cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አቡ ዒክሪማ أبو عكرمة

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ትምህርቶችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 832
Obunachilar
+4324 soatlar
+587 kunlar
+22530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዲን ያለው ወንድ ከቤተሰቡ ጋር ቢጨቃጨቅ ሚሄደው ወደ መስጂድ ነው። መስጂድ ገብቶ ቁርኣኑን ይቀራል ወይም ጋደም ይላል። 👉ዲን የሌለው ሰው ግን የሚሄደው ብስጭቴን ያስረሳኛል ብሎ ወደሚያስበው አላስፈላጊ ቦታ ነው። አላህ ይጠብቀን🤲 አንድ ጊዜ ዓሊይ እና የነብዩ ልጅ ፋጢማ ተኮራረፉ ከዛም ዓሊይ ከቤት ወጥቶ ወደ መስጂድ ሄደ ። ነብዩ ዓልይን ፈልገውት ቤቱ ሲሄዱ አጡት ከዛም ዓሊይ የት ሄደ አሏቸው እነሱም፦ መስጂድ ሄዶ ተኝቷል አሏቸው። ነብዩም መስጂድ ውስጥ ዓሊይ ፎጣው ከጎኑ ወድቆ የተወሰኑ የሰወነቱ ክፍሎች አፈር ነክቷቸው ተኝቶ አገኙት ከዛም አቧራውን እያራገፉለት አንተ አባ ቱራብ ተነስ አሉት። ሁሌም ምርጫቹ ዲን ይሁን ዲን ያለበት ቤት ጨልሞ አይውልም ሁሌም ብርሃን አለ ችግሩም ደስታ አለው። ምክንያቱም መፅናኛቸው ቁርኣን ወይም የነብዩ ሀዲስ ስለሆነ። ዲን የሌለበት ነገር ግን ዱንያ የተትረፈረፈበት ቤት ሆኖ ደስታ ከራቀው የሰነባበተ ቤት ሞልቷል። ያጡት ገንዘብ ሳይሆን ዲን ነው። ዲን ያጣ አካል ደስታን ለማግኘት ፈፅሞ ይቸገራል። 👉https://t.me/AbuEkrima
Hammasini ko'rsatish...
👍 1💯 1
03:07
Video unavailableShow in Telegram
📻የስሜት ባልተቤቶች ባህሪ . 🎙በኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሙሀመድ ሰዒድ حفظه الله . ↪️ https://t.me/fahemuselef ┈┉┅━❀🍃🌸🍃❀━┅┉┈ 🔗 t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/3865
Hammasini ko'rsatish...
3.57 MB
👍 3💯 1
03:07
Video unavailableShow in Telegram
3.57 MB
وداوِ ضميرَ القلبِ بالبرِّ والتُّقى ولا يستوي قلبان قاسٍ وخاشعُ مروان بن الحكم በመልካም ስራና በአላህ ፍራቻ ልብህን አክመው አላህን የምትፈራ ልብና የደረቀች ልብ እኩኩል አይሆኑም❗️ https://t.me/AbuEkrima
Hammasini ko'rsatish...
💯 1
✍     ወደ ሱትራ መስገድ: የተረሳው ሱና!! ⭕️ሱትራ ማለት፦    አንድ ሰጋጅ ለሰላት በሚቆምበት ጊዜ ከፊት ለፊቱ ሰውም ይሁን እንስሳ ሰላቱን እንዳይቆርጥበት ከለላ እንዲሆን የሚጠቀመው የሚያስቀምጠው የሆነ ነገር ነው። ይህ ሱትራ መጠቀም ፍርዱ ምንድን ነው በሚለው ከፊል ዑለማዎች "የጠነከረ የማይተው ሱና ነው" ሲሉ ከፊሎቹ "ከዚህም ከፍ ብሎ ግዴታ የሆነ ነገር ነው" ይላሉ። በሁለቱም ብይን ከሄድን የአላህ መልእክተኛﷺ አጥብቀው ያዘዙበት ተግባር ስለሆነ ለየትኛውም ሰጋጅ ቸላ ሊለው አይፈቀድለትም። ኢማሙ ቲርሚዚ በዘገቡት እና አቡ ሰዒድ ባስተላለፈው የተረጋገጠ ሓዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦ 📚 «إذا صلى أحدكم فليصل إلى سترة، وليدن منها» «አንደኛችሁ በሰገደ ጊዜ ወደ ሱትራ ይስገድ፤ ወደ እሷም ይጠጋ።»   ግልፅ በሆነ ትዕዛዝ ስንሰግድ ሱትራ እንድናደርግ እና ወደ እሱም እንድንጠጋ አዘውናል። ⭕️የሱትራው መጠን በተመለከተ………   በሓዲስ በመጣው መሰረት የኮርቻ የኋለኛው ያህል ቁመት ሊኖረው ይገባል። የዚህ መጠን ግልፅ ለማድረግ ዑለማዎች እንደሚያስቀምጡት የአንድ ክንድ ያህል ወይም የክንድ 2/3ኛ ያህል መሆን አለበት ይላሉ። መልእክተኛውﷺ እንዲህ ይላሉ፦ 📚«إذا وضع أحدكم بين يديه مثل مؤخرة الرحل فليصل ولا يبال من مر وراء ذلك» «አንደኛችሁ ከፊት ለፊቱ የኮርቻ መደገፊያ ያህል ካስቀመጠ: ከዚህ በስተጀርባ ስለ ሚያልፈው ሳይጨነቅ ይስገድ።»   ሱትራ ከተደረገ በኋላ ከሱትራው ወድያ በኩል ምንም ነገር ቢመላለስ ቢተላለፍ የሰጋጁ ሰላት ላይ የሚያመጣው እንከን የለም። ⭕️በሱትራው እና በሰጋጁ መሃል ለማለፍ የሚሞክር ካለ:   ሰጋጁ በተቻለው ልክ ሊያልፍ የፈለገውን አካል እንዳያልፍ ይከለክላል። ከተግባቡ እጁ አንስቶ ምልክት ይሰጠዋል፤ ካልገባው ሊያልፍ ሲል እጁ ዘርግቶ ይከላከለዋል፤ እምቢ ብሎ ቢታገል እንኳ ሰላቱ ላይ ባለበት ታግሎም ቢሆን ይመልሰዋል። ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፦ 📚«إذا صلى أحدكم إلى شيء يستره من الناس، فأراد أحد أن يجتاز بين يديه فليدفعه، فإن أبى فليقاتله، فإنما هو شيطان» «አንደኛችሁ ከሰዎች ወደ ሚከልለው ነገር ተቀጣጭቶ እየሰገደ ባለበት አንዱ ከፊት ለፊቱ ሊያልፈው ቢሞክር ይመልሰው፤ እምቢ ካለውም ይጋደለው (ይታገለው)፤ ምክንያቱም እሱ ሸይጣን ነው።» ⭕️ሰጋጁ ሱትራ ሳያደርግ እየሰገደ ወይም ሱትራ አድርጎ በሱትራው እና በእሱ መሃል የሆነ ነገር ቢያልፍ ሰላቱ ውድቅ አይሆንበትም፤ አጅሩ ግን ይቀንስበታል፤ ያለፈው ሰው ከሆነም ወንጀለኛ ይሆናል; ከሦሥት ነገሮች አንዱ ካለፈ ግን ሰላቱ ውድቅ ይሆንበታል። በሐዲስ እንደመጣው፦ 📚«يقطع صلاة المرء المسلم إذا لم يكن بين يديه مثل مؤخرة الرحل المرأة والحمار والكلب الأسود» «አንድ ሙስሊም ከፊት ለፊቱ የኮርቻ መደገፊያ ያህል ነገር ሳይኖር እየሰገደ ሴት፣ አህያ እና ጥቁር ውሻ ካለፉ ሰላቱ ይቆረጥበታል።»   ከተጠቀሱት ውስጥ ከሦሥት አንዳቸው ሰጋጁ እና ሱትራው መሃል ካለፉ: ሰላቱ ውድቅ ስለሚሆንበት ያቋርጥና በአዲስ ሀርሞ ይሰግዳል። ⭕️ሱትራ መሆን የሚችሉት፦   ከላይ የተጠቀሰው ልክ ያህል ቁመት ያለው ነገር በአጠቃላይ ሱትራ መሆን ይችላል። ግድግዳ, ምሶሶ, የተቀመጠ ሰው, ወንበር, ዱላ, የትኛውም ወደላይ የሚረዝም ዕቃ, ፣፣፣፣፣፣ ሱትራ አደርጎ መጠቀም ይችላል። ⭕️ሱትራ ከማድረግ መጠንቀቅ ያለበት፦ 📖ቁርኣን እና የሓዲስ ኪታቦች: ያላቸው ክብር ከመጠቃቀሚያነት ከፍ ያለ ስለሆነ። 👟ጫማ: ነብዩﷺ ያዘዙን ለብሰነው እንድንሰግድ ካልሆነም ከበስተ ግራ ወይም እግሮቻችን መሃል እንድናስቀምጠው ነው። 🔥የእሳት ማንደጃ እና መሰል ነገሮች: ከአላህ ውጭ የሚሰገድላቸው ነገሮች ስለሆኑ ከከሓዲያኖች ጋ መመሳሰል እንዳይሆን።   ነብዩﷺ ከቤት ሲወጡ ወይም ከከተማ ሲርቁ ይዘውት የሚንቀሳቀሱ ዱላ ነበረቻቸው። ዱላው ንግግር ሲያደርጉ ይደገፉበት ከነበረው በተጨማሪ ይሰጣቸው የነበረው ትልቁ አገልግሎት: ሜዳ ላይ ወይም ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ላይ መስገድ ከፈለጉ ሱትራ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር ነው። ይህ የሚያመለክተው ነገር ቢኖር የሱትራ አሳሳቢነት እና ያለው ደረጃ ነው። ⭕️ያስተውሉ!!   ሱትራ ማድረግ ግድ የሚሆነው ኢማም በሆነ ሰው ላይ እና ብቻውን በሚሰግድ ሰው ላይ ነው። ከኢማም ኋላ ተከትሎ የሚሰግድ ሰው ኢማሙ ያደረገው ሱትራ ለሁሉም ስለሚያብቃቃ እያንዳንዱ ላይ ግዴታ አይሆንም። በዚህም መሰረት ጀምዐ እየተሰገደ ከኋላ በሚሰግዱ ሰዎች (በሰፍ መሃል) መሄድ ማለፍ ይቻላል። ምክንያቱም የኢማሙ ሱትራ ስላለ ከኢማሙ ኋላ ያሉ ሰዎች ከፊታቸው ቢታለፍም ችግር የለውም።
ወደ መልካም ያመላከተ የሰሪው ምንዳ ያገኛልና ሌላውንም አስታውሱ!!
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!! https://t.me/hamdquante
Hammasini ko'rsatish...
🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ 👇🏾👇🏾👇🏾 @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል 👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

👍 3💯 1
ወሬ ይሻላል❓ ምክር ለምን ወሬ ዝባዝንኬ፣ ስድብ ጭቅጭቅ የሚበዛበት ቦታ ላይ እንሰባሰባለን ❓ለምን❓ እንደው ለዲናችን ጠቃሚ ነገራቶችን ልናገኝባቸው የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ግሩፖች እያሉ ለምን በፊትና የተሞሉ በስድብና በዘለፋ የታጨቁ ጉሩፕችን ታሞቃላቹ ። አንድ ነገር እወቁ ምታዩትን ነገር ኢንካር ማድረግ ካልቻላቹ ወይም ካልጠላቹ ወይም ደግሞ ትታችሁ ካልወጣችሁ ቀስ በቀስ የሰዎቹን በሽታ መሸከማቹ አይቀርም ልብ ደካማ ናት ሹብሃ ደግሞ ትቀጥፋለች❗️ ውሸት ሲደጋገም እውነት እየመሰለ ይሄዳል ውስጥህ ይሸረሸራል ትጎዳለክም መጎዳት ብቻም አይደለም በጣም ከባድ የሆነ የአመለካከት ችግር ውስጥ ትገባለህ ። ማመን ያለብህን ትተህ ማመን የሌለብህን ሰው ታምናለክ የእሱ ጭራ ትሆናለክ ምን ይሄ ብቻ አግዝፈህ ምታያቸው እንደው ስታያቸው ሁላ በስስት የምትመለከታቸውን ዑለሞች ለመጥላት ትገደዳለህ ዑለማን መጥላት ዲንን መጥላት ነው፣ ዑለማን መስደብ ዲንን መስደብ ነው። ምክንያቱም የተሸከሙት ዲንን ስለሆነ ወንድሜ እንዲህ አይነት ዑለሞችን የሚያንቋሽሽ መጅሙዓ መከታተተል ልብህን ያደርቅብሃል። ትሰማለህ ወንድሜ ሁሉ ነገር ልክ አለው የተበደለ ሰው በደሉን ሚገልፅበት መንገድ አለው እውነት ይህ አካል ተበድሎ ከሆነ ። ዑለሞቹ በህይወት አሉ ። እነዚህ አካሎች እውነት ከዳዕዋው ጋር የመሄድ ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ መክፈል የነበረባቸውን መስዋእት ይከፍሉ ነበር። ግና ሁሉም አትንኩኝ ባይ ሆነ ። ኡስታዞቻችን ከሚባለው በላይ ትግስት አድርገዋል ባይሆን ኖሮ ድሮ ነበር የራሱ ጉዳይ ብለው ሚተውት ነገር ግን ከዛሬ ነገ ይስተካከላል አንድ አቋም ላይ ይደረሳል በማለት በጣም ብዙ ጥረት አድርገዋል። አንዳንድ ሰዎች ከሩቅ ሆናችሁ አትፍረዱ ኡስታዞቻችሁ ነገሩን ተኝተው አይደለም ያሳለፉት ወላሂ ታግለዋል እንቀልፍ አጥተዋል መስራት ያለባቸውን ነገር ጥግ ድረስ ሰርተዋል። አመድ አፋሽ አታድርጓቸው እነሱም እንደኛ ቤተሰብ አላቸው ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ሳይተኙ ሚያድሩት ብር ሊሰበስቡ አይደለም ዑማውን ለመሰብሰብ ቢሆን እንጂ አንድ ነገር ሳናደርግ ዘሎ አስተማሪዎቻችንን መጠራጠር ትልቅ ድፍረት እንዲሁም አሳፋሪ ተግባር ነው። አንድ ሁለት ቀን ቁጭ ብለህ ተወያይ ብትባል ምን አልባትም ራስህን ሊያምህ ይችላል ። እናስብ እንጂ ወገን ውለታ ሚባል ነገር አለ ስንት ትምህርት ወስደህባቸዋል ስንትና ስንት አመት አብረካቸው አሳልፈሃል ዛሬ ስለ ምንም ነገር ግድ የማይሰጠው "ሰው ጤፉ" ከሆነ አካል ጋር አሸሼ ገዳሜ ማለት ያሳፍራል። ወንድሜ ነገሩ የስሜት አይደለም❗️ ተበድሏል ካልክ ጠይቅ ዑለሞችን እነሱን መጠየቅ ካልቻልክ በጉዳዩ ላይ ለረጅም ጊዜ ያለውን ነገር ሲከታተሉ የነበሩ ወንድሞችን ጠይቅና ተረዳ። ከዛም ተበድለዋል የሚልን ነገር ከተረዳክ የተበደለ ሰው በዚህ ልክ በምንም ከማይገናኛቸው ዓሊሞች ጋር እንዲህ አፍ መካፈት አለበት❓ ነገሩን ማስተካከያ መንገድ የለምን ❓ እንዴት በዚህ ልክ ለጆሮ በሚሰቀጥጥ መልኩ ስድብና ዘለፋ እንዲሁም ማንቋሸሽ ይከሰታል ትላንትና ስታወድሳቸው የነበሩ ዑለሞች ዛሬ ተራ ሰው ሆነው ለተራ ሰው ራሱ ማይባሉ ስድቦች ተሰደቡ ❗️እስቲ ማናቹ ❓እናንተ ለደዕዋ ሰለፊያ ምን አደረጋቹ❓ እስቲ መፅሃፎቻችሁን አሳዩን፣ ወዘተ ሚገርመው ግን ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገር ሲከሰት ወጣ ይሉና ድሮም እናውቃችኋለን እነ ኢብን ሂዛም ከዳዕዋው የወጡት ተገፍተው ነው እነ ዓብድረህማን አል ዐደኒ እነ ፉላን እያሉ ለራሳቸው ማስረጃ ያደርጋሉ ። ሱዳን ላይ ያሉ ሰዎች ከነ ሸይኽ አቢ ዓምር ጋር ሳይስማሙ ሲቀሩ ወዲው የሄዱት ዑለሞችን ወደ መዝለፍ ነበር ከዛም እነሱን ትተው እነ ዑበይድ አልጃቢሪን፣ እነ ረስላንን ማወደስ ጀመሩ ። ነገሩ እንዲህ ነው እነዚህ ሰዎችማ ጭራሽ አብሰውታል ዑለሞችን በጣም እያሳነሱ እያንቋሸሹ ጭራሽ እንደ ጭራቅ እንድትቆጥራቸው ለማድረግ በጥረት ላይ ናቸው። ወንድሜ ይህን ዳዕዋ የወደድነው በዑለሞች ነው የነሱ መልካም ስብእና ነው ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ሰውን በአንድ ቦታ እንዲሰበሰብ ያደረገው❗️ ምንኛ ያማረ ደዕዋ ነው በእዝነት የተሞላ ወላሂ ዑለሞቻችን ሙተዋዲዕ ናቸው በጣም ዝቅ ብለው ተናንሰው የሚኖሩ ናቸው። ሀገራቹ መጥተው አይተሃል አትክድም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ላይ አይደለም ያረፉት አንተን መስለው አንተን ሆነው ነው አስተምረውክ የተመለሱት። መቼም አትክድም ዛሬም ብዙ ደረሶች ያሉት አንተ እንደ ቆሻሻ የምትገልፃቸው ዑለሞቻችን ዘንድ ናቸው እንደው ትንሽ አያሳፍርም የአስተማሪያችሁን ምግብ እየበላችሁ እዛው እያደራችሁ ደርስ ላይ ለመውጣት ስትሞክሩ ይሄ ጨለምተኝነት ነው ። ካልፈለክ ለቀህ መውጣት ወይም ስርኣት ይዘክ ተቀመጥ ባሉክ መሰረት መቀመጥ እንጂ በዚህ ልክ አስተማሪህን እየዘረጠጥክ ከጎናቸው ለመቀመጥ መሞከር በራሱ የሆነ የተዛባባቹ ነገር እንዳለ ያመላክታል። ለዳዕዋ ምታስቡ እንዲሁም አንድነትንት ምትፈልጉ በነበር የተመከራችሁትን ምክር ለመተግበር ትሞክሩ ነበር። ።።።።።።።።። እንደው ትንሽ እንኳን ለተሸከማችሁት ዳዕዋና ከኋላ ለሚከተላቹ ሰው እንኳን አታስቡም ለምን ተነካው ብላችሁ መጮሁ መሳደቡ የሆነ የተደበቀ አጀንዳ ያለ ያስመስላል። 👉 በመጨረሻም ውድ ሰለፍዮች ዑለሞችን እንዲሁም ዱዓቶችን አክብረህ ይህን ከብዙ ነገር በአላህ ፍቃድ የጠበቀህን ዳዕዋ እንደወደድከው መቀጠል ከፈለክ ነገ ዛሬ አትበል አሁኑኑ ይህን መንጀኒቅ የተባለ የስድብ ቋት ለቀህ ውጣ ይህን ካላረክ እመነኝ ነገ ዑለሞች መጡ ሲባል ግድ አይሰጥህም ለዛ ነው ኢብን ዑሰይሚን ዑለሞችን ስለመሳደብ ሲናገሩ እንዲህ ያሉት፦እነሱን መስደብ አንድ ተራ ሰውን እንደመስደብ አይደለም ዑለሞችን መስደብ ዲንን መስደብ ነው። አንድ ተራ ሰውን ብትሰድብ ስድቡ እሱ ላይ ይቀራል ዑለሞችን ስትሰድብ ግን እነሱን በሚከተሉ ሰዎች ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነትና ተሰሚነት ያሳጣል ይሄ ደግሞ ዲንን ይጎዳል ❗️ ነገሩ ይህ ከሆነ ወንድሜ የዚህ ወንጀል ተካፋይ አትሁን ቶሎ ለቀህ ውጣ ❗️ 👉https://t.me/AbuEkrima
Hammasini ko'rsatish...
👍 24💯 2🆒 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
🤌 በራሳችን ላይ እናልቅስ ❗️ 🚨 ﻳﺬﻛﺮ ﺃﻥ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﺠﻮﺯﻱ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ: 🚨 ከኢብኑል ጀውዚይ ራህመቱላሂ አለይሂ ይውሳል: ✅ ﺃﺳﻠﻢ ﻋﻠﻰ ﻳﺪﻩ ﺃﻛﺜﺮ ﻣﻦ ﻋﺸﺮﻳﻦ ﺃﻟﻒ ﻳﻬﻮﺩﻱ ﻭﻧﺼﺮﺍﻧﻲ ! ✅ 20,000 የሁዳ እና ነሳራ በጁ ላይ ሰልሟል። 🔘 ﻭﺗﺎﺏ ﺑﺴﺒﺒﻪ 100 ﺃﻟﻒ ! 🔘 100,000 ሰው ተውበት በጁ ላይ አድርጓል። 📚 ﻭﺻﻨﻒ ﺃﻛﺜﺮ ﻣﻦ 2000 ﻣﺼﻨﻒ ! 📚 2000 በላይ ኪታብ ፅፏል። ↩️ ﻭﻫﻮ ﺍﻟﻘﺎﺋﻞ ﻟﻄﻼﺑﻪ: 🌺 ‏« ﺇﺫﺍ ﺩﺧﻠﺘﻢ الجنة ﻭﻟﻢ ﺗﺠﺪﻭﻧﻲ ﺑﻴﻨﻜﻢ ﻓﺴﺄﻟﻮﺍ ﻋﻨﻲ ﻭﻗﻮﻟﻮﺍ ﻳﺎﺭﺏ ﺇﻥ ﻋﺒﺪﻙ ﻓﻼﻥ ﻛﺎﻥ ﻳﺬﻛﺮﻧﺎ ﺑﻚ، ﺛﻢ ﺑﻜﻰ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ !‏ » ↪️ ከዚህ ጋ ለተማሪዎቹ እንዲህ ይል ነበር: 🌺 "ጀነት ገብታችሁ በመሃከላችው እኔን ካላገኛችሁኝ ስለኔ :- "ጌታችን ሆይ እከሌ ባሪያክ ባንተ ያስታውሰን ነበር" ብላችሁ ጠይቁልኝ ... ከዚያም አለቀሰ አለይሂ ራህመቱላሂ።" 🫵 ﻭﻧﺤﻦ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﻣﻘﻠﻮﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻭﻣﺎ ﺃﻛﺒﺮ ﺃﻣﺎﻧﻴﻨﺎ ..!! 🫵 እኛ ግን ዛሬ ስራችን ትንሽ ምኞታችን ግን ትልቀቱ ይህ ነው አይባልም! 🕌 ﺑﻌﻀﻨﺎ ﺇﺫﺍ ﺻﻠﻲ ﺍﻟﺼﻠﻮﺍﺕ ﺍﻟﺨﻤﺲ ﻓﻲ ﻳﻮﻡ ﻇﻦ ﺃﻧﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﻤﺒﺸﺮﻳﻦ ﺑﺎﻟﺠﻨﺔ ..!! 🕌 ከፊላችን በቀን አምስቱን ሰለዋት ከሰገደ በጀነት የተመሰከረለት ይመስለዋል..!! 📚 ﺑﻌﻀﻨﺎ ﺇﺫﺍ ﺣﻔﻆ ﺍﻷﺭﺑﻌﻴﻦ ﺍﻟﻨﻮﻭﻳﺔ ﻇﻦ ﺃﻧﻪ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﻭﺇﻣﺎﻡ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ..!! 📚 ከፊላችን አርበዒን አነወዊ ከሓፈዘ በቃ ሸይኹል ኢስላም የዱንያ ኢማም ደረጃ የደረሰ ይመስለዋል! ﻭﻻ ﺣﻮﻝ ﻭﻻ ﻗﻮﺓ ﺇﻻ ﺑﺎﻟﻠﻪ ..!! ✍ ﺫﻛﺮﻩ ﺍﻻﻣﺎﻡ ﺍﺑﻦ ﺭﺟﺐ ﺍﻟﺤﻨﺒﻠﻲ - ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ تعالى - ‏[ﻓﻲ ﺫﻳﻞ ﻃﺒﻘﺎﺕ ﺍﻟﺤﻨﺎﺑﻠﺔ ‏(2/481‏)] ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇 🔗 https://t.me/mesjidalsunnah/14435
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
👆
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
📖ቁርአንን በአንድ ረክአ ካኸተሙ የጓደኛዬ ባለቤት ናት ይላል ፀሀፊው ግሩፔ ላይ አድሚን ነው ዋትስ አፕ ላይ ሙሀመድ አሹሜሪ ይባላል እና ከወር በፊት ሰለፊይ እንዲሁም ወደ አላህ ተጣሪ የሆነች ሴትን እንዳገባ አበስሮን ነበር ትላንት ደሞ ወደ አኼራ እንደሄደች ለቆ ነበር አላህ ይዘንላት ፊርደውስም ይወፍቃት 📌ወር ነው ከሷጋ የቆየው መልካም ተግባሯን ሲናገር የተከሰተላትንም ከራማ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦ 📖ቁርኣንን በሶስት ቀን ሶስት ጊዜ አኽትማለች በነዚህ ሦስት ቀናቶች ውስጥ በአንዱ ረከዓ ብቻ ሙሉ ቁርኣንን አኽትማለች ። 📌መጨረሻ ላይ ወባ ነገር ይዟት ነበር የሞተችው አላህ ለሱም ሰብሩን ይስጠው። 📌ይሄን የላኩላቹ ዛሬ በለቀቀው ንግግሩ ነው። ምን አለ፦ ጀናዛ ማጠብያ ውስጥ አንድ ሴት ብቻ ነበረች 👉ጥዋት 1 ሰአት ማጠብያ ቦታ አስገባናት ከዛም 5 ደቂቃ አልቆየንም አጣቢዋ ጨርሳለች❗️ በጣም ተግርሜ ጠየኳት እንዴት ለብቻሽ ቶሎ ጨረሽ አልኳት❓ ወላሂ ማን ያግዘኝ እንደነበር አላውቅም ውሃውን ከፈኑን ማን እንዳቀረበ ሁሉንም አላቅም አለችኝ❗️ 👉ወላሂ ይህማ ለሷ ከራማ ነው አልኩኝ 👉ከዛ ጀናዛዋን ተሸክመን ስንሄድ በጣም ያፈጥነናል ወደ ቀብሯ አልደረስንም ነፍሳችን ሊወጣ እስኪደርስ እንጂ በጣም ከሚገፋን ነገር የተነሳ 👉ቀብር ገባንና እኔና ወንድሟ ያዝናት በጣም በጣም ደስ የሚል ሽታም አገኘን ማነው እንደዚ የቀባት እስክል ድረስ 👉አጣቢዋን ጠየኳት ከፈኗ ላይ ደስ ሚል ሽቶ ቀብታቹ ነበር አልኳት❓ ወላሂ ምንም አልቀባንም አለች ❗️ 👉ለአላህ ጥራት ይገባው ቀብር ቦታ የነበሩት ሁሉም አይተዋል የሽቶውን ሽታም አግኝተዋል ከዛ መሀል አንዱ እንዲህ አለ እቺ ሴት ምን አይነት መልካም ስራ ቢኖራት ነው እንዲህ አይነት ደስ የሚል መአዛ ከአካሏ ሚወጣው ከአላህ ጋር የነበራት ሁኔታ እንዴት ቢሆን ነው❓ 👉ይህ ወላሂ የተመለከትኩት ነገር ነው በአይኔ ያየሁት ነው። የሷ መለየት አሁን አንድ አካሌን ያጣሁም ነው የመሰለኝ ❗️ መጀመሪያም መጨረሻም ጉዳይ በአጠቃላይ ለአላህ ነው። ንግግሩ አብቅቷል አላህ የተሻለ እንዲተካለት ልቡንም እዲያፀናለት እንጠይቅለታለን 🤲 በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ሴቶች በጣም አናሳ ናቸው ❗️ 👉ምድር ላይ ፈሳድ ተበትኗል ማስሚዲያዎችም ቤቶችን ዘምተዋል ለሴቶችም መኝታቸው ቦታ ላይ ቀርበዋል አላህ ይጠብቀን ይጠብቃቸው والحمدلله رب العالمين ١٤٤٦/١/٣ محرم ከአረብኛ ተወስዶ የተተረጎመ ✍አቡ ዓብደላህ
Hammasini ko'rsatish...
👍 9
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.