cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር

"ወደ ደግነት በጎ አድራጎ ማህበር እንኳን በደህና መጡ" የድግነት ዋናው አላማ ለተቸገሩ ያቅማችንን ማድረግ እና እርስ በርሳችን መጠያየቅ መረዳዳት ነው ✍️ "ደግነት የአቅም ጉዳይ ሳይሆን የልብ ጉዳይ ነው " ባለን ነገር ሁሉ እንረዳዳ፤እንተዛዘን 👉"ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"👈 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ( 1000532242685 ) ናትናኤል ታደለ እና ቴዎድሮስ አበራ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
14 229
Obunachilar
+7624 soatlar
+2947 kunlar
+1 52630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  †  ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል  †  🕊 † እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ [አፍኒና ፊንሐስ] ያስተዳድሩ ጀመር:: በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና:: ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች [አፍኒና ፊንሐስ] ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ:: ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ:: ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ [ሳዖል] እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው:: ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን [ሳዖልን] ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም:: ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ [ቀንድ] አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :-
"ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል::
🕊  † ቅዱስ ሉክያኖስ  †   🕊 † ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር:: ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን [ሰኔ ፱ (9) ] ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል::
† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን::
† ሰኔ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩. ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ ፪. ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት ፫. ቅዱስ ዮሐንስ † ወርኀዊ በዓላት ፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት ] ፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ ኢትዮጵያዊ ] ፫. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት [ ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ ] ፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን ፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ ኢትዮጵያዊ ] ፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት ]
† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " † [ዕብ. ፲፩፥፴፪]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †
ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ 
         †              †               † @degnitKindness
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
ስንክሳር ሰኔ - ፱ - .mp38.35 MB
Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
የጥናት መዝሙሮች
ያሬዳዊ ወረቦሽ
የአጨብር ወረቦች
የሰርግ መዝሙሮች
የ ንግስ መዝሙሮች
የመዝሙር ግጥሞች
የማህበረ ቅዱሳን መዝሙሮች
መዝሙር ለማጥናት
🙋‍♂አንድጥያቄ ✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ?✟           👇👇👇 https://t.me/addlist/2TkBck2rFoxMjNk https://t.me/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk
Hammasini ko'rsatish...
⚫️ ሀ. በ አቤል
🔴 ለ. በቃየል
⚪️ ሐ.በ ዳዊት
🔵መ.በ እዮብ
Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
የጥናት መዝሙሮች
ያሬዳዊ ወረቦሽ
የአጨብር ወረቦች
የሰርግ መዝሙሮች
የ ንግስ መዝሙሮች
የመዝሙር ግጥሞች
የማህበረ ቅዱሳን መዝሙሮች
መዝሙር ለማጥናት
Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
💕መስከረም🌸
💕ጥቅምት🌸
💕ኅዳር🌸
💕ታህሳስ🌸
💕ጥር🌸
💕የካቲት🌸
💕መጋቢት🌸
💕ሚያዝያ🌸
💕ግንቦት🌸
💕ሰኔ🌸
💕ሀምሌ🌸
💕ነሀሴ🌸
💕🌸🌸ጷግሜ🌸🌸💕
🔹 ✥● ከሚከተሉት ውስጥ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ በየትኛው ትጠራ ነበር?? ✥●
Hammasini ko'rsatish...
🎤ድምፅ ተዋህዶ🎙
⚫️ሀ. ቶኔቶር
🔴ለ. የኩሽ ምድር
🔵ሐ. የሳባ ምድር
⚪️መ. ሁሉም መልስ ነው