cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️

በዚህ channel ውስጥ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና የየዕለቱን ስንክሳር ያገኛሉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 112
Obunachilar
+124 soatlar
+77 kunlar
+2430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

መልክዐ አርባዕቱ እንሥሳ.pdf1.37 MB
👍 2
መልክአ አቡነ ኪሮስ.pdf4.24 KB
08/10/22016                      የዕለቱ የወንጌል ክፍል                          ዮሐንስ 4:1-15      እንግዲህ፦ “ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል፡ ያጠምቅማል፡” ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥ ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት። ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ። ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ “ውኃ አጠጪኝ፡” አላት፤ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። ኢየሱስ መልሶ፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ‘ውኃ አጠጪኝ፥’ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፡ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር፡” አላት። ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም፡ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል፡” አለችው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ።” ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ፡” አለችው። ኤፌሶን 2:13-ፍጻሜ 1 ጴጥሮስ 1:10-13 ሐዋ.ሥራ 7:44-51                             ምስባክ                    መዝሙር 77:15-16 ወአስተዮሙ ከመ ዘእምቀላይ ብዙኅ ወአውኀዘ ማየ ከመ ዘእም አፍላግ ወአውጽአ ማየ እም እብን https://t.me/religious_books_lover
Hammasini ko'rsatish...
ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️

በዚህ channel ውስጥ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና የየዕለቱን ስንክሳር ያገኛሉ።

ጸሎተ ማዕድ.mp311.97 MB
👍 2
መልክዐ ሥላሴ.pdf6.15 MB
ገድሊ_ኣቡነ_ጊዮርጊዮስን_ኣቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል.pdf2.59 MB
ገድለ_ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት_ኣምሓረኛ.pdf14.89 MB
መልክዐ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ.pdf1.43 MB
ድርሳነ ኤልያስ ነቢይ.pdf3.75 MB
መልክዐ ነቢይ ኤልያስ.pdf3.54 MB
ገድለ_ቅድስት_ማርያም_እንተዕፍረትእኅተ_አልአዛር.pdf11.76 MB
መልክዐ ማርያም መግደላዊት.pdf8.12 KB
📚⛪️ ዜና ሥላሴ ⛪️📚  📗 ስለ ነገረ ቅንዋቱና ቡና አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት 👇🏾📽 ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና የየዕለቱን ስንክሳር የምንልበት ቻነል ነው🖥👇🏾 ➮ከወደዱት ያጋሩ share & join    🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 @religious_books_lover    🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺 https://t.me/religious_books_lover
Hammasini ko'rsatish...
ዜና ሥላሴ ብዛዕባ ቡና (4).pdf3.59 KB
ዜና ሥላሴ.pdf21.55 MB
🖊 ገድለ ሰማዕት ወቅድስት አርሴማ ➠ ግእዝ አማርኛ 🙏 አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት 👇🏾📽 ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና የየዕለቱን ስንክሳር የምንልበት ቻነል ነው🖥👇🏾 ➮ከወደዱት ያጋሩ share & join    🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 @religious_books_lover    🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺 https://t.me/religious_books_lover
Hammasini ko'rsatish...
ገድለ_ሰማዕት_ወቅድስት_አርሴማ_ግእዝ_አምሐርኛ.pdf128.60 MB
መልክዐ_ቅድስት_አርሴማ_ብግእዝን_ብአማርኛ_.pdf8.37 MB
አርኬ ✍️ሰላም ለአበስኪሮን ዘተዓገሠ መከራ። እስኪቱ ወርእሱ እስከ በመጥባሕት ተመትራ። በእደ መኰንን ምውት ለሕይወተ ክርስቶስ ዘኢተዘከራ። ወለዘተቀትሉ ምስሌሁ ወዘተከለሉ ጌራ። ሰላመ ዕብሎሙ ለሐምስ ሐራ። 🔔 በዚችም ዕለት መኰንን አርማንዮስ ያሠቃያቸው የዐስራ ስድስት ሺህ ሰማዕታት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ዕብል እልፈ ወስሳ ፻ተ ዘትፈቀዱ። እንበለ ዘውዕዩ ሰብእ ወእንበለ ተሰዱ። እለ ፈጸሙ ምንዳቤ ለአርማንዮስ በእዱ። አርእስተ ዐርየ ከመ በአእጋር ትኪዱ። መንገለ ነገዱ አንትሙ ንግዱ። 🔔 በዚችም ዕለት አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተከፈተችበትና የከበረችበት ነው። እርሷም ዌላ በሚባል አደባባይ ያለች ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ተዘግታ የኖረች ነበረች። ይኸውም በአንድ ሽህ ሃያ ዓመተ ሰማዕታት ነው። ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ለሆነ ሕይወትና መድኃኒት አድርጎ እርሷን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። አርኬ ✍️ሰላም ዕብል ለርኅወተ ቤትኪ ዮም። ከመ ኤልያስ አርኅወ ኆኀተ ዝናም። በስሱ አውራኅ ወበሠላስ ዓም። ማርያም ሥመሪ አርኅዎቶ ለሕሊናየ ሕቱም። ከመ ላዕሌሁ ይትከዐው ምስለ ጽድቅ ሰላም። 📌 ሰኔ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 2.ቅዱስ: ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን (ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት) 3."16,000" ሰማዕታት (በአንድ ቀን የተገደሉ) 4.የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ700 ዓመታት በፊት ምስር (CAIRO) ውስጥ) 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) ✍️" ይሕንን እዘዝና አስተምር በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው፤ እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር: ለማስተማርም ተጠንቀቅ" 📖1ኛ ጢሞ 4፥11-13
Hammasini ko'rsatish...

✝️ ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፯ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሰባት በዚች ቀን ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም የሆነው አባ አበስኪሮን በሰማዕትነት ሞተ። 🔔 ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ❖ በቤተክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው፤ አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው፤ ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ፤ ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው፤ የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምሥጢር ተገለጸለትና ✍️እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ፤ ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው ምን ምን አሉት፤ እርሱም 1. ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ 2. ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ 3. ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ አላቸው፤ ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚህ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሐ በቅተዋል:: ❖ ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት፤ በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: ❖ በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን፤ አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት፤ እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው፤ "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል፤ ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ❖ ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን ዕጸበ ገዳምን ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: ❖ በድንግልናው ጸንቶ ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል፤ በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: 📌በዘመኑም 1. የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: 2. ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: 3. በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4. ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: ❖ በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ.ም በዚሕች ቀን አርፏል፤ አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ፤ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ በጸሎቱም ይማረን:: 🔔 አባ አበስኪሮን ❖ ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዙ በደረሰች ጊዜ፤ ወዲያውኑ ይህ ቅዱስ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት። ❖ መኰንኑም ወደ ሀገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስ፣ ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮን ጋራ ተስማሙ። ❖ በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው፤ ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ። ❖ የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ❖ ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር። ❖ ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት፤ እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ፤ እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም፤ ያም መሠርይ የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ❖ ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለቤት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል አንተን ይቀጣሃል አለው፤ ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው፤ መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። ❖ በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር፤ ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ❖ ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን አንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ከፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው፤ ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞቱ። ❖ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር፤ የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ አላቸው እነርሱም ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራችው። ❖ እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ። ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላዕላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅድሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት፤ የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፤ ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን።
Hammasini ko'rsatish...

Hammasini ko'rsatish...
የአምላካችን የክርስቶስ ዕርገት

         የአምላካችን የክርስቶስ ዕርገት ❖ የባሕርይ አምላክ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት መጽሐፈ ኪዳንን እያስተማራቸው ለ40 ቀናት በምድር ላይ ቆየ:: ስለምን 40 ቀናት ቆየ ቢሉ? ፩ኛ. ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አለማድረጉ መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ነው ብለው እንዳያስቡ ሲኾን፤ ፪ኛ. አዳም በተፈጠረ በ40 ቀኑ አግኝቶ ኋላ በምክረ ከይሲ ያጣውን የጸጋ ልጅነትን እንደመለሰለት ለማጠየቅ ለ፵ ቀናት ለሐዋርያት እየተገለጸ መነሣቱን ሲያስተምራቸው ከቈየ በኋላ በ40ኛው ቀን ኹሉንም ወደ ቢታንያ አውጥቶ በአንብሮተ እድ ባርኮ የሥልጣነ ክህነትን ጸጋ ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ዐርጓል፡፡ ፫ኛ በአርባ ቀናት ፅንሱ ተስዕሎተ መልክዑ ተፈጽሞለት ሙሉ እንዲኾን የእግዚአብሔርም ልጅ ሐዋርያቱን በእምነት ፍጹም አደረገ፤ በአርባ ቀናት የአዋጁን መንገድ ፍጹም አደረገ፤ እስትንፋስን…