የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
925
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
+930 kun
Postlar arxiv
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም
👉🏼 ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆኑ ቀበሌያትን በመፍጠር ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል እንደሚቻል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የመንግስት ቀዳሚ አጀንዳ በዘላቂ ልማት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው!!!
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 የግብር ዘመን 207 ሚሊዮን 860 ሺህ 225 ብር ገቢ በመሠብሠብ የተያዘውን እቅድ 92 በመቶ ተፈጻሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ 30-40-30 የአቮካዶ ልማት በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ድጋፍ የተሰጠ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመንግስት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከላ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን በዘንድሮ የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራዎች ቁጥራቸዉ ከ805 ሺህ 268 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማስጠቀም ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የ2017/18 በጀት አመት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የመክፈቻ መርሃ-ግብር በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ አፅንኦት ሠጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨
👉🏼የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም ወረዳዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ችግኝ ተከላ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨
ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም
ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆኑ ቀበሌያትን በመፍጠር ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል እንደሚቻል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በወለጋዲሴ ቀበሌ ከአይነ-ምድር ነፃ የሆነ መንደር በመፍጠር የምረቃ ፕሮግራም በዛሬው እለት በተካሄደበት ወቅት ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የቀበሌው ደጋፊ አመራር አቶ ረሻድ ኢብራሂም እንደተናገሩት ጤናችንን በተገቢው ስንጠብቅ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ አቅማችን ከፍ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።
ተግባሩ ቀጣይነት እንዲኖረው አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው የቀበሌው ማህበረሰብ ሳይዘናጋ የጤና ተግባር ቀጣይነት እንዲኖር በትኩረት መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብድልቃሃር ረሻድ በበኩላቸው ንጽህናው ያልተጠበቀ አካባቢ ምግብና ውሃን በመበከል ለተለያዩ በሽታዎች መንስኤ እንደሆነ ጠቁመው እንቅስቃሴው ጤናማ ዜጋ ለማፍራት ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።
የግልና አካባቢ ንጽህና ለእናቶችና ህጻናት ጤና መጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ በግለሰብ ደረጃም ሆነ መንገዶች ዳር አካባቢ የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶችን ማስፋፋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ሞዴል መጸዳጃ ቤት የገነቡ አርሶ አደሮች መጸዳጃ ቤት የመስክ ምልከታ የተካሄደ ሲሆን ቀበሌው ከአይነ-ምድር ጽዱ መንደር በመፍጠር ለምርቃት እንዲበቃ ላደረጉ የቀበሌ አመራሮች የተዘጀላቸውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከዕለቱ ተጋባዥ እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።
ዘገባው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 የግብር ዘመን 207 ሚሊዮን 860 ሺህ 225 ብር ገቢ በመሠብሠብ የተያዘውን እቅድ 92 በመቶ ተፈጻሚ ማድረግ መቻሉን ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገቢ አፈጻጸሙ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በብር 85,047,582 ብልጫ እንዳለው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልጀሊል ቱሉ እንዳሉት በበጀት አመቱ የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት ግብ ተጥሎ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
ቅ/ጽ/ቤቱ በግብር አመቱ ከመደበኛ ገቢ 193 ሚሊዮን 934 ሺህ 336 ብር ገቢ ለመሰብሰብ ያቀደ ሲሆን 183 ሚሊዮን 784 ሺህ 122 ብር በመሰብሰብ 94.77 % ማስካቱን የገለፁት አቶ አብድልጀሊል ቱሉ ከማዘጋጃ ቤት ገቢ 31 ሚሊዮን 070 ሺህ 462 ብር ለመሰብሰብ በማቀድ 24 ሚሊዮን 076 ሺህ 103 ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 77.5 ተፈፃሚ ተደርጓል ሲሉ ኃላፊው አስታውቀዋል።
በድምሩ 225 ሚሊዮን 004 ሺህ 798 ብር ለመሰብሠብ ታቅዶ 207 ሚሊዮን 860 ሺህ 225 ብር ገቢ በመሠብሠብ የተያዘውን እቅድ 92.4 በመቶ ተፈጻሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
የገቢ አፈጻጸሙ ከባለፈው 2016 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በመደበኛ 75,297,886/69.41% እና ከመዘጋጃ አንፃር 9,749,695 ብር ብልጫ ያለው መሆኑን አቶ አ/ጀሊል ቱሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ኃላፊው ባስተላለፉት መልዕክት
ግብር ለማህበረሰብ የሚያስፈልጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በውጤታማነት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሠውየገቢ አሰባሰብ ስራውን ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንዲቻል ባለድርሻ አካላት እያደረጉት ያለውን ተሳትፎና ቅንጅታዊ አስራር ከወትሮ በላቀ መልኩ አጠናክረው ማስቀስጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ሲል የወረዳው የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ ቤት ዘግቧል።
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም
የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ 30-40-30 የአቮካዶ ልማት በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ግብርና ጽ/ቤት ድጋፍ የተሰጠ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመንግስት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከላ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ 30-40-30 የአቮካዶ ልማት በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ግብርና ጽ/ቤት ድጋፍ የተሰጠ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ በመንግስት ተቋማት ማለትም በገደባኖ 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች፣ በመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ፍይናንስ እና ግብርና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከላ ተካሄደ።
ተከላው ልዩ የሚያደርገው በገደባኖ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ባህር ዛፍ በመቁረጥ ወደ አቮካዶ ልማት በመቀየር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ሽግግር ጉዞ ተቋማት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ።
በተከላው መርሃ ግብር ላይ የጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን፣የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን፣ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊና ም/አስተዳዳሪ አቶ ከድር መርጋ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖልቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል እንዲሁም የወረዳው አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች፣የት/ት ቤቶች ር/መምራንና መምህራኖች በተገኙበት የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ሐምሌ 09/2017 ዓ ም
የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የ2017 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የዜጎች ቻርተር ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በሁሉም ተቋማት ለማህበረሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ተማም አደም ገልጸዋል።
በመድረኩ የጽ/ቤቱ የልማት ና የመልካም አሰተዳደር የቡደን መሪ የሆኑት አቶ ሙስጠፍ ሽፍ አማካኝነት
የ2017 ዓ.ም በ4ኛ ሩብ አመት በሴክተሩ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ከባለድርሻ አካላት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮች ምላሽና አስተያየቶች ተሰጥቶባቸዋል።
የወረዳው የፐብሊክ ሠርቪስ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ተማም አደም በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት የተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመፍታትና አገልግሎት አሰጣጡን ሊያረጋግጡ የሚችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በጽ/ቤቱ በተቋማት የሚነሱ የመልካም አሰተዳደር ችግሮች ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ በመስጠት የህ/ሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚሰሩ ተግባራት የህዝብ ክንፉ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናክር እንደሚገባም ገልጸዋል ::
አክለውም አቶ ተማም አደም ተቋማት የሚቀርቡ አቤቶታና ቅሬታዎች የመፍታት እና ሚፈለጉ መረጃ በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ከማስተላለፍ አንጻር የማስተዋሉ ችግሮች በቀጣይ ሊታረሙ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በሁሉም ተቋምት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በአግባቡ እንዲያገኝ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
የአገልግሎት ፈላጊውን የማህበረሰብ ክፍል ፍላጎት ማሟላት የፐብሊክ ሠርቪስ ተቋም ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት እና የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ወስደው በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የህዝብ ክንፎች፣ እንዲሁም የሴክተር የልማት እቅድና የሰው ሀብት ባለሙያዎች
እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን በዘንድሮ የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራዎች ቁጥራቸዉ ከ805 ሺህ 268 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማስጠቀም ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዞን ዓቀፍ የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ እወጃ መርሃ-ግብር ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመርሃ-ግብሩም የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪ አካል ጉዳተኛ ለሆኑት ወ/ሮ ሃዋ ረዲ ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚፈጅ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።
በዚህ ወቅትም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት እያከናወናቸው ባሉ ሠው ተኮር ስራዎች በሃገር ዓቀፍ እና በወረዳ ደረጃ በርካታ ዜጎችን ማስጠቀም እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ በበኩላቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት እና መልካም ፈቃድ በህብረተሰቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍ ነፃ አገልግሎት የሚያበረክቱበት ተግባር ሲሆን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እድሜና ፆታ ሳይገድበው ሰብዓዊነት መርህን ብቻ መሰረት በማድረግ የሚሰጠን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ነው ብለዋል፡፡
አክለውም በዘንድሮ በጀት አመት በዞኑ 395 ሺህ 183 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በ14 የስምሪት መስኮች በማሰማራት፣ 805 ሺህ 268 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና 386 ሚሊዮን 267 ሺህ 475 ብር የሚገመት አገልግሎት ለመስጠት ግብ መያዙን ያወሱት አቶ ሙራድ ረሻድ በአጠቃላይ በዞን ደረጃ በዘንድሮው የበጎ አድራጎት ተግባር ውስጥ መጠለያ ቤት ለሌላቸው አቅመ-ደካማ ዜጎች ከ295 በላይ አዲስ ቤት ለመገንባት መታቀዱን ጠቅሰው የዚህ አንድ አካል የሆነው የወይዘሮ ሀዋ ረዲ አዲስ መኖሪያ ቤት ግንባታ በዋናነት ተጠቃሽ እንደሆነ ገልጸው ለቤት ግንባታው ወጪ የጉራጌ ዞን መንግስት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የሚሸፈን ሲሆን 150 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት የወረዳው መንግስት በነፃ ማቅረቡን አስታውቀዋል።
የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሠን
እንደገለፁት በጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የጀመሩት የበጎ አድራጎት ተግባር አሁን ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና መተሳሰብ ባህል ማጎልበት ያስቻለ ስለመሆኑ ጠቁመው በበጎ ተግባራት አማካኝነትም በዞናችን በርካታ የማህበራዊ ችግር ያለባቸውንና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማስጠቀም እንደተቻለ በማንሳት በዞን ዓቀፍም ሆነ በወረዳው የተያዙ የበጎ ስራዎች ተግባራት ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የሚደረገውን ርብርብ ወጣቶችና ህብረተሰቡ ማገዝ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በዕለቱ ለአቅመ ደካማና አካል ጉዳተኛ የሆኑት ወ/ሮ ሀዋ ረዲ የአዲስ መኖሪያ ቤት ማስጀመር ስራ እና በመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።
