cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ግጥም በአስታወሰኝ ረጋሳ

የአሰታወሰኝ ረጋሳ የተለያዩ ግጥሞች እና የመድረክ ስራዎች እዚህ ቻናል ላይ ይለቀቃሉ ቻናሉን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 999
Obunachilar
+824 soatlar
+577 kunlar
+14830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

​​➢➢ላ’ንዲት የገጠር ሴት➢➢ ስትፈጭ የኖረች ሴት፣ መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣ ጓያ ትፈጫለች ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!    አስባው አታውቅም… ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣ ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች…… ተዚያን ቀን ጀምራ፣ ተዚያን ቀን ጀምሮ፣ ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣ ትፈጫለች ሽሮ…… አታውቅም፣ ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አታውቅም፣ ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣ አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣ ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣ ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣ ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣ ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣ ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣ ወደዚህ መጅ መሳብ ወደዚያ መጅ መግፋት…… እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣ ሽህ ዓመት ቢንጣለል፣ ቢጎርፍም ዱቄቱ፣ እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ!     ከዘመናት ባንዱ መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣ ራሷን ለማየት፣ ከጸጉራ ላይ ያለው ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት፣ ያኔ ይገባታል የተሰጣት ዕጣ፣ ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…     የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣ ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣ ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣ ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣ "ስትፈጭ የኖረች ሴት" ይህ ነው መጠሪያዋ! ➛➛ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም @eliyasshitahun                  @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
👍 5😢 1
Notcoin ግቡና ዕድላቹን ሞክሩ ስል አሻፈረኝ ያላቹ  ምን እንደተፈጠረ እስካሁን ሰምታችኋል መቼም 😁 ይኼኛው ደግሞ Hamster Kombat ይባላል። ይሄም ከ Notcoin ጋር ተመሳሳይነት አለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ተቀባይነት አግኝቷል ከናንተ የሚጠበቀው ገብቶ Tap ማድረግ እና በዋናነት ደግሞ Friend invite ማድረግ የሚሰጡ Task'ኦችን በመፈፀም የሚሰጣቹን Coin መሰብሰብ ብቻ ! ባለፈውም እንዳልኩት በመሞከር የምናጣው ነገር የለም
Hammasini ko'rsatish...
Click
ማመን እና ማወቅ (በላይ በቀለ ወያ) . . ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ ያወኩትን እውነት ... ማመን ቢቸግረኝ ፣ "ትመጣለች " እያልኩ ፣ እጠብቅሻለሁ፡፡ "አትመጣም" እያለ... ለሚነግረኝ ሁሉ ፣ መቅረትሽን አውቆ "የቀረበት እንጂ ... የመጣለትማ ፣ አያውቅም ጠብቆ" ስል እመለሳለሁ በቃ ትመጫለሽ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ!!! @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
14👍 5😢 3
አልሞትም! (በእውቀቱ ስዩም) ስሚ! እኔ በዚህ ዐለም ፤ብዙ ብሰቃይም አንድ ሀሙስ የቀረው፤ መስየ ብታይም አምሮቴን ሳላገኝ፤ሱሴን ሳላከትም በመሬት ከርስ ውስጥ ፤ገላየን አልከትም አልሞትም! ማንም ባልደፈረው፤ መንገድ ሳልገሰግስ እንደ ንጉስ አይዙር፤ግማሽ ቀን ሳልነግስ በጠገበው ሳልስቅ፤ ለራበው ሳልደግስ አልሞትም! ዝማሜን ሳላወልቅ፤ ያንድበቴን ግድብ ዙፋን ላይ ሳልሸና፤ ጌቶቼን ሳልሰድብ ከድሃ ሳላብር፤ ከገባር ሳልወግን ከምድር በረከት፤ ድርሻየን ሳልዘግን አልሞትም፤ ስሚ! ልቤ እንደምኞቱ፤ ቢያገኝ እንደምርጫው ያላማየ ማብቂያ፤ አንቺ ነሽ መቁዋጫው እና አገሬን ለቅቄግ፤ ልብሽህ ላይ ሳልከትም በውብ ከንፈርሽ ላይ፤ ከንፈሬን ሳላትም አልሞትም! @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 2
ካንቺ ጋር... ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ_ደስታ , ካንቺ ጋር ሁሉም ነገር ሄዷል ሰዓቱ ተረስቷል ቀኑም ሌላ ሆኗል ዓመተ ምህረቱ በጋና ጸሀዩ የኖርሽበት ቤቱ አልጋ ጠረጴዛው ስጋጃ ወንበሩ መስኮቱና በሩ ስዕሉ ግርግዳው ካንቺ ጋራ ጠፍቷል ሁሉም ተለውጠው ዛሬ ነገ የለም ቅናትና ፍቅሩ ሀዘኑ ጨዋታው ደስታና መከራው ፈጥሯል ሌላ ቀለም ገርጥቶ ጠውልጎ መልኩ የነበዘ ሞቷል መታሰቢያሽ ሆኗል የፈዘዘ ፈራርሷል የካብሽው ትዝታው የድሮው ቀርተሸ ተረስተሻል ጠፍተሻል ከልቤ ወጥተሻል ከቤቴ ወጥተሻል ካንጀቴ ወጥተሻል ካጥንቴ ሄደሻል ካሳቤ፡፡ የለሽም የለሽም ሙዚቃ ድምጽሽን እንደ ዱሮ አልሰማም ቅዠት ዘፈንሽ ዜማሽ እንጉርጉሮሽ ጭጋግ ነው ውበትሽ የጊዜው መለወጥ ገላሽን ደብቆ ጋርዶታል መልክሽን ጥላሽ ነው የቀረው አካልሽ ተሰርቶ ጨብጦ ቅርጽሽን ሳቅና ፈገግታሽ ጨዋታና ቀልድሽ ለዛና ወሬሽ ቅንድብሽ ሽፋልሽ የሚያበሩ አይኖችሽ ጣፋጩ ከንፈርሽ ለስላሳው ምላስሽ በረዶ ጥርሶችሽ ተለውጠው የሉም ካሳቤ ጨለማ ገብተው አይታዩም ያ ውብ ቆንጆ ባትሽ የሚዋጋው ጡትሽ የሚቆጣው ዳሌሽ ካንቺ ጋር ሄዷል፡፡ @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 3
ፍቅር- ፈራን:ጠላን (ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን) "ፈራን" ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን "ፈራን" ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን "ናቅን" በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን እልህ ተናነቅን "ናቅን" መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን "ጠላን" መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ መናናቅ በርክቶ መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ "ራቅን" የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
2👍 1😢 1
የባከነ ሌሊት! (በዕውቀቱ ስዩም) ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ። ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ “በኡራኤል ርዱኝ ” ብሎ የሚጣራ ምስኪን አባወራ ብብት ሥር ገብቼ አፋፍሼ አንስቼ ተሸክሜ አድኜ ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ ወይ ምግባር አልሠራሁ ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ። አንድ በትረ-ሙሴ ሁለት ስስ አሎሎ ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ ሲባክን ዝምብሎ ” እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ” የምትል መለሎ ልቤን ሳትሰውረው አልጋየን ሳትሰብረው። ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ ” እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጥፍ። አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት ሲገፉ ሲስቧት ” እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን ልመናዋ ስቦኝ እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ ከሁዋላ ደርሼ ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን በማረግ ቃኝቼ ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ። ድል ሳላስመዘግብ ውጥረት ሳለረግብ ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ። @astawesegnregasa @astawesegnregasa
Hammasini ko'rsatish...
👍 6 6
Photo unavailableShow in Telegram
አባቴ ያቺን ሰዐት - ደረጀ ደምሴ (Replay) https://www.clubhouse.com/room/PN2652wP?utm_medium=ch_room_pxr
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
Did you know reading books can significantly reduce stress levels? 🌺A University of Sussex study found reading for just 6 minutes can lower stress by up to 68%, more effective than going for a walk or listening to music. Dr. David Lewis, the cognitive neuropsychologist who led the study, said
"It really doesn't matter what book you read, by losing yourself in a thoroughly engrossing book you can escape from the worries and stresses of the everyday world and spend a while exploring the domain of the author's imagination."
The researchers concluded this escape from stressful thoughts reduces muscle tension and heart rate caused by stress.
Hammasini ko'rsatish...
👍 3 1