የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
Kanalga Telegram’da o‘tish
Ko'proq ko'rsatish
925
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+67 kun
+1130 kun
Postlar arxiv
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ "ከተማዬን አፀዳለሁ ውብና ፅዱ የመኖሪያ ከባቢ እፈጥራለሁ '' በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በየሳምንቱ ቅዳሜ ጠዋት 12 ሠዓት እስከ 2 ሠዓት በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ማዘጋጃ ቤት ከተሞች ነዋሪዎችን በማሳተፍ የፅዳት ዘመቻ በቋሚነት የሚካሄድ ይሆናል።
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደሳ ቀበሌ በመኸር በወጣቶች ማህበር እየለማ ያለ የጤፍ ማሳ በከፊል፦
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
“International call Organization” የተሰኘው ግብረ-ሰናይ ድርጅት በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ገሬኖ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከ10 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚያስገነባው የትምህርት ፕሮጀክት ከወረዳው ት/ቤቶች ጽ/ቤት እና ፋይናንስ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር የውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራረመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በውል ስምምነቱ ወቅትም የ”International call Organization” ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሪስ በሽር እንዳሉት ድርጅታቸው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ምቹ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የውል ስምምነቱ ስለሚያካትተው የትምህርት ቤት ግንባታን አስመልክተው እንደገለጹት በወረዳው ገሬኖ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ባለ 2 ብሎክ 8 መማሪያ ክፍል እና ከ 400 በላይ ኮምባይን መቀመጫ ወንበር የሚያካትት ስለመሆኑ ጠቅሰው ፕሮጀክቱም ከ10 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር በላይ በጀት እንደሚጨርስ አስታውቀዋል።
አቶ ፋሪስ በሽር የበጀት ምንጩን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን 80 በመቶውን ድርጅቱ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ በህብረተሰብ ተሳትፎ እንደሚሸፈን እንደሆነ አብራርተዋል።
በአጭር ጊዜ ወደ ግንባታ እንደሚገቡም ስራ አስኪያጁ አክለው ገልጸዋል።
የወረዳው ት/ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ መንግስት ተደራሽ ባልሆነባቸው የልማት ስራዎች ላይ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
አያይዘም በወረዳው የተጀመረውን የትምህርት ልማት በማገዝ ረገድ “International call Organization” እያበረከተ ያለው ሚና ተደናቂ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ከሚያከናውናቸው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ ቀደም ሲል አንጮት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አንድ ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል የያዘ የማስፋፊያ ግንባታ አጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራ ማስረከቡን አስታውሰው በቅርቡ ወደ ግንባታ የሚያስገባውን የዉል ስምምነት መፈጸም በመቻሉ በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የትምህርት ተቋሙ ተገንብቶ ለአገልግሎት ሲበቃ በተማሪ ውጤት ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ አለማየሁ ኬኔ በስምምነቱ ወቅት ገልጸዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅህፈት ቤት የከተሞች ልማትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስተወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከ/ል/ኮ/ል/ፅ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቢሮ ግንባታ፣ የመሀል አምባ ጌጠኛ ንጠፍ መንገድ፣በመንገድ ከፈታና ጠጠር የማልበስ የእስትራክቸር ስራ እና የድልድይ ፣ የወለጋዲሴ የማዘጋጃ ቤት የቢሮ ግንባታ በበጀቱ ከተከናወኑ ተግባራት በዋናነት ተጠቃሾች መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተማም አደም አስታውቀዋል።
ጽህፈት ቤቱ በ2018 በጀት አመት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመያዝ በከተሞች የተለያዩ መሰረተ-ልማቶች ዝርጋታ ለመከወን እቅድ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን አቶ ተማም አደም ተናግረዋል።
በበጀት አመቱ ከተያዙ ዋና ዋና ተግባራት መካከል የመሀ አምባ ከተማ ከቦኖ-ሀጂ ገረሱያ ፔንሲዮን ጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድ እና መነህሪያ እስከ ጨፌ ከልቨርት የከተማ ማስፍፊያ የተከፈተው መንገድ እና ጠጠር የማልበስ ፣ ጎራ ማዘጋጃ ቢሮ ግንባታ፣ወለጋዲሴ የማዘጋጃ ቢሮ ግንባታ ማጠናቀቂያ፣ ኢንጌ ከተማ አዳራሽ ማስጨረሻ፣ በከተሞች የመብራት የማስፋፊያ እና ሌሎች የልማት ስራዎች ለመስራት እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የመሀል አምባ ከተማ አስተዳደር ጥያቄ ከፈርጅ 4 ወደ ፈርጅ 3 እና የገጠር እሰኬች ማእከላት ወደ ማዘጋጃ ቤት ማሳደግ በዘንድሮ በጀት አመት ትኩረት ተስጥቶት እንደሚሰራ ጠቁመው በበጀት አመቱ በከተሞች በነባር እና በአዲስ ኢንቨስትመንት በሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች እንዲለሙ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በተያየዘም በ2018 በጀት አመት ማህበራት የቤት ባለቤት ለማድረግ መሬት በሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ ትኩረት ተሰጥቶ በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት በሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች ከተሞች ላይ ህብረተሠቡን በማሳተፍ የቅድመ አንደኛ ክፍል ወይም መዋለ ህጻናት ግንባታ እና የፅ/ቤት ግንባታ ለመስራት መታቀዱን አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በየከተሞች ታጠረው ብቻ የተቀመጡ ነባር የኢንቨስትመንት ቦታዎች ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ገልጸው ተቋማቸው አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ የማይለሙ የኢንቨትመነት ስፍራዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል።
ዘገባው የወረዳው የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገ/ጉ/ወ/ወረዳ በ2017 ዓ/ም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ78 ሺህ 70 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስጠቀም ህዝብና መንግስት ሊያወጣ ይችል የነበረውን 44 ሚሊዮን 568 ሺህ 395 ብር ማዳን መቻሉን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በክረምት ወራት የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ን በበጋ ወራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተገልጿል።
ጽ/ቤቱ የ2017 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያ እና የ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ መክፈቻ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አከናውኗል።
በዕለቱ የ2018 ዓ/ም የስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ ተካሂዶ ውሏል።
በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸዉ እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የጀመሩት የበጎ አድራጎት ተግባር አሁን ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት ባህል ማጎልበት ያስቻለ ስለመሆኑ ጠቁመው በበጎ ተግባራት አማካኝነትም በወረዳችን በርካታ የማህበራዊ ችግር ያለባቸውንና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማስጠቀም እንደተቻለ በማንሳት በወረዳው የተያዙ የበጎ ስራዎች ተግባራት ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በተደረገው ርብርብ ወጣቶችና ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ባደረጉት እገዛ ሰፊ ቁጥር ያላቸውንና ማህበራዊ ችግር ያለባቸው ነዋሪዎችን ማስጠቀም ስለመቻሉ ገልጸዋል።
አቶ ሚፍታ ሁሴን አክለውም በክረምቱ ወራት የተመዘገቡ ስኬቶችን በበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀው መንግስት እያደረገ ያለውን እገዛ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታዉምውቀዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በበኩላቸው የበጎ ፍቃድ ስራ ግዴታ ያልታከለበት፣ ዜጎች ከሰብዓዊነት አመለካከት ተነስተዉምው ነፃ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ እዉቀታቸውንና በጎ አመለካከታቸውን ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማት የሚያውሉበት ክዋኔ ነው ብለዋል።
የበጎ ስራ በወረዳችን እንደ ባህል የተለመደበት ደረጃ ላይ መድረስ ችሏል ያሉት አቶ ሸምሱ መንግስት ለዘርፉ በሰጠዉ ልዩ ትኩረት “ በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል የ2017 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማና ተጨባጭ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በ17 የስምሪት መስኮች ላይ 39 ሺህ 655 ወጣቶች የተሳተፉ ስለመሆናቸው ያወሱት ኃላፊው ከ78 ሺህ 70 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስጠቀም ህዝብና መንግስት ሊያወጣ ይችል የነበረውን 44 ሚሊዮን 568 ሺህ 395 ብር ማዳን መቻሉን አብራርተዋል።
አክለውም በ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ ስራ በ17 ዘርፎች 9 ሺህ 500 የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ 22 ሺህ ዜጎችን በማስጠቀም 8 ሚሊዮን 125 ሺህ 350 ብር ለማዳን መታቀዱን አስታውቀዋል።
በየደረጃው የሚገኙ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸን አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ጀማል ናስር የ2017 ዓ/ም የክረምት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት እቅድ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አ/ረሂም ባልቻ የ2017 ዓ/ም የስፖርት ምክር ቤት ሪፖርትና የ2018 ዓ/ም የበጋ ወራት እቅድ አቅርበዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ በተካሄደው የስፖርት ምክር ቤቱ ጉባኤ አባላቱ ባደረጉት ሰፊ ውይይትና ምክር 3 ውሳኔዎችን አጽድቀዋል።
ይኸውም 1ኛ የ2018 አመት የስፖርት ምክር ቤት በጀትን 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ሆኖ የጸደቀ ሲሆን
2ኛ የስፖርተኞች ውሎ አበል ቀደም ሲል ከነበረበት መሻሻሉን እና የምክር ቤቱን የ2017 ዓ/ም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት የስራ ዘመን እቅድ በሙሉ ድምጽ ም/ቤቱ አጽድቋል።
መድረኩን የመሩት የወረዳው ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ ባስተላለፉት መልዕክት በክረምቱ ወራት በ17 የስምሪት መስኮች የተከናወኑ የበጎነት ማሳያ ስራዎች በልዩነት መመራት በመቻላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ በመሆን ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ ማሳየት መቻሉን ጠቁመው በፓርቲው ልዩ ትኩረት ሰጪነት በ2018 ዓ/ም የበጋ በጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በ17 የስራ ዘርፎች እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው በየደረጃው የሚገኙ አካላት በክረምቱ የተገኙ ውጤቶችን በበጋ ወራትም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በማጠቃለያቸው እንዳሉት በክረምቱ ወራት የበጎ ፍቃድ ስራ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ለማረም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
አያይዘውም በየደረጃው የመገኙ አካላት በበጎነት ያከናወኗቸዉ የበጎነት ማሳያ ስራዎች እውቅናቸው የላቀ ስለመሆኑ በመግለፅ በስፖርት ዘርፍ ያሉትን አማራጮች አሟጦ በመጠቀም ማልማት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግት ተቋማት፣ቀበሌዎችና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተዘጋጀላቸውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከእለቱ ተጋባዥ አንግዶች ተቀብለዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።
