የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
918
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+27 kun
+930 kun
Postlar arxiv
በምርጫ ብቻ፡- የነገዋ ኢትዮጵያ በዛሬ ካርዳችን
******
ኢትዮጵያ ወደ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምታደርገው ጉዞ፣ ከስጋት ወጥተን እንደ በሰለ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለነገው ብሩህ ተስፋ የምንሰለፍበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
ምርጫ ሥልጣን በጋራ ስምምነትና በውክልና የሚገኝበት ዘመናዊ የፖለቲካ መገለጫ ነው።
ምርጫ የሀገር ሕዝባዊ ውል የሚታደስበት፣ የዜጎች ፍላጎትና የሀገር አቅጣጫ የሚናበቡበት የሥልጣኔ መድረክ ነው::
ከዚህም በላይ ደግሞ ሥልጣን ከጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን በምርጫ ሳጥን የሚረጋገጥ መሆኑ ለሀገራችን የሥልጣኔ ጉዞ ወሳኝ እርምጃ ነው።
ይህ ሂደት ቅቡልነት ያለው መንግሥት እንዲፈጠር፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለው መተማመን እንዲጨምር፣ ተጠያቂነት እንዲሰፍንና በኃይል የመገፋፋት ፖለቲካ ቀርቶ የሐሳብ የበላይነት እንዲነግሥ ያደርጋል።
ምርጫን ማካሄድ መቻል የዲሞክራሲያዊ ብስለት ማሳያ ሲሆን፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለፍትሕ ሥርዓቱ መጠናከር የሚያስፈልገውን የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠርም ትልቅ መሣሪያ ነው።
#ኢትዮጵያ #7ኛውጠቅላላምርጫ #ዴሞክራሲ #የነገዋኢትዮጵያ #EBC
ጥር 29/2018 ዓ.ም
በአዋጁ የተከለከሉት የፕላስቲክ ከረጢቶች የትኞቹ ናቸው?
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ ካሳለፍነው ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ሕብረተሰቡም አዋጁ የወጣበትን ዓላማ በመረዳት የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ባለመጠቀም የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ በአዋጁ የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች የትኞቹ ናቸው የሚለው በሕብረተሰቡ ዘንድ ግርታ መፍጠሩን ፋና ዲጂታል ባደረገው ቅኝት ለመረዳት ችሏል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ባለሱቆች እና ሸማቾች እንደሚሉት÷ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች የሚለው ሃሳብ በተወሰነ መልኩ ግርታን ፈጥሯል፡፡
ስለሆነም የፕላስቲክ ከረጢቶች ማለትም አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እና መልሶ ዑደት (ሪሳይክል) የሚደረጉትን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የከተማ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ክትትል ዴስክ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ዓለሙ ለፋና ዲጂታል በሰጡት ማብራሪያ÷ በአዋጁ የተከለከሉት የፕላስቲክ ከረጢቶች በተለምዶ “ፌስታል” ተብለው የሚጠሩት ናቸው፡፡
እነዚህ ፕላስቲኮችም አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ውለው በቀጥታ የሚወገዱ ሲሆን÷ በመልሶ ዑደትም ጥቅም ላይ እንደማይውሉ አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ክልከላው ኩርቱ በሚል ስያሜ የሚታወቀውን ፌስታል ጨምሮ በተለያየ ዲዛይን የተሰሩና በቀላሉ በስብሰው ከአፈር ጋር የማይዋሃዱ የፕላስቲክ ከረጢቶች ወይም ፌስታሎችን እንደሚያካትት አብራርተዋል፡፡
ከጥር 23 ቀን ጀምሮ ባለው የትግበራ ሒደት ላይ ዳሰሳ መደረጉን ጠቁመው÷ በዚህም ሕብረተሰቡ አዋጁን ለመተግበር ያሳየው ተነሳሽነት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
በአተገባበር ሒደቱ ላይ ከግንዛቤ ማነስ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለማስተካከል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
ለዚህም መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻዎች በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው÷ ሕብረተሰቡም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል ከፕላስቲክ ያልተሰሩ የተኪ መያዣዎች ዋጋ ገበያ ላይ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸው÷ ይህም ሁሉም ባለድርሻዎች በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው የተከሰተ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከፕላስቲክ ያልተሰሩ የተኪ መያዣዎችን አቅርቦት ለማሳደግ ይሰራል ነው ያሉት፡፡
በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ 1383/2017 መሰረት የፕላስቲክ ከረጢቶችን የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ ከ2 ሺህ ብር የማያንስ ከ5 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት ይጣልበታል፡፡
FMC (ኤፍ ኤም ሲ)
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ መራዘምን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!!
ቦርዱ የካቲት 1/2018 ዓ/ም የሚጠናቀቅ የነበረው የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም ማራዘሙን ገልጿል!!
ጥር 29/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ግምገማና የጠቅላላ አመራር የምዘና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ባለፉት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ላይ የነበሩ የተግባር ውጤታማነትን፣ ሃላፊነትን በብቃት ከመወጣት ፣የአመራር ስብዕናን ከመላበስና ሌሎች የፓርቲ ግዴታዎችን ከመወጣት አንፃር የአመራሩ ቁመና የሚታይበት እንደሆነ ተገልጿል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የምዘና መድረክ የውይይቱ መነሻ ሰነድ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት በማድረግና ለአመራሩ ኦረንቴሽን በመስጠት የተጀመረ ሲሆን በሶስት ቡድኖች ተከፋፍሎ ምዘናው ቀጥሏል።
በምዘና መድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን እንደተናገሩት የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን መሠረት ያደረገ የአመራር ምዘና ማድረግ በወረዳው ሁለንተናዊ ልማትን ሊያረጋግጥ የሚችል አመራር ለመፍጠር አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል።
አቶ አብዶ አክለውም አክለውም ከምዘናው ትምህርት በመውሰድ ወቅቱን የሚመጥን የተሻለ እይታ ያለው በመፍጠርና በመፍጠን እሳቤ የሚመራ አመራር መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፈወታ ሁሴን እንደገለጹት በምዘና መድረኩ የመገነባባት መርህ በመከተል አመራሩ ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎች በትክክል ገምግሞና ተረድቶ ከመምራት አንጻር የሚታዩ ውስንነቶች በማረም የአስተሳሰብ አንድነት ፈጥሮ ውጤት ለማስመዝገብ አጋዠ መድረክ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አ/ረሂም ርዳን ምዘናው በአመራሩ መካከል የተግባር እና የአስተሳሰብ አንድነትና ተግባቦት በማጠናከር የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ትልቅ አቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አ/ረሂም ርዳን ጨምሮ አጠቃላይ የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል።
ጥር 28/2018 ዓ.ም
የእቅድ ፣ሪፖርት አዘገጃጀትና የሶሽዮ ኢኮኖሚ መረጃ የአሰራር መመሪያ ጠቀሜታ ዙርያ ስልጠና መሰጠቱን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፕላን ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
የገ/ጉ/ወ//ወረዳ ፕላን ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አ/ከሪም ናስር በስልጠናው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የአንድ እቅድ ጥራት የአፈፃፀም ችግሮች የሶሺዮ መረጃ ጥራት በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ የወጥነት ችግሮች መኖራቸውና አጠቃላይ መመሪያዎች ተግባራዊነት ላይ ክፍተቶችን ለመሙላት ስልጠና መሰጠቱ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።
አክለውም ስልጠናው የሶሺዮ–ኢኮኖሚ ሁኔታ ትንታኔ፣ የልማት እቅድ አዘገጃጅትና አፈጻጸም፣ የሀብት አጠቃቀም እና የህዝብ ተሳትፎ አስፈላጊነት ያተኮረ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው ፣ ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሶሺዮ–ኢኮኖሚ እቅዶችን በሳይንሳዊ መንገድ መንደፍና በትክክለኛ አፈጻጸም ለመተግበር አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል ።
የዕለቱ የስልጠና ስነድና የሶሺዮ ኢኮኖሚ በወ/ሮ ኑሪቱ በዳኔ እና በአቶ በህሩ ጀማል ቀርቦ ሰፊ የቡድን ውይይት እና ገለጻ በማድረግ ስልጠናው መረዳታቸውን እና ለቀጣይ ስራዎቻቸው አስተዋጽኦ እንደሚያደርግላቸው ሰልጣኞቹ ገለጻ በማድረግ አሳይተዋል።
በመጨረሻም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፕላን ልማት ፅ/ቤት የኃላፊ ተወካይ አቶ አ/ከሪም ናስር ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው እለት ያገኙትን ግንዛቤ ይበልጥ በማዳበር በየተቋማቸው በተገቢው መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው በቀጣይ ተጨማሪ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ያሉብንን የግንዛቤ ክፍተት ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ እንሰራለን ብለዋል።
በስልጠናው ልማት እቅድና የሶሺዮ ኢኮኖሚ በለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ሲሆን
በቀረበው ውይይት እና ገለጻ ከዚህ በፊት ያልነበረላቸው ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ጥር 26/2018 ዓ.ም
የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ ገለጽ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጊ/ዲመቱ ቀበሌ በጎንግ ንዕስ ተፋሰስ የ2018 ዓ.ም ወረዳዊ የተፋሰስ እወጃ ፕሮግራም በተካሄደበት ወቅት ነው።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ስራ ግብርናን ከማዘመን ባሻገር የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ እንዲሻሻል፣ገቢው እንዲጨምር፣ እድገትና ብልፅግናው እንዲረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ በተያዘለት ቀን ተሰርቶ መጠናቀቅ እንዳለበት ዋና የመንግስት ተጠሪው አሳስበዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ እና የተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ሰማን በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።
በዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በወረዳው በ37 ቀበሌዎች በ32 ንዑስ ተፋሰስ 10 ሺህ 4 መቶ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለጽት አቶ አ/ረሂም ሰማን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በማልማት የተጣለውን ግብ ለማሳካት የማህበረሰቡ ጉልበት በአግባቡ ለመጠቀም እየተሰራ ሲሆን በዚህም በዘንድሮ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ላይ 54 ሺህ 2 መቶ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አስታወቀዋል።
በዘንድሮ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ 30 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
ጥር 26/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በጊ/ዲመቱ ቀበሌ በጎንግ ንዕስ ተፋሰስ የ2018 ዓ.ም ወረዳዊ የተፋሰስ እወጃ ፕሮግራም ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች የ2018 ዓ.ም የተፋሰስ እወጃ ፕሮግራም ተካሄዷል።
በዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በወረዳዉ በ37 ቀበሌዎች በ32 ንዑስ ተፋሰስ 10 ሺህ 4 መቶ ሄክታር መሬት ለማልማት ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው።
ባለፉት ዓመታት በወረዳዉ በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ችሏል።
በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ለማልማት የተጣለውን ግብ ለማሳካት የማህበረሰቡ ጉልበት በአግባቡ ለመጠቀም እየተሰራ ሲሆን በዚህም በወረዳዉ በዘንድሮ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ላይ 54 ሺህ 2 መቶ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም ተመላክቷል።
በዘንድሮ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ 30 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
በእወጃ ፕሮግራሙ ላይ የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ እና የወረደው የግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ሰማን በጊ/ዲምቱ ቀበሌ ተገኝተው አስጀምረዋል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ጥር 25/2018 ዓ.ም
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኢንተርናሽናል ኮል ኦርጋናይዜሽን የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የገሬኖ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 "የተቀናጀ የግብርና ልማት ጥረት ለቤተሰብ ብልጽግና ስኬት "በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት 2018 ዓ.ም የበልግ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
"ደም እንለግስ ህይወት እናድን" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሀ ግብር በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሃል አምባ ከተማ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት የከተሞች ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስተወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅህፈት ቤት የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃልያ ፈተና ተሰጠ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
