cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ChristianTube

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
201
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

እንኳን አደረሳችሁ... ተወዳጁ ዘማሪ ዮሴፍ በቀለና ባለቤቱ 25ኛ ዓመት የጋብቻ በ በዓላቸውን እያከበሩ ይገኛሉ🎈። እኛም ለዘማሪ ዮሴፍና ለባለቤቱHappy 25th Anniversary ብለናል🎂🎉🎈
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ወ/ዊ ኤርሚያስ አበበ በጠና ታሟል 😔😓 (ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ በእግዚአብሔር ርህራሄ እለምናችኋለሁ!) በወገቡ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ የነርቭ ችግር ለረጅም ጊዜ ሲሰቃይ ቆይቷል። አሁን ባለበት በኒውዚላንድ ነጻ ህክምና ቢኖርም ካለው ወረፋ የተነሳ የወንድማችን ህመሙን ሊቋቋመው የሚችለው አልሆነም። ስለዚህም በግል ሆስፒታል አሊያም ህክምና ሊያገኝ ወደሚችልበት ስፍራ ሄዶ መታከም ስላለበት፣ ወጭውም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሁላችንም የጌታን ፍቅር እንድናሳይ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ጎፈንድሚ https://gofund.me/8909ff30
Hammasini ko'rsatish...
አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ የስራ አይነት የሶሻል ሚዲያ ማኔጀር ሆኖ በግራፊክስ ዲዛይን; በሶሻል ሚዲያ ፕሮሞሽን;በኦንላይን ሴልስ; ቡስቲንግ እና ሶሻል ፕሮሞሽን በሙያው የስራ ልምድ ያለው/ያላት የስራው ቦታ አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ ደሞዝ በስምምነት ለበለጠ መረጃ በ0951699962 ይደውሉ
Hammasini ko'rsatish...
#የወንጌላውያን_ሚድያ_ባለሙያዎች_ማህበር_ተመሰረተ። በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት በተካሄደ ምስረታ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት ዘርፍ የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በማህበሩ ምስረታ ወቅት ማህበሩን ለመመስረት የተካሄደባቸውን የስራ ሪፖርቶች ለተሳታፊዎቹ ያቀረበ ሲሆን በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቋል። በእለቱም የማህበሩን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቦርድ አባላት የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመሆን ወንድም ዘሪሁን ግርማ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንድም መሳይ አለማየሁ የተመረጡ ሲሆን ዘጠኝ የማህበሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል። እነርሱም አብይ ታደለ፣ ፓስተር ዳንኤል ዋለልኝ፣ ትዕግስት እጅጉ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ፌቨን ጋሻው፣ አክሊሉ ተስፋዬ፣ ትዝታ ተክሉ፣ ህይወት ወልዱ፣ አክሊለ ሽመልስ ናቸው። በእለቱም የጸሎትና የእግዚአብሄር ቃል በመካፈል ፕሮግራምም ተካሄዷል።
Hammasini ko'rsatish...
#አሳዛኝ_መረጃ 😭 ዘማሪ ካሌብ ጉዳት ደርሶበታል 😭😭 በአስቸኳይ ሼር ይደረግ ( ✍ አቤል ደመላሽ ) ባሳለፍንው ቅዳሜ የአገልጋዮች ህብረት በሚያዘጋጁት የማለዳ ጸሎት እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መካከል ካሌቦ እንደወትሮው ኳስ ለመጫዎት ከወገኖች ጋር ህብረትም ለማድረግ በማሰብ ተገኝቶ ነበር ። ጥቂት እንደተጫወቱ ካለብ በፍጥነት ሲሮት ወደቀ አወዳደቁ ከባድ ስለነበረ የቀኝ እጁ ክፉኛ ተጎዳ አጥንቱ ተሰበረ ። ጓደኞቹ ተደናግጠው ሆስፒታል ቢወስዱትም ጉዳቱ ቀላል አልሆነም ከባድ ሰርጀሪ መሰራት እንዳለበት ተነገረው ። ነገሩን ለማሳጠር ያክል በካሌብ ዝማሬዎች በእውነት ጠቅሞናል "ሳቄ ነው " "የኔ የኔ " ሌሎችም ይጠቀሳሉ ። ስለሆነም ቅዱሳን የካሌብ ወላጅ ዘመዶች በቅርብ የሉምና እንደ መልካም ቤተሰብ አለንልህ እንበለው ። በጸሎት እናስበው ከጎኑም እንቁምለት ለሰርጀሪ እና ለተለያዩ ወጪዎች ይሆን ዘንድ የቻልንውን ሁሉ ወደ አካውንቱ እናስገባለት ። 👉 Commercial bank of ethiopia👉 1000362843441 ፍቅራችሁን ግለጡለት እየደወላችሁ አይዞህ በሉት ። ስልክ ቁጥሩ +251 911524288 ነው ። ከተረባረብን እና ካገዝንው አሁን ካለበት ሆስፒታል ይልቅ የተሻለ ህክምና ማግኘት ወደሚችልበት ይሄዳል ። ሁላችንም ብዙ ሰው ጋር እንዲደርስ #ሼር እናድርገው ።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
የምንሰብከው ወንጌል እግዚአብሔርን ካላከበረ፣ ክርስቶስን ካላገነነ፣ ሰውንም ትሁት ካለደረገ ወንጌል አይደለም። ወንጌል ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም እርሱ ስለ ሠራው ሥራ ነው። ወንጌል ሙሉ ነው ፣  ቃል ሥጋ ስለመሆን ፣ ከድንጌል ስለመወለድ ፣ ስለ ኃጢአተኞች መሰቀል ፣ በሦስተኛው ቀን መነሳቱ እንዲሁም እንደገና በፍርድ እንደሚመለስ እኛን ክርስቲያኖችን ወደ ራሱ እንደሚሰበስብ የሚተርክ ነው። ወንጌል ተስፋ የለላቸው ኃጢአተኞች አምነው የሚድኑበት ፣ ከኃጢአታቸው ንስሐ የሚገቡበት ፣ እግዘብሔርን መፍራት የምንማርበት ፣ እንዲሁም ክርስቶስ ስለሚመሠርተው መንግሥት ነው ፣ ወንጌል ሙሉ ነው። አሜን! @Christiantube11
Hammasini ko'rsatish...
🔥 1
አንድ ትንሽ ልጅ ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ? ተብሎ ሲጠየቅ " መልካም ሰው" ብሎ መለሰ። ምኞቱም ልጁም መልካም ናቸው። መልካም ሰው አቋሙ ያማረ፣ ንግግሩ የተቀመመ ሳይሆን እግዚአብሔር ያለው ነው። መልካም መሆን የማይሻ የለም ግን ያቅተዋል። መልካም ለመሆን ብዙ ነገሮች አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም እውነተኛ ለውጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ምክንያቱም እድሜ አይለውጥም፤ የትምህርት ደረጃ አይለውጥም፤ ሀብት ንብረት አይለውጥም። እግዚአብሔር ብቻ ይለውጣል፤ አዲስ ያደርጋል፤ ሙት ማንነትን ወስዶ ህይወትን ይዘራል።
Hammasini ko'rsatish...