uz
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

Kanalga Telegram’da o‘tish

Bashewam School Grade 1-8

Ko'proq ko'rsatish
2 763
Obunachilar
+524 soatlar
+157 kunlar
+6530 kunlar
Postlar arxiv
Share 'የተማሪዎች የክፍል ዝውውር መመሪያ .pdf'

🪀የቡድን አመራር ችሎታዎች/Team Leadership Skills – ተማሪዎች በተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ  ከክፍል ወይም ከሌሎች ክፍል ጓደኞቻቸው ጋር አብረው በሚሳተፉበት ጊዜ የመሪነት ክህሎታቸው፣የተሟላ የቡድን አቋም የመፍጠር(team integrity) እና  የማስተባበር  ክህሎቶቻቸው(coordination skills) እንዲያድግ/ እንዲዳብር ይረዳል፡፡ 🏀የሞራል እሴቶች/Moral Values –ተማሪዎች በተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ ባህሎች እሴቶችን፣ሀይማኖት፣ ብሔራዊና አለማቀፋዊ ክስተቶች፣የተማሪነት ህይወት ሥነ-ምግባር፣ማህበራዊ ሥነ-ምግባር(social ethics)፣ትዕግሥት(patience)፣ እንደራስ/የሌላውን ስሜት መረዳትን(empathy)፣የማበረታታት ክህሎት፣ከሌላው ጋር አብሮ መኖርን (compatibility) ፣መደሰትን/መርካትን(contentment.)…ይማራሉ ፡፡ 🥎አመክንዮዋዊ እና ትንተናዊ አስተሳሰብ/Logical and analytical thinking – ሁኔታዎችንና ክስተቶችን በምክንያት የማሰብና የመተንተን አቅም እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል፡፡ 🏓በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ/Critical thinking –ፅንስ ሀሳቦችን (concepts)፣ ሀሳቦችን (ideas)፣ችግሮችን/ተግዳሮቶችን/እንቅፋቶችን/ጉዳዮችን (problems/case/challenge/trouble) እና ርዕሰ ጉዳይን (issues) የማጤን/የመመርመር አቅም ይሰጣቸዋል፡፡ ⚽️የፈጠራ አስተሳሰብ/Creative thinking – አዳዲስ ሀሳቦችን/ነገሮችን የማመንጨት/የመፍጠር/የማምረት አቅም እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

👉የተጓዳኝ  ትምህርት ክበባት ተግባራት 👯🌿የተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት የምንላቸው ተማሪዎች  ላይ ሁለንተናዊ እድገት ለማምጣት በመማሪያ ክፍልና ከመማሪያ ክፍል ውጪ የሚተገበሩ ተግባራት ናቸው፤ 🏃‍♂🌿የተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት በግል ወይም በቡድን፣በመማሪያ ክፍል ወይም ከመማሪያ ክፍል ውጪ እንደ ተገባራቱ  ሁኔታና ባህሪ ሊከናወኑ ይችላሉ፤ 🏃‍♀የተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ሥርዓተ-ትምህርት ጋር በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተዛማችነት ያላቸው ሲሆኑ ለሚማሩት ትምህርት መስታወት ናቸው፤ 👩‍👧🌿የተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት ለተማሪነት ህይወት እጅግ አስፈላጊ/መሰረታዊ ክፍሎች ናቸው፤ 👭🌿ተማሪዎች በተጓዳኝ  ክበባት ተግባራት ላይ የመሳተፍ ግዴታ አለባቸው (compulsory activities)። 👉የተጓዳኝ ክበባት ተግባራት ሚና እና ጠቃሚነት 🏈ለአካላዊና አእምሯዊ ጤና /Physical and Mental Health ተማሪዎች በአትሌቲክስ (athletics)፣ በጂምናስቲክ (gymnastics)... እና በመሳሰሉት የክበባት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሲሳተፉ ለአካል ብቃት መዳበር (physical fitness) እና ለአእምሮ ጤንነት (mental health)  ሁነኛ አስተዋፅኦ ይሰጣል/ያበረክታል፡፡ይህ ደግሞ ንቁ  እንዲሆኑ ያደርጋቸውል፣በትምህርት አማካኝነት ከሚመጣ አላስፈላጊ ጭንቀት/መጨናነቅ እፎይታ ይሰጣቸዋል… ፡፡ 🥏የመማር ልምድ/Learning Experience -ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ የመገኘት ፍላጎታቸውን/ልምዳቸውን ይጨምራል/ያሻሽላል/ያዳብራል፡፡ ከትምህርት ገበታቸው ላይ የመቅረት፣የመፎረፍ እና የማቋረጥ ባህሪያትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፡፡

✅ Learn phrasal verbs with KICK : "kick back", "kick out", "kick up"... ❖•🌺🌸•❖       

4_6026061548349295332.mp415.33 MB

❌DON'T SAY❌'Can you repeat?'❌ IT IS WRONG! Learn these correct alternatives✔️ ══❖•🌺🌸•❖═══╗        

4_5971995559429410756.mp43.10 MB

4_6048648712639482743.mp37.60 KB

“Language is the blood of the soul into which thoughts run and out of which they grow.” ― Oliver Wendell Holmes ══❖•🌺🌸•❖═══╗        BASHEWAM SCHOOL HAPPY LEARNING ══❖•🌺🌸•❖═══╝“Language

ለባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ ከ1ኛ - 4ኛ ያሉ ተማሪዎች ከሰኞ 19/02/2016 ጀምሮ የሙከራ ፈተና የሚሰጣቸው ስለሆነ በተላከላችሁ መረሐ ግብር መሰረት ልጆቻችሁን እንድታዘጋጁ ወይም እንድታስጠኑ እናሳስባለን፡ ፈተናው የሚሰጠው ትምህርት እየተማሩ ይሆናል።

በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች! ======================== 👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዘዴዎች፤ ------------------------------------------------ ☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ 👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 

የጥናት እቅድ አወጣጥ (ለተማሪዎች ሼር) 1. ለነገ ዝግጁ ሁኑ ሁሌም ዛሬ ለምነሰራው ብቻ ሳይሆን ነገ ለምንሰራው ስራ እቅድ በማውጣት ዝግጁ ልንሆን ይገባል! ለነገ ዝግጁ ሰትሆኑ ሰአታችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁ የቤት ስራችሁን በብቃት ወይንም በጊዜው ለማጠናቀቅ ይረዳችኃል! 2. የጥናት ቡድን ፍጠሩ ይህ የድሮ ዘዴ ሊመሰል ይችል ይሆናል! ነገር ግን አሁንም ቢሆን የጥናት ቡድን መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው! እድሜ ለቴክኖሎጂ መሻሻል በሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በምንጠቀምባቸው ስልኮች የሚገኙት እንደ ጎግል ፕላስ የመሰሉ ማህበራዊ ድረገፆች ከአስር በላይ ለሆኑ የጥናት ቡድኖች በቀጥታ የምስል እና የድምፅ ውይይት ለማድረገ ያስችላሉ! ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ የትምህርት አቻ ጓደኞች ጋር በአካልም ሆነ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መገልገያዎች የጥናት ቡድኖች በመፍጠር እውቀትን እና ልምዶችን ልንጋራ ይገባል! 3. አንድ ነገር ለመስራት መደበኛ ልምድ ይኑራችሁ! – ከትምህርት ጋር የተገናኙ ስራዎችን ለመስራት እለታዊ የሆነ መደበኛ ጊዜ ስትመድቡ ሁሌም ቢሆን የሚሰጣችሁን የትምህርት ሀላፊነቶች እና የቤትስራዎች በአግባቡ እና በጊዜው ሰርቶ ለመጨረስ ይረዳችኃል! በአካባቢያችሁ ያሉ ሰዎችም ይህን ተረድተው ከአላማችሁ እንዳያሰናክሏችሁ አድርጉ! 4. ለጥናት ምቹ የሆነ ቦታ ያመቻቹ ! – ሁሌም ቢሆን የምታጠኑበት ስፍራ ምቾት ሊሰጣችሁና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳችሁ ሊሆን ይገባል! 5. ሁሌም ቢሆን ተጠባባቂ እቅድ ይኑራችሁ – ብዙ ጊዜ ለትምህርት እና ለጥናት የምንገለገልባቸው እንደ ኮምፒውተር የመሳሰሉ መሳሪያዎች በማንጠብቃቸው ሰአቶች ሊበላሹ ብሎም ሊጠፉና ሊሰረቁ ይችላሉ! ስለዚህም አስፈላጊ የምንላቸውን ፋይሎች በተለያየ መልኩ በተጠባባቂነት ልንይዛቸው ይገባል! 6. የቀን መቁጠርያ አዘጋጁና ተጠቀሙ – በሁሉም የትምህርት ተቋማትና ደረጃዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ የጥናት ስራዎች ይሰጣሉ! ታዲያ እንደ ርዝመታቸው እና እጥረታቸው ተማሪዎች በመዘናጋት ስራቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ሲቀሩ ይስተዋላል! ይህን አስወግዶ ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ከእለት ተእለት የትምህርት እና የጥናት እንቅስቀሴ ጀምሮ የረጅምና የአጭር ጊዜ ሀላፊነቶቻችንን በቀን መቁጠርያ አማካይነት እቅድ ልናወጣላቸው እና ልንተገብራቸው ይገባል! 7. የተደራጃችሁ ሁኑ በትምህርት ቆይታችሁ የምትገለገሉባቸውን መሳሪያዎች የትምህርት ሰአት የጥናት ሰአታችሁን የመዝናኛ ሰአታችሁን የገንዘብ አጠቃቀም እቅዳችሁን በመለየት ሁሉንም በስርአት በቦታውና በሰአቱ በመጠቀም የተደራጃችሁ ሁኑ! 8. አዎንታዊ አስተሳሰብን ያጎልብቱ ! የትምህርት ቤት ሕይወት ጠንካራ ስራን የሚፈልግና በጭንቀት ብሎም በመሰናክሎች የተመላ ነው! እነዚህን የሚገጥሙንን ጭንቀቶችና መሰናክሎች ተቋቁመን ስኬታማ ለመሆን ከምንመኛው የምረቃ በዓላችንም ለመድረስ አዎንታዊ አስተሳሰብን ልናጎለብት ይገባል! እንዴት አዎንታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት እንደምንችል ኩሉ ኔትወርክ በቀጣይ ጠቃሚ ምክሮች ይዞላችሁ የሚመጣ ይሆናል! 9. እረፍት ውሰዱ ጥናት ከመጀመራችሁ በፊት ሆነ በጥናት መሀል አጭር የእረፍት ጊዜ መውሰድ ችግር እንደሌለው ልንረዳ ይገባል! ምክንያቱም የእረፍት ጊዜያቶች መንፈሳችሁን እንድታድሱ እና ወደጥናት ስትመለሱ ትኩረት አድርጋችሁ እንድትሰሩ ይረዳችኃል! 10. ዝርዝር የስራ እቅድ ወይንም check list ይኑራችሁ! – ብዙን ጊዜ የምንማራችው ትምህርቶች እለታዊ የሙከራ ስራ እና የቤት ስራዎች ይኖራቸዋል! በመሆኑም የሁሉንም የምንማራቸውን የትምህርት አይነቶች ሀላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት እቅድ ልናዘጋጅላቸው ይገባል! ይህም የስራ ሀላፊነታችንን በአግባቡ ለመወጣት ይረዳናል! ባሸዋም ትምህርት ቤት ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን ! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

"Discipline is not about becoming perfect. It's about becoming the best version of yourself." Here are ten practical lessons from the book 365 Days with Discipline by Martin Meadows: 1. Start small. Don't try to change too much too quickly. Start with small, achievable goals and gradually work your way up to bigger ones. 2. Be consistent. The key to discipline is consistency. Even if you can only do a little bit each day, make sure you do it consistently. 3. Forgive yourself for setbacks. Everyone slips up from time to time. Don't beat yourself up if you make a mistake. Just pick yourself up and keep going. 4. Find a support system. Having people who support your goals and encourage you along the way can make a big difference. Find a friend, family member, or mentor who can help you stay on track. 5. Make discipline fun. If you find discipline to be boring or unpleasant, you're less likely to stick with it. Find ways to make discipline more enjoyable, such as listening to music while you work out or setting rewards for yourself. 6. Visualize success. Take some time each day to visualize yourself achieving your goals. This will help you stay motivated and focused. 7. Celebrate your successes. When you reach a goal, take the time to celebrate your accomplishment. This will help you stay motivated and keep moving forward. 8. Don't be afraid to fail. Failure is a part of life. Everyone fails at some point. The important thing is to learn from your mistakes and keep trying. 9. Don't compare yourself to others. Everyone is on their own unique journey. Don't compare yourself to others and focus on your own progress. 10. Enjoy the process. Discipline is not about becoming perfect. It's about becoming the best version of yourself. Enjoy the process of growth and development. Developing discipline is not easy, but it is worth it. Discipline can help you achieve your goals, live a healthier and more fulfilling life.

ውድ ወላጆች ከ1ኛ-6ኛ ክፍል መፅሐፍ ስለመጣ ከሰኞ ጀምሮ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ የቅዳሜ ቀን የማጠናከሪያ ትምህርት የተጀመረ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን ፡ የትራንስፖርት የሰርቪስ አገልግሎትም ቅዳሜ 17/02/2016 ይጀመራል ፡ ስለዚህ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲማሩ ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኩልን እናሳስባለን ። ተማሪዎች ከ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ትምህርት ቤት ግቢ መገኘት አለባቸው ፡ የመውጫ ሰዓት 6:30 ስለሆነ በሰዓቱ መጥታችሁ ልጆቻችሁን እንድትወስዱ እናሳስባለን።