cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 127
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+97 kunlar
+14230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - "ኢኽላስ ማለትኮ : መላኢካ ይፅፈዋል አይባል አያውቀው ፣ ጠላት ያበላሸዋል አይባል እሱም አያውቀው ፣ ባለቤቱ ራሱ ያበላሸዋል አይባል አይገረምበት።" 📚 ۞【الفــوائــــد【٩٩】۞ ◈
Hammasini ko'rsatish...
·•● የሰለፎች ኮቴ ●•·

በየቀኑ የቀደምቶችን ድንቃድንቅ ንግግሮች እንዲደርስዎ ይቀላቀሉን ፣ ሼር ያድርጉ👇

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ أولى الناسِ بي يومَ القيامةِ أكثرُهم عليَّ صلاةً﴾ “በትንሳዔ ዕለት ከሰዎች ሁሉ ለኔ በላጭ (ቅርብ) የሚሆነው በኔ ላይ በብዛት ሰለዋት የሚያወርድ ነው።” 📚 ሶሂህ አተርጊብ
Hammasini ko'rsatish...
ቢላል ኢብኑ ረባህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ እስልምናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ካደረጉት ውስጥ አንዱ ነው። ⇨እስልምናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ያወጡት 7 ናቸው እነሱም ረሱል (ﷺ) ፣ አቡበክር ፣ ዐማር ፣ የዐማር እናት ሱመያህ ፣ ቢላል ፣ ሱሀይብ እና ሚቅዳድ ናቸው። ๏ መስለሙን ግልፅ ባወጣ ጊዜ በአለቃው ኡመያህ ኢብኑ ኸለፍ በጣም ከባድ ቅጣት ደርሶበት ነበር ነገር ግን እሱ አሀዱን አሀድ ከማለት አልተወገደም ነበር (ረ.ዐ) እየተቀጣ እያለ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) መጣና ገዝቶት ነፃ አወጣው። በዚህም ንግግሩ "አሀዱን አሀድ " በጣም ታዋቂ ሆነ አሀዱን አሀድ ሲባል በሁሉም ሰው ፊት የሚመጣው ቢላል እና ታሪኩ ነው። ๏ ለሰላት መጀመሪያ ጊዜ አዛን ያደረገው ነው ๏ በድር ዘመቻ ላይ አለቃው የነበረውን ኡመያን የገደለው እሱ ነው ๏ ረሱል (ﷺ) ዘንድ በጣም ትልቅ ደረጃ ነበረው ስለርሱ ብዙ ብለዋል ከነዛ ውስጥ‥ ⇨ጀነት ውስጥ የቢላልን ኮቴ መስማታቸውን ⇨ቀዳሚዎች 4 ናቸው እኔ የዐረብ ቀዳሚው ነኝ ፣ ስልማን የፋሪስ ቀዳሚ ነው ፣ ቢላል የሐበሻ ቀዳሚ ነው ፣ ሱሀይብ የሮም ቀዳሚ ነው ማለታቸውና ሌሎችም ተናግረዋል። ๏ እድሜው ወደ 60 ምናምን ሲደርስ አጀሉ ቀረበ ሊሞት አከባቢ ሚስቱ ወ ሀዘኔ አለች እሱም " ዋ ደስታዬ ነገ ወዳጆችን እንገናኛለን ሙሐመድን (ﷺ) እና ህዝቦቹን " (الأحبة نلقى غدا وحزبة محمدا) ሻም ውስጥ ሞተ እዛውም ተቀበረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ቢላል ኢብኑ ረባህ ይባላል የረሱል (ﷺ) ሙአዚን ተብሎም ይታወቃል ๏ የረሱል (ﷺ) ሙአዚኖች 4 ናቸው አንደኛው ቢላል ሲሆን ሁለተኛው አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ሶስተኛው አቡ መህዙረህ አራተኛው ሰዐድ አልቁረዚ ናቸው። ⇨የእናቱ ስም ሀማመህ ትባላለች https://t.me/Hassendawd
Hammasini ko'rsatish...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

የኒካህ ቀለበት ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ የተሰራጨው ኒካህ ላሰረላት ሴት ቀለበት ማድረግ የሚባለው ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ይተገበር ያልነበረ ከክርስቲያኖች የተወሰደ ተግባር ነው። የዘመናችን ሙሀዲስ የሆኑት ሸይክ ናሲረዲነል አልባኒ እንዲህ ይላሉ "ይህ ተግባር ወደ ቀደመ (የክርስቲያኖች) ተለምዶ ይመለሳል። ሙሽራው በሙሽሪት የግራ እጅ አውራ ጣቷ ጫፍ ላይ ቀለበቱን ያደርግና በስመ አብ ይላል ከዛም አመልካች ጣቷ ጫፍ ላይ ያደርግና በወልድ ይላል ከዛም የመሀከለኛ ጣቷ ላይ ያደርግና በመንፈስ ቅዱስ ይላል በመጨረሻም አሚን በሚል ግዜ ከትንሿ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣቷ ላይ ያደርገውና በዛው ይቀራል። ለንደን የሚታተም women የሚል ጋዜጣ (ቁ 19 1960 ገፅ 8) ላይ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ Why is the wedding ring placed on the third finger of the left hand? ለምንድነው የሰርግ ቀለበት በግራ እጅ ሶስተኛ ጣት ላይሚቀመተው? በርእሱ ላይ መልስ የሚሰጠው Angela Talbot እንዲህ ብሎ “it is said there is a vein runs directly from the the finger to the heart. Also,there is the ancient origin whereby the bridegroom placed the ring on the tip of bride’s left thumb,saying ; “in the name of the father” on the first finger, saying “in the name of the son “ on the second finger, saying ; “And of the holy ghost”,on the word “Amen” , the ring was finally placed on the third finger where it remained” "ከዚህ ጣት ቀጥታ ከቀልብ የሚያገናኝ ደም ስር አለ ይባላል። ከዛም በተጨማሪ የቀደመ መሰረት አለው ካለ በሗላ ከላይ የጠቀስነውን በስምአብ...የሚለውን እስከመጨረሻው ጠቀሰ" በዚህ ንግግር እንደምንረዳው ይህ ተግባር የመጣው ከክርስቲያኖች እንደሆነና ጥንታዊ የሆነ እምነታዊ መሰረትም እንዳለው ነው። ይህንን የሚጠቅሱም ብዙ ኡለሞች አሉ። በመሆኑም ▪️ይህ ተግባር የክርስቲያኖች እምነታዊ መገለጫ ነው። ከነሱ መመሳሰል ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች ነው። ▪️ ይህን ቀለበት ግራ እጅ ከትንሿ ጣት ጎን ሚያደርጉበት ምክንያት ይህ ጣት ከልብ ጋር ግንኙነት አለው የሚል ከንቱ እምነት ይዘው ነው ይህ ደግሞ በእስልምና ቦታ የለውም ▪️ ብዙ ሰዎች ዘንድ ቀለበት ማሰሩ በመሀከላቸው ውዴታን ያመጣል የሚል እምነት አለ ይህም ከእስልምና አቂዳ ጋር ቀጥታ የሚጣረስ የሽርክ አይነት ነው። ▪️ አንዳንዶች ደግሞ ቀለበት ካለበሰ ወይም ካለበሰች ኒካው ትክክል አይመስላቸውም ይህም መሰረት የሌለው አጉል እምነት ነው። ▪️ ይህ ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ያልተለመደ ከክርስቲያኖች የተወረሰ ነው ▪️ አንዳንዶች ገና ሲተጫጩ ኒካም ሳያስሩ ወስዶ ቀለበት ያደርግላታል ይህ ደግሞ የተከለከለችን አጅነብይ ሴት እጅ መንካት ነው ያም ከባድ ወንጀል ነው። እንዳጠቃላይ ለኒካህ ወይም ሰርግ ብሎ ቀለበትን መልበስ የሙስሊሞች ሳይሆን የክርስቲያኖች ሱና ነው። ኢብን ኡሰይሚን ስለዚህ ሲናገሩ "እኔ ማየው አነሰ ቢባል ይህ ተግባር የተጠላ ነው ይላሉ።” ኢብን ባዝም ለሰርግ ብሎ ቀለበት ማሰር የሙስሊሞች ሱና እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ሸይኽ አልባኒም እንደማይቻል ይገልፃሉ። ከዛ ውጪ ባለ ሁኔታ ግን ለኒካህ አስበህ ሳይሆን እንዲሁ ቀለበትን በኖርማል ግዜ ብትለብስ ችግር የለውም። ለወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለበት አይፈቀድም። https://t.me/Hassendawd
Hammasini ko'rsatish...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

👍 4
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የተከበራችሁ እህትና ወንድሞች እንኳን ወደ ዛድ ኦንላይን የቂርአት ማዕከል በሰላም መጣችሁ እያልን መመዝገቢያ ፎርም እንደሚከተለው ይቀርባል። 1, ስም ከነ አያት__ 2, አሁን ያለንበት ሀገር____ 3,ዋሳፕና ቴሌግራም ምትጠቀሙበት ስልክ ቁጥር____ 4,ፆታ____ 5,የቂርአት ደረጃ_ 6.መቅራት የሚፈልጉት_ ማሳሰቢያ:- 👉🏿መድረሳችን በአንድ አመት 4 ሴሚስተር የሚኖሩት ሲሆን ክፍያ የሚፈፀመው በየ ሴሜስተሩ ነው። 👉🏿በቁርጠኝነት መማር የምትፈልጉ ብቻ እንድመዘገቡ በትህትና እንጠይቃለን። 👉🏿ትምህርቱ የሚሰጠው በዙም አፕ እና በ ቴሌግራም ስለሆነ ከወዲሁ አፑን በማውረድ ለትምህር እንድትዘጋጁ እናሳስባለን። _ መመዝገቢያ ሊንክ👉🏿 https://forms.gle/Ve6Fcex92Nu5sbRQ8 ይህን ሊንክ በመጫን ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ መመዝገብትችላላችሁ።
Hammasini ko'rsatish...
1
አቡ ዑበይድ ኢብኑል ጀራህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሳሃቦች አንዱ ነው። ๏ በሁለተኛው ጊዜ ወደ ሐበሻ ከተሰደዱት ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ቁርአንን ከሀፈዙት (በቃል ከያዙት) ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ረሱል (ﷺ) የተለያዩ ልኡካንን ሲልኩ አባ ዑበይዳን መሪ አድርጎ ነበር የሚልከው እርሱ ዘንድም በጣም ተወዳጅ ሰሃቢይ ነበር ከዛ የተነሳ ረሱል (ﷺ) ከሞቱ በኋላ አቡበክር ኺላፋው ለአቡ ዑበይዳህ ነው የሚገባው እስከማለት ደርሶ ነበር ከዛ በኋላ ነው ዑመር " አይ አለቃችን ፣ በላጫችን ፣ ረሱልም ዘንድ ይበልጠ ተወዳጅ የሆንከው አንተ ነህ " ብሎ አለ። ኺላፈውም ለአቡ በክር ቃል ተገባ‥ ⇨በአቡ በክር ኺላፋ ዘመን ሻምን ለመክፈት አቡ ዑበይዳን መሪ አድርጎት ነበር የላከው ተሳክቶለት ከፈታት…የተለያዩ ሀገራትንም ከፍቷል። ⇨በዑመር ኺላፋ ዘምንም ዑመር በሰራዊቶችና በሻም ሀገር ላይ መሪ አድርጎት ነበር። ⇨አቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችው በዑመር ኺላፋነት ዘመንና በአቡ ዑበይደህ ጦር መሪነት ነበር በዚህም ሰበብ የመሪዎች መሪ ይባላል። ๏ ሻም ሀገር ላይ ወባ ተከስቶ ነበር በዛ ሰበብ ከዚህች አለም ወደ ሌላኛው አለም ተሻገረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ዓሚር ኢብኑ አብደላህ ኢብኑል ጀራህ ይባላል ๏ የዚህች ኡማህ (ህዝብ) ታማኝ ተብሎም ይታወቃል ምክኒያቱ ደግሞ … ረሱል (ﷺ) ዘንድ የየመን ሰዎች መጡና " ከኛ ጋር ሱናን እና እስልምናን የሚያሰተምረን አንድን ሰው ላክ " አሉት ከዛም ረሱል (ﷺ) የአባ ዑበይዳህን እጅ ይዘው የዚህች ኡማህ ታማኝ እሱ ነው " አሉ። ⇨በሌላ ዘገባም " ለሁሉም ህዝብ ታማኝ አላቸው የዚህች ህዝብ ታማኝ ደግሞ አቡ ዑበይደህ ኢብኑል ጀራህ ነው " ብለዋል። ⇨የእናቱ ስም ኡመይመህ ቢንት ገነም ኢብኑ ጃቢር ትባላለች ๏ ኢብኑ ሀዝም አል አንደሉሲ ኡመይመህ ቢንት ዑስማን ኢብኑ ጃቢር ኢብኑ አብዱል ዑዛህ ብለውም አስቀምጠዋል ‥ https://t.me/Hassendawd
Hammasini ko'rsatish...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

ለኒካህ ዱፍ መምታት ዱፍ የሚባለው ከአንድ በኩሉ በቆዳ የተሸፈነ በሌላ ጎኑ ክፍት የሆነ ትንሽ ከበሮን የሚመስል በእጅ የሚመታ የሙዚቃ መሳሪያ ነው በዲነል ኢስላም የሙዚቃ መሳሪያዎች በሙሉ የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃውም ኢማም ቡኻሪ ሰሒሀቸው ላይ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል {{ ْلَیَكُونَنَّ من َأُمَّتِي أَقْوَامٌ یَسْتَحِلُّونَ حِرَ وَالْحَرِیرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِف}} {ከኔ ኡማ ሰዎች ይመጣሉ ፦ ዝሙትን ፣ ሀር ልብስን (ለወንድ ልጅ) ፣ አሰካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ} ይህ ሀዲስ ሁሉም የሙዚቃ መሣሪያ ዱፍንም ጨምሮ መከልከሉን ይጠቁማል በተጨማሪም ኢማም አልበይሀቂ በዘገቡት ሀዲስ አብደላህ ኢብን አባስ ዱፍ ሀራም ነው ማለቱ ተወርቷል።¹⁶² እንደጥቅል ሁሉም የሙዚቃ መሳሪያዎች የተከለከሉ ቢሆንም ዱፍ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ተፈቅዷል እነሱም በሰርግ፣ በኢድ እና የሩቅ እንግዳን ለመቀበል ነው።በነዚህ ሶስት ቦታዎች ላይ ዱፍ መምታትን የሚፈቅዱ የመጡ የተረጋገጡ ሀዲሶች አሉ።¹⁶³ ከነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ውጪ ዱፍን መምታት የተፈቀደበት አናገኝም በመሆኑም የሙዚቃ መሳሪያ እንደመሆኑ እንደሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ሁሉ በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የተከለከለ ይሆናል። በሸሪአ የተከለከለ ነገር ለሆነ ነገር ተነጥሎ ከተፈቀደ በዛ ላይ ብቻ ነው ፈቃዱ የሚሆነው እንጂ ለሁሉም ሁኔታዎች የተፈቀደ አይሆንም።ስለዚህ ሰርግ ላይ ዱፍን መጠቀም ይቻላል። በሰርግ ላይ እንኳን ቢሆን ከዱፍ ውጪ ያሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም በጭራሽ አይፈቀድም። ለወንድ ልጅስ ይፈቀዳል ወይስ በሴት ልጅ ብቻ የተነጠለ ነው? ለወንድ ልጅ ዱፍ መምታትን በተመለከተ ኡለሞች መሀከል ኺላፍ ያለበት ሲሆን አመዛኝ በሆነው የኡለሞች አቋም መሰረት ዱፋ መመታት የሚፈቀደው ለሴቶች ብቻ ነው።ምክንያቱም በሰሀቦች ዘመን ይህ ሚታወቀው ከሴቶች ዘንድ ነበር ከወንዶች መሀከል ይህን መስራት ደግሞ በሴቶች መመሳሰል ይሆናል።ከሴቶች መመሳሰል ደግሞ ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንዲህ ይላል “ከሰሀቦች መሀከል ዱፋ በመምታት የሚታወቅ ወንድ አንድም አልነበረም።እንዲያውም ይህንን የሚያደርግን ሰው ቀደምቶች ሴታሴት ብለው ይጠሩት ነበር” ¹⁶⁴ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል “ጠንካራ የሆኑ ሀዲሶች ላይ ለሴቶች መፈቀዱን ይጠቁማል። በዚህ ላይ ወንዶች አይገቡበትም ጥቅል የሆነ ከሴቶች ጋር መመሳሰልን የሚከለክሉ ሀዲሶች ስላሉ።” ባጠቃላይ መልኩ ለወንድ ልጅ ጦር ውርወራ ፣ ፈረስ ግልቢያ እና የመሳሰሉት ተግባሮች ላይ መገኘት ነው ተገቢ ሚሆነው እንጂ የሴቶች ተግባር በሆኑት ዱፍ መምታት እና ማጨብጨብ ላይ መገኘት የለበትም። ስንጠቀልል ሴቶች ከወንዶች ጋር ሳይቀላቀሉ በሰርግ ስርአት ላይ ዱፍ እየመቱ እና ግጥምን እየገጠሙ መጫወት ይወደድላቸዋል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 1
ሰኢድ ኢብኑ ዘይድ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ አንዱ ነው ሲሰልምም ከሚስቱ ጋር ነበር የሰለመው ከዑመር ኢብኑል ኸጣብ በፊትም ነበር የሰለመው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) አጎት ልጅ ነው እህቱ ደግሞ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ ሚስት ናት ሚስቱ ደግሞ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ መስለም ሰበብ የሆነችዋ እህቱ ፋጢማህ ቢንቱል ኸጣብ ናት። ๏ ወደ መዲና መጀመሪያ ከተሰደዱት አንዱ ነበር። ๏ በሙዓዊያህ ኢብኑ አቢ ሱፍያን (ረ.ዐ) ኺላፋ ዘመን እድሜው ወደ 73 ከደረሰ በኋላ ጊዜው ደርሶ ይህችን ዱንያ ለቆ ወጣ ጁሙዓህ ቀን ነበር የሞተው ቦታውም ዐቂቅ ነበር ይባላል ከዛ ወደ መዲና ተይዞ ተመጣ ጀናዛውን ሰዐድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረ.ዐ) አጥቦት ነበር መዲናም ተቀበረ… ⇨ትክክለኛ ስሙ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይል ይባላል። ๏ የሰዒድ አባት በነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሐይማኖት ላይ ነበር ለጣኦቶች አይሰግድም ነበር ቁረይሾች የሚያርዱትን ነገር አይበላምም ነበር ረሱል (ﷺ) ከመላኩ በፊት ተገናኝቶት ነበርና ሱፍራ አቅርቦላቸው ነበር ረሱል (ﷺ) አይ አለው ከዛም ዘይድ እንዲህ አለ " እኔ እናንተ ጣኦቶቻችሁ ላይ የምታርዱትን አልበላም የአላህ ስም ያልተወሳበት ነገርም አልበላም " ๏ ረሱል (ﷺ) ስለ ዘይድ ተጠይቀው ነበር እንዲህም አሉ‥ " ቂያም ቀን ልክ እንደ አንድ ኡማህ (ህዝብ) ሆኖ ይቀሰቀሳል " ๏ በሌላም ቦታ እንዲህ ብለው ነበር " ጀነት ገብቼ ለዘይድ ሁለት ትላልቅ ዛፎችን አይቼ ነበር " ⇨የእናቱ ስም ፈጢማህ ቢንት በዕጀህ ኢብኑ ኡመያህ ትባላለች። https://t.me/Hassendawd
Hammasini ko'rsatish...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

2👍 1
2.3 ለሰርግ ተጠርተህ ግን ፆመኘ ከሆንክ ጾመኛ ስለሆንኩ ብለህ ከጥሪው መቅረት የለብሀም። ይልቁንስ ጥሪውን አክብረህ ትሄድና ከዛሀም ሁለት አማራጮች አሉህ አንደኛው፦ጾምህን ሳታጠፋ ቦታው ላይ ትገኝና ለሱ ዱአ ታደርግለታለህ መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {{إذا دعي أحدكم إلى طعام فلیجب فإن كان مفطراً فلیطعم وإن كان صائما فلیصل. يعني :الدعاء }} {{አንዳችሁ ወደ ምግብ ከተጠራ ይሂድ ጾመኛ ካልሆነ ይመገብ ጾመኛ ከሆነ ደግሞ ዱአ ያድርግ}} ሁለተኛው፦ ጾምህ ሱና ጾም ከሆን ወንድምህን ለማስደሰት ስትል ማፍጠርም ትችላለህ።በተለይ ደግሞ ወንድምህ እንድትመገብ የጠነከረ ፍላጎት ካለው።ሱና ጾም መጾሙ ግዴታ እንዳልሆነው ሁላ ጀምሮት ከነበረ መጨረሱም ግዴታ አይሆንም። በዚህ ላይ የመጣ ሀዲስ አለ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል {{ الصائم المتطوع أمیر نفسھ إن شاء صام وإن شاء أفطر }} {{ሱና ጾም የሚጾም ሰው የራሱ አዛዥ ነው።ከፈለገ ይጾማል ከፈለገ ያፈጥራል}} 📖 ጾሙ ሱና እስከሆነ ድረስ ያፈጠረውን ቀን በሌላ ግዜ ቀዳ ማውጣት ግዴታ አይሆንበትም ነገር ግን ቀዳ ቢያወጣውም ይችላል። ይህንን የሚጠቁም ኢማመል በይሀቂ የዘገቡት ሀዲስ አለ። ጾሙ ግን የግዴታ ጾም ከሆነ ለምሳሌ የረመዳን ቀዳ ከሆነ ወይ ደግሞ የመሀላ ከፋራ ከሆነ ማፍጠር አይፈቀድለትም።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
‏قال سفيان الثوري رحمه الله : -  لما التقى يعقوب ويوسف عانق كل واحد منهما صاحبه وبكى، فقال يوسف : - يا أبتا ، بكيت علي حتى ذهب بصرك ، ألم تعلم أن القيامة تجمعنا قال : - بلى ، يا بني ولكني خشيت أن تسلب دينك فيحال بيني وبينك• ﴿ شعب الإيمان للبيهقي ( 183/3 ))•
Hammasini ko'rsatish...