cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qilingÂť, bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ETV ዜና 57(🇪🇹)

https://t.me/wwetvzena1 ይህ ETV ZENA 57 (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።👇👇👇👇👇 https://t.me/ETVSPORTGole https://t.me/ETVzenaSPORT https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 964
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+327 kunlar
+8230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Hammasini ko'rsatish...
ETV AFAAN OROMOO

Etv zena57 (Afaan oromoo)《🇪🇹》

https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

https://t.me/ETVzenaSPORT

https://t.me/wwetvzena1

https://t.me/ETVSPORTGole

👍 11❤ 8
Photo unavailableShow in Telegram
በጋዛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች ድጋፎችን ማድረስ እንዳልተቻለ ተነገረ‼️ ድርጅቶቹ የሚሠጡትን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸውን ተከትሎ ንጹሐን ሊራቡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ የበይነ-መረብ እና የሥልክ አገልግሎት የተቋረጠው ወደ ጋዛ ይደርስ የነበረው ነዳጅ መቆሙን ተከትሎ ነው፡፡ አሁን ላይ የግንኙነት መሥመሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚደርሰው በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚኖረው የጋዛ ሕዝብ ለመገናኘት መቸገሩ ነው የተገለጸው፡፡ በሌላ በኩል የእስራዔል ጦር በሰሜናዊው የጋዛ ክፍል እያካሄደ ያለውን ጥቃት ወደ ደቡብም ማስፋት እንደሚፈልግ ምልክት አሳይቷል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 11❤ 2😍 2🔥 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል‼️ የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ትናንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው። ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም። በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ "ሸኔ" ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል። አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል። " በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል። አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ።" ብለዋል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 3❤ 3👏 2🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቻይና የዓለማችን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አዋለች‼️ ቻይና በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራባይት ፍጥነት ያለው ዓለማችንን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አውላለች፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሰኮንድ 150 ፊልሞችን መላክ የሚያስችል የዓለማችን ፈጣኑ ኢንተርኔትም ነው ተብሏል፡፡ "ሁዋዌ" እና "ቻይና ሞባይል" የተሰኙት ሁለት ኩባንያዎች በጋራ ስራ ላይ ያዋሉት ይህ የኢንተርኔት አገልግሎት በሰኮንድ 1 ሺህ 200 ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው ነው፡፡ ፈጣኑ የኢንተርኔት አገልግሎት ከቤይጂንግ ወደ ጉዋንዡ ከተማ በተዘረጋ 300 ኪሎሜትር ኦብቲክ የፋይበር መስመር ነው አገልግሎት ላይ የዋለው፡፡ አገልግሎቱ ይጀምራል ተብሎ ከተገመተበት ሁለት አመት አስቀድሞ ስራ ላይ መዋሉም ተጠቅሷል፡፡ አሁን ላይ አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያለው የኢንተርኔት ፍጥነት ከ100 እስከ 400 ባይት በሰኮንድ ነው፡፡ አሁን ቻይና ስራ ላይ ያዋለችው በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራ ባይት ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት ለቤት አገልግሎት አይውልም መባሉን አሪራንግ ዘግቧል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 5❤ 1🔥 1😁 1
#Update ከአንድ ቀን አድማ በኋላ በከፊል ጀምሮ የነበረው የመቐለ የታክሲ አገልግሎት መልሶ ተቋርጠዋል። የታክሲ አገልግሎቱ ህዳር 3 ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የተናገሩት ተገልጋዮች ህዳር 4/2016 ዓ.ም ከሰአት በኃላ በከፊል የጀመረ ቢሆንም ፤ ከህዳር 5 ጀምሮ መልሶ በመቋረጡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው ይገልፃሉ። ስለ አገልግሎቱ መቋረጥ የታክሲ ማህበራት አቤቱታ ሲያቀርቡ ፤መንግስት ደግሞ ለሚድያ መግለጫ ሰጥቷል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አቤቱታውና መግለጫው ተመልክቶታል። ህዳር 05/2016 አምስት የመቐለ የታክሲ ማህበራት በጋራ ለመንግስት ያቀረቡት የፅሁፍ አቤቱታ እንደሚያመለክተው። "ስራ የማቆም አድማው ከእወቅናችን ውጭ የተደረገ ኢ-ህጋዊ ተግባር ቢሆንም ያለውን የኑሮና የመለዋወጫ እቃ ውድነትና ግምት ውስጥ  ያስገባ የታሪፍ ማስተካከያ ተደርጎ አገልግሎቱ እንዲቀጥል እንጠይቃለን "  ይላል። የክልሉ መንግስት በትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በኩል ለሚድያ በሰጠው መግለጫ ፤ " በተቀመጠው የታሪፍ መመሪያ መሰረት ትርፍ መጫንና ያልተፈቀደ ታሪፍ ማስከፈል ህጋዊ አይደለም ፍፁም የተከለከለ ነው ፤ ስለዚህ ይህንን በመቀበል አገልግሎቱ መቀጠል ይገባል " ብሏል። ቢሮው አያይዞ በአገልግሎት የማቆም አድማው የተሳተፈ የታክሲ ባለቤትና አሽከርካሪ እያንዳንዱ ብር 1200 እየተቀጣ እንዲመለስ ያሳሰበ ሲሆን የተቀመጠው ቅጣት የማይተገብሩ ታክሲዎች የሰሌዳ ቁጥራቸው እየተፈታ አገልግሎት ከመስጠት እየተከለከሉ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጠዋል። የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ህዳር 3/2016 ዓ.ም ለሚድያ በሰጠው መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መምከሩ ፤ የመንግስት ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲል ማስጠንቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል
Hammasini ko'rsatish...
👍 1❤ 1
👍 2
የሕዳሴው ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታወቁ‼️ ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውስጥ ፈተና በውጭ ጫና ነበረብን፤ ከፈጣሪ ጋር የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚህ ደርሰናል፤ ነገር ግን የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም ብለዋል። በቀጣዩ ጊዜ ያቀድነውን አጠናቅቀን ፈጣሪን እንደምናመሰግን እምነቴ ነው ሲሉም ገልፀዋል። ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ ሲሉም መልዕክት አስረተላልፈዋል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
👍 37❤ 14
#ኢትዮጵያ ዜጎች በኑሮ ውድነት / በዋጋ ንረት ምክንያት ክፉኛ እየተማረሩ፤ እየተቸገሩ ይገኛል። በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ላይ በየጊዜው የሚታየው የዋጋ ጭማሪ ዜጎች ኑሯቸውን ከባድ ካደረገው ቆይቷል። ከምንም በላይ በዚህ ወቅት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ተስኗቸዋል። ልጆች ወልደው ለማሳደግ ፣ ለማስተማር፣ ፣ በልቶ ለማደር፣ ህልማቸውንና ሀሳባቸውን ለማሳካት በየጊዜው አየናረ ያለው የኑሮ ውድነት ለዜጎች እንቅፋት ሆኗል። የዋጋ ንረትን በተመለከተ አሀዱ ሬድዮ ዛሬ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጠቅሶ ባሰራጨው አንድ ዘገባ ላይ ፤ ሚኒስቴሩ " የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠንና የፀጥታ ችግር ለንግድ ስርአቱ እንከን ሆኖበታል " ብሏል። ህዝቡን እያማረረ ላለው የኑሮ ውድነት ምክንያት " በክልሎች የሚፈጠረዉ የሰላም መደፍረስ እንዲሁም የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን " እንደሆነ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በልሁ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። " መንግስት የኑሮ ዉድነት እንዳለ ያምናል " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ " ፍላጎትን የሚያሟላ አቅርቦትን ለማከናወን ከዉጭም ከዉስጥም ያለዉ ችግር እንከን ሆኗል " ብለዋል። ሆኖም እነዚህ ተግዳሮቶች እንዳሉ ሆነዉ፤ ህብረት ስራ ማህበራት በቀጥታ ከቦታዉ ምርት አምጥተዉ እንዲያሰራጩ ስምምነት ተደርጎ እየተሰራ ነው ብለዋል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 19🔥 2
መላው የኦርቶዶክስ ልጆች አዲሱን ዓመት በዘፈንና ዳንኪራ ሳይሆን በቤተክርስቲያናቸው በጸሎት ፣ በምህላ፣ የቻለም ደግሞ በመጾም፣ እግዚአብሔርን በመመለመን እንዲቀለበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላለፈች። ቤተክርስቲያን ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው የአዲሱን ዓመት አቀባበል በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ ነው። በዚህም የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ ታውጇል። ቤተክርስቲያን ፤ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ጥሪዋን አቅርባለች። ምዕመናን በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ አሳስባለች። ብፁህ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ ፤ " አንዳንድ የዘፈን ግብዣዎችን እየሰማን ነው ፤ ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት የዳንኪራ ግብዣ እየሰማን ነው " ብለዋል። " ለምንም የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች እየተስተጋቡ ነው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይህን እየሰማን ያለነው መደፋፈሩ በዝቶ ፣ ከመጠን በላይ ኑሮ፣ ንቀቱ በዝቶ፣ ማንአለብኝነቱ እንደልብ ተናጋሪው ፣ ፀብ አጫሪው ሃይ የሚለው ጠፍቶ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ብፁዕነታቸው አለኝ ባሉት መረጃ " ቤተክርስቲያን ዘቅዝቆ እሳት ያያያዘ ፣ መስቀል ዘቅዝቆ አንገቱ ላይ ያጠለቀ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊዘፍን ተዘጋጅቷል፤ ግብዣም ተደርጓል። " ብለዋል። " የሰዎችን መብት መንካት ስለማንችል እንደ ኢትዮጵያውያን እገሌ እገሌ ሳይል ከእንዲህ አይነቱ ማንም ተካፋይ ሳይሆን እንደ ኦርቶዶክሳዊያን ዳግሞ የኦርቶዶክስ ልጆች ለፀሎት ታውጇል ፣ ለጾም ለጸሎት እራስን ከማዘጋጀት ውጭ ምንም ትርፍ የሌለው ከሳንቲም ውጭ ትርፍ ለሌለው የሀገርን ገፅታ የሚንድ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከመሆን #እንድትቆጠቡ " ብለዋል። " አባቶቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት ለጾም ፣ለጸሎት ለፍቅር፣ ለሰላም ነው ፤ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚሉት አባቶች በዘፈን እና በዳንኪራ እያሳሳቀ ወደ ሞት፣ ወደ ማዕበሉ የሚገፋ ነገር ላይ ተሳታፊ እንድንሆን ቤተክርስቲያን አትፈቅድም ፣ የሃይማኖት ሰዎችም ድርሻ አይደለም " ሲሉ አስግዝበዋል። ብፁዕነታቸው ፤ " እኔ ምን አገባኝ በሚል በዘመናዊ ስሜት እንደልብ ተካፋይ መሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ነውር ነው ፤ ወንጀልም ነው " ያሉ ሲሆን " ፀብ አጫሪ መሆንም አስፈላጊ ስላልሆነ የኦርቶዶክስ ልጆች በቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ተቀመጡ፤ የሚመለከተው እንደፈለገ ይሁን ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔርን ለምኑ አብረን ተያይዘን እንዳንጠፋ " ብለዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በጳጉሜን 6 ቀናት ሁሉም ምዕመናን እግዚአብሔር መጪውን ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ የአንድነት፣ ብሶተኛ የማይኖርበት ተራብኩ ተጠማሁ ተፈናቀልኩ ተሰቃየሁ ተንገላታሁ የሚል የማይኖርበት ፣ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ዘመን እንዲሰጠን ጸሎት በማድረግ እናሳልፍ ስትል አደራ ብላለች። ጸሎት ለሁሉም የታወጀ ሲሆን ፤ ጾምን በተመለከተ የወደደ ይጹም ፤ ያልወደደም / ፕሮግራሞች ቀደሞ የያዘም እንዲጾም አይገደደም በነፃነቱ መጠቀም ይችላል ተብሏል።
Hammasini ko'rsatish...
👎 4👍 3
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.