uz
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish
917
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+27 kun
+930 kun
Postlar arxiv
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ! ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን አስተዳደርና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መካከል የጉራጌ የማህበረሰብ ቴሌቪዥን እስቲዲዮ መገንቢያ ህንፃ ርክክብና በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተከናውኗል!! የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለፁት የጉራጌ ዞን ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነሃሴ 2/2017 ዓመተ ምህረት ጉራጊኛ ቋንቋ የትምህርት የስራና የሚዲያ ቋንቋ እንዲሆን መወሰኑን አስታውሰው የምክር ቤቱ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ጉራጊኛን የትምህርት ቋንቋ ከማድረግ አንፃር በዞኑ ከ96 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ እየተደረገ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የስራ ቋንቋ ለማድረግም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ጠቁመዋል!! ጉራጊኛን የሚዲያ ቋንቋ የማድረግ ስራ የጀመረው ኦቢኤን (OBN) ነው ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው ለኦቢኤን ሚዲያ እና ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸው ታላቅ ምስጋናና ክብር በራሳቸውና በጉራጌ ህዝብ ስም ገልፀዋል!! የወልቂጤ ኤፍ ኤም 89.2 እየሰራ ያለውም ስራ የሚበረታታና ምስጋና የሚቸረው ነው ያሉት አቶ ላጫ ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አመላክተዋል!! እንደ ማህበረሰብ ያሉን ፀጋዎች ለመላው ዓለም የምናሳያው ሚዲያን በመጠቀም ነው ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው በቁጥራችን እና በስማችን ልክ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው ላይ ያለመስራታችን ቁጭት ሊፈጥርብን ይገባል ብለዋል!! የጉራጌ ህዝብ ያሉት እሴቶች ባህሎችና ሀገር በቀል እውቀቶች በተገቢው ለሀገራችንም ሆነ ለአለም ህዝብ አልተሸጠም ያሉት አቶ ላጫ የማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያው ይሄን ጉድለት ይሞላል ብለዋል። የማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ ላይ ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም የዚሁ አካል ነው ብለዋል!! የቴሌቭዥን ጣቢያውን እውን ለማድረግ ሁለቱ ዞኖች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላትም ጋር ተቀራርቦ መስራት ይገባል ያሉት አቶ ላጫ ለስኬቱም የሁሉም የጉራጌ ተወላጅና ወዳጆች ድጋፍ ይሻል ብለዋል!! የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማህበረሰብ መገናኛ ተቋማት እንዲኖራቸው ህጉ የሚፈቅድ መሆኑን ጠቅሰው የጉራጌ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ለማስጀመር ከዩኒቨርስቲ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት መወሰኑ መልካ እድል ነው ብለዋል። ዩኒቨርስቲው ለማህበረሰቡ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም ሆኑ ሌሎች የጥናትና ምርምር ስራዎች ለሌሎች ተደራሽ ለማድረግ ሚዲያ ትልቅ አቅም አለው ያሉት ፕሬዝደንቱ ለማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያው ውጤታማነትም በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል!! ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለምታደርገው ጉዞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንበሳውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ያሉት ዶ/ር ፋሪስ ለዚህም ማሳለጫነት የሚዲያ ድርሻ የጎላ መሆኑን አብራርተዋል!! በመግባቢያ ሰነድ ፊሪማ ስነስርዓቱ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የፊት አመራሮችና የካቢኔ አባላት እንደዚሁም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል!!

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት የባንክ ሂሳቦን የማያያዝ ሂደት ተጀምሯል። ባንኮች ለዚህ አገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ደንበኞቻቸውን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ። ደንበኞች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና ባንኮች ባስቀመጡት የማጣመሪያ መንገድ በወቅቱ በማጣመር ካላስፈላጊ እንግልት እንዲድኑ እናሳስባለን። ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ከዚህ በታች ይመልከቱ። PS: አንዳንድ ባንኮች በዘመነ መንገድ ኦንላይን ትስስር “Online Harmonization” የጀመሩ ስላሉ በአካል መሄድ ሳያስፈልግዎ ማጣመር ይችላሉ።

የሥራ ዕድሎችን በማስፋት፣ የዜጎችን የገቢና የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና የሥራ ባህልን ለማሳደግ አበክረን እንሠራለን ። ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ( ዶ/ር )

ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን ይገባል ሲሉ የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የቤደርና አምበልታ አከባቢ ተወላጅ የከተማ ነዋሪዎች 275 ሺህ ብር በላይ የሚገመት 1201 የትምህርት መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍቶች ለቤደር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ነው። በመጽሃፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙት የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለቤደር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያና ማጠቀሻ መጽሃፍትን በማዘጋጀት ያቀረቡትን የአካባቢው ተወላጆችን አመስግነው የተደረገው የመጽሃፍት ድጋፍ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በማንሳት በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን እንደሚገባ አስታውቀዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው መንግስት ጠንካራ የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በመንደፍ ህብረተሠቡን ተወላጅ ባለሃብቱንና ረጂ ድርጅቶችን በማሳተፍ የትምህርት ተቋማትን ከማስፍፍት በተጨማሪ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት አጽኖት ሠጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመሆኑም እንደ ወረዳ ተወላጆች የአዲሱ ካሪኩልም መጽሃፍት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለትም ከ1201 የመማሪያና ማጠቀሻ መጽሃፍ ድጋፍ ያደረጉ የአካባቢው ተወላጆች የሰሩት ስራ ለሌሎች አርዓያነት የሚጠቀስ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው ድጋፉን በማድረግ የተሳተፉ አካላትን በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም አመስግነዋል። የመጽሃፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ተወካይ የሆኑት አቶ ሀይደር ጀማል ድጋፋን አስመልክተው እንዳሉት ለቤደርና አምበልታ ለሚገኙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጠቅላላ 1171 የተማሪዎች መማሪያ መፅሀፍ እና 30 አጋዥ መፅሀፍ 275 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸው ገልፀው በየትምህርት ቤቱ የሚስተዋሉ የመማሪያ መጽሃፍ፣ የመማሪያ ክፍል የጥራትና የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደ ተወላጅ ህብረተሠቡን ለማገዝ በቀጣይም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ለወላጆች የትምህርት ጉዳይ አደራ የሰጡ ሲሆን ለተማሪዎች ምክራቸውን ለግሰዋል። በመጨረሻም ለተማሪዎች መመሪያ መጽሓፍት በማዘጋጀት ላይ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የእውቅናና የምስክር ወርቀት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሙስሊም ኤይድ ዩ ኤስ ኤ እና በኬር ዘንጊ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተገነባው የአበልታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፈያ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ተመረቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ፕሮጀክቱ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ ሲሆን 2 ብሎክና 8 የመማሪያ ክፍሎች፣ ደረጃውን የጠበቀ መጸዳጃ ቤት፣ 2 መቶ ዴስኮችና የውሃ ፓንፕ ያካተተ መሆኑን ተገልጿል። በዚህ ወቅትም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግር ያደረጉ ሲሆን በመንግስት ልዩ ትኩረት ከተሰጠባቸው ዘርፎች አንዱና ዋነኛው የትምህርት ልማት መሆኑን አብራርተዋል። ትምህርት ለአንድ ሃገር እድገት ቁልፍ መሳሪያ እንደሆነ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ሆኖም ግን በወረዳ ደረጃ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ባለፉት ስርዓት የተከናወነው የትምህርት ልማት ስራ ዝቅተኛ መሆኑን አውስተዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም በወረዳችን 53 አንደኛ ደረጃ እና 7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሠው 40 ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች በመሆናቸው ችግሩን ለማቃለል በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶና ከፍተኛ በጀት በመመደብ እንዲሁም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ህዝቡን በማስተባበር እየተሠራ እንደሚገኝ በመግለጽ በዛሬው ዕለት በኬር ዘንጊ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስተባባሪነት በሙስሊም ኤይድ ዩ ኤስ ኤ ድጋፍ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ ሲሆን 2 ብሎክና 8 የመማሪያ ክፍሎች፣ ደረጃውን የጠበቀ መጸዳጃ ቤት፣ 2 መቶ ዴስኮች እንዲሁም የውሃ ፓንፕ ያካተተ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሠው በዚህ አኩሪ ልማታዊ ስራ ላይ በመሳተፍም ሆነ ሌሎችን ያስተባበሩ አካላት በወረዳው ህዝብና አስተዳደር ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም በምረቃ ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ለአንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ተናግረዋል። በጉራጌ ዞን መንግስት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ህዝቡን በማስተባበር ባለፉት አመታት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል በርካታ ተግባራት መከናወናወኑን የገለጹት አቶ መብራቴ ወ/ማርያም በዛሬ እለት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አንበልታ ቀበሌ ተገንብቶ የተመረቀው ትምህርት ቤት ግንባታ በዘርፉ የገጠመውን የውጤት ስብራት ለማስተካከል ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ ይሄን በጎ ተግባር ልስተባበሩና ድጋፍ ላደረጉ አካላት በጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። የሙስሊም ኤይድ ዩ ኤስ ኤ ስራስኪያጅ አቶ ፈቱዲን ኢብራሂም በወረዳው በበርካታ የልማት ስራዎች ድርጅታቸው ሲሳተፍ መቆየቱን አስታውሠው በዛሬው ግንባታ ተጠናቆ ለተማሪዎች ክፍት የሆነውን ትምህርት ቤት በማየተቸው ደስተኛ እንደሆነ ተናግረው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል። የኬር ዘንጊ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃይደር ናስር በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለምረቃ በመብቃቱ መደሠታቸውን ገልጸው ለስኬቱ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ አካላትን በድርጅታቸው ስም አመሰግነው መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። አቶ አ/ረሂም ጧላሃ እና ተማሪ ሂንዲያ ኑርአህመድ የአንበልታ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ በአካባቢው ምቹ የመማሪያ ቦታ እና ቁሳቁስ የተሟላበት ትምህርት ቤት ባለማግኘታቸው ተማሪዎች ትምህርት ለማቋረጥና ራቅ ያሉ አካባቢ ይሄዱ እንደነበር አስታውሰው ምስጋና በሙስሊም ኤይድ ዩ ኤስ ኤ እና በኬር ዘንጊ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ይግባውና በዛሬው እለት ለተገነባው መማሪያ ክፍሎችና ቁሳቁሶች ችግሩን እንደሚያቃልለው በመግለፅ መደሠታቸውን ተናግረዋል። በመጨረሻም በዚህ ዘመን ተሻጋሪና አኩሪ ስራ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ሠርተፍኬትና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም 🎤 የከተሞች ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፍኖስ ገለጹ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማልማት የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ቢሮ ገለጸ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 በጉራጌ ዞን አዘጋጅነት በወልቂጤ ከተማ ለሚካሄደው ዞናዊ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ተሳታፊ ስፖርተኞች ሽኝት ተደረገለት። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ2018 በጀት አመት በመንግስትና ማህበረሰቡ በማሳተፍ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ ለማከናወን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቁ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የ2018 በጀት አመት የ5 ወራት አፈጻጸም አስመልክቶ የማኔጅመንት ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ድጋፍና ክትትል ማድረጉ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ለወረዳ ማዕከል ባለሙያዎች ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና መጠናቀቁን ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 🎤 "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሃል አምባ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ማካሄዱ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨ 🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ማዕከል እና ታዳጊ ከተሞች ላይ "የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት መካሄዱ። ፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨