uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish
925
Obunachilar
+224 soatlar
+27 kun
+830 kun
Postlar arxiv
ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም የሐይማኖት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በመወጣት የሰላም እሴቶችን ለትውልድ ለማስረጽ የሚደረገውን ርብርብ ማገዝ እንዳለባቸው ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው በገ/ጉ/ወ/ወረዳ በሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አማካኝነት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቀበሌ ለሚገኙ የሀይማኖት አባቶችና ባለድርሻዎች ያሳተፈ የግንዛቤ መድረክ ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው። በዚህ ጊዜም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሰላም የጋራ ሀብት ነው ብለዋል። ሰላም ለልማታችን አስፈላጊና ጠቃሚ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሰው ልጆች ህይወት መሰረት መሆኑን ጠቅሰው በአንጻሩ የሠላም እጦት አሉታዊ ጫናው የከፋ ስለመሆኑ አብራርተዋል። አክለውም በወረዳችን ያሉ ቤተ-እምነቶች ህብረታቸውን በማጠናከር ያለውን የሰላም እሴቶች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የጽ/ቤቱ የሃይማኖት ዕምነት ጉዳዮች እሴት ግንባታ ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ ወይዘሮ አስቴር አለሙ ለመድረክ የተዘጋጀ መወያያ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል። የጉባኤው መካሄድ ለቀጣይ ስራዎች ስኬታማነት የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ያስቻለ መሆኑን፣ በወረዳው ያለውን አበረታች የሆነ የሃይማኖት ተቋማት መቻቻልና መከባበር ይበልጥ አጠናክረን በማስቀጠል ለሰላም እሴቶች ግንባታ የሚጠበቅብንን እንወጣለን፣ በወረዳና በቀበሌ ያሉ የቤተ እምነቶች አደረጃጀቶች ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ተሳታፊዎቹ መንግስት በተሻለ መልኩ ህብረቱን በበጀት ሊደግፈው እንደሚገባም ጠይቀዋል። የወረዳው የሃይማኖት ተቋማት ህብረት ሰብሳቢ ሼህ አብድልበር ዘይኑ ከመድረክ ለተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ተከትሎ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን በማንሳት በቤተ እምነቶች መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር በማጎልበት የወረዳችንና የሃገራችን ልዕልና ከዳር ማድረስ ይጠበቃል ብለዋል። አያይዘውም በተተኪው ትውልድ ላይ የስነ- ምግባር ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ያነሱ ሲሆን ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከር እንዳለበት አውስተው ከመድረክ የተገኙ ግብዓቶች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራም ገልጸዋል። የወረዳው የሃይማኖት ተቋማት ህብረት ምክትል  ሰብሳቢ ቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል ሳሙኤል በበኩላቸው ጉባኤተኞች የግንኙነት አግባባቸውን በማጠናከር ጸረ-ሰላም ሃይሎች ሊያስከትሉ የሚችሉትን የሰላም እጦት አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሰማ በድሩ መንግስት ከሐይማኖት ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻዎች ጋር በትብብር ይሰራል፣ የሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ተቀናጅተን በመስራት የጸረ-ሰላም ሃይሎችን ሴራ መከላከልና የህዝባችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጡን ሂደት አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ያሉት አቶ ሙሰማ መንግስት ለሐይማኖት ተቋማት እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን የስነ-ምግባር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ከወረዳው የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኦፊሰር የጋራ የውል ስምምነት ገብተዋል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በተፈጠረው የስምምነት መድረክ ቀጣይ ተቀናጅቶ ለመስራት ትልቅ አቅም የሚሰጥ ከመሆኑ አንጻር ቀጣይ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ ለመሆን ለማምጣት አጋዥ ነው። በመድረኩ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን የስነ-ምግባር ኮሚሽን አመታዊ አፈጻጸምና የቀጣይ አመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል። በውይይቱ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን የስነ-ምግባር ኮሚሽን አመራሮች እና በየተቋሙ የሚገኙ የስነ-ምግባር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። በመጨረሻም የውል ስምምነቱን የሁለቱም ተቋም ኃላፊዎች በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።

ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የክረምት በጎ ፍቃድ አካል የሆነው በመሃል አምባ ከተማ ለአቅመ ደካማ ግለሠቦች የቤት ግንባታ ማስጀመር እና አነስተኛ የእንጨት ድልድይ ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገልጿል። "በጎ ፈቃደኝነት፣ለማህበረሰብ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል 2018 በክርምት ወራት በጎ ፍቃድ በ15 የስራ መስኮች 39113 ወጣቶችን በማሳታፍና አገልግሎት በመስጠት 77 ሺህ 143 የህ/ተሰብ ክፍሎች ለማስጠቀም እና 44 ሚሊዮን 144,854 ወጪ ለማዳን ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል።

ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጅማ ወለኔ ከተማ 1.2 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ መብራት ዝርጋታ እና የጥልቅ ጉድጓድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ወደ መብራት ለመቀየር 4 ኪ.ሜ የዝርጋታ ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ጠቅላላ አመራር በወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በውይይቱም በቅርቡ በጉራጌ ዞን የሚነገሩ ቋንቋዎች እንደየ ዘዬው የስራ ፤ የትምህርትና የሚዲያ ቋንቋ እንዲሆን ተዘጋጅቶ በዞኑ ምክር ቤት በጸደቀው ረቂቅ ደንብ መነሻ ተደርጎ የሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎችን በተመለከተ በውይይቱ የተዳሰሰ ሲሆን የመድረኩ አላማም የወረዳው አመራር በዚህ ጉዳይ እና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ግልጸኝነት በመያዝ ረገድ ያለን ጉድለት በመሙላት በተዛባ መንገድ እየተሠራጩ ያሉ መረጃዎችን በማስተካከል ለህብረተሠቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲሰጥ ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡  በመድረኩም ይህን ጉዳይ የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት በተለይም የዞናችንና የወረዳችን ህዝብ ቋንቋውንና ባህሉን በማሳደግና ከፓርቲያችን ብልጽግና ጎን ሆኖ እንዳይጠቀምና እንዳይሳተፍ አካባቢውን የተረጋጋ ፖለቲካ እንዳይኖር የተለያዩ አካላቶች በተለይም በማህበራዊ ድህረ ገጽ የጉራጌ ዞን አንድ ወጥ የሆነ የቋንቋ ዘዬ ተዘጋጅቶ በሁሉም ወረዳዎች የስራና የትምህርት ቋንቋ በማድረግ የየወረዳውን ዘዬ በማጥፋት ተግባራዊ ይደረጋል የሚል የፈጠራ ወሬ በመፍጠርና በማራገብ እንዲሁም የተሳሳተ መረጃ በመልቀቅ ህዝብን ለማሳሳት እየሰሩ የሚገኙ የተለያዩ አካላቶች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በመጨረሻም የወረዳው አመራር ተገቢውን ግንዛቤ መፍጠር የረቂቅ ደንቡ አላማ ቋንቋውን ለማሳደግ የተያዘው እቅድ በተገቢው በመረዳት ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ መግባባት ላይ በመድረስ እንደ ወረዳም ዘዬውን ተከትሎ ቋንቋውን ማሳደግ እንደሚገባና በተለያየ መንገድ ከሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች እራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባ እንዲሁም መረጃዎችን ከትክክለኛ ምንጭ ወይንም የመንግስት መዋቅር ሊያገኝ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው የሆስፒታሉ የቦርድ አመራሮች የ2017 ዓ.ም የ12 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሞ የተለያዩ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ዛሬ ባስቀመጠበት ወቅት ነው። በዚህ ጊዜም የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ተወካይ ዶክተር ሙሉጌታ ቱሉ የተቋሙን የ2017 ዓ.ም የ12 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት በማጠናከር ለሁሉም ህብረተሰብ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በጥራትና በፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማዳረስ ዕቅድ ይዞ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ጥልቀት ያለው ውይይትና ምክክር የተደረገ ሲሆን የተቋሙ የአገልግሎት አሠጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እየተስተዋለ ቢሆንም በአንፃሩ በጉድለት የተነሱትን ወስዶ ማረም እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ሆስፒታሉን በግብዓት ለማሟላት እየተደረገ ያለው ርብርብ መቀጣጠል እንደሚኖርበት፣ የህክምና ግብዓቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ ያነሱት ተሳታፊዎች ያሉትን ግብዓቶች እና የሰው ሃይል አቀናጅቶ በመምራት ለተሻለ ውጤት መስራት እንደሚገባ በማንሳት ከመድረኩ የተገኙትን ግብዓቶችን ወስዶ አፅንኦት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅ የሚሉት ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፈይሰል ሀሰን መንግስት ተቋሙን በግብዓትና በሰው ሃይል ለማሟላት የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው በጉድለት የተነሱ ጉዳዮችን በባለቤትነት ወስዶ መስራት ይገባል ብለዋል። የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ውይይቱ የማህበረሰብ ችግር ሊፈቱ የሚያስችሉ ቁልፍ ጉዳዮች የተዳሰሰበትና ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል። አክለውም ተቋሙን የመረጃ ጥራት ላይ አፅንኦት ሰጥቶ መስራት ይኖርበታል፣ መላው ህብረተሰብ እና ተወላጅ ባለሃብቶች የሆስፒታሉን የግብዓትና ተያያዥ ችግሮች መቅረፍ እንዲቻል እያደረጉት ላለው እገዛ ምስጋናቸውን በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም አመስግነው በቀጣይ ጉድለቶችን ለመፍታት የትኩረት አጀንዳ ተደርጎ ይሰራልም ብለዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበበኩላቸው ሆስፒታሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችን እያሳየ መሆኑን ጠቅሰው ከህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎት አንፃር የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሹ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ መስራት ይጠበቃልም ብለዋል። አያይዘውም መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል በአንፃሩ ባለሙያዎች ሙያዊ ስነ- ምግባር በተላበሰ መልኩ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት የዜጎች ጤና ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ርብርብ ማገዝ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል። በዉይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን የቦርድ አባላቱ አሳልፈዋል ከነዚህ መካከልም የሜዲካል ዳይሬክተር እና የስራ አስኪያጅ ምደባ፣ የእናቶች ማረፊያ ክፍል ግንባታ፣ Radiographer ባለሙያ ቅጥርና የባለሙያዎች የትርፍ ጊዜ ክፍያ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል። በመጨረሻም ዶክተር ሙሉጌታ ቱሉ አለሙ የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ሆነው በአብላጫ ድምፅ ተሹመዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአብይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ከዞን በተሰጠው ግብረ መልስ ላይ ውይይት ተካሄዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን የበጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት በተደረገው ድጋፍና ክትትል በተሰጠው ግብረ ላይ እንዲሁም የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም የአብይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የበጎ ፈቃድ ስራዎች በተገኙ አበረታች ውጤቶችና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተቀምጧል። በውይይቱ ላይ የጉረጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው ደጋፊ አመራር፣የጉረጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሸሃቡ እንዲሁም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እና የወረዳው የበጎ ፍቃድ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ስኬታማነት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድል ረሂም ርዳ ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ግምገማ አካሂዷል። የወረዳው ወጣቶችና ስፓርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በወረዳ ደረጃ እስካሁን በ15 የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ26 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ከ49 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ከመንግስትና ከህብረተሠቡ ሊወጣ የነበረውን 29 ሚሊዮን 221 ሺህ 490 ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውቀዋል። 12 የአቅመ ደካማና አረጋዊያን አዳዲስ ቤቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን እንዲሁም 17 ቤቶች የማደስ ስራ መከናወኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል። የውይይት መድረኩን የመሩት ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራ የመልካም አስተሳሰብ እሴቶች መገለጫ መሆኑን ገልጸው ውጤቱ የግለሰብን ብሎም የሀገርን የመልካምነት እሴት አጉልቶ የሚያሳይ መረዳዳትን፣ አብሮነትንና አንድነትን የሚያስተሳስር ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል። አቶ አብዳል ረሂም ርዳ አክለውም የብልጽግና ፓርቲ አንዱ መለያ እሴቱ ሠው ተኮር መሆኑን ጠቅሠው የበጎ ፍቃድ ተግባራት በረካታ አቅመ ደከማ ዜጎችን ማዕካል አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ስኬታማነቱ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑንም አስተውቀዋል። የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም አብይ ኮሚቴው በየ ሴክተሩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በማኔጅመንት ዋና አጀንደ አድርጎ ሊገመግም እንደሚገባ ገልጸው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ የድጋፍና የክትትል አግባብ ሂደት በማጠናከር በየደረጃው ያለውን ማህበረሰብ በማስተባበር ተግባሩን ቅንጅተዊ አሰራር በመጠቀም በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የውይይት መድረኩ በተሻለ ሁኔታ የተፈጸሙ ተግባራት በተገቢው ማጠናከር እንዲሁም በጉድለት በተለዩትን በቀሪ የክረምት ጊዜያት አሟጠው በመጠቀም ከችግራቸው ፈጥነው እንዲወጡ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።