cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቅድስት ሆይ ለምኝልን

@እንደ ኤፍሬም ባይሆን በአቅሜ በምችለው ማርያምን ማርያም በጣም እወድሻለው @dnglemaryamenate

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 694
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+547 kunlar
+14230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ሙት ነኝ ሲታወጅ የሙታን ትንሣኤ በቅዱሳን መላእክቱ ሲጎሰም ነጋሪት ...ሲነፋ መለከቱ እግዚአብሔር ይመጣል ከነሠራዊቱ ዝምም አይልም! እሳትም ...ይነዳል በፊቱ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ እግሮቹ ሲቆሙ በምድር ትቢያ ውስጥ ...ያንቀላፉት ይነቃሉ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እንደሚታይ ስንዴውን ከእንክርዳዱ ሊለይ በኃይል እና በክብር ይመጣል ከሰማይ በዚያች በአስፈሪዋ ሰዓት... የተባረኩት ተጠርተው መንግሥቱን ሲወርሱ ሙት ነኝና ...ሂድ አንዳልባል በገሃነም እሳት እንባዎቼ እንዳይፈሱ፡፡ መት ነኝ የሰገነቱ ላይ ባለፀጋ በዓለም ላይ የከበርኩ ለሥጋየ ኖሬ ነፍሴን አፍኘ የገደልኩ፡፡ ድሀው አልአዛር ከደጃፌ ሥር ወድቆ በረኃብ አለንጋ እየተገረፈ አንጀቱ ከሆዱ ጋር ተጣብቆ ከማዕዱ ፍርፋሪ ሊበላ እንደናፈቀ የሞሰቡ እንጀራ ሻግቶ እየወደቀ ድሀው አልአዛር በሞቱ ፀደቀ ከምጸዋት ተከልክሎ እጄ እንደታሰረ ከሕይወት መዝገብ ላይ የኔ ስም ተፋቀ አንድ የከፋው እንግዳ ሰው ሀገር ጥሎ የተሰደደ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎች እጅ ወደቀ ገፍፈው ደበደቡት ...ደሙን አፈሰሱት አጥንቱ ደቀቀ በሕይወት እና በሞት መካከል እስትፋሱን እየቆጠረ ዓይኔ እንደአላየ ሁኖ መንገዱን ቀጠለ ብራብ አብልታችሁ ፤ ብጠማ አጠጥታችሁኛል እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁ ፤ ታርዤ አልብሳችሁኛል ብታመም ፤ ብታሰር ጠይቃችሁኛል ፤ መንግሥቴን ውረሱ እናንተ የአባቴ ብሩካን ተብለው ሲወደሱ ጠቁሬ እንዳልነሣ ጽልመትን ለብሼ ...ዳግም ሞትን ሞቼ እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁ ፤ ታርዤ አልብሳችሁኛል ብታመም ፡ ብታሰር ጠይቃችሁኛል ፤ መንግሥቴን ውረሱ እናንተ የአባቴ ብሩካን ተብለው ሲወደሱ ቀፊ እንዳልነሣ ጽልመትን ለብሽ ዳግም ሞትን ሞቼ ከበላኤሰብእ የተረፈ ጥርኝ ውኃ አጥቼ ከእልፍ አእላፍ ቅዱሳን የአንዱን ስም ሳልጠራ በግራህ እንዳልቆም ከዲያቢሎስ ጋራ ጎስቋላው ልጅህን በምሕረት እየኝ እንደ ሥራዬማ ሙት ነኝ ዓለም የገደለኝ በዚያች በፍርድ ቀን አምላክ ተዘከረኝ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
🙏 13
Photo unavailableShow in Telegram
ከመላእክት ጋር አብረን የምንዘምርበትን የዜማ ሥርዓት ለሠራልን፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወረደውን የምስጋና ማዕድ ለእኛ እንደሚገባ አድርጎ ላደረሰ ታማኝ መጋቢ፣ ለዘማሪው፣ ለተርጓሚው፣ ለባለ ቅኔው ለቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። -የአንደበት አመጽ ጸጋን አስገፍፎ እንዴት የመልአክነትን ክብር እንደሚያሳጣ በሳጥናኤል አየን! -የአንደበት ፍሬ እንዴት እንደሚያከብር እና ምድራዊ መልአክ እንደሚያደርግ ደግሞ በቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ተመለከትን! አቤቱ የያሬድን ልሳን ስጠኝ! ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected] https://t.me/Dnabel
Hammasini ko'rsatish...
11👍 4
👆👆👆 ክፍል ኹለት - የቀጠለ በዚኽም ምስክርነት ዜማው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ መኾኑ ታምኖ ከዚያን ዕለት ዠምሮ የቅዱስ ያሬድ ዜማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገልገያ ኾነ፤ ይኽም ቀን ስብከት ተብሎ ተሰይሟል። ስብከት መባሉም ቅዱስ ያሬድ ዜማ ማስተማር የዠመረበት፣ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው የተናገሩት ትንቢት ለመፈጸሙ ምሳሌ ነው በማለት አባቶቻችን ሊቃውንት ይተርካሉ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የግእዝ ሥነ-ጽሑፍ መሥራች ብቻ ሳይኾን የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ መሥራች ነው ብንል ማጋነን አይኾንም። ይኽንንም ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የቅዱስ ያሬድ ታሪክና የግእዝ ሥነ-ጽሑፍ፤ 1999፤ ጥናታቸው ገጽ 3 ላይ እንዳብራሩት 'የግእዝ ሥነ-ጽሑፍን ለኹለት ልንከፍለው እንችላለን' ይላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ፥ 'አንዱ ክፍል ከባሕር ማዶ ተጽፈው ወደ ግእዝ የተተረጎሙትን መጻሕፍት ይይዛል። ኹለተኛው ክፍል በቀጥታ በግእዝ የተደረሱትን ድርሰቶች ያጠቃልላል። እነዚኽም የቅዱስ ያሬድ፣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ የርቱዐ ሃይማኖት፣ የዐጼ ዘርአ ያዕቆብ፣ የዐርከ ሥሉስ፣ የአባ ባሕርይ ድርሰቶችን የሚቀድም በግእዝ ቋንቋ የተደረሰ ድርሰት እስከ አኹን አለመገኘቱን በጥናታቸው ይገልጻሉ። ቅዱስ ያሬድ ከኹሉም በተለየ ድርሰቶቹን ሲያዘጋጅ ከቅዱሳን መጻሕፍት የወሰዳቸውን ርእሰ ጉዳዮች በፈርጅ በፈርጁ እየለየ በዜማ የድርሰት ሥራዎቹ እንድ ዕንቁ ፈርጥ ተጠቅሞባቸዋል። ምንም እንኳ ረድኤተ እግዚአብሔር ቢኖርበትም ብሉያትን ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንት እያጣቀሰ ያለምንም ችግር የድርሰት ሥራውን ጥንቅቅ አድርጎ ሊያከናውን ችሏል። የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ናቸው። በድርሰቶቹ የሚታዩት የቃላት አመራረጥ፣ የዐረፍተ ነገር አወቃቀር፣ የምሥጢር፣ የዘይቤ አገላለጥ የቅዱስ ያሬድን ድንቅ የኾነ የሥነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ የሚያሳዩ ናቸው። ቅዱስ ያሬድ የደረሳቸው የዜማ መጻሕፍት ዐምስት ሲኾኑ እነርሱም፥ #ድጓ #ጾመ ድጓ #ምዕራፍ #ዝማሬ እና #መዋሥዕት ናቸው። እነዚኽ የዜማ መጻሕፍት ስንዱ እመቤት በኾነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዓመት እስከ ዓመት ያለዕረፍት እና ያለማቋረጥ እግዚአብሔር አምላካችን የሚመሰገንባቸው ድርሰቶች ናቸው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያበረከታቸው የዜማ ስልት ዐይነቶችም ሦስት ሲኾኑ ግእዝ፣ ዕዝል እና አራራይ ይባላሉ። ቅዱስ ያሬድ እነዚኽን የዜማ ስልቶች በምልክት ወይም በኖታ አድርጎ አዘጋጅቷቸዋል። ይኽንንም ያደረገበት ምክንያት ምንም እንኳ ርሱ የእያንዳንዱን የዜማ ባሕርይ በእግዚአብሔር ቸርነት ከቅዱሳን መላእክት ሰምቶ በቃሉ ጥንቅቅ አድርጎ ቢያውቃቸውም ከርሱ በኋላ ለሚነሱ የርሱ ደቀ መዛሙርት የዜማ መለያ፣ መማሪያና ማጥኛ እንዲኾን ደቀ መዛሙርቱም በቀላሉ የሚያስታውሱበትን ዜማውና ድርሰቶቹም ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ በአግባቡ እንዲተላለፉበት ነው። ይኸው የቅዱስ ያሬድ ዜማና የዜማ ምልክቶች ከአንድ ሺኽ ዐምስት መቶ ዓመታት በላይ ተሻግሮ እዚኽ እኛ ዘመን መድረሱ የዚኽ ማሳያ ነው። የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን! +++++++++++++++++++
ምንጭ፥ 2015 ዓ.ም. ከተተረጎመው ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ መጽሐፍ የተወሰደ (ገጽ 1 - 9) አዘጋጅና ተርጓሚ: መጋቤ ምሥጢር ቡሩክ ጌታቸው ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም
++++++++++++++++ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ዐዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
👆👆👆 ክፍል አንድ - የቀጠለ በንጹሕ ልብ ኾነው የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔርም ልምናውን ሰምቶ ልቡናው በርቶለት በዐጭር ጊዜ የግእዝ ፊደላትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ መኃልየ ሰሎሞንን ጨርሶ መዐርገ ዲቁና ተቀብሎ መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን ተምሮ ፈጸመ። እግዚአብሔርም ለቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት። እነርሱም ቅዱስ ያሬድ ከቆመበት ፊት ለፊት በአየር ላይ ኾነው በሰው አንደበት "ብፁዕ ያሬድ! ብፅዕት ከርሥ እንተ ጾረተከ ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናከ፤ የተመሰገንክና የተከበርክ ያሬድ ሆይ አንተን የተሸከመች ማሕፀን የተመሰገነች ናት አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው" በማለት ተናገሩት። ቅዱስ ያሬድም ይኽንን ቃል በሰማ ጊዜ ወደ ሰማይ ተመልክቶ 'እናንት በሰው አንደበት የምትናገሩ ወፎች ከወዴት መጣችኹ?' አላቸው። እነርሱም መልሰው "ከኤዶም ገነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልከን ከኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ማኅሌትን ትማር ዘንድ ልንነግርኽ መጣን" አሉት። ከዚያም ቅዱሳን መላእክት በዜማ እግዚአብሔርን ወደ ሚያመሰግኑባት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በአካል ተነጠቀ። በዚያም ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን እጅግ ድንቅ በኾነ ሰማያዊ ዜማ ያለማቋረጥ በመንበሩ ዙሪያ ኾነው ሲያመሰግኑት በሰማ ጊዜ ካለበት ሥፍራ ተነሥቶ እነርሱ ወደ አሉበት ቦታ ሊገባ ወደደ። ነገር ግን አልተቻለውም። እነዚያ አዕዋፍም ወደ ርሱ ተመልሰው "ያሬድ ሆይ የሰማኸውን አስተውለኸዋልን?" ብለው ጠየቁት። ርሱም 'አላስተዋልኹም' ብሎ መለሰላቸው። እነርሱም "እንግዲያውስ ዐዲሱን የእግዚአብሔርን ምስጋና ጥራ ርሱም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው" አሉት። ከዚኽም በኋላ ቅዱስ ያሬድ ቅዱሳን መላእክት ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበትን ሰማያዊ ዜማ በአርያም እግዚአብሔር ገልጾለት የመላእክት ሥርዐታቸውን ዐይቶ ማኅሌታቸውን ተምሮ ወደ ቀድሞ ቦታው ተመልሷል። ከዚያም ወደ አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በዐውደ ምሕረቱ ቆሞ ድምጹን ከፍ አድርጎ "ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚ ዜማ" ብሎ በልሳነ ግእዝ አዜመ። ቅዱስ ያሬድ በአካለ ሥጋ ከሰማይ እንደ ተመለሰ ለመዠመሪያ ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ያሰማበት ቦታ "ሙራደ ቃል" እየተባለ ይጠራል። ይኸውም ዜማው ከሰማይ የወረደ ለመኾኑ እሙን ማስረጃ ነው። ቅዱስ ያሬድ በዘመኑ ዜማውን ከፍ አድርጎ በሚያሰማና በሚያዜም ጊዜ ሰው፣ እንስሳትና አዕዋፍ ኹሉ ርሱ ወደ አለበት ቦታ ተሰብስበው ከጣዕሙ የተነሣ መንፈስን የሚያድሰውን፣ ልቡናን ደስ የሚያሰኘውንና አጥንትን የሚያለመልመውን ሰማያዊ ዜማ ይሰሙ ነበር። በዓለም ታሪክም ኾነ በኢትዮጵያ እስከ ቅዱስ ያሬድ ዘመን ድረስ እንደ ዛሬው በከፍተኛ ቃል ድምጽን ከፍ አድርጎ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ዜማ አልነበረም። በትሑት ቃል እንደ ውርድ ንባብ ያለ ብቻ ነበር እንጂ። ቅዱስ ያሬድ በአርያም ከቅዱሳን መላእክት ሰምቶ እግዚአብሔርም ገልጾለት የተማረውን ዜማ በግእዝ፣ በዕዝልና በአራራይ የዜማ ስልቶች እግዚአብሔርን እያመሰገነ የዜማ ድርሰቱንም ከዓመት እስከ ዓመት በየዘመኑ እየከፈለ በክረምትና በበጋ፣ በመጸውና በጸደይ፣ በአጽዋማትና በበዓላት፣ በሰንበታትም እንዲኹም በቅዱሳን መላእክት፣ በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓላት እንዲኾን አድርጎ አዘጋጀ። .... ይቀጥላል
Hammasini ko'rsatish...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ስለ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ - ክፍል አንድ +++++++++++++++++++ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ.ም. ከአባቱ አብዩድ (ይስሐቅ) እና ከእናቱ ታውክልያ (ክርስቲና) በአክሱም ከተማ ተወለደ። ቅዱስ ያሬድ በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ ታውክልያ የአክሱም ገበዝና መምህር ለነበረው ለአጎቱ ጌዲዎን በትምህርትና በዕውቀት እንዲያሳድገውና እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው። ቅዱስ ያሬድ ከአጎቱ ጊዴዎን ዘንድ በዘመኑ የነበረውን የኢትዮጵያውያን ትምህርት መማር እንደ ዠመረ ለብዙ ጊዜያት ትምህርቱን መቀበልም ኾነ መያዝ ተስኖት ነበር። በዚኽም የተነሣ አጎቱና መምህሩ ተበሳጭተው ቅዱስ ያሬድን ገረፉት። ርሱም ከኅዘኑ የተነሣ ቁጣውንና ግርፊያውን መታገስ ስላቃተው ሸሽቶ ሲኼድ 'ማይኪራሕ' በምትባል ሥፍራ ድካመ-ሥጋ ይዞት ከአንዲት ዛፍ ሥር ዐረፍ አለ። በዚያች ዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንድ ነገር ይመለከታል። ይኸውም አንዲት ትል የዛፉን ፍሬ ለመብላት ስትወጣ ስትወድቅ፣ እንደገና ስተወጣ ከዛፉ ጫፍ ደርሳ ስትወድቅ፣ እንዲኽ እንዲኽ እያለች 6 ጊዜ ወድቃ በ7ኛው ከዛፉ ላይ ወጥታ ፍሬውን ስትበላ ተመለከተ። በዚኽም የትሏን ተስፋ አለመቁረጥ ተመልክቶ በትጋቷ ተደንቆ የፈለጉትን መሻት የወደዱትን ማግኘት ያለድካም እንደማይኾን ዐውቆና ተረድቶ ወደ አጎቱ ተመልሶ መምህሬ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝ እንደወደድኽና እንደ ፈቀድኽ አድርገኽ አስተምረኝ አለው። አጎቱም በደስታ ተቀብሎት ያስተምረው ዠመር። ከዚኽ በኋላ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን እየኼደ 'የጌታዬ እናቱ እመቤቴ ሆይ ጥበብና ዕውቀትን የሚገልጽ እግዚአብሔር ነውና ዐይነ ልቡናዬን ያበራልኝ ዘንድ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ለምኝልኝ' እያለ ዘወትር ይጸልይ ነበር። 👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ስለ ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ - ክፍል ኹለት +++++++++++++ ከዕለታት አንድ ቀን ቅዱስ ያሬድ በዘመኑ ከነበረው ከንጉሡ ዐጼ ገብረ መስቀል ፊት ቆሞ ሲዘምር ንጉሡ ከዜማው ጣዕም የተነሣ ቅዱስ ያሬድን እያዳመደ በተመሥጦ ልቡና ሳለ የጦር ዘንግ ከእጁ ወድቆ የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው፤ ቅዱስ ያሬድም ዝማሬውን እስከሚጨርስ ድረስ ሕመሙ ፈጽሞ አልተሰማውም ነበር። ንጉሥ ገብረ መስቀልም የዜማውን ጣዕም ከሰማና ከተረዳ በኋላ እግዚአብሔር በዘመኑ ለቤተ ክርስቲያን መገልገያና ለሕዝቡ መባረኪያ የሰጣቸው መኾኑን በመገንዘብ ሊቃውንቱንና ካህናቱን ሰብስበው "ለቤተ ክርስቲያን መገልገያ ይኹን" ብለው አዘዙ። ካህናቱና ሊቃውንቱም 'ምን ምልክት ዐይተን እንቀበለው' ብለው መለሱለት። ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ይግለጽልን ብለው ከታኅሣሥ አንድ ቀን ዠምሮ እስከ ታኅሣሥ ሰባት ቀን ሱባዔ እንዲያዝ ዐወጁ። ታኅሣሥ አንድ ቀን ሰኞ ዕለት ውሎ ነበርና ከሰኞ እስከ እሑድ አንድ ሱባዔ ይዘው በየቀኑ የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን እየዞሩ አራት መቶ እግዚኦታና አርባ አንድ በእንተ ማርያም እያደረሱ ምሕላ ያዙ። በሰባተኛው ቀን እሑድ ምሕላውን ጨርሰው ሲያሳርጉ ጌታ በዕለተ ዐርብ እንደ ተሰቀለ ኾኖ በቤተ ክርስቲያኑ ጉልላት ላይ ተገለጸላቸው። ቅዱስ ያሬድም ከዚኽ አያይዞ           'ዘበመስቀሉ ተቀነወ ወበነቢያት ተሰብከ መላእክት ወሊቃነ መላእክት ሰብሕዎ ኪያሁ ንሰብክ መድኅነ' ብሎ ነገረ መስቀሉን በማውሳት የወልድ ምሳሌ በኾነው በዕዝል ዜማ ዘመረ። ትርጓሜውም            'በነቢያት ትንቢት የተነገረለትና በመስቀሉ ላይ የተቸነከረውን ጌታ መላእክትና የመላእክት አለቆች አመሰገኑት፤ እኛም ርሱ መድኃኒት እንደ ኾነ እንናገራለን' ማለት ነው። 👇👇👇
Hammasini ko'rsatish...
ብዙዎች በሰርጋቸው ቀን "የአገራችን ባሕል ነው" የዘፈን ድግስን ያዘጋጃሉ። ወይም ደግሞ "ቤተሰብ እሺ አይልም" በማለት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህን የቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ቃል ማስታወስ ይገባል "ጋብቻ ዝሙትን የምናጠፋበት መድኃኒት ነው። ስለዚህ በዲያብሎስ ስራ (በዘፈን) ጋብቻን አናቃልል። ከዚህ ይልቅ አሁን የሚያገቡ ሰዎች በቃና ዘገሊላ እንደ ኾነው ያድርጉ። በመካከላቸው ጌታችን ክርስቶስ እንዲኖር ያድርጉ። "እንዴት ይህን ማድረግ ይችላሉ? ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል። ካህናትን በመጥራት! 'እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል' ይላልና (ማቴ 10:40)። ስለዚህ ዲያብሎስን አርቁት። የሴሰኝነት ዘፈኖችን፣ የርኵሰት ዜማዎችን፣ ሥርዓት የለሽ ጭፈራዎችን፣ የሚያሳፍሩ ቃሎችን፣ ዲያብሎሳዊ ትርኢቶችን፣ ሁከቶችን፣ቅጥ ያጡ ሳቆችን፣ ሌሎች እነዚህን የመሰሉ አግባብ ያይደሉ ነገሮችንም አስወግዱ። በእነዚህ ፈንታም የጌታችን ክርስቶስ ቅዱሳን አገልጋዮችን ጥሩ ፣ በእነርሱም በእውነት ያለ ሐሰት ከእናቱና ከወንድሞቹ ጋር በሰርጋችሁ ላይ ይገኛል። " በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነው" ብሏልና (ማቴ 12:50)። አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ያሉ ተግሣጻትን ስለምናገርና የጥንት ባሕሎችን ስለማስቀር አሰልቺና አስቸጋሪ እንደ ኾንኩ አድርገው እንደሚያስቡ ዐውቃለው። ነገር ግን እነርሱ ስለ ተቃወሙኝ በፍጹም አልጨነቅም። እኔ የምፈልገው በእናንተ ዘንድ ተቀባይነትን ማግኝት ሳይኾን የእናንተን ጥቅም ነውና። ከዚህ ጥበብ ጥቅምን እንድታገኙ እንጂ እንድታመሰግኑኝ አልፈልግምና። ስለዚህ "ይህ ባሕል ነው" ብሎ አንድ ሰውስ እንኳ አይንገረኝ። ኀጢአት በድፍረት የሚፈፀምበት እስከ ኾነ ድረስ ባሕሉን እርሱት። ክፉ ሣራ የሚሰራባቸው እስከ ኾኑ ድረስ ባህሎቹ የቱንም ያህል ጥንታውያን ቢሆኑ ከእናንተ አስወግዷቸው። ክፉ ስራ የማይሰራባቸው ከኾኑ ግን ያልተለመዱ እንኳን ቢሆኑ ተቀበሏቸው።
Hammasini ko'rsatish...
5🙏 3👍 1
+ የሚሮጥ ዲያቆን + የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ዲበ ሠረገላ ሰማይ ለኢጃት ዲያቆናት ሲመት ግንቦት 6 2016 ዓ.ም.
Hammasini ko'rsatish...
🙏 7👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
🙏 7👍 2
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት ርሷንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኘውንም አይ ዘንድ፥መቅደሱንም እመለከት ዘንድ። መዝ 26:4
Hammasini ko'rsatish...
11👍 2🙏 1