cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Merkato Media

#merkato_media #መርካቶ_ሚድያ በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ቻናል ነው። ''We testify about the Truth ''

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
7 320
Obunachilar
-524 soatlar
-367 kunlar
-28230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥርና ምደባ የአገሪቱን ብሄረሰቦች ብዝኀነትና የጾታና የአካል ጉዳተኞችን ተዋጽዖ የጠበቀ እንዲኾን የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ምክር ቤቱ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ትናንት ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ፣ በመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ጭማሪ፣ ደሞዝ እርከን፣ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ላይ ማሻሻያ እንዳደረገም ተገልጧል። የአነሳ ብሄረሰቦችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ በሥራ ደረጃ እድገት፣ በትምህርትና ሥልጠና ረገድ ተጨማሪ መንግሥታዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል። ምክር ቤቱ፣ ረቂቅ አዋጁን ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል። [ዋዜማ]
Hammasini ko'rsatish...
👍 7👎 5
Photo unavailableShow in Telegram
ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ🙆‼️ በሀድያ ዞን ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀን አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀን (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰነድ ማስረጃዎችን፣ጥቆማዎችን እና መመሪያዎችን በማጣቀስ ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ሌላም የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱን እና ፍቃድ የሌለው የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታውን እንዲሰራ ያለ ጨረታ እንደተሰጠው በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል። በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተመሳሳይ ምርመራ ቢደረግ ከዚህም በላይ የሙስና ወንጀል እንደሚገኝ እሙን ነው። @sheger_press @sheger_press
Hammasini ko'rsatish...
👍 21 1
Photo unavailableShow in Telegram
2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡ መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:— ✔ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ✔ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት @sheger_press @sheger_press
Hammasini ko'rsatish...
👍 5
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በአፋርና ሱማሌ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች በአፋር እና ኢሳ ጎሳዎች መካከል በሚያጋጥሙ ግጭቶች ሳቢያ ከ38 ሺህ በላይ ዜጎች አፋር ክልል ውስጥ በሦስት ወረዳዎች መፈናቀላቸውን ባካባቢው ባደረገው ጉብኝት ማረጋገጡን አስታውቋል። የኹለቱ ጎሳዎች ታጣቂዎች ባብዛኛው ግጭት ውስጥ የሚገቡት፣ በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን እና በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ሲኾን፣ በተለይ በተያዘው ዓመት ተደጋጋሚ ግጭቶች ተካሂደዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ በኹለቱ ጎሳዎች መካከል በተደጋጋሚ የሚካሄደውን ግጭት ለመፍታት ከሳምንታት በፊት አሸማጋይ ኮሚቴ ማቋቋሙ አይዘነጋም። ኾኖም የጎሳ ግጭቱ እስካለፈው ሳምንት ድረስ ቀጥሎ እንደነበር ተሰምቷል። @merkato_media
Hammasini ko'rsatish...
👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
ታሰረ ‼️ በቲክቶክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መሌ ፌዳው በሚል ስም የምናውቀው የፌደራል ፖሊስ አባል መለሰ ብርሃኑ መታሰሩ ተሰምቷል። የፖሊስ አባሉ የታሰረበት ምክንያት የመከላከያን የክብር ልብስ ለብሶ የሰራዊቱን ስም የሚያጎድፍ ቪድዮ ሰርቷል በሚል ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ዋስትና ሳይፈቀድለት ቀጠሮ እንደተሰጠበት እንደቀረ ታውቋል። @sheger_press @sheger_press
Hammasini ko'rsatish...
👍 17😁 6😢 3
ባለፉት ጥቂት ቀናት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች እንደተካሄዱ ዋዜማ ከምንጮች ሰምታለች። በግጭቱ ሳቢያ፣ የክልሉን ዋና ከተማ ባሕርዳርን ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና መቀመጫ ደብረማርቆስ ጋር የሚያገናኘው መንገድ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተዘግቶ እንደነበር ተሰምቷል። በተመሳሳይ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ውርጌሳ ከተማ እና አካባቢዋ በኹለቱ ወገኖች መካከል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ግጭት እንደተካሄደ ምንጮች ተናግረዋል። @merkato_media @merkato_media
Hammasini ko'rsatish...
👍 12
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሕወሃት ኃይሎች ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት ያቀረበውን ውንጀላ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል። የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ውንጀላ "በጥብቅ እንደሚያወግዝ" የገለጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይህን ውንጀላ ያሰማው ዓለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ነው በማለት አጣጥሎታል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ሕወሃት የፖለቲካ ፓርቲ በመኾኑ "የታጠቀ ኃይል ወይም ሚሊሺያ የለውም" በማለትም ምላሽ ሰጥቷል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ አያይዞም፣ ሱዳን በትግራዩ ጦርነት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉን ስደተኞች ያስጠለለች እንደመኾኗ ትግራይ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ የምትገባበት ምክንያት ሊኖራት አይችልም ብሏል። ኹለቱ ወገኖች ጦርነቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲቆጠቡና ጦርነቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጠይቋል። @merkato_media @merkato_media
Hammasini ko'rsatish...
👍 7
ለመላው የመርካቶ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ   እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ  ይሆን ዘንድ እየተመኘን በዓሉን ስናከብር ዓቅመ ደካሞችን በመርዳት ይሆን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን። መልካም በዓል @merkato_media @merkato_media
Hammasini ko'rsatish...
👍 19 2
Photo unavailableShow in Telegram
ተፈታ‼️ ልጅ ያሬድ ተፈቷል💇‍♂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካ ቃላት ተናገሮ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረው ልጅ ያሬድ በዛሬው ዕለት ተፈቷል። @sheger_press @sheger_press
Hammasini ko'rsatish...
👎 33👍 7🖕 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጌታቸው ረዳ‼️ "በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር። በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል። " የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል። ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል። " ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ  ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል። (Tikvah)
Hammasini ko'rsatish...
😁 18👍 15🕊 3👎 2