cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ስብከት | ORTHODOX SIBKET

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶችን በሥርዓተ ቤተከርስቲያን ለማነጽ ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው የስነልቦና ማማከር ከፈለጉ በ @binigirmachew ላይ ያናግሩን

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
16 271
Obunachilar
+324 soatlar
+337 kunlar
+10630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አዎ እርሱ ተነሥቷል እኛም እንነሣለን ። ከሞት በፊት የሚያውቁትን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በኋላም አውቀውታልና እኛም በሰማይ እንተዋወቃለን ። በትንሣኤ አካል እንከን የለም ። ዛሬ ዓይኑ የታወረ ፣ እግሩ የሚያነክስ በትንሣኤ አካል ሙሉ ነው ። የማይታየው አብን ወልድ እንደ ተረከው ክርስቶስም ወደ ረቂቅ ግዛቱ ሲገባ ሐዋርያት ተረኩት ። እንዲተረክልን እንሰወር ። ተፈጸመ
Hammasini ko'rsatish...
👍 16 7🙏 7
በተዘጋው የሚመጣ /4/  “ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት ፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ፥ ኢየሱስ መጣ ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው ።” /ዮሐ. 20፡19 ።/ ሦስት ዓይነት መሰባሰቦች እንዳሉ እናያለን ። ደቀ መዛሙርት በምሴተ ሐሙስ ፣ በሰንበት ፣ በእሁድ ምሽት የተሰባሰቡት መሰባሰብ ልዩ ልዩ ፍቺ አለው ። በምሴተ ሐሙስ ክርስቶስ መምህረ ፍቅር ወትሕትና ሁኖ ኪዳን ያደረጉበት ነው ። ሰንበት ሕግን በማክበር አንድ ላይ የሆኑበት ነው ። እሁድ ምሽት በፍርሃት ብርድ ተመትተው እንዲሞቃቸው የተጠጋጉበት ነው ። ከመከራ ሰዓቶች በፊት አስደናቂ ኅብረቶች ይታያሉ ። የክርስቶስን ፍቅር የሚካፈሉበት ፣ ትሕትናን እንደ ልብስ የሚታጠቁበት ውብ ጊዜዎች ያልፋሉ ። ይህን ኅብረት አንዳንድ ጊዜ መከራ ያፈርሰዋል ። መከራው የክርስቶስ ፣ ፈተናው ግን የደቀ መዛሙርቱ ነበረ ። እርሱ መከራ ለተቀበለ እነርሱ ተናወጡ ። እኛ ለተጎዳን ሰዎች መራቃቸውና መለወጣቸው ይገርመን ይሆናል ። በጌታችን የሆነውም ይህ ነው ። ሰንበት የሰበሰባቸው ሕግን መተላለፍ ስለማይችሉ ነው ። ሰንበትን የተላለፈ ታላቅ ቅጣት ይገጥመው ነበር ። የሕግ ቅንዓት የሚሰበስበው ኅብረት አለ ። ይቀጣ ፣  ይወገዝ ፣ ይወገድ ፣ ይወገር የሚሉ አንቀጾች አንድ የሚያደርጉአቸው ፣ በሌሎች ለመፍረድ የሚሰባሰብ ሸንጎ አለ ። ይህ ኅብረት ሰንበት ሲያልፍና መውጣት ሲቻል ይበተናል ። ጉዳያቸው ያሰባሰባቸው ጉዳያቸው ሲሞላ ይለያያሉ ። ድንበር ላይ የሚሰባሰቡ ድንበሩ ሲከፈት ይለያያሉ ። ሌላውን ለማጥፋት የሚሰባሰቡ በመጨረሻ ይጠፋሉ ። የእሑድ ስብስብም ፍርሃት የወለደው ስብስብ ነበር ። ብርድ ሲያንቀጠቅጠን እርስ በርስ እንጠጋጋለን ። የጋራ ችግርና ፍርሃት አንድ የሚያደርጋቸው ሰዎች አሉ ። እውነተኛ ኅብረት ግን በክርስቶስ ፍቅር ተማርኮ ፣ በክርስቶስ ትሕትና ለመኖር የሚፈልግ ነው ። ለክርስቶስ ብዙ የሚጋደሉ ፣ እስከ ሞት ድረስም አብረውት የሚቆሙ የሚመስላቸው ደቀ መዛሙርት ስሜታቸውና እውነታቸው ተለያየ ። የተሰማን ሁሉ ቢሆን ጠቃሚም ጎጂም ነው ። ስሜት የእርግጠኛ ጉዳትና የአጠራጣሪ ጥቅም መገኛ ነው ። ብናገኝ ወርቅ የምናለብሳቸው የሚመስለን ሰዎች አሉ ። ስናገኝ ትዝ አይሉንም ። ስንሾም አማካሪ የምናደርጋቸው የሚመስሉን ሰዎች አሉ ። ስንሾም እንደ ተቀናቃኝ እናያቸዋለን ። ጊዜውን ስንቀበል በቅን እንደምንፈርድ እናስባለን ። ጊዜን ስንቀበል ግን ቅንቅን እንሆናለን ። ወዳጃችን ቢነካ ከፊት ለፊቱ ቆመን፡- “እኔን በመጀመሪያ ግደሉኝ” የምንል ይመስለናል ። ወዳጃችን ሲነካ ግን፡- “ይህ ዓለም ለደጎች አይሆንም” እያልን ሹልክ እንላለን ። ስለራሳችን ያለን ከፍ ያለ ግምትና ስለ ሰዎች ያለን ዝቅ ያለ ግምት በትንሣኤው መነጽር መስተካከል አለበት ። ስንት ዘመን ተፈትነን ቀለን ተገኘን ? ጎረቤታችን ተርቦ መቼ አካፈልነው ?  የምንወደው ሰው ታሞ መቼ ጠየቅነው ? የሥራ ባልደረባችን ታስሮ መቼ ጎበኘነው ? በልጅነታችን በጣም ይወደን የነበረውን ያንን ሽማግሌ መቼ አሁን ፍቅር ሰጠነው ? እርሳስ የገዙልንን መቼ አስታወስናቸው ? ቃለ እግዚአብሔርን ያስተማሩንን መምህራን መቼ እግዚአብሔር ይስጥልኝ አልናቸው ? መስቀሉ ዛሬም አለ ። ትንሣኤም ዛሬ አለ ። መስቀል መሆንና መስቀል መሸከም ግን ልዩነት አለው። ለሌሎች መከራ መሆንና የሌሎችን መከራ መካፈል ልዩነት አለው ። ብዙ ብናበላ ብዙ የሚደርስልን ወገን የምናገኝ ይመስለናል ። ይህ ፍጹም የተሳሳተ ግምት ነው ። ዓርብ ሲመጣ የበሉ አይገኙም ። እንዲሁ ደግ እንሁን እንጂ ለዓርብ/ለመከራ ቀን እያልን ገንዘባችንን አንጨርስ ። ዓርብ ሲመጣ እስከ መስቀል የሚጓዙ ወዳጆች ብቅ ይላሉ ። እነዚህ የማይፎክሩት እመቤታችንና ዮሐንስ ወንጌላዊን የሚመስሉ ናቸው ። በሩቅ የሚከተሉ ከኅሊና ክስና ከልብ ፍቅር ጋር የሚታገሉ ጴጥሮሶች አሉ ። ገበያ ከተገኘ የማይሸጥ የለም ብለው እንደ ይሁዳ የሚሸጡንም አሉ ። “መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል” እንዲሉ ። ሰንበት የበለጠ ቁጭ ያደርጋል ። የሮጠም የበረረም የግድ መቀመጡ አይቀርም ። መቀመጥና ማረፍ ግን ልዩነት አለው ። መቀመጥ በሕግ ፣ ማረፍ ግን በክርስቶስ ነው ። ዓርብ ምሽት የገባው ሰንበት ቁጭ ባያደርጋቸው ኖሮ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሩሳሌምን ለቀው ፣ ድንበርም ጥሰው ደማስቆ ይገኙ ነበር ። እስከ መጨረሻው እንዳንቀል እግዚአብሔር ሰንበትን ያመጣል ። እሑድ ጠዋት ጉዞ እንዳይጀምሩ መግደላዊት ማርያምን ላከባቸው ። ክህደትን ያልጀመረ የለም ፤ ያልጨረሰ እንጂ ። የሕይወት ሰንበት ሲመጣ ማለት በእስር ቤት ፣ በአልጋ ፣ በማጣት ፣ በብቸኝነት ስናሳልፍ ጨርሰን እንዳንጠፋ መጠበቂያ ነው ። እግዚአብሔር ምሽትን እያመጣ ሰውን ባይሰበስበው ኑሮ ስንቱ እቤቱ ሳይገባ ያረጅ ነበር ። ብቻ ዕድሜአችን ሲገፋ ዓለምን ለማትረፍ ክርስቶስን መካድ ከንቱ መሆኑን እንረዳለን ። ቅዱሳን ሐዋርያት አይሁድን በጣም ፈርተው ነበረ ። አይሁድ እነርሱን እንዳይፈልጉም ክርስቶስ ቤዛ ሁኖላቸዋል ። ጨካኞች እኛን የማይፈልጉን ለእኛ ቤዛ የሆኑ ሰዎች ስላሉ ነው ። ያለ ቤዛ መኖር ይቅርና መዋል አይቻልም ። ተክሉ ተቆርጦ ሲቀቀል እኛን ለማጥገብ ነው ። ለማኖር መሞት አለበት ። በጉ ታርዶ ሲበላ ይህም እኛ እንድንኖር ዛሬ የሞተ እንስሳ አለ ማለት ነው ። ከበደል በኋላ ሕይወት ያለ ቤዛነት አይቀጥልም ። ደቀ መዛሙርቱ የፈሩት የሚያስፈራ ነገርን ሳይሆን የሚያስፈራራቸውን የአእምሮ ሥዕል ነው ። ራሱ ፍርሃት እንጂ ሌላ አስፈራሪ አልመጣባቸውም ። ፍርሃት ቁልፍ ይወዳልና የውጭውን በር ቆለፉት ። ፍርሃት ቁልፍ አይጠግብምና የሳሎኑን በር ከረቸሙት ። ፍርሃት ልክ የለውምና ወደ ሰገነቱ የሚያወጣውን የደረጃውን በር ቀረቀሩት ። ፍርሃት እስከዚህ አይልምና የሰገነቱን በር ዘጉት ። ይህ ሁሉ ሁኖ በፍርሃት ይናጣሉ ። የተዘጋው ደጅ ሳይሆን ደጆች ናቸው ። ከኤማሁስ የተመለሱ ሉቃስና ቀለዮጳ የሆነውን ሁሉ ተናገሩ ። ችግር ለየራስ ነውና የኤማሁስ መንገደኞች ተስፋ መቍረጥ ፣ ሐዋርያትን ደግሞ ፍርሃት ይዋጋቸው ነበር ። ተመስጠው ያንን የኤማሁስ ገጠመኝ ሲሰሙ ጌታችን በመካከላቸው ቆመ ። በር አልተንኳኳም ። በሩን ቢያንኳኳ ልባቸው የሚከዳቸው ፣ ደማቸው የሚፈላባቸው ብዙዎች ነበሩ ። ጌታ ግን አቅማቸውን አየ ። አዘነላቸው ። ያሉበት አቅም የበር ማንኳኳትን እንኳ የማይቋቋም እንደሆነ ተረዳላቸው ። የስልክ ጥሪ የሚረብሻቸው ፣ የደወሉለት ሰው ስልክ ካላነሣ የሚጨንቃቸው ፣ መረሳት የሚያስፈራቸው ፣ ለአትርሱኝ ሰው የሚበጠብጡ ብዙ ናቸው ። ጌታ ለእነዚህ ሁሉ ደንባሮች “ሰላም ለእናንተ ይሁን” ይላል ። ቅዱሳን ሐዋርያት የተነሣውን ጌታ በዓይናቸው አዩ ። እኛ ደግሞ በዓይናቸው ያዩት የመሰከሩልንን እናምነዋለን ። አይተው አመኑ ፣ አምነን እናያለን ። ከፊት ለፊት ያለውን ያመኑ ነቢያት ተባሉ ። ከኋላ ያለውን ያመኑ ሐዋርያት ተባሉ ። ነቢዩ ኢሳይያስ፡- “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች” ብሎ ስለ አማኑኤል ተናገረ ፣ አመነ ። ሐዋርያት ክርስቶስ ከሞት እንደ ተነሣ አመኑ ። ከሞት ከተነሣ ሰው ጋር ግንኙነት አድርገን ብናውቅ ብዙ ነገሮች ይገቡን ነበር ። ከሞት የተነሣ ወዳጅ ስስት ነው ። ክርስቶስ ከሞት የተነሣ ወዳጃችን ነው ። እናቶቻችን፡- “የሞት ትራፊዬን አትንኩብኝ” ይላሉ  ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 2🙏 1
በተዘጋው የሚመጣ /3/  “ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት ፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው ።”/ዮሐ. 20፡19 ።/ እርሱ አስቀድሞ፡- “ያከበሩኝን አከብራለሁ” ብሏል ። /1ሳሙ. 2፡30 ።/ ቅዱሳን ሴቶች ማልደው ወደ መቃብሩ ስለገሰገሱ እርሱም ማልዶ የምሥራቹን አሰማቸው ። “ለገቢህ ተንገብገብለት” ይባላል ። ገቢህ የተባለው ስትጠራው አቤት ለሚልህ ፣ ስትጮህ ለሚደርስልህ ፣ እሳት ውስጥ ስትገባ እሳት ገብቶ ለሚያወጣህ ፣ ሲከፋህ አብሮ ለሚከፋ ፣ ስትታመም ለሚያገላብጥህ ለእርሱ ተንገብገብለት ፣ ኑርለት ፣ አልቅስለት ፣ ራራለት ፣ ሁለመናህን ስጠው ማለት ነው ።  ጌታም ለገቢዎቹ ይንገበገባል  ። እግዚአብሔር ማለዳ የገቡትንና ሠርክ የገቡትን በፍቅር ቢቀበልም ማለዳ መግባት ቢያንስ የቀኑ ሐሩርና የት ልሄድ የሚለው ሥቃይ ፣ ሥራ ፈትነት የሚያመጣውን የልብ ውዝዋዜ እንዲቀር ያደርጋል ። ደግሞም ከነትጥቁ የተማረከና ትጥቁን አራግፎ የተማረከ እኩል አይደለም ። በማለዳ የገቡ ቆስለው የተማረኩ አይደሉም ፣ ትጥቃቸውን ወይም ጉልበታቸውን አባክነው የመጡም አይደሉም ። እኩል በክርስቶስ ብንድንም እኩል አንሸለምም ። ማልደው የገቡ ክብራቸው ከፍ ይላል ። ቅዱሳን ሴቶችና መግደላዊት ማርያም ማልደው ቢሄዱ ትንሣኤን ሰሙ ። ማልደው ወደ እግዚአብሔር በጸሎት የሚገሰግሱ የሚያቆምና የሚያጸና መንፈስን ያገኛሉ ። ቀኑን ብቻ ሳይሆን ቀኑን የሚያውል ቃል እግዚአብሔር ሰጥቶናል ። ያንን  የሚያገኙ ማልደው ቃለ እግዚአብሔርን የሚያነቡ ናቸው ። ቀኑን ያለ ኃይል መዋል ከባድ ነው ። ከእንቅልፍ እንደ ነቃን እንቅልፍ ሲሰማን ፣ ተኝተን አድረን ድካም መልሶ ሲጫጫነን ፣ ተስፋችን ተሟጦ ፊታችን ሲጨማደድ ፣ የትዳር ጓደኞቻችንንና ልጆቻችንን በጠዋቱ በቍጣ ስናስደነብር ይህ ኃይልን ያለ መሞላት ችግር ነው ። ሰው ሁሉ ማልዶ ተነሥቶ ውኃ መኖሩን ያረጋግጣል ፣ ለቁርስ የሚሆኑ ነገሮች በቤት እንዳሉ ይፈትሻል ፣ ቆሞ ያደረው መኪናው ዘይት አፍስሶ እንደሆነ ያጣራል  ። ሰው ግን ስለ መኪናውና ስለ ቁርሱ የሚያስበውን ያህል ስለ ነፍሱ አያስብም ። የሥጋ ጥጋቦቻችን ሁሉ እርካታ ያልሰጡን የነፍስ ጠኔ ስላለብን ነው ። እነ ጴጥሮስ የመነሣቱን ዜና በመግደላዊት ማርያም ሰሙ ፣ ሮጠው ወደ መቃብሩ በመገስገስ አረጋገጡ ። ነገር ግን ዝምታን መርጠው ዋሉ ። እስቀድመው የሰሙት ወንዶች ቢሆኑ ኑሮ ሰብአዊ ኩራታቸው የምሥራቹን ታግሠው እንዲውሉ ያደርጋቸው ነበር ። ደስታቸውን ሊያጋሩ ሁልጊዜም ፈቃደኛ ለሆኑ ሴቶች ጌታ ትንሣኤውን ገለጠ ። እርሱ ለማን ምን መንገር እንዳለበት ያውቃል ። መግደላዊት ማርያም ከመቃብሩ ባዶ መሆን ፣ ከመላእክት ምስክርነት በላይ ራሱን ጌታን አግኝታ ትንሣኤውን አረጋግጣለች ። ያ ቀን የዓርብ ዕለት ተቃራኒ ነበር ። ዓርብ ከማለዳው እስከ ምሽት የኀዘን ቀን ነበር ። እሑድ ደግሞ ከማለዳው እስከ ምሽት የምሥራች ነበር ። የዓርብን መከራ ያመኑ የእሑድን ደስታና ክብር ማመን አልቻሉም ። ጭንቅን የሚቀበል ደስታን የማይቀበል ፣ የሰይጣንን ሀልወት የሚያምን የእግዚአብሔርን መኖር የሚክድ ፣ በአዳም መኰነኑን የሚቀበል በክርስቶስ መዳኑን ችላ የሚል ፣ የምድርን አታካችነት የሚናገር የሰማይን ደስታ የማይቋደስ አእምሮ የሚደንቅ ነው ። ክፉ ነገር አገሩ እዚህ ነውና ይፈጥናል ። መልካም ነገር ደግሞ ይዘገያል ። በሰዎች ተጎዳሁ እያለ በክርስቶስ የማይጠቀም ፣ በምድር ተገፋሁ እያለ የሰማይን ምሰሶ የማይጨብጥ ፣ አጋንንት ተሰለፉብኝ እያለ የመላእክትን ተራዳኢነት የማይቀበል ፣ የሚጠሉትን እየተከተለ ለወዳጆቹ ጀርባው የሚሰጥ ፣ ቀሙኝ ብሎ እያለቀሰ ሲሰጡት የሚጠራጠር ፣ የክፋት ዜና መረረኝ እያለ የልማት ዜናን የማይወድ … የሚደንቅ ፍጡር ነው ። ሰው ሊጸልየው ከሚገባ ጸሎት አንዱ፡- “መከራዬን አስረሳኝ” ብሎ ነው ። አስተዳደጋቸው አኗኗራቸውን የሚዋጋባቸው ብዙ ናቸው ። የማጣት ዘመናቸው ዛሬ ወርቅ እንዳይለምዱና እንዲያግበሰብሱ ያደረጋቸው አያሌ ናቸው ። አንድ ወንድ ጎዳኝ ብለው ሺህ ወንድ የሚበቀሉ ፣ አንድ ሴት አታለለችኝ ብለው ሺህ ሴት የሚጠራጠሩ ብዙ ናቸው ። የዛሬው ኑሮ የሚበጠበጠው የትላንቱን መርሳት ባለ መቻላችን ነው ። ዓርብን ስላልረሱ እሑድን ሲተክዙ ዋሉ ። እግዚአብሔር ሲክስ ከተጎዳነው በላይ ነው ። የትላንቱን መዘባበቻ መሆን ፣ የትላንቱን ከፀጉር የበዙ ጠላቶች ማስተናገድ ፣ የትላንቱን በአደባባይ መራቆት ፣ የትላንቱን የወደዱትን ማጣት ፣ የትላንቱን የአስገባሪዎች ክፋት ፣ የአስጨናቂዎችን ዘንግ ፣ የጫንቃውን በትር ፣ የጀርባውን ሰንበር መርሳት የዛሬን ትንሣኤ ለመቀበል አስፈላጊ ነው ። ደርግ አሥራ ሰባት ዓመት ጃንሆይን አልረሳም ፣ ሲራገም ነበር ። ሬሳ መደብደብ ጀግና አያሰኝም ። ያንን በደል ማውራት ጥቅም የለውም ። መካስ ግን ጥቅም አለው ። ደርግንም እስካሁን እንራገማለን ። አካሉ ሂዶ መንፈሱ አልሄድ ብሎን እንጨነቃለን ። የትላንቱን ተምረንበት መርሳት ያስፈልጋል ። ዛሬ ላይ ትላንትን መኖር አለማወቅ ነው ። እገሌ ጎዳን ከማለት እኔስ ምን ጠቀምኩኝ ? ማለት እውነተኛ ጥቄ ነው ። ሁለት ነገሮች ለሕክምና አስቸጋሪ ናቸው፡- ራስን አለመቀበልና ትላንትን አለመርሳት ። ክረምትና በጋ ፣ ደስታና ኀዘን የሕይወት ዑደት እንጂ አደጋ አይደሉም ። ደቀ መዛሙርቱ የጌታን መነሣት ጠብቀዋል ። ሲነሣ ግን ማመን አቃታቸው ። ትልቅ ደስታ ማመን ይከለክላል ። ይህ ቅዱስ አለማመን ነው ። እየጠበቁም አለማመን አለ ። እየጠበቁ አይሁድ ክርስቶስን ሰቀሉ ። እግዚአብሔርን የማንቀበለው በእኛ ሥዕል ስለምንጠብቀው ነው ። እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ብቻ የታወቀ ፣ እግዚአብሔር በራሱ መንገድ የሚሠራ አምላክ ነው ። ሲሆንና ሲፈጸም ለመቀበል አቅም የሚጠይቅ ደስታ አለ ። ደስታንም ለመሸከም አቅም ያስፈልጋል ። በዓለም ላይ እውነትን ለመሸከም አቅም ስለሚያስፈልግ መመጠን ያስፈልጋል ። የጋኑን በገንቦ እየገለበጡ ማፍሰስ ብክነት ነው ። እንዲህ ያለ የትንሣኤ ደስታ የዘመናትን ትካዜ ጠራርጎ የሚወስድ የብርሃን ጎርፍ ነው ። እሑድ ምሽት ላይ ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው እንዳልተሰረቀ አረጋግጠዋል ። በሥፍራው ማለት በመቃብሩ እናገኘዋለን ብለው ጠብቀው ስላጡት በስፍራቸው ሁነው ጠበቁት ። በስፍራው የተሰወረብንን ነገር በስፍራችን ሁነን መጠበቅ ግድ ነው ። መፈላለግ ያጠፋፋልና ። የክርስቶስን መነሣት በግማሽ ልብ ቢቀበሉም ጠላቶቹ እስካላለቁ ደስታችን ሙሉ አይሆንም ብለው ያሰቡ ይመስላል ። በዚህም የነቢዩን ጸሎት ዘነጉ፡- “በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ ” ይላል ። ጠላቶቼ እያዩ ፣ አለ እንጂ ጠላቶቼ ሬሳ ላይ ራሴን በዘይት ቀባህ አይልም ። የምንለምነው የጠላቶችን ሬሳ እንጂ የእግዚአብሔርን ዘይት አይደለም ። ሙት ግን ይዞ ይሞታልና ቅባቱ ይሻለናል ። የጠላት ድርብ ሞቱ የእኛን መቀባት ማየቱ ነው ። ጠላት ቅባታችንን ሊያጥብ ፣ ጸጋችንን ሊያራቁት ይነሣል ። እግዚአብሔር ግን በክብር ላይ ክብር ይጨምራል ። ሞት አንድ ጊዜ ነው ። ጠላት ደጋግሞ የሚሞተው ግን ቀበርሁት ያለው አደባባዩን ሲሞላው ነው ። ክርስቶስ ሲሰቀል ደቀ መዛሙርቱ በሕሊና ሙተው ነበር ። ክርስቶስ ሲነሣ ጠላቶቹ በሕሊና ሞቱ ። አቤቱ ቅዱስ ዘይትህ አይለፈን ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 11🙏 7 5
ሁላችንም ዓርብ አለንና በዚያ ቀን ከተማውን እንዳልሞላን ከከተማ ውጭ እንደ ጉድፍ እንጣላለን ። ስንደሰት ዝም ያሉ ስንሰቀል ሊያዩ ይወጣሉ ። በምድም በሰማይም የተገፋን መስሎ ይሰማናል ። ትልልቅ ተስፋዎች ወደ ትልልቅ ፍርሃቶች ይለወጣሉ ። ዕድሎቻችን ሁሉ የክሳችን አንቀጽ ይሆናሉ ። ምድር ከድታን ስንጠለጠል ፣ ሰማይ ተቀይሞን ፊቱን ሲያጠቁርብን ። ቀትሩ ጨልሞ ሁሉ ሲተወን ፣ እግዚአብሔርም እንደ ሰው የሆነ ሲመስለን ፣ የጸለይነው ጸሎት እንደ ገደል ማሚቱ ለራሳችን መልሶ ሲሰማን ፣ ካህናት ከሳሽ ፣ ንጉሥ ወቃሽ ሲሆንብን ፣ ሚሊየኖች ለአንድ እኛነታችን ሲያድሙብን ያን ቀን የዓርቡን ባለ ጽዋ ፣ ክርስቶስን እናስብ ። በቀደመበት በድል ያስከትለናል ። ለቀኑና ለስሜታችን አሳልፎ አይሰጠንም ። ዓርብ ቀትሩ እንደ ጨለመ ፣ እሑድ እኩለ ሌሊቱ ይበራልናል ። ያን ቀን የምስጋና ደቦ ጠርተንም ውለታውን ለመዝለቅ ፣ ክብሩን ለመዘመር አንችልም ። አቤቱ ሕዝብህ ነንና አድነን ፣ ርስትህ ነንና ጠብቀን ። ይቀጥላል
Hammasini ko'rsatish...
🙏 10👍 5 5
በተዘጋው የሚመጣ/2  “ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት ፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው ።”/ዮሐ. 20፡19 ።/ የጌታችንን መነሣት ቀድመው ያወቁ የሮማ ወታደሮች ናቸው ። ወዳጆቹ ሳያውቁ ጠላቶቹ አወቁ ። ሲሰቅሉት ከትሕትናውና ከፍቅሩ አልተማሩም ። መግደል እየቻለ መሞቱ ትሕትና ፣ ስለ ኃጢአተኞች ራሱን አሳልፎ መስጠቱ ፍቅር ነው ። ሲነሣ ታላቅ ብርሃንና ኃይልን አዩ ። በትሕትና ያልተሳቡ በግርማው  ፣ በፍቅሩ ያልተማረኩ በኃይሉ ቢማረኩ መልካም ነበር ። ሰው ወይ ትሕትና ወይም ግርማዊነት ፤ ወይ ፍቅር ወይም ኃይል ይማርከዋል ። ጌታችን ሰዎች ሁሉ በሚማረኩበት መንገድ ቢገለጽም አላመኑበትም ። ለማመን እንዲችሉ ራሱን አሳያቸው ። ለማመን ካልፈቀዱ ለፍርድ እንዲመቻቹ ምክንያት ያሳጣቸዋል ። ሰዎች በከተማ የተቀመጠውን አገልጋይ “የከተማ ቅዱስ አለ ወይ?” ይሉታል ። በበረሃ ያለውን መናኝ ሰባኪ ደግሞ “የምንኖረውን ኑሮ ፣ የምናልፍበትን ፈተና ሳያውቅ በእኛ የሚፈርድ እርሱ ማነው?” እያሉ ችላ ይሉታል ። ጌታችን በከተማ እየበላና እየጠጣ ፣ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ እያጠመቀ ማገልገላቸው ተናባቢነት ያለው ፣ የሰዎችን ተቺነት ዝም ለማሰኘትና ለንስሐ ለማብቃት የተደረገ ነው ። ወደ ክርስቶስ ሲመጡ በዘላለም እቅፉ ይሰውራቸዋል ፣ ወደ ዮሐንስ ሲሄዱም ወደ ክርስቶስ ያመለክታቸዋል ። የሮማ ወታደሮች መነሣቱን ቢያረጋግጡም አላመኑበትም ። ማረጋገጥ ማለት ማመን አይደለም ። አረጋግጠው ያላመኑ አሉ ። ክርስትናን እንደ ምርምር ጣቢያ ቆጥረው የትምህርት ማዕረግ የሚደረድሩ የአምልኮ ልብ ግን የሌላቸው አያሌ ናቸው ። ክርስቶስን ማወቅ አስፈላጊ ቢሆንም ማወቅ ግን ከእርሱ ጋር ላለን ግንኙነት መጨረሻው አይደለም ። ክርስትና ከማወቅ ቀጥሎ ማመን ፣ ከማመን ቀጥሎ መኖር ፣ እንደ ገና ታውቆ ወደማይጨረሰው ክብሩ መገስገስ ነው ። ወታደሮቹ ትንሣኤው እርግጥ መሆኑ ሪፖርት አድርገዋል ፣ የምሥራቹንም በቤተ መንግሥት በማለዳ አድርሰዋል ። በወታደራዊ ሙያቸው መሞቱን አረጋግጠው እንዲቀበር ፈቅደዋል ፣ አሁን ደግሞ መነሣቱን ሪፖርት አደረጉ ። ይህ ለእነርሱ መደበኛ ሥራቸው ነው ። የሃይማኖት ሰዎች ግን አንድ ነገር አስተማሯቸው ። ገንዘብ ተቀብለው ያዩትን እንዲክዱ ፣ ተሰረቀ ብለው እንዲያወሩ አግባቡአቸው ። የሃይማኖት ሰዎች ጋር ያለው ክፋት ረቂቅ ነው ። የዓለም ሰዎች ቢጣሉ ይፈነካከታሉ ፣ የሃይማኖት ሰዎች ውስጡን እንዴት እንስበረው ፣ ዘላቂ ሕመም እንዴት እናስታቅፈው ? ይላሉ ። ሰማያዊውንና ረቂቁን ነገር ያመኑ ሰዎች ካልኖሩበት እንዳመኑት መጠን ይክዳሉ ። ሰው የሚወድቀው በወጣበት ልክ ነው ። መግደላዊት ማርያም ከወታደሮቹ ቀጥሎ ትንሣኤውን አየች ። ጴጥሮስና ዮሐንስም መቃብሩ ባዶ መሆኑን አረጋገጡ ። ጌታችንም ለመግደላዊት ማርያም ተገለጠ ። ቀጥሎ ለሴቶቹ ሁሉ ተገለጠ ። ለኤማሁስ መንገደኞች ተገለጠ ። የኤማሁስ መንገደኞችም እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ተሰብስበው ወደ ነበሩት ደቀ መዛሙርት መጡ ። እነርሱ ሲመጡ ጊዜው ምሽት ነበረ ። የኤማሁስ መንገደኞችም የክርስቶስን መነሣትና እንደ ተገለጠላቸው ሲተርኩ ሳለ ክርስቶስ ተገለጠላቸው ። ምስክርነታቸውን ሊያትም ተገለጠ ። ስለ እርሱ እያወሩ ሲሄዱ አብሯቸው በኤማሁስ መንገድ የተጓዘ ጌታ ስለ እርሱ ሲመሰክሩ በሰገነቱ ተገለጠ ። እርሱ ስሙ በተጠራበት አለ ። እርሱ የመሰከርነውን ሊያትም ይገለጣል ። ጌታችን ሕይወት ያዛላትን የመከራ ቋጥኝ ስትገፋ የኖረችውን መግደላዊት ማርያምን አስቀደመ ። እርሱ የደካሞችን ድካም ያውቃል ። ትንሣኤውንም ለእርስዋ ቀድሞ ባይገልጥ ኑሮ ትጎዳ ነበር ። ጌታ ቀብራ ለማረፍ ለመጣችው ፣ ለመሰናበትም ሽቱ ለያዘችው  አዲስ ምዕራፍ ከፈተላት ። ሰዓቱን የሚያውቅ አምላክ በሰዓቱ ይደርስልናል ። የኤማሁስ መንገደኞችም ተስፋ ቆርጠው ወደ ፀሐይ መጥለቂያ ይጓዙ ነበር ። እነርሱም በተሰበረ ልብ ፣ ተስፋ በቆረጠ መንፈስ እንዳያድሩ  ደረሰላቸው ። ምሽቱን ግን ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ ። “አጥብቀው ያሰሩትን ዘቅዝቀው ይሸከሙታል” እንዲሉ ደቀ መዛሙርቱን ስለ ተማመነባቸው እስከ ምሽት ዝም አላቸው ። ቢሆንም እስከዚያው የምሥራቹን ይልክላቸው ነበር ። በቃሉ ቀኑን አውሎ በመገለጡ አሳደራቸው ። ነቢዩ፡- “በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም አቤቱ ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና” ይላል ። /መዝ. 4፡8 ።/ በሰላም እንዲያንቀላፉ ፣ በእምነት እንዲያድሩ ተገለጠላቸው ። ቀኑ የሁከት ፣ የመጠራጠር ነበርና ። ሞቶአል የሚለው ኀዘን ነው ፣ ተነሥቷል የሚለው ግን ጥርጣሬ ነው ። ሞት ቁርጥ ነው ፣ ጥርጣሬ ግን ሲወዘወዙ መኖር ነው ። ከካዱት በላይ የሚጠራጠሩት ሲታወኩ ይታያሉ ። ጎረቤት የሚረብሽ ጸሎት የሚጸልዩት ለዚህ ነው ። ያዩት ሰው ሁሉ ላይ መንፈስ አለበት እያሉ የሚገሥጹት ለዚህ ነው ። ምግቡ ላይ ጋኔን አርፏል እያሉ ሲባርሩ የሚውሉት ለዚህ ነው ። አንዱን እግዜር ማመን ትተው የዛርና የቃልቻ ስም እየዘረዘሩ ሲቃወሙ ፣ ያንን የደርግ መፈክር “ይውደም” ሲሉ የሚውሉት ለዚህ ነው ። በግብራችን የምንስመውን ዲያብሎስ ፣ በቃላችን መርገም ከንቱ ጨዋታ ነው ። በአትክልቱ ስፍራ ለመግደላዊት ማርያም ፣ በመቃብሩ ቦታ ለሴቶች ፣ በኤማሁስ ለመንገደኞች ፣ በሰገነቱ ላይ ለሐዋርያት ተገለጠ ። ቀኑን በሙሉ ሰዎች ሲያደክሙት ዋሉ ። ዓርብ ሙሉ ቀን ለማስታረቅ የደከመው አሁን ደግሞ እንዲያምኑት ደከመ ። እርሱ ወደ ሰው ካልመጣ በኃጢአት ዓይኑ የጨለመው የሰው ልጅ ወደ እርሱ መምጣት አይችልም ። እኛስ ከልጅነት እስከ እውቀት ብዙ እንዳደከምነው ተስምቶን ይሆን ? ስንክድም ስናምንም አላምርብን እያለ አስቸግረነዋል ። ስንክድ ሰዎችን መንቀፍ ፣ አምነን ደግሞ ስንወጋገዝ መኖር እርሱን ያደክመዋል ። አንዳንዴ ቀትሩ ይጨልማል ። ሙሉ ብርሃን ነው ሲሉት ድቅድቅ ጨለማ ይሆናል ። ምድርም ትከዳለች ። የሚረገጥ እስኪጠፋ እግር መደላደያ ያጣል ። ሰማይ ጠቁሮ ያስፈራል ። እግዚአብሔርም ዝም ያለ ፣ ከቀኑ ጋር ያደመ ይመስላል ። ባል በጫጉላ ቤት ሲሞት ፣ ልጅ ፊት ለፊታችን የጥይት እራት ሲሆን ፣ ጠዋት ጤነኛ የነበርነው ከሰዓት የአልጋ ቁራኝ ስንሆን ፣ ኬክ ይዘው ይመጡልን የነበሩ መርዝ ጋግረው የት ነው ? እያሉ ሲፈልጉን ፣ የቅጥር ተሳዳቢዎች የተሞሉትን ሳንቲም እስኪጨርሱ ሲሰድቡን ፣ አለሁ ያሉን አርባ ክንድ ሲርቁን ፣ እንኳን ሰውን ልባችንን ማመን ሲከብደን የሚያድነንን እንፈልጋለን ። ሁሉም ነገር ዘላለማዊ ጸጥታን የተላበሰ የሚመስልበት የተዘጋ ቀን አለ ። “አምላኬ ሆይ ለምን ተውኸኝ ?” የሚል ጥያቄ አዘል ልመና ፣ ከመጉዳት ስሜታችን የሚወጣ ጩኸት በውስጣችን ያስተጋባል ። የወዳጅ ፊት ቅጭም ቢል ሰማይ ግን አይጠቁርም እንል ነበር ፣ መኖሪያ ቤት እንጂ መርገጫ ምድር አጣሁ እንደማንል እርግጠኛ ነበርን ። ነገር ግን ሰማይም የሚጠቁርበት ፣ ምድርም የሚከዳበት ዘመን አለ ።
Hammasini ko'rsatish...
👍 8 2🙏 2
አሁን ONLINE ላይ ✅ ላላችሁ ብቻ መንፈሳዊ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው ገብታችሁ ተሳተፉ 👇🏾በጥያቄ እና መልሱ 1⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ 💸 2⃣ ለወጣ 250 ብር ካርድ 💸 3⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 💸 📍👉🏾 ዝግጁ ከሆናችሁ ብቻ 💸𝐒𝐓𝐀𝐑𝐓💸 የሚለውን ይጫኑት።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1🙏 1
💸𝐒𝐓𝐀𝐑𝐓💸
በተዘጋው የሚመጣ “ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ።” ዮሐ. 20፡26  ። በጫካ ውስጥ በምሽት የሚገኝ መንገድ የጠፋው ነው ። በጫካ ውስጥ የሚደበቅ ወንበዴ የሚያሳድደው ነው ። በጫካ ውስጥ የጨለመበት ቀኑን ያባከነ ነው ። በጫካ ውስጥ ጨለማ ድርብ ነው ። ሌሊቱም መንታ ነው ። ግርማ ሌሊቱ ፣ ፀብአ አራዊቱ የሚያስፈራ ነው ። አዳም ስለ መሄጃው መንገድ እንጂ ስለ መመለሻው አላሰበም ። በገነት መጥፋት በጣም የሚደንቅ ነው ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው ለጠፉት ምሳሌ ነው ። በምድር የጠፋ ይታዘንለታል ፣ በገነት የጠፋ ምን እንደሚባል ቃላት የሚያውስ ሰው ያስፈልጋል ። አዳም መንገድ እንደ ሳተ ወዴት ነህ ? የሚለው አምላካዊ ድምፅ አመልካች ነው ። አዳም የጠፋው መንገድ የዱሩ ሳይሆን የሕይወት መንገድ ነው ። የዱሩም የሕይወትም መንገድ ሲጠፋ ሁለቱም ጊዜ ያባክናሉ ፣ መንፈስን ያስጨንቃሉ ። መንገድ የሚጠፋው በሚያውቀው ነገር ውስጥ የማያውቀው ነገር እንዳለ ያሳያል ። አዳም አውቆ በመጥፋቱ ፍርድን ተቀበለ ፣ በማወቁ ውስጥ አለማወቅ ስለ ነበረ የመዳን ተስፋን ሰማ ። “አዳምና ሔዋን ጠፍቷቸው መንገዱ ፣ ለሰው ልጅ መከራን ትተውለት ሄዱ፤” ተብሏል ። ይደብቃሉ የተባሉ ነገሮች ሁሉ አዳምን መሸሸግ አልቻሉም ። ከእግዚአብሔር መደበቅ አይቻልም ፣ በእግዚአብሔር መደበቅ ግን ይቻላል ። ከእግዚአብሔር መደበቅ ምክንያታዊነት ፣ በእግዚአብሔር መደበቅ ንስሐ ነው ። አዳም የተዘጋ ደጅ ባይታየውም መውጣት አልቻለምና ደጁ ተዘግቶበታል ። እውቀት ሲሰወርም የደጅ መዘጋት ነው ። አዳም ደጁን የዘጋው ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰይጣንን ፣ ሚስቱንና ምኞቱን በመስማቱ ነው ። ከዚህ በፊት ባያውቀውም የኃጢአት እውቀትን ተለማመደ ፣ ከዚህ በፊት ባያውቀውም የንስሐን መድኃኒት ግን እንቢ አለ ። ለኃጢአት ፈጣን ፣ ለንስሐ ዳተኛ ሆነ ። በተዘጋው ደጅ ኢየሱስ መጣ ። በገነት ውስጥ የሰው ሕሊና ተዘግቶ ፣ በአዳምና በሔዋን መካከልም ግድግዳ ተገንብቶ ነበር ። መንገድ የጠፋው የዓለሙ ንጉሥ የሆነው አዳም ምሽት ደርሶበት ፣ ፀብአ አጋንንት በክስ ያስጨንቁት ነበር ። ምንም ያህል ጥፋት እንሥራ ከሳሽ ሰይጣን ነው ። ወቃሽ ሕሊና ግን የመንፈስ ቅዱስ መቅረብ ምስክር ነው ። አዳም ከእግዚአብሔር ሲጣላ አጋንንት ደፈሩት ። አራዊት ጠላት ሆኑበት ። የገዛ ሕሊናውም ከዳው ። እግዚአብሔር ለመንግሥተ ሰማያት ብቻ ሳይሆን ለሕሊና ሰላምም ያስፈልጋል ። ምኞታችንን የሚያረኩ ፣ እልህአችንን የሚያደምቁ ግፎች የሕሊና ሰላምን ያሳጡናል ። አዳም ተራቁቷል ፣ ነገር ግን ተራቁቻለሁ ማለት አልፈለገም ። ሰብአዊ ውድቀት ወደ ሰብአዊ ኩራት ወሰደው ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጆች መንገዱ ጣለን እንጂ እኛ አልወደቅንም ይላሉ ። ገዥዎችም ከያዢዎቻችን ድክመት እንጂ እኛ አልወደቅንም በማለት ይናገራሉ ። ወድቆ መፎከር በንስሐ ፣ ወድቆ መሸለል በአምላክ ምሕረት ይቻላል ። ነቢዩ፡- “ጠላቴ ሆይ ፥ ብወድቅ እነሣለሁና ፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ ” ብሏል ። /ሚክ. 7 ፡ 8 ።/ አዳምን ለምን ወደቅህ ? አላለውም ። እንዴት ወደቅህም አልተባለም ። አዳም ግን በማን ምክንያት እንደ ወደቀ ለመናገር ቸኮለ ። ለምሕረት ተጠርቶ ሌላውን ከሰሰ ። የእግዚአብሔር ምሕረት የእርሱንም የሌላውንም በደል መሸፈን ይችላል ። የራሱ የጸጸት ድምፅ የሸሸገው አዳም አሁን ወዴት ነህ? በሚለው የእግዚአብሔር የፍለጋ ድምፅ ብቅ አለ ። ወዴት ነህ ? ሲባል እዚህ ነኝ ማለትም አልቻለም ። የወደቀ ሰው እዚህ ነኝ ለማለትም እውቀት ያስፈልገዋል ። በደሉን አልተናዘዘም ፣ በደሉ ያመጣበትን ዕራቁትነት ግን ተናገረ ። ቀድሞ ደስ የሚለው የእግዚአብሔር ድምፅ አሁን ፍርሃት ሆነበት ። የእግዚአብሔርን ቃል መሸሽ ስንጀምር በጣም ወድቀናል ማለት ነው ። ሰው የሚወደው ምግብ እያስጠላው ሲመጣ ታሟል ማለት ነው ። አዳም ለበደሉ ምክንያት እስኪያገኝለት ተጨነቀ ። እግዚአብሔር ያን በደለኛውን ይጠይቃል እንጂ ምክንያቱ እንደማይጠየቅለት አላወቀም ። እግዚአብሔር ሰውን በመውቀስ አልጀመረም ። ውስጡ የሚናገረውን መናገር ተገቢ አይደለም ። አስፈቅዶ ማዳን ግን መለኮታዊ ግብር ነው ። ወዴት ነህ ? በማለት ያለበትን ሁኔታ እንዲያይ አደረገው ። ያለበትን ሁኔታ አይቶ አውጣኝ ካለ እንደ ጴጥሮስ ሰጥሞ ሳያልቅ እጁን ይዘረጋለታል ። ሰው በመለኮታዊ ርኅራኄ ካልተወቀሰ ወድቆ ሊቀር ይችላል ። የሕክምና ስህተት የሚባለው በሽታው ሳይሆን በሽታውን ለማዳን በተደረገ ሥራ የተፈጠረ አደጋ ነው ። አጽናናለሁ እያሉ ማቍሰል ፣ አተርፋለሁ እያሉ የበለጠ በእሳት ውስጥ መማገድ ሊኖር ይችላልና ጥንቃቄ ያስፈልጋል ። የአንዳንድ ሰዎች አቀራረብና አሰባበክ የበለጠ ሊያስክድ ይችላል ። የንስሐ ድምፆች በሰው ኃጢአተኝነት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ማተኮር አለባቸው ። የንስሐንና የማማከርን ሥራ የሚሠሩ አባቶችም እንደ መርማሪ ፖሊስ ሊሆኑ በርግጥ አይገባቸውም ። ሰውዬው እስከዚህ ድረስ ነው የሚሸከመኝ ብሎ ያመነውን ያህል ቢያማክራቸው የተሻለ ነው ። ወዴት ነህ ? የሚለው ድምፅ የሕይወት ደጃፍ ለተዘጋበት ለአዳም የተነገረ ነው ። በኋለኛው ዘመን ወዴት ነህ ? ብዬ እፈልግሃለሁ ፣ ዛሬ በቃል በኋለኛው ዘመን ግን ሥጋ ለብሼ አድንሃለሁ ማለቱ ነው ። ፍለጋው በገነት ጫካዎች ጀመረ ፣ በቀራንዮ ፈጸመ ። ልብ አድርጉ እንጨት በልቶ የጠፋውን አዳምን ጌታችን እንጨት ተሸክሞ አዳነው ። ጸጋን ተራቁቶ ነበርና አምላካችን ዕርቃኑን ተሰቅሎ ክብር አለበሰው ። የዓለሙ ደጃፍ ሁሉ ተዘግቶ ፣ የገነት በርም ተቆልፎ ሳለ ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ ። ዓለም ሁሉ ግራ ተጋብቶ ነበር ። የነቢያት ትንቢት ፣ የሱባዔ ቆጠራ ፣ የጠቢባን የጥበብ ፍለጋ ሕዝብና አሕዛብ መሢሑን እንደ ጠበቁ ያሳያል ። በቤተ ልሔም የተገኙት መላውን ዓለም የወከሉ ናቸው  ። እረኞችና ነገሥታት ተገኝተዋል ። ሕዝብና አሕዛብም ሰግደዋል ። ደጆች ተዘግተው ሳለ ክርስቶስ መጣ   ። በዝግ ማኅጸን ተፀነሰ ። በዝግ ማኅጸንም ተወለደ ። ዘመናችንን ልዩ የሚያደርገው ሁሉም እንደ ተቆለፈበት ግራ ሲጋባ ስናይ ነው ። በገዛ ቤቱም የተቆለፈበት በእስር ቤትም የተቆለፈበት ሁለቱም ስሜታቸው አንድ ዓይነት ነው ። ቤት ከእስር ቤት የማይሻልበት የስሜት እስራት ያለበት እየሆነ ነው ። የአዋቂዎች እውቀት አለማወቅ ለመሆን እየቸኮለ ነው ። አንዱን ቀዳዳ የሚደፍነው ሥልጣኔ ዘጠና ዘጠኝ ቀዳዳ የሚከፍት ነው ። ከአድማስ አድማስ በደቂቃ መገናኘትና ማውራት ይቻላል ፣ እንደዚህ ዘመን የሰው ልብ አልተራራቀም ። ሰዎች በሚመለከታቸው ርእስ ጠበኛ ናቸው ፣ የማውራት ትዕግሥት የላቸውም ። በማይመለከታቸው ርእስ ግን ቀኑን ሙሉ ያወራሉ ። ብዙ ደጆች ተዘግተው ሊሆን ይችላል ። የዓለሙ ፣ የአገሩ ፣ የቤቱ ፣ የሥራው ፣ የአገልግሎቱ ፣ … ደጆች ቢዘጉም ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን ይመጣል ። በስሜታችን ሳይፈርድ የሚረዳን ጌታ ይመጣል ። በንስሐ በእምነት ሁነን እንጠብቀው ። የተበዳደልን ይቅርታ እንጠያየቅ ፤ ዘመኑ እንኳን ክፉ ሠርቶ ፣ ደግ ሠርቶም የሚያስጨንቅ ነው ። ይቀጥላል
Hammasini ko'rsatish...
👍 25 9🙏 9
Photo unavailableShow in Telegram
30👍 9🙏 7
+ ረቢ ወዴት ትኖራለህ? + ከመጥምቁ ዮሐንስ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ "የእግዚአብሔር በግ እነሆ" የሚለውን የመምህራቸውን ስብከት ሰምተው ጌታን ተከተሉት:: "ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉትም አይቶ፦ ምን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ አሥር ሰዓት ያህል ነበረ" ዮሐ. 1:37-39 ጌታን ተከትለው የሚኖርበትን ካዩት ደቀ መዛሙርት አንደኛው ስም እንድርያስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራሱን ስም በወንጌሉ ላይ እኔ የማይጽፈውና ቤተ ክርስቲያን ግን የራሱን ነገር ሲገልፅ በሚጠቀመው ቋንቋ የምታውቀው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበረ:: "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ መጥታችሁ እዩ፡ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ" የሚለው ቃል በእርግጥ በጣም አስገራሚ ነው:: የክርስቶስን መኖሪያ ማየት መፈለጋቸው ፈልገው እንዳያጡት አድራሻውን ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ነበረ:: ሆኖም ክርስቶስ በምድር ላይ ሲኖር ቋሚ አድራሻ አልነበረውም:: ራሱ እንደተናገረ :-ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" (ማቴ. 8:20) እነዚህ ሁለት ደቀ መዛሙርት የጠየቁት "ረቢ፥ ወዴት ትኖራለህ?" የሚለው ጥያቄ አድራሻ ከመጠየቅ ከፍ ያለ ጥልቅ ጥያቄ ነው:: ነቢያቱ "የጥበብ ሀገርዋ ወዴት ነው? ማደሪያዋስ ወዴት ነው?" ብለው የተጨነቁለት የጥበብ ክርስቶስ ማደሪያ የት እንደሆነ ማወቅ የነፍስ ዕረፍት ነውና ተራ ጥያቄ አይደለም? ይህ ጥያቄ ዳዊት ለዓይኖቹ እንቅልፍ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት ያልሠጠበት "የያዕቆብ አምላክን ማደሪያ እስኪያገኝ ድረስ" የለመነበት ጥያቄ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? የሚለው ጥያቄ እንድርያስና ዮሐንስ በአንድ ቀን ብቻ የሚመለስ ጥያቄ መስሎአቸው አብረውት ሔደው አብረውት ዋሉ እንጂ የጌታ መኖሪያ ግን ያን ቀን የዋለበት ብቻ አይደለም:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ" መዝ. 43:3 ረቢ ወዴት ትኖራለህ? "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች" መዝ. 139:8 ለአድራሻ የሚያስቸግረው የረቢ መኖሪያው ብዙ ስለሆነ የት ትኖራለህ ለሚለው ጥያቄ መልሱ "መጥታችሁ እዩ" ብቻ ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ብለው ለጠየቁት ደቀ መዛሙርቱ ቦታውን ከመናገር ይልቅ "መጥታችሁ እዩ" ያለው ጌታ እርሱን ጸንተው እስከተከተሉ ድረስ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልፎም ከሞቱ በኋላ የሚያዩት ብዙ መኖሪያ ስላለው ነበር:: የረቢ መኖሪያው ብዙ ነው:: "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፡ ወደ እርሱም እንመጣለን፡ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን" እንዳለ ቃሉን የሚጠብቅ ሰው ሰውነትም የእርሱ ማደሪያ ነው:: (ዮሐ. 14:23) ረቢ ወዴት ትኖራለህ? " በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና" ስትል ሰምተንህ ነበር:: (ዮሐ. 14:2) የአንተ መኖሪያ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? ቅዱስ ጳውሎስ "ልሔድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ" ሲል እንደሰማነው እስከ ዐሥር ሰዓት ድረስ እንደመዋል ዐሥሩ መዓርጋት ላይ የደረሱ በጽድቅ መንገድ የሔዱ የሚያዩት ማደሪያህ መንግሥተ ሰማያት አይደለምን? መጥተን ለማየት "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" እስክትለን በተስፋ እየጠበቅን አይደለምን? ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ካሉት ጠያቂዎች መካከል አንዱ ዮሐንስ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ዮሐንስ ያያቸው የረቢ መኖሪያዎች ከገሊላ እስከ ታቦር ተራራ ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ፣ ከወንጌል እስከ ራእይ እጅግ ብዙ እንደነበሩ ታየኝ:: "ወዴት ትኖራለህ?" ብሎ ጠይቆ ጌታን የተከተለው ዮሐንስ "መጥተህ እይ" በተባለው መሠረት የጌታን መኖሪያ የእርሱን ያህል ያየም ሰው የለም:: ዮሐንስ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" ለሚል ጥያቄው ግን አንጀት የሚያርስ ልብ የሚያሳርፍ መልስ ያገኘው አርብ ዕለት መስቀሉ ሥር ነበር:: ወዴት ትኖራለህ? ላለው ዮሐንስ የዘጠኝ ወር ከተማውን የዘላለም ማረፊያውን "እነኋት እናትህ" ብሎ ሲሠጠው መጥቶ ካያቸው የረቢ መኖሪያዎች ሁሉ የምትበልጠውን መኖሪያ አየ:: "እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ" ብሎ የመረጣትን ማደሪያ ከማየት በላይ ምን ክብር አለ? (መዝ. 132:13) ዮሐንስ ይህችን የረቢ መኖሪያ ወዲያው ወደ ቤቱ ወሰዳት:: ዮሴፍ ሊወስዳት ስላልፈራ ምን እንዳገኘ ያውቃልና እርሱም ይህችን የዕንቁ ሳጥን ወደ ቤቱ ወስዶ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋን ተጎናጸፈ:: ጌታ እናቱን ለዮሐንስ መሥጠቱ የሁለት ድንግልናዎች ማስረጃ ሆነ:: የድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልናም የዮሐንስ ድንግልናም በጌታ ንግግር ታወቀ:: አንዳንዶች እንደሚመስላቸው ድንግል ማርያም ከጌታ ሌላ ልጆች ቢኖሩአት ኖሮ "እናቴን ከልጆችዋ ነጥለህ ወደ ቤትህ ውሰዳት" "አንቺም ልጆችሽን ይዘሽ ወደ ሰው ቤት ሒጂ" ብሎ ለዮሐንስ አይሠጣትም ነበር:: ድንግል ማርያም የአብን አንድያ ልጅ አንድያ ልጅዋ አድርጋለችና አምላክ ባደረበት ዙፋን ሌላ ፍጡር ያላስቀመጠች የአምላክ ብቸኛ ዙፋን ፣ እግዚአብሔርን አስገብታ በርዋን የዘጋች ዘላለማዊት ድንግል መሆንዋ ለዮሐንስ በመሠጠትዋ ታወቀ:: ዮሐንስም ቤት ንብረት የሌለው መናኝ ባይሆንና ሚስት ድስት ያለው ሰው ቢሆን ድንገት ወደ ቤቱ ይዞአት እንዲሔድ እናቱን ባልሠጠው ነበር:: የሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ በሁለት "እነሆ"ዎች መሃል መከናወኑ እጅግ ይደንቃል:: የሰው መዳን የተጀመረው "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ራስዋን ለፈጣሪ በሠጠችው ድንግል ቃል ሲሆን የተጠናቀቀው ደግሞ "እነኋት እናትህ" ብሎ በደም በታጠበ አንደበቱ በነገረን የኑዛዜ ቃል ነው:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ለእኛም አታሳየን ይሆን? እስከ ዐሥር ሰዓት መዋል ፣ ዐሠርቱን ትእዛዛትህን ፣ ዐሥሩን የቅድስና ደረጃዎችን መውጣት ላቃተን ለእኛስ መኖሪያህን ታሳየን ይሆን? መጥታችሁ እዩ የሚለውን ጥሪ ሰምተን ለማምጣት አቅም ላነሰን መጻጉዕዎች ፣ ዓይን ላጣን በርጤሜዎሶች ተነሡ እዩ ብለህ መኖሪያህን አታሳየን ይሆን? መቅደስህን እንመለከት ዘንድ ፣ መኖሪያህን መንግሥትህን እናያት ዘንድ ፣ ዮሐንስ ያያትን መኖሪያህ እናትህን እናይ ዘንድ እንመኛለን:: ረቢ ወዴት ትኖራለህ? ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 21 2016 ዓ.ም. ተጻፈ "ማርያም ገጸኪ እፈቱ ርእየ ድንግል ድንግል ንዒ ኀቤየ እስመ ኪያኪ ጸምአት ነፍስየ" ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም
Hammasini ko'rsatish...
👍 17 8🙏 3