍ ​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ የቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ              ክፍል ❾ promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት ምን መሰለህ ጆን...ወሬው ላንተ ምንም አይጠቅምም ስትለኝ ይጠቅማል እንጂ ማወቅ አለብኝ አልኳት እንደዛ ነው? በቃ ፍቅር ይዞኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች🤔 ዘንድሮ እኮ አልቃሽ በዝቶ ተቸገርን🤔🤔 ፍቅር የያዘው ሰው ማልቀስ ነው😆 ሚስት ያገባ ወንድ ማልቀስ ነው😅 ትዳር የያዘች ሴት ማልቀስ ነው😆 ትዳር ያጣች ሴት ማልቀስ ነው😅   አሁንማ ሰው ለደስታ ብሎ እስከ አፍንጫው ጠጥቶ ሁሉ ማልቀስ ጀምሯል🤔🤔 አንቺ በይ ወደዛ ሂጅ አትነፋረቂብኝ የወደደ ሰው መውደድ የሚችል ልብ ስላለው ደስ ማለት ነው እንጂ ያለበት  ምን የሚሉት ለቅሶ ነው? ተይ ግን አንቺ ልጅ ቀልብ ግዥ በትንሽ በትልቁ አታልቅሽ ስላት አንተ ምን አለብህ በውስጤ ያለውን እሳት እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ስትለኝ ውስጥሽ ያለው እሳት ከሆነ ያንቺን እሳት ለማጥፋት ልብሽ ውስጥ የሚገባ ማንም አይኖርም ባይሆን በእሳቱ ቦታ  ወተት ምናምን ቢኖር ከኑሮ ውድነት ሸሽቶም ቢሆን ብዙ ሰው ይገባ ነበረ ብዬ መሳቅ ቀጠልኩኝ ጥርሳም ነህ እሺ የኔ ልብ የወተት መደብር መሰለህ እንዴ ማንም ሰው ገብቶ ገዝቶ የሚወጣው እኔ ነኝ እንጂ ቁም ነገር አለህ ብዬ የልቤን ስሜት የምናግረው ስትለኝ ውይይይ መቅዲ አንቺ እና ቴሌ ደሞ ቀልድ አታውቁም      ሁሉንም ነገር መቁጠር ስትወዱ በቃ እሺ ይቅርታ ከማነው ፍቅር የያዘሽ? ከባለሱቁ ደስታ ነው አይደል አልኳት ባክህ ከእሱ አይደለም አለችኝ ምን😬😬😬 ታድያ ከማን ሊሆን ይችላል አልኳት? ከፌስቡክ ጓደኛዬ ደስታ ነዋ ስትለኝ በድንጋጤ ቆሜ ቀረሁ😎አንቺ እሱ እኮ ደስታ አይደለም ምን እያልሽ ነው አልኳት ምን? ምን እያልክ እንደሆነ አንተ ንገረኝ እንጂ ታድያ ደስታ ካልሆነ ማነው ስትለኝ የቱ? ማን? ብዬ ድንብርብር ማለት ቀጠልኩኝ ጆን ምን ሆነካል? የፌስቡክ ጓደኛዬ ማነው ብላ በድጋሚ መጠየቅ ጀመረች እኔም መልሼ የትኛው የፌስቡክ ጓደኛሽ አልኳት🤔🤔🤔 ልጁ ጤና የለውም እንዴ ሆሆሆ በቃ እንደውም ተው ባለሱቁ ደስታ ራሱ ነው መሰለኝ ስትል መቅዲ እኔ እኮ ብዬሽ ነበረ ደስታ ማለት እኮ በቃ ሁለት ሰው ነው አልኳት የምን ሁለት ሰው ስትለኝ አይ እሱማ ያው አንድ ሰው ነው እኔ እኮ በፊትም ብዬሻለሁ ደስታ ሴት በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ሴቶች እፊት ለፊቱ ሲሆኑ ምን እንደሚያወራ ራሱ አያውቅም ችግሩ በቃ ይኼ ብቻ ነው እንጂ እሱም እኮ ይወድሻል አልኳት እርግጠኛ ነህ ጆን ስትለኝ አዎ መቅዲ አልኳት እንደዛ ከሆነ እንደምወደው እነግረዋለሁ በቃ የምን ጭንቀት ነው ስትለኝ ዋውውው መቅዲ ምርጥ ሃሳብ እንደውም ዛሬ እንሂድ አልኳት እሺ ግን አሁን አይደለም ከሰአት በኋላ እንሄዳለን አለችኝ እኔ ደስ ብሎኝ እሺ አልኳት ሰአቱ እየቀረበ ሲመጣ መቅዲን ይዤ እሄዳለሁ ባልኩት ነገር ልቤ ቅር ተሰኝቶ ነው መሰለኝ መሄድ በጣም አስጠላኝ ልብስ ምናምን ቀይር እንሂድ ጆን ስትለኝ ድብርት ድብርት አለኝ ደሞ በጣም አምሮባታል😎😍😋 እንሂድ እንዴ አልኳት እንደ አዲስ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ እንዴ ቶሎ በል እንሂድ አለችኝ ደስ ባይለኝም መኪና ውስጥ ገብተን ጉዞ ቀጠልን..... ክፍል አስር አርብ   ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄ https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
Hammasini ko'rsatish...
ሳሎዳ ትሬዲንግ ️

📣 ለቤቶ ቢሉ ለመስርያ ቤቶ የሚሆኑ ህይወቶን ቀለል የሚያደርጉ ቁልፎች | እጀታዎች | ማጣበቂያዎች | ኤምዲኤፎች እኛ ጋር ያገኛሉ ይጎብኙን 🌐 :: ስልክ +251914855557

👍 3
​​.               💓❦የልቤ ትርታ❦💓            💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘                        #ክፍል_21 ...🖌የመቅደስ ድንጋጤ አንደበቷን አሰረው ሰውነቷን አደነዘዘው የምትሆነው ግራ ገባት ብቻ ደጋግማ ጌዲ ጌዲ ትላለች ጌዲዮ ግን አውቆ ስለነበር መጨረሻ ላይ በሳቅ ተንፈራፈረ ወይኔ መቅዲ ብሞትም አትጮሂም ማለት ነው እያለ የማያቋርጠውን ሳቁን ይስቅ ጀመር....በድንጋጤ ብቻ ቢሞት መቅደስ ሞታ ነበር ሞቶ መመለስም እንዲህ ከሆነ መቅደስ ግማሽ መንገድ ሄዳ ነው የመጣችው...እንደምንም እራሷን አረጋግታ እውን ቀልድ መሆኑ ሲገባት ንዴት ፊቷን በርበሬ አለበሰው...እሱ ግን አሁንም ይስቅ ነበር ቀልደህ ልብህ ወልቋል አለችው ጌዲም እየሳቀ እንዲህ ልበቢስ መሆንሽን ባቅ ኖሮኮ እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀልድም ነበር ሲላት መቅደስ ቦርሳዋን አንስታ ያዘዘችውም ቁርስ ሳይመጣ ጥላው ወጣች እሱም አረ ቁርሱ ቢቀር ልልበስና አብረን እኔዳለን አላት እሷ ግን እንዳልሰማች ሆና ከንዴቷ ብዛት መሬቱን አጥብቃ እየረገጠች ጥላው ሄደች።..ከዛም ቡሀላ ደጋግሞ ብዙ ጊዜ ቢደውልላትም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም በመጨረሻም እንደተቀየመችውና እንደማታነሳው ሲገባው ወይንሸት ጋር ደወለ ወይናም ገና ከማንሳቷ አንተ ልጅቱን ምን አርገሀት ነው እንዲህ አደንዝዘህ የላካት ነው ወይስ ድንግልናዋን ዛሬ ነው የወሰድከው ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ጌድዮም ባማረው ሳቁ አጅቦ እሱንማ እኮ ቆየሁ ከተረከብኩት ባይሆን ትዝታው ይሆናል አላት ወይናም ሳቁን ተቀብላ እየሳቀች ትዝታ እንዲህ ቢያረግማ እኔ በሽተኛ እሆን ነበር አለችው እሱም ወይናዬ ባክሽ በሆነ ነገር አስቀይሚያት እኮ ነው ስልኳንም አላነሳም አለችኝ በማሪያም አገናኚኝ አላት እሷም ውይ ጌዲዬ ገና ስወጣ ነው የደወልክልኝ አሁን ደግሞ ላይብረሪ ልገባ ነው ባይሆን ብርሀንና ሰአዳ ዶርም ስላሉ አንድኛቸው ጋር ደውል አለችው እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት..... የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ አላት...መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው... ✎ ክፍል ሀያ ሁለት(22) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉          ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ                  💗💗------💗💗------ 💛 @yefkr_kalee 💜 💛 @yefkr_kalee 💜
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
00:36
Video unavailableShow in Telegram
Be Fetariyachu Emenu 🙏 @marakye22
Hammasini ko'rsatish...
2.16 MB
👍 4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እንዲሁም የደስታ እንዲሆን እንመኛለን። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1
💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 ✎ ክፍል (9) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌 20 reaction please ❤️😘
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 2
💓❦የልቤ ትርታ❦💓 ✎ ክፍል (21) ይቀጥላል...  ዛሬ ማታ 2:00 ሰዓት ሲል 🙌 20 reaction please ❤️😘
Hammasini ko'rsatish...
👍 6🔥 1
ለማታዉቀኝ 2 ገጣሚ እና አንባቢ✍ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
ለማታዉቀኝ 2 ✍️በዔደን.mp31.21 MB
👍 4 1
‍ ​​​​​💟🌹ሚስጥራዊ ሚስት💟🌹 በጣም አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በ የፍቅር ታሪክ የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ                            ክፍል 8⃣ እሷ ግን አሁንም ማልቀስ አላቆመችም ቆይ ግን ችግሯ ምንድነው? መቅዲ በእናትሽ በጭንቀት መሞቴ ነው የሆንሽውን ነገር ንገሪኝ አልኳት ጆን በቃ ቤት እንሂድ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መኪና ውስጥ ገባች🤔🤔 እኔም ዝም ብዬ መኪና ውስጥ ገብቼ ወደ ቤት መጣን.... ቤት እንደገባች በፍጥነት ወደ ክፍሏ ገብታ በሩን ዘጋች፣ መቅዲ እንደዚህ ስትሆን የመጀመርያ ነው የሆነ አዲስ ነገር መኖሩ ግልጽ ነው፤ ግን ምን ሊሆን ይችላል? ቆይ ውሸቴን ሰምታ ይሁን? እንደሱ ቢሆን ነው እኔንም ዘግታ ብቻዋን መሆን የመረጠችው? ቆይ ቆይ እንደዛ ብሆን በዝምታ ብቻ ማለፍ ትችላለች? ኖ በፍጹም አትችልም በዝምታ ማለፍ የምትችል ቢሆንማ ዛሬውኑ እውነቱን አፍርጬ እርፍ አልልም ነበረ! ለማንኛውም ለሁሉም ነገር ጊዜ መስጠት  ያስፈልጋል ውሃ ራሱ ድፍርስ ሲል ሰአት ስሰጡት እኮ ቆሻሸው ለብቻው ንጹህ የሆነ ውሃ ደሞ ለብቻው ይሆናል፤ የሰውም ስሜት እንደዛ ሲሆን ትንሽ ጊዜ መስጠት ከምንም በላይ ጠቃሚ ነው። እዛው በር አጠገብ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ስለ መቅዲ ማሰብ ጀመርኩኝ መቅዲ ትንሽ ከቆየች በኋላ ከክፍሏ ስትወጣ እኔ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ በሃሳብ ግን ህንድ ውቅያኖስ በመርከብ በማቋረጥ ላይ ነኝ😆😃😅 ሃሳብ እኮ ግፍ አያውቅም አንድ አንድ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ በልቶ ሀገሩ በደስታ ሲዋጥ አንተም በዚያን ጊዜ ተጫዋች እንደነበርክ ሁሉ አድርገው አምጥቶ ፊትህ ላይ ድቅን ያደርገዋል😆😅😃 በዚያን ቀን ብራዚል ላይ ሃትሪክ የሠራክ ሁሉ ሊመስልክ ይችላል😛😛 ከሃሳብ መርከብ ወረድ ስትል ነው ባህር ውስጥ ሳትሆን ደረቅ መሬት ላይ እንደሆንክ የሚታውቀው፣ እኔም እኮ በዚህ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ እኔ እና መቅዲ ፍቅረኛሞች ሆነን ልጅ ምናምን ቢኖረን እያልኩ ነበረ😉😉😃 እንደውም የልጁን መልክ ራሱ የማውቀው ይመስለኛል😛😛😛 መቅዲ በበር ጭንቅላቴን ባትለው ቆይ በሃሳብ መርከብ የት ልደርስ ነበረ🤔🤔 አንቺ መቅዲ ወይኔ ጭንቅላቴ ስል እሷም ተደናግጣ አይዞህ እሺ ጆን እኔን ይምታኝ ሲጀምር ቆይ እዚህ በር ስር ምን ትሠራለህ ለዛውም መሬት ላይ፣ ደሞ እንቅልፍ ወስዶህ ነበረ እንዴ በር ስከፍት እንኳን አትነሳም እያለች ጭንቅላቴን በእጇ ማሸት ጀመረች😗😗 የሷ እጅ ጭንቅላቴ ላይ አይደል ያለው? ቆይ ምንድነው ልቤን እንደዚህ ደስ ደስ አለው😍😍 ህመሙ ትቶኛል ግን ዝም አልኩኝ እጇን ከጭንቅላቴ ላይ ታነሳዋለች ብዬ ይበልጥ እእእእ ወይኔ ጭንቅላቴ ወይኔ ጭንቅላቴ እያልኩ ጎንበስ ብዬ ቀስ አልኩና ትንሽ ምራቅ ከአፌ በእጄ አምጥቼ አይኔ ላይ ቀብቼ ማልቀስ ቀጠልኩኝ😛😛😛 የኔ ምስኪን የእውነቴን መስሏት ጆን አይዞህ ጆን ይቅርታ እያለችኝ ነው፣ አሁን ጥሩ ሃሳብ መጣልኝ ቆይ ቅድም እሷ ያለቀሰችበትን ምክንያት ለምን ይኼን አጋጣሚ ተጠቅሜ እላውቅም ብዬ መቅዲ ዞር በይ እንደውም ያንቺን እርዳታ አልፈልግም አልኳት😉 ምን እያልክ ነው ጆን ጭንቅላትህ እኮ አብጧል ቆይ ትንሽ ልሸው ስትል በቃ አልፈልግም አንቺ ምን ስለሆንሽ ነው እኔ ስጎዳ እኔን ለመርዳት የመጣሽው? ቅድም አንቺ አልቅሰሽ አይዞሽ ሲል አይደል ክፍልሽ ገብተሽ በር የዘጋሺው አልኳት ጆን እሱ እኮ ሌላ ጉዳይ ነው ይኼ ደሞ ህመም እስቲ ቆይ ስትለኝ አልፈልግም አልኩሽ እኮ በቃ ዞር በይ አልኳት እሺ እኔም የሆንኩትን እናግራለሁ ግን በመጀመርያ ጭንቅላትህን ልሸው ስትል ኖ መጀመርያ ቃል ግቢልኝ አልኳት ከአንተ ይነጥለኝ እነግርሃለሁ አለችኝ ህመሜ የውሸት እንደሆነ እንደታውቅ  ትንሽ ዝም አልኳትና መቅዲ እጅሽ እኮ መድኃኒት ነው ዳንኩኝ እኮ አልኳት😛😛 አየህ የኔ እጅ እንደዚህ ነው ስትለኝ እንኳንም የኔ ሆንሽ አሁን የቅድሙን ምስጢር አልኳት ጆን እሱ ላንተ  ምን ያደርጋል ስትለኝ Promise ብለሽኛል ሌላ ነገር አልፈልግም አልኳት ጆን ምን መሰለህ.... ክፍል ዘጠኝ ማክሰኞ ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄ https://t.me/+5IB6ndsrPnw3NzJk       ‌‌‌‌‌‌‌     ••●◉Join us share   💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌 @yefkrtarik @yefkrtarik     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
Hammasini ko'rsatish...
ሳሎዳ ትሬዲንግ ️

📣 ለቤቶ ቢሉ ለመስርያ ቤቶ የሚሆኑ ህይወቶን ቀለል የሚያደርጉ ቁልፎች | እጀታዎች | ማጣበቂያዎች | ኤምዲኤፎች እኛ ጋር ያገኛሉ ይጎብኙን 🌐 :: ስልክ +251914855557

👍 6