cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
342
Obunachilar
-224 soatlar
+47 kunlar
+3530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የተዋሕዶን ምስጢር በምን እንመስለዋለን? የተዋሕዶን ነገር ጠንቅቀው የሚገልጹ ምሳሌዎች ባይገኙም ምስጢሩን ለሰዎች ለማስረዳት ያህል አባቶቻችን ያስተማሩንን ፍጹም ያልሆኑ ምሳሌዎች (ምሳሌ ዘየሐፅፅ፣ ከሚመሰልለት የሚያንስ ምሳሌ) እንጠቀማለን፡፡ የተዋሕዶ ምስጢር ከምሳሌዎች በላይ መሆኑን ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሲናገር “ወልድ ዋሕድ ከአብ መወለዱ እንዴት እንደ ሆነ፣ ከቅድስት ድንግልም መወለዱ እንዴት እንደ ሆነ አትጠይቀኝ፤ እርሱ በባሕርይው ከአብ ተወልዶዋልና፤ ለራሱ በአደረገው ተዋሕዶም ከድንግል ተወልዶዋልና አምላክ ነው፤ ሰውም ነው” ብሏል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎዶጦስ 53፡16) ቅዱስ ኤፍሬምም “ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል፤ ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው፣ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ፤ ከእርሷም እርሱ ፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም 47፡2) በማለት እንደተናገረው የተዋሕዶ ነገር ከምሳሌዎች በላይ እጅግ ድንቅ ነው፡፡እነዚህም ምሳሌዎች ከቅዱሳት መጻሕፍትና ከሥነ ፍጥረት የተገኙ ናቸው፡፡ ሙሴ ባያት ዕፀ ጳጦስ:-  ሐመልማሉ የትስብእት ምሳሌ ነበልባሉ የመለኮት ምሳሌ ነው፡፡ ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው ሐመልማሉ ነበልባሉን ሳያጠፋው በአንድነት ታይተዋል (ዘፀ 3:2)፡፡ አንዱ አንዱን ሳያጠፋ እንደታዩ ሥጋ ከመለኮት ጋር ሳይጠፋፉ አንድ የመሆናቸው ምሳሌ ነው፡፡ በኢሳይያስ ፍሕም:  ምሳሌነት ደግሞ እሳት የመለኮት ከሰል የሥጋ ምሳሌ ናቸው፡፡ እሳቱ ተለውጦ ከሰል ፤ ከሰሉ ተለውጦ እሳት አልሆነም፡፡ ሁለቱም ከሰል ከሰልነቱን እሳትም እሳትነቱን ሳይለቅ ተዋሕደው ፍሕም ሆነዋል (ኢሳ 6:6)፡፡ የጋለ ብረት ምሳሌነት፡- አንድን ብረት ከእሳት ባስገቡት ጊዜ ብረትነቱን ሳይለቅ እሳቱም እሳትነቱን ሳይለቅ በብረቱ ቅርፅ ልክ እሳት ይሆናል፡፡ ይህንንም እሳትና ብረቱ ስለተዋሐዱ የጋለ ብረት ብለን እንጠራዋለን እንጂ ብረት ወይም እሳት ብቻ ብለን አንጠራውም፡፡  ይሁንና ብረት እሳት ሲነካው በቀላሉ ስለሚቀጠቀጥ ይህ “ምሳሌ ዘየሐፅፅ” ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ስለዚህ ምሳሌ ሲናገር “በእግዚአብሔር ቃል በረቂቅ ባሕርይ የሆነውን ተዋሕዶ አንካድ፤ ብረት ከእሳት በተዋሐደ ጊዜ ከእሳትም በመዋሐዱ የእሳትን ባሕርይ ገንዘብ እንዲያደርግ፤ ብረት በመዶሻ በተመታ ጊዜ ከእሳት ጋር በአንድነት እንደሚመታ ግን ከመዶሻው የተነሣ የእሳት ባሕርይ በምንም በምን እንዳይጎዳ ሰው የሆነ አምላክ ቃል በመለኮቱ ሕማም ሳይኖርበት በሥጋ እንደታመመ እንዲህ እናስተውል፡፡” ብሏል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ 73፡12) የሰው ነፍስና ሥጋ ውሕደት ምሳሌ፡- የሰው ልጅ ከእናቱ ማሕፀን ሥጋና ነፍስን ነስቶ ፅንስ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ይህ ነፍስ ነው ይህ ሥጋ ነው ብሎ መለያየት እንደማይቻል ሁሉ ሥጋና መለኮትም ከተዋሕዶ በኋላ ይህ ሥጋ ነው ይህ መለኮት ነው፤ ይህ ሥጋዊ ሥራ ነው ይህ መለኮታዊ ሥራ ነው ተብሎ መክፈል አይቻልም፡፡ ነገር ግን ነፍስና ሥጋ በሞት ስለሚለያዩ ይህም “ምሳሌ ዘየሐፅፅ” ነው፡፡ http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
22/10/2016                    የዕለቱ የወንጌል ክፍል                     ማቴዎስ 5:39-ፍጻሜ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል። ‘ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።” 1 ቆሮንጦስ 5:6-ፍጻሜ ያዕቆብ 5:14-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ13:44-ፍጻሜ                  ምስባክ               መዝሙር 36:7-8 ወኢትቅናዕ ላዕለ ዘይዴሎ በሕይወቱ ወላዕለ ሰብእ ዘይገብር ዓመፃ ኅድጋ ለመዓት ወግድፋ ለቁጥዓ http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
📌 ቅዱሳን ስእል ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ማነው❓ 📌 የቅዱሳን ስእሎች ጥቅም ምንድን ነው❓ 📌 በቅዱሳን ስእል ፊት ለምን እንፀልያለን❓
ስእል ከእግዚአብሔር ጋር የተያያዘና በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ያለ ነው ስእል በእግዚአብሔር ፊት የተሠጠ ሕግ ነው። ስእል በብሉይ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ነብዩ ሙሴ ነው። ስርየት መክደኛውም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታደርገዋለህ በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ (ዘጸ 25:21-22) በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ በኪሩቤል ናዘንባባ የፈነዳ አበባ ምስል ቀረፀ (1 ነገ 6:29) ሠለሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሱን ቤት ጨረሠ በእግዚአብሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠራው ዘንድ በልብ ያሰበውን ሁሉ አከናወነ እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው ፀሎትህን ሰምቻለሁ ይህም ስፍራ ለራሴ ለመስዋት ቤት መርጫለሁ (2 ዜና 7:11-12) እግዚአብሔር ስእሉን መቀበሉን ያሳያል።። አንተ የሰው ልጅ ሆይ ጡቡን ወስደህ በፊትህ አኑረው የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት ምሽግም ስራባት ይህም የእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል (ሕዝ 4:1-3) ስእል በሐዲስ ኪዳን ለሀዲስ ኪዳን ስዕል መሠረቱ ብሉይ ኪዳን ነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ ሠላሳ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር በዚች ምድር በተመላለሰ ጊዜ ስዕል ኪሩቤል ባለበት ቤተ መቅደስ የተለየበት ጊዜ አልነበረም ዕለት ዕለት ሥዕለ ኪሩብ ባለበት ቤተ መቅደስ ተገኝቶ አስተምሯል። (ማቴ 26:55) ቤተ መቅደስም የአባቴ ቤት ብሎታል (ዮሐ 2:16) ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው (ማቴ 21:12-3) በሽተኞችን በመቅደስ ውስጥ ተገኝቶ ፈውሶዋቸዋል (ማቴ 21:14) ይህ ሁሉ የተደረገው ስዕለ ኪሩቤል ያለበት መቅደስ ውስጥ ነው። ባያስፈልግ ኖሮ ሥዕሎቹ አግባብ እንዳልሆኑ ባመለከታቸው ነበር። ገንዘብ ለዋጮችን ገበታዎችን የርግብ ሻጮችን ወንበር ገልብጦ ከቤተ መቅደስ ባስወጣ ጊዜ ሥዕል ባስወጣ ነበር። ማታስተውሉ የገላቲያ ሰዎች ሆኖ በዓይኖቹ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሰቅሎ ነበር (ገላ ፣3:1) ቅዱሳን ስዕላት ጥቅሙ ለትምህርተ ወንጌል ይጠቅማል ማንበብ መስማት የማይችሉ ሰዎች ስእሉን ተመልክተው መማር ይችላሉ። ለምሳሌ የጌታችን ብስራቱን፣ ልደቱን ፣ ጥምቀቱን፣ ተአምራቱን ፣ መከራ መሰቀሉን ፣ ርደተ መቃብሩን ፣ ትንሣኤውን ፣ እርገቱን ፣ ዳግም ምፃቱን የሚያመለክቱ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ስዕላት ማስተማሪያ ብቻ አይደሉም ልክ እንደ በትረ ሙሴ እንደ ኤልያስ መጎናፀፊያ እንደ ኤልያስ ቅርፊት እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የልብስ ቁራጭ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስም ጥላ የሀይለ እግዚአብሔር መገለጫዎች ናቸው። በቅዱሳን ስዕል ፊት ለምን እንፀልያለን? በስዕል ፊት ቆሞ መፀለይና መስገድ ስዕሉን አምላክ ነው ብሎ ማምለክ ሳይሆን ለስዕሉ ባለቤት ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽና በረከት ለማግኘት ነው እግዚአብሔር በኦሪት አትስገዱላቸው ያለው ለአህዛብ ጣዖታት ምስሎች ነው እንጂ ለቅዱሳን ስዕላት አለመሆኑን (ዘውልቅ 16:45) ,ሙሴና አሮን ወደመገናኛው ድንኳን መጥተው በታቦትና በስዕል ኪሩብ ፊት እየሰገዱ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ይቀበሉ እንደነበርና የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥላቸው እንደ ነበር እናያለን ስለዚህ ለቅዱሳን ስዕል ክብር ልንሰጥ ይገባል አንዳንዶቹ ስዕል የምናመልክ የሚመስላቸው አሉ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል (2 ጢሞ 1:12) እኔ ግን አላፍርም ያመንኩትን አውቀዋለሁ ይላል። ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂ http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
📌 ቅዱሳን ስእል ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ማነው❓ 📌 የቅዱሳን ስእሎች ጥቅም ምንድን ነው❓ 📌 በቅዱሳን ስእል ፊት ለምን እንፀልያለን❓
ስእል ከእግዚአብሔር ጋር የተያያዘና በብሉይም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ያለ ነው ስእል በእግዚአብሔር ፊት የተሠጠ ሕግ ነው። ስእል በብሉይ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የሳለው ነብዩ ሙሴ ነው። ስርየት መክደኛውም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታደርገዋለህ በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ (ዘጸ 25:21-22) በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ በኪሩቤል ናዘንባባ የፈነዳ አበባ ምስል ቀረፀ (1 ነገ 6:29) ሠለሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሱን ቤት ጨረሠ በእግዚአብሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠራው ዘንድ በልብ ያሰበውን ሁሉ አከናወነ እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው ፀሎትህን ሰምቻለሁ ይህም ስፍራ ለራሴ ለመስዋት ቤት መርጫለሁ (2 ዜና 7:11-12) እግዚአብሔር ስእሉን መቀበሉን ያሳያል።። አንተ የሰው ልጅ ሆይ ጡቡን ወስደህ በፊትህ አኑረው የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት ምሽግም ስራባት ይህም የእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል (ሕዝ 4:1-3) ስእል በሐዲስ ኪዳን ለሀዲስ ኪዳን ስዕል መሠረቱ ብሉይ ኪዳን ነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ ሠላሳ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር በዚች ምድር በተመላለሰ ጊዜ ስዕል ኪሩቤል ባለበት ቤተ መቅደስ የተለየበት ጊዜ አልነበረም ዕለት ዕለት ሥዕለ ኪሩብ ባለበት ቤተ መቅደስ ተገኝቶ አስተምሯል። (ማቴ 26:55) ቤተ መቅደስም የአባቴ ቤት ብሎታል (ዮሐ 2:16) ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው (ማቴ 21:12-3) በሽተኞችን በመቅደስ ውስጥ ተገኝቶ ፈውሶዋቸዋል (ማቴ 21:14) ይህ ሁሉ የተደረገው ስዕለ ኪሩቤል ያለበት መቅደስ ውስጥ ነው። ባያስፈልግ ኖሮ ሥዕሎቹ አግባብ እንዳልሆኑ ባመለከታቸው ነበር። ገንዘብ ለዋጮችን ገበታዎችን የርግብ ሻጮችን ወንበር ገልብጦ ከቤተ መቅደስ ባስወጣ ጊዜ ሥዕል ባስወጣ ነበር። ማታስተውሉ የገላቲያ ሰዎች ሆኖ በዓይኖቹ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሰቅሎ ነበር (ገላ ፣3:1) ቅዱሳን ስዕላት ጥቅሙ ለትምህርተ ወንጌል ይጠቅማል ማንበብ መስማት የማይችሉ ሰዎች ስእሉን ተመልክተው መማር ይችላሉ። ለምሳሌ የጌታችን ብስራቱን፣ ልደቱን ፣ ጥምቀቱን፣ ተአምራቱን ፣ መከራ መሰቀሉን ፣ ርደተ መቃብሩን ፣ ትንሣኤውን ፣ እርገቱን ፣ ዳግም ምፃቱን የሚያመለክቱ ናቸው። በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ስዕላት ማስተማሪያ ብቻ አይደሉም ልክ እንደ በትረ ሙሴ እንደ ኤልያስ መጎናፀፊያ እንደ ኤልያስ ቅርፊት እንደ ቅዱስ ጳውሎስ የልብስ ቁራጭ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስም ጥላ የሀይለ እግዚአብሔር መገለጫዎች ናቸው። በቅዱሳን ስዕል ፊት ለምን እንፀልያለን? በስዕል ፊት ቆሞ መፀለይና መስገድ ስዕሉን አምላክ ነው ብሎ ማምለክ ሳይሆን ለስዕሉ ባለቤት ያለንን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽና በረከት ለማግኘት ነው እግዚአብሔር በኦሪት አትስገዱላቸው ያለው ለአህዛብ ጣዖታት ምስሎች ነው እንጂ ለቅዱሳን ስዕላት አለመሆኑን (ዘውልቅ 16:45) ,ሙሴና አሮን ወደመገናኛው ድንኳን መጥተው በታቦትና በስዕል ኪሩብ ፊት እየሰገዱ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ይቀበሉ እንደነበርና የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥላቸው እንደ ነበር እናያለን ስለዚህ ለቅዱሳን ስዕል ክብር ልንሰጥ ይገባል አንዳንዶቹ ስዕል የምናመልክ የሚመስላቸው አሉ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል (2 ጢሞ 1:12) እኔ ግን አላፍርም ያመንኩትን አውቀዋለሁ ይላል። ꧁  ይ🀄 ላ 🀄ሉ ꧂ http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

መንፈሳዊ ቻናል እንጋብዛቹ @EOTCY ምን አይነት ነገሮችን ነው የሚፈልጉት? ➢ የተለያዩ ትምህርቶችን ➢ መጣጥፎችን ➢ መንፈሳዊ ግጥሞችን ➢ ተከታታይ ትምህርቶችን ➢ ብሒለ አበው ➢ ወይስ ዜና ቤተክርስቲያን አሁኑኑ ይቀላቀሉን የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቀጥተኛ አስተምህሮ ያገኙበታል👇👇👇 @EOTCY

🕊 [  † እንኳን ለቅዱሱ አባታችን የዋህ ዻውሊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †   ] †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  †  ቅዱስ ዻውሎስ የዋህ  †  🕊 † በ፬ [ 4 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ግብፅ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ቅዱሱ ስሙ ዻውሎስ ቢሆንም ብዙ ጊዜ የሚጠራው "የዋህ ዻውሊ" በሚል ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- የዋህ ዻውሊ ከሕጻንነቱ ጀምሮ መጻሕፍትን የተማረ: ግን ደግሞ ትዕቢት: ቁጣና ቂምን የማያውቅ ገራገር ሰው ነው:: እድሜው ለአካለ መጠን ሲደርስ ቤተሰቦቹ ሚስት አግባ አሉት:: እርሱ ባያስብበትም ወገኖቹን ላለማሳዘን አገባ:: እንዳለመታደል ሆኖ ግን ያገባት ሴት በጣም ቆንጆ በዚያም ላይ ክፉ ነበረች:: የዋህ ዻውሊ ክፋቷን ሁሉ ታግሶ ለበርካታ ዓመታት አብሮ ኖረ:: ልጆችንም አፈሩ:: አሁንም ግን እርሷ ከክፋቷ ልትታገስ አልቻለችም:: ይባስ ብሎ ዻውሊ በሌለበት ከሌሎች ወንዶች ጋር ትዘሙት ያዘች:: የዋሁ ሰው ይሕንኑ ያውቃል ግን የእግዚአብሔርን ሥራ ዝም ብሎ በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ለነገሩስ እሱ ያርሳል: ይቆፍራል: ነዳያንን ያበላል: እንግዳ ይቀበላል እንጂ ክፋትን ለማሰብ ጊዜ አልነበረውም:: አንድ ቀን ግን ለሥራ ወደ በርሃ ወጥቶ አንድ ግሩም ዜና ሰማ:: "አባ እንጦንስ ምንኩስና የሚባል ሕይወተ መላእክትን ጀምሯል: ደቀ መዛሙርትንም ይቀበላል" አሉት:: ግን ሚስትና ልጆች አሉትና ምን ያደርጋል? የዋህ ዻውሊ ሙሉ ቀን ሢሠራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ ግን የጠበቀው ሌላ ነው:: ሚስቱ በራሱ መኝታ ላይ ከአገልጋይ እረኛው ጋር ራቁታቸውን አገኛቸው:: ልብ በሉልኝ በትክሻው ሞፈርና ምሳር: መጥረቢያም ይዟል:: እርሱ ግን ክፉን አላሰበም:: ጥሩ ልብስ አንስቶ ሁለቱንም አለበሳቸው:: እንዲሕም አላቸው:- "ከዚሕ በሁዋላ እኔ አልመለስም:: ሀብት ንብረቴን ውረሱ: በደስታም ኑሩ:: የልጆቼን ነገር ግን አደራ" ብሏቸው ተነሳ:: በእጁ ምንም አልያዘም:: በትከሻው ያለችውን ብጣሽ ጨርቅ ይዞ ወደ በርሀ ተጉዋዘ:: አባ እንጦንስም ተቀብለው አስተምረው አመነኮሱት:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ራስን ዝቅ በማድረግ: በመታዘዝ አገለገለ:: ጾም: ጸሎትና ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት:: እያለ እያለ ከብቅዐት ማዕርግ ደረሰ:: ምዕመናንም ሆነ መነኮሳት ሊጠይቁት ሲመጡ የእያንዳንዱ ኃጢአት በግንባራቸው ተጽፎ ይመለከት ነበርና ስለነሱ ሲያለቅስ ቅንድቡ ተላጠ:: ሰውነቱም አለቀ:: አንድ ቀን ጋኔን የያዘውን ሰው ፈውስ ብለው አመጡለት:: እርሱ ግን በአጋንንት ላይ ሥልጣን እያለው በትሕትና ተጠግቶ ጋኔኑን "አባ እንጦንስን ከምጠራብህ ቀስ ብለህ ውጣ" አለው:: ጋኔኑ ግን የፈራው መስሎት በትዕቢት "እንጦንስ ማነው?" አለው:: ያን ጊዜ የዋህ ዻውሊ እንደ እሳት ከጋለ ድንጋይ ላይ ቁሞ "ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው:: ይሕ ጋኔን ካልወጣ አልወርድም" አለ:: ወዲያው በዘንዶ አምሳል ከሴትዮዋ ወጥቶ እየጮኸ ወደ ቀይ ባሕር ገባ:: ቅዱስ ዻውሊ የዋሕም እንዲሕ በቅድስና ተመላልሶ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል:: " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር: ደስታ: ሰላም: ትእግስት: ቸርነት: በጐነት: እምነት: የውሃት: ራስን መግዛት ነው:: እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም:: የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ::" [ገላ.፭፥፳፪] (5:22) 🕊 [  † ሰኔ ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. ቅዱስ አባ ዻውሊ የዋሕ ፪. ቅዱሳን ወክቡራን ቆዝሞስና ድምያኖስ [ ሰማዕታት ] ፫. ቅድስት ቴዎዳዳ ሰማዕት [ እናታቸው ] ፬. አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ [ ሰማዕታት ] [   †  ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [ የእመቤታችን ወዳጅ ] ፬. አባ እንጦንዮስ [ አበ መነኮሳት ] [  † አምላካችን ከቅዱስ ዻውሊ የውሃትን: ትእግስትን : በጐነትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን:: አሜን:: †  ] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " የድካም ዓይነቶችና መፍትሔው !  " [    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ ፊትህን ከእኔ አትሰውር ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል ፤ ረዳት ሁነኝ ፥ አትጣለኝም ፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ ፥ አትተውኝ። ❞ [  መዝ . ፳፯ ፥ ፱  ] ❝ ምንም እንኳ የማልጠቅምና ሀጢያተኛ ብሆንም ያለማቋረጥ ደጆችህን አንኳኳለሁ፡፡ ❞ [  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  ] 🕊                        💖                     🕊                              👇 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችና ትርጓሜያቸው ✝️ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ክፍሎች ያሏት ሲሆን እነዚህም ቅኔ ማኅሌት፣ ቅድስትና መቅደስ በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፍሎች ክፍሎቿም ጎልተው የሚታዩት በክብ ቅርጽ በታነፀ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎችም ሦስት የሆኑበት ምክንያት አንደኛው በሦስቱ ዓለማተ መላእክት ማለትም በኢዮር፣በራማ፣በኤረር ምሳሌ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሦስቱ መዓረጋት ክህነት ዲቁና፣ቅስና፣ኤጲስቆጶሳት ምሳሌ ሲሆን በሦስቱ ጾታ ምእመናን፡ ማለትም ካህናት፣ ወንዶች፣ ሴቶች የሦስቱ ኆኅተ ገነት (የገነት በሮች) ምሳሌም በመሆኑ ነው፡፡ አገልግሎታቸው ፦ ፩. ቅኔ ማኅሌት በዚህ ክፍል ውስጥ መዘምራን፣ ደባትር ካህናት ማኅሌተ እግዚአብሔር ያደርሱበታል፡፡ በመስዕ (ሰሜን ምሥራቅ) ንዑሰ ማዕዘን በኩል ቀሳውስትና ዲያቆናት በመንፈቀ ሌሊት ሰዓታት በነግህ ኪዳን ያደርሱበታል፤ ለጥምቀት ለቊርባን ያልበቁ በትምህርት በንስሓ የሚፈተኑ /ንዑሰ ክርስቲያን/ ‹‹ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን›› እስከሚባል ድረስ የሚቆዩበት ክፍልም ነው፤ ወንዶች ምእመናንም ቆመው ያስቀድሱበታል፤ በሌብ /ደቡብ ምሥራቅ/ ንዑስ ማእዘን በኩል የሚገኘው ቦታ የሴቶች መቆሚያ ነው፡፡ ከውጭ ወደ ቤተ መቅደስ ስንገባ የምናገኘው የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ሦስት በሮችም አሉት፤ የካህናት፣ የወንዶችና የሴቶች ምእመናት መግቢያዎች ናቸው፡፡ ፪.ቅድስት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ ክፍል ቅድስት ይባላል፡፡ ካህናት በድርገት ጊዜ ምእመናንን የሚያቆርቡበት ክፍል ሲሆን በስብከተ ወንጌል ጊዜም መምህራን ቆመው ያስተምሩበታል ክፍል፡፡ በተክሊልና በቊርባን አንድ ለሚሆኑ ሙሽሮች ጸሎት የሚደርስበትና በካህናት እጅ የሚባረኩበት በዚህ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ በስቅለት ዕለት ሥርዓተ ጸሎት ይፈጸምበታል፤ በምዕራብ በኩል ቆሞሳት፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት ይቆሙበታል፤ በሰሜን መነኮሳትና የሚቈርቡ ወንዶች ምእመናን ይቆሙበታል፤ በደቡብ የሚቆሙት ደናግል መነኮሳይያት፣ የቀሳውስትና የዲያቆናት ሚስቶች ናቸው፤ በምሥራቅ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ዐራት በሮች ይኖሩታል፤  ነገር ግን የማይቆርቡ ምእመናን በዚህ ክፍል ቆመው አያስቀድሱም፡፡ ፫.መቅደስ በብሉይ ኪዳን ቅድስተ ቅዱሳን በሚል ስያሜ ይጠራ የነበረው የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚገኝበት ክፍል መቅደስ ነው፡፡ ንዋያተ ቅድሳትም ከመንበረ ታቦቱ ጋር በዚህ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ ሦስት በሮች ሲኖሩት እያንዳንዱ በር በመንጦላዕት ወይም በመጋረጃ የሚጋረድ ነው፡፡ ከዲያቆናትና ሥልጣነ ክህነት ካላቸው በቀር ወደ መቅደሱ ማንም መግባት አይችልም፡፡ በዚህ ክፍል ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት ቆመው ያስቀድሱበታል፤ የጌታችን ሥጋና ደም የሚፈተተው በዚሁ ክፍል ውስጥ ነው፡፡ 💒 እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም ያድርግልን ለሁላችሁም ቃለ ሕይወት ቃለ በረከት ያሰማልን ተስፋ ርእሰ መንግስተ ሰማያት ያውርስልን🙏 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
#ዝክረ_ቅዱሳን_ሰኔ_22 (ስንክሳር)
እንኳን ለከበሩ #ለቅዱሳን_የቆዝሞስና_የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው ቤተ ክርስቲያናቸውም ለከበረችበት፣ ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ ለነበረው #ለየዋህ_ጳውሎስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ቅዱሳን_ቆዝሞስ_ወድምያኖስ
-  ሰኔ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን የከበሩ ቅዱሳን የቆዝሞስና የድምያኖስ የእናታቸውና የወንድሞቻቸው የበዓላቸው መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያናቸውም የከበረችበት ተአምራታቸውም የተገለጠበት ነው። - እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዎዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ዶኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ። - ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ። ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምእመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም የንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው አጋግዩስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ። - ቆዝሞስና ድምያኖስ በሀገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደርሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበትም ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ አስመጣቸውና አምስቱንም በመኰራኲር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨመሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳትን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው። - መኰንኑም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች። - በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትንት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብሎ ጮኸ የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት። - ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።#ቅዱስ_አባ_ጳውሊ_የዋሕ (ስንክሳር) - በዚህችም ዕለት ለመነኰሳት መጀመሪያቸው ለሆነ ለከበረ እንጦንስ ረድእ የነበረው የዋህ ጳውሎስ አረፈ። ይህም ጳውሎስ በረኸኛና እጅግ የዋህ ነበረ ደም ግባቷ ውብ ሥራዋ ግን ክፉ የሆነ ሚስት አገባ ከእርሱም ልጆችን ወለደች። - በአንዲትም ቀን ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ከሎሌው ጋራ ስታመነዝር አገኛት በአያቸውም ጊዜ ሣቀ ያንን ሎሌውንም ከልጆቿ ከቤቷና ከንብረቷ ጋራ ውሰዳት እኔ ምንም አላዝንም እግዚአብሔርም ወደ ፈቀደልኝ እሔዳለሁ አለው። - ከዚህም በኋላ ወጥቶ ወደ አባ እንጦንስ ሒዶ የምንኵስና ልብስ ለበሰ የአባ እንጦንስንም ሥራ ተከተለ። በደዌያትና በሰይጣናት ላይ ጸጋና ኃይል እስከተሰጠው ድረስ በጾምና በጸሎት ተጋደለ። - በአንዲት ዕለትም ጋኔን የያዘውን ሰው ያድነው ዘንድ ወደ አባ እንጦንስ አመጡ። አባ እንጦንስም ይፈውሰው ዘንድ ረድኡ ጳውሊን አዘዘው ጳውሊም ጋኔናሙን ሰው ወስዶ አባቴ እንጦንስ ውጣ ይልሃል አለው ሰይጣኑ ግን መውጣትን እምቢ አለ። እርሱንም እንጦንስንም ተሳደበ። ጳውሊም ካልወጣህስ ለእንጦንስ እነግረዋለሁ እንደሚቀጣህም ታያለህ አለ። - ይህንንም ብሎ በቀትር ጊዜ ወጥቶ ፀሐይ በአጋለው ደንጊያ ላይ ቁሞ ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው እስኪድን ድረስ ከዚህ አለት እንዳልወርድ እንዳልበላና እንዳልጠጣ ሕያው እግዚአብሔርን አለ። - በዚያንም ጊዜ ጋኔኑ ጮኸ በታላቅ ዘንዶ አምሳልም ከሰውዬው ላይ ወጥቶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ገባ። ይህም የዋህ ጳውሊ የሰዎችን ሥራ ሁሉ እያየ ስለ ኃጥአን ያለቅስ ነበር ስለ እነርሱም ይማልድ ነበር። በመልካም እርጅናም በሰላም አረፈ። - ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። #ስንክሳር ሰኔ 22 http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
"ለዛቲ ቤት አነጻ ወልድ፤ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ።" ​​​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! ሰኔ 20 እና 21 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸችው በዛሬዋ ቀን ነው፤ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...
​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። #ሰኔ_20_እና_21 👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች። ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን! http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780http://t.me/tewahdo2780❤https://t.me/tewahdo2780
Hammasini ko'rsatish...

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.