cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የኢየሱስ ወታደር

መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
224
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+37 kunlar
+430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

+ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ + ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል:: እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል:: ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል:: #ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት #ስም : #ከሰማይ በታች #እንድንበት ዘንድ የተሠጠን #ስም : #ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት #ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል:: #ኢየሱስ ✍🏽 አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ? ኢየሱስ በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል:: ኢየሱስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12) እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ:: ወዳጄ ኢየሱስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው:: "ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ሉቃ 10:20 )
Hammasini ko'rsatish...
ዲያቆን ሔኖክ ሃይሌ + የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ + ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል:: እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል:: ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል:: #ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት #ስም : #ከሰማይ በታች #እንድንበት ዘንድ የተሠጠን #ስም : #ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት #ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል:: #ኢየሱስ ✍🏽 አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ? ኢየሱስ በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል:: ኢየሱስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12) እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ:: ወዳጄ ኢየሱስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው:: "ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ሉቃ 10:20 )
Hammasini ko'rsatish...
ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በቀጥታ ከሚናገሩ ብዙ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል በጥቂቱ ========================================== ♦ኢሳ 7፥14 (Isaiah ) ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም #አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ♦ኢሳ 9፥6 (Isaiah) ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ #ኃያል #አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ♦ኢሳ 40፥3፣4 ( Isaiah) ማቴ 3፡1-3 (Matthew) የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ #የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ #ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ♦ሚክያስ 5 ፡2 (Micah) አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ #ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ #ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል። ♦ማቴ 1፥18-23 (Matthew) እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው ♦ዩሐ 1፥1-14 (John) በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ #ቃልም #እግዚአብሔር #ነበረ።ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ♦ዩሐ 1፥3 (John) #ሁሉ #በእርሱ #ሆነ (#ተፈጠረ)፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ♦ዩሐ 5፥17፣18 (John) ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ♦ዩሐ 8፥24-27 (John) እንግዲህ፦ አንተ ማን ነህ? አሉት። ኢየሱስም፦ #ከመጀመሪያ #ለእናንተ #የተናገርሁት #ነኝ። ♦ዩሐ 8፥58 (John) ዘፀ 3፡14 (Exodus) ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ #እኔ #አለሁ አላቸው።( before Abraham was born #I #AM) ♦ዮሐንስ 10 (John) 30፤ እኔና አብ #አንድ #ነን። ♦ዩሐ 14፥9 ( John) ኢየሱስም..... #እኔን #ያየ #አብን #አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ? ♦ዮሐንስ 14 (John) 1፤ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ♦ዩሐ 20፥28 (John) ቶማስም፦ #ጌታዬ #አምላኬም ብሎ መለሰለት። ♦ሮሜ 9፥5 (Romans) አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ #እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ #ለዘላለም #የተባረከ #አምላክ #ነው፤ አሜን። ♦ፊልጵስዩስ 2፡6 (Philippians) #እርሱ ^በእግዚአብሔር #መልክ #ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ♦ቆላ 1፥16 ( Colaossins) ^እርሱም #የማይታይ #አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ #ሁሉ #በእርሱና #ለእርሱ #ተፈጥሮአል፤ ♦ቆላ 2፥9 (Colaossins) #በእርሱ #የመለኮት #ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤ ♦1ኛጢሞ 3፥16 (Timothy) እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ #በሥጋ #የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። ♦ቲቶ 2፥13፣14 ( Titus) ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን #የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል። ♦ዕብራውያን 1፡3 (Hebrews ) #እርሱም #የክብሩ #መንጸባረቅና #የባሕርዩ #ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ♦ዕብራውያን 1፡8,10 ( Hebrews) ስለ ልጁ ግን፡— #አምላክ #ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። ደግሞ፡— #ጌታ #ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ ♦1 ዮሐንስ 5 ፡20 (1 John) ...እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው #እርሱ #እውነተኛ #አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ። አሜን
Hammasini ko'rsatish...
ኢየሱስ ሰውም አምላክም “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥” ፊልጵስዩስ 2፥6 ይህ ክፍል ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ከሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ነው። "በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ" የሚለው ቃል "በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። "በባሕርዩ" የሚለው ቃል "መልክ" ማለት ሲሆን በግሪክ "μορφή=ሞርፌ" ሲሆን በአዲስ ኪዳን ወስጥ 3 ጊዜ የተጻፈ ሲሆን ሁለቱ ያሉት በዚህ ክፍል ሲሆን አንዱ ደግሞ ማርቆስ16:12 ነው። "መልክ" የሚለው ቃል ባሕርይን የሚወክል የሆነበት ምክንያት አምላክ ስጋዊ አካል ስለሌለው ነው። በዚህ ክፍል "በባሕረዩ አምላክ" ሆኖ ሳለ ማለት "አምላክ" ሆኖ ሳለ ማለት ነው። ይህ ሀሳብ ግልጽ እንዲሆንልን "ባሪያ" ነው ለማለት የተጠቀመው ይህኑ "መልክ" የሚለውን ቃል እንደሆነ ቀጣዩ ክፍል ፍንትው አድርጎ ይናገራል። “ነገር ግን የባሪያን 👉መልክ👈 ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ ፊልጵስዩስ 2፥7 "ባሪያ" የሚለው ቃል በግሪክ δοῦλος=ዱሎስ ሲሆን "አገልጋይ" ማለት ነው። "የባሪያን መልክ ይዞ" ማለት "ባሪያ" ወይም "አገልጋይ" ሆኖ ማለት ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ማለት እግዚአብሔር አይደለም ማለት ከሆነ የባሪያን መልክ ይዞ ማለት ባሪያ አይደለም ማለት ነው። ነገር ግን እርሱ "አምላክ" ነበረ እንዲሁ "ባሪያ ወይም አገልጋይ" ሆኖ ተገልጧል። ይህ ብቻ ሳይሆን "በሰው ምሳሌ" በማለት ሰው ሆኖ መገለጡትን ፍንትው አድርጎ ይነግረናል። "በሰውም ምሳሌ" ማለት "ሰው ነው" ማለት እንጂ "ሰው ያልሆነ ሰው የሚመስል" ማለት አይደለም። እንዲሁም የእግዚአብሔር መልክ ማለት "እግዚአብሔርን የሚመስል እግዚአብሔር ያልሆነ ማለት አይደለም።" "ራሱን ባዶ አደረገ" የሚለው ቃል የሚነግረን የቀድሞ ማንነቱ የላቀ እንደሆነ ነው። ይህ የቀድሞ ማንነቱ "አምላክነቱ" ሲሆን ራሱን ባዶ ማድረጉ ደግሞ "ባሪያ የሆነ ሰው" መሆኑ ነው። ይህን ሲያደርግ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን እኩልነት እንደመቀማት አልቆጠረውም። "እኩልነት" የሚለው ቃል "መተካከል" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ከዚሁም ቃል እንደምንረዳው ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሆነ ወይም የተስተካከለ "አምላክ" መሆኑን እና እጅግ ትሑት "አምላክ" መሆኑን ነው። ይህ የትህትና ጥልቅ የትምህርት መለኪያ እና እኛ ልትከተለው የሚገባ የትህትና መንገድ ነው። እኛ በማንነታችን "ሰው" ሆነን "ሰውን" በመታዘዝ እንዲናከብር እርሱ አምላክ ሆኖ ለአምላክ በመታዘዝ ትሕትናውን አስተማረን። "ሰው" በማንነቱ "ከሌላ ሰው" አያንስም ነገር ግን አንዱ ለሌላው መታዘዝ እንዳለበት ቃሉ ይናገራል። ቃሉንም እንዲህ ሲል ይመክራል። “በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።” ፊልጵስዩስ 2፥5
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
2ኛ ቆሮ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ ⁴ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ ⁵ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ ⁶ መታዘዛችሁም በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
#ውድ የዚህ channel አባላት ያሎትን መጻሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ በዚህ account https://t.me/getanehabera መጠየቅ ትችላላችሁ ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
እግዚአብሔር በሰማይ በአካል እና በክብሩ አለ፤ በምድር ደግሞ በመንፈስ እኛ ውስጥ አለ። እኛ በአካል በምድር አለን፤ በመንፈስ ደግሞ በሰማይ እርሱ ውስጥ ተሰውረን አለን። ከሞት ሲነሳ ሰማይ መግባታችን ተጨባጭ ሆነ። ከሄደ በኋላም መንፈሱን ላከልን። መንፈሱም ስለተሰጠን በመንፈሰ አማካኝነት ከአበቱ ጋር እኛ ውስጥ መጥቶ ኖረ። ትንሳኤው ባይኖር ይሄን የመሰለ እውነት ውሸት ይሆን ነበር። ኢየሱስ ከሞት ባይነሳ አሁን የምንኮራበት እምነት ከንቱ ይሆን ነበር። “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥17 ዲ/ን ዮሐንስ ደሳለኝ ህዳር 30 2016 ዓ.ም የተጻፈ
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
#ክፍል #አራት #፬ ========= ✍️ ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች ከዚህ በኃላ ያሉት ሁለቱ 4ኛው እና 5ኛው የፍርድ አይነቶች በክርስቶስ አምነው የዳኑትን እውነተኛ አማኞች አይመለከታቸውም 📌2 ጢሞቴዎስ 2:15 የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 4) #ባልተነጠቁ #በምድር #በሚኖሩ #ላይ ነው። ምክንያት፦ የመንግስት ወንጌልን ባለማመን እና እስራኤላውያንን የማጥፋት ሙከራ ጊዜ፦ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በክብር ሲገለጥ ማቴ 25:31-33, ዘካ 14:5 ቦታ፦ በኢዮሳፍጥ ሸለቆ ( አርማጌዶን) ኢዮኤል 3:2,12...,ራዕ 16:16 ውጤት፦ ♦ የመንግስት ወንጌልን ያመኑ ወደ ሺው አመት በረከት ይገባሉ ። ማቴ 25:31-32 ♦ የመንግስት ወንጌልን አናምንም እስራኤላውያንን እናጠፍለን የሚሉት ፍርድ= ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ ። ራዕ 19:21 ✍️ ይህ ፍርድ ከአማኞች ጋር ግንኙነት የሌለው እና አማኞች ከተነጠቁ ከ ሰባት(7) አመት በኃላ የሚፈፀም ፍርድ ነው። ✍️ ፍርዱ በዋናነት ባልተነጠቁ እና የመንግስት ወንጌል አናምንም እስራኤልንም እናጠፋለን በሚሉት አህዛብ (የአውሬው= የአውሮፓ ህብረት እና ጦር) ላይ የሚፈፀም ነው። ✍️ ይህ አራተኛው ፍርድ ከ አምስተኛው(5) የነጬ ዙፋን ፍርድ እንደሚለይ ልብ ልንል ይገባል። 📌 ማቴዎስ 25:31-33 31፤ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ 32፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ 33፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። 📌 መዝሙር 96፡13 ይመጣልና፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። 📌 ዘካርያስ 14:5 = ማቴ 25:31-33 የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፤ 👉አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።👈 📌 ዘካርያስ 14 :12-13 = ራዕ 19:17-21 ፤ እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። 13፤ በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፤ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል። 📌 ራእይ 1፡7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። 📌 1 ተሰሎንቄ 5:9 ፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። ✍️ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
Hammasini ko'rsatish...
2
#ክፍል #ሶስት(፫) ======== ✍️ ቅዱሳን ልብ ሊሉት እና ሊያስተውሉት የሚገባ ነገር ከ 5ቱ የፍርድ አይነቶች የመጀመሪያወቹ ሶስቱ ብቻ አማኞችን የሚመለከቱ መሆኑን ነው።እነዚህም 1) በአማኝ የእድሜ ዘመን ሃጥያት 2)በአማኝ ስጋ(እኔነት) 3)በአማኝ ሥራ ላይ የሚፈረዱ ፍርዶች ናቸው። 📌2 ጢሞቴዎስ 2:15 የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 3, #በአማኝ #ሥራ ላይ የሚፈረድ ፍርድ ነው 👉ፍርዱ ፦በአማኝ ሥራ ላይ ነው 👉ጊዜው፦ ቅዱሳን ሁሉ ስንነጠቅ 👉የፍርዱ ቦታ፦ የክርስቶስ የፍርድ ወንበር(Bema) ፊት ነው። 📌አንባቢያን የፍርድ ወንበር እና የነጩ ዙፋን ፍርድ መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩን ልብ ሊሉ ይገባል፦ ♦የፍርድ ወንበር(Bema) አማኞችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን ♦የነጩ ዙፋን ፍርድ ያላመኑ ሙታንን ብቻ የሚመለከት የመጨረሻው ፍርርድ ነው። 👉የፍርዱ ውጤት ፦#ሽልማት #መቀበል ወይም #ሽልማት #አለመቀበል ✍️ቅዱሳን ሁሉ የዳኑት እና ከእግዚአብሔር ቁጣ ያመለጡት በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ በእምነት እና በጸጋው ብቻ እና ብቻ ነው። ✍️የጸጋው ሀይል ግን ከእግዚአብሔር ቁጣ ማዳን ብቻ ሳይሆን ሀጥያተኝነትን እና አለማዊ ምኞትን በማስካድ በዚህ ዘመን በጽድቅ፣ በቅድስና እና እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር እና ሽልማትን (ደሞዝን) ከጌታ ኢየሱስ እንድንቀበል ያደርገናል። ✍️ጌታ በቤዛነት ስራው ከቁጣ አድኖ ደግሞ በእኛ ሆኖ መልካም ስራን በመስራት ራሱ በእኛ በሰራው ስራ ግን ሽልማቱ ለእኛ መሆኑ ያስደንቃል ያስገርማልም። 📌1ቆሮ 3፡11-15 ---------- 11፤ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 12፤ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ 👉በወርቅ ቢሆን 👉 በብርም 👉 በከበረ ድንጋይም 👉በእንጨትም 👉 በሣርም ወይም 👉 በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ 👉ሥራ👈 ይገለጣል፤ 13፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም 👉ሥራ👈 እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። 14፤ ማንም በእርሱ ላይ 👉ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤👈 15፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ 👉እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።👈 📌1 ቆሮንቶስ 4 5፤ ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል። 📌ሮሜ14:10) " አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? 👉ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና👈።" 📌2ቆሮ 5:10) " መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ 👉በሥጋው👈 የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን 👉በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።👈" 📌2 ጢሞቴዎስ 4 8፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። 👉ስራችን ,ኑሮአችን እና ንግግራችን እንደቃሉ ከሆነ ሽልማት ከጌታ ዘንድ አለን። ጌታ ኢየሱስም ከሽልማት ጋር እንደሚመጣም ነግሮናል። 📌የዮሐንስ ራእይ 22:12) " እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ 👉ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ(reward) ከእኔ ጋር አለ።👈" 📌ራእይ 22 20፤ ይህን የሚመሰክር፡— አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ፡ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና። 21፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
Hammasini ko'rsatish...
3
#ክፍል #ሁለት (#2) ========== 2ኛው የፍርድ አይነት #በአማኝ #ስጋ ላይ 👉ምክንያት፦ #የተገለጠ #ሀጥያት 👉 ቦታ፦ በምድር ላይ 👉 ጊዜ፦ አማኙ በህይወት በምድር ሲኖር 👉ውጤት፦ አማኙ በተለያየ መንገድ በስጋው ይገሰጻል ይህም ለአማኙ ጥቅም ነው። ✍️አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ ከዳነ በኃላ በምድር ላይ በዋጋ የተገዛ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሲሆን የሰማይን ሕይወት እንዲገልጥ እና የክርስቶስ የጽድቁ እና የቅድስናው መገለጫ ለመሆን ተጠርቷል። ነገር ግን በዚህ ደካማ ስጋ ምድር ላይ ሲኖር መድከሙ የማይቀር ነው በሚደክምበትም ጊዜ በሕብረት ንስሃ በድካሙ ሊራራለት ከሚችለው እና ጸጋና አቅምን ከሚሰጠው ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር መጨረስ ይችላል። ✍️ነገር ግን አንድ ክርስቲያን ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ ጋር በንስሃ መጨረስ አቅቶት ቤተመቅደስነቱን ረስቶ በተገለጠ ሃጥያት ውስጥ ቢገኝ እና የጌታውንም ስም ቢያሰድብ #በስጋው ጌታ #ይገስጸዋል ፍርድንም ይቀበላል። ✍️1 ጢሞቴዎስ 5 (1 Timothy) 24፤ የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ ነው ፍርድንም ያመለክታል፥ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤ 1 ቆሮንቶስ 3 (1 Corinthians) 16፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 17፤ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።(1 Corinthians 3 17: If any man defile the temple of God, him shall God destroy; for the temple of God is holy, which temple ye are.) ✍️1 ቆሮንቶስ 5 (1 Corinthians) 1፤ በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።....... 3-4፤ እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ 5፤ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው። ✍️1 ቆሮንቶስ 11 (1 Corinthians) 30፤ ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል። 31፤ ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ 32፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን። ✍️ገላትያ 6 (Galatians) 7፤ አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤ 8፤ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና ✍️ዕብራውያን 12 (Hebrews) 7፤ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? 8፤ ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። 9፤ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? 10፤ እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 2 2
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.