@ᴀвuѕhα_thσughtѕ
Kanalga Telegram’da o‘tish
የ ፍቅር ጥቅሶች ♥️ የ ናፍቆት ጥቅሶች 😭 የ ህይወት ጥቅሶች ✨ የ ብቸኝነት ጥቅሶች 💔 አስቂኝ ጥቅሶች 😂🤣 ለ Tg Profile 🖼️ ሁሉም አንድ ላይ ምታገኙበት https://t.me/Abusha_Thoughts Other channel https://t.me/abushaieurjfkeve
Ko'proq ko'rsatish513
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-47 kun
-1630 kun
Postlar arxiv
ማቃጠር በጓደኝነት መሃል እጅግ የረከሰው ተግባር ነው። ወዳጅ ከሚያቃጥር በሳለ ብረት ቢቆርጠን ይሻላል። ግልጽ ቁስል ይድናል፤ የማንጠብቀው ህመም ግን ዘላለም ይጠዘጥዛል። አዎን አንድ ግዜ የከዳን ሺህ ግዜ ይከዳናል፤ ባህሩ ጨው መሆኑን ለመረዳት ሁሉንም ጠጥተን መጨረስ አይጠበቅንም!።
🌟🎺 አዲስ አመት እና የሰው ልጅ ህይወት የተያያዙ ናቸው ፦ የሰው ልጅ የህይወት ጉዞ ልክ እንደ አንድ ትልቅ መጽሐፍ ነው ። እያንዳንዱ አመት ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ሆኖ ይከፈታል ። ባለፈው አመት ውስጥ ብዙ ደስታ እና ሀዘን አሳልፈን ሊሆን ይችላል ። የተሳካልን እና የወደቅንባቸው ጊዜያትም ብዙ ናቸው ። ነገር ግን አሮጌው አመት ሲያልቅ ያለፈው ስህተት እና ቁጭት ሁሉ አብሮ ማለቅ አለበት ። አዲሱ አመት ፊት ለፊታችን የተዘረጋ ባዶ ነጭ ወረቀት ነው ። በዚህ ወረቀት ላይ ምን አይነት ታሪክ እንደምንጽፍ የሚወስነው የራሳችን ውሳኔ ነው ። ትላንት ባሰብነው ልክ ያልተሳኩ ነገሮች ዛሬ አዲስ እድል ይዘው መጥተዋል ። የሰው ልጅ ትልቁ ጥንካሬው ከወደቀበት ተነስቶ አዲስ ጅምር ማድረግ መቻሉ ላይ ነው ። ስለዚህ በውስጣችን ያለውን ትካዜ ከአሮጌው አመት ጋር ጥለን በአዲስ መንፈስ እንነሳ ።
አህያና ውሻ ወደ ሩቅ አገር ሲጓዙ መንገድ ላይ የተጠቀለለ ደብዳቤ ያገኛሉ። አህያው ደብዳቤውን ገልጦ ማንበብ ጀመረ።
...
ይዘቱም ስለ ጭድ፣ ስለ ገብስና ስለ ተለያዩ የእንስሳት መኖዎች የሚያወራ ነበር። ውሻው በጉጉት ወደ አህያው ቀረብ ብሎ፣ "እስኪ በደንብ እየው! ስለ ሥጋና ስለ አጥንት የሚያወራ ክፍል የለውም?" አለው።
...
አህያውም በጥንቃቄ ፈለገ፣ ግን ምንም አላገኘም። ውሻውም ጅራቱን እያወዛወዘ፣ "እንዲህ ከሆነማ አይረባም፣ ምንም ዋጋ የሌለው ደብዳቤ ነው።ወዲያ ጣለው!" ብሎት ጉዟቸውን ቀጠሉ።
..
ሰው ሁልጊዜ የሚፈልገውና የሚስበው የራሱን ፍላጎት የሚያሟላውን ነገር ብቻ ነው። ካላሆነ እርባና የለሽ ይመስለዋል፤ ጣል ብሎ ያስጥልሃል።
የደረቀው ዛፍ 🌳
አንድ ሰው በየቀኑ አንድ ደረቅ ዛፍ አጠገብ ይሄድ ነበር።
ዛፉ ምንም ቅጠል አልነበረውም።
አንድ ቀን እየተመለከተው፦
“ይህ ዛፍ ከእንግዲህ አይኖርም” አለ።
ነገር ግን ከዛፉ ሥር ያለውን ትንሽ አረንጓዴ ቅጠል አላየውም።
ጊዜ አለፈ…
ዝናብ መጣ።
ፀሐይ ወጣች።
ከዚያም ያ ደረቅ የመሰለው ዛፍ እንደገና ቅጠል አወጣ። 🌿
እኛም እንደዚያ ዛፍ ነን።
ዛሬ ሕይወትህ ደርቆ ሊመስልህ ይችላል።
ምንም ተስፋ እንደሌለ ሊሰማህ ይችላል።
ግን ዛሬ የማታየው ነገር ነገ ሊበቅል ይችላል።
ተስፋ አትቁረጥ።
ዝናብህ እየመጣ ሊሆን ይችላል። ❤️🙏
