cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ሰራዊተ ገብርኤል ዘአራብሳ 🙏🙏

ንዌድሰከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዊ ፍሱሐ ገፅ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
215
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-230 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

©ተወለደችልን        ጥራዝ3.ቁ.91 ተወለደችልን ድንግል ማርያም የነቢያት ትንቢት ሕይወተ አዳም/፪/ ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ የአምላክን ስጦታ ፀንተው ሲፈልጉ በሕግ በሥርዓት ሆነው ሲማልዱ የፀሓይን እናት ሰማይን ወለዱ አባቶች ነቢያት ያደረጓት ተስፋ ምልክት የሆነች በሞት እንዳንጠፋ የቀረችልን ዘር የአምላክ መገኛ የሕይወት ውሃ ምንጭ ተወለደች ለእኛ የጥል ምክንያት ብትሆን ሔዋን በድንግል መወለድ እርቅ ሆነልን ለአዳም ዘር ኹሉ መድኃኒት ናትና እናቱን የሰጠን ይድረሰው ምስጋና
Hammasini ko'rsatish...
voice-changer-2022-04-25-23-34.mp32.26 MB
Photo unavailableShow in Telegram
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው ፤ ንህብ ከሁሉ እንዲቀስም አስቀድሞ ከከርስቶስ ኋላ ከሐዋርያት ተምሯልና፤ አንበሳ ማለት ነው ። አንበሳ ለላም ጌታው እንደሆነ እንዲሰብረው አምልኮተ ላሕምን ከግብጽ አጥፍቷልና ፤ አንድም ካህን ልኡክ ማለት ነው፣ በዚህች በከበረች ዕለት በሚያዝያ 30 ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነ ወንጌላዊ ሐዋርያ ሰማዕት ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል። ረድኤት እና በረከቱ በሁላችንም ላይ አድሮ ይኑር ። "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር "     "የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነዉ" መዝ፡ 115፥6
Hammasini ko'rsatish...
ከትንሳኤ በኃላ ያለው አራተኛዉ ቀን አልዓዛር ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ በዚህ ዕለት የማርያምና የማርታ ወንድም የሆነው አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን ሆኖት ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት አስነሥቶታል፡፡ #ለትንሣኤ_ክርስቶስ_ምሳሌ_ነው፡፡ ለአይሁድ የአልዓዛር መነሣት ቅናት ፈጥሮባቸዋል፡፡እርሱ ሁሉ ትንሣኤና ሕይወት መሆኑን ገልጦ ይህንን ቀን ለአልዓዛር መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አልዓዛር ተብሎ ተሰይሞ ታስቦ ይውላል፡፡ዮሐ 11፥1-42 በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን። አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያምና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር። ስለዚህ እኅቶቹ ጌታ ሆይ፥ እነሆ የምትወደው ታሟአል ብለው ወደ እርሱ ላኩ። ኢየሱስም ሰምቶ፦ ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ። ይህን ተናገረ፤ ከዚህም በኋላ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ አላቸው። ኢየሱስ በቢታንያ አቅራቢያ ከማርታ ከዚያም ከማርያም ጋር ከተገናኘ በኋላ ወደ አልዓዛር መቃብር አብረው ሄዱ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን መግቢያው በድንጋይ ተዘግቷል። ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት”አለ። ማርታ፣ ኢየሱስ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ስላልገባት “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል”አለች። ኢየሱስ ግን “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?”አላት። ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ እየተመለከተ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።”ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት መጸለዩ፣ ቀጥሎ ከዚያም በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!”አለ። አልዓዛር እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ”አላቸው። አልዓዛር ማርያም እና ማርታ ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል። በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም። ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ። ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#ዓለም_ቶማስ_ናት ትንሣኤ በዋለ በሶስተኛው ቀን ቶማስ በመባል ይታወቃል ከቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ክርስቶስ ተነሣ ሲባል ሲሰማ ካላየሁኝ ካልዳሰስኩኝ አላምንም አለ ወዲያውኑ ክርስቶስ መጣ ቶማስ እጁን ሰዶ በጦር የተወጋው ጎኑን እዳስሳለሁ ሲል እንደ ጅማት ተኮማተረ ቶማስ ዋይ አለ አምላኬ ይቅር በለኝ አለ አመነ ዓለምም እንደዚሁ ነች እግዚአብሔር ዓለምን ለማስተማር የሚያደርጋቸውን ተአምራት ላለመቀበል ከቴክኖሎጂ ጋር ያያዙታል ነገሩ ጠንከር እያለ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ሲመጣ ያንጊዜ ሁሉም እጁን ያነሳል የምገድልም የማድንም የምቀስፍም ይቅር የምልም እኔ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ዓለም ካላየሁ አላምንም ትላለች በዘመነ ኖኅ የሆነው እሱ ነው ኖኅ የጥፋት ውሃ ይመጣል የምትድኑበትን መርከብ ስሩ ሲል ያመነ የተቀበለው አልነበረም እግዚአብሔርን ያወቁት በፍል ውሃ ሲቀቀሉ ነው ኢየሩሳሌም ትጠፋለች እያለ ነቢዩ ሲናገር እስራኤላውያን እንደሟርት ይቆጥሩት ነበር እስራኤላውያን ማረን ያሉት የነቢዩ ትንቢት ተፈጽሞ ኢየሩሳሌም ከተወረረች ከአራት ዓመት የምርኮ የባርነት ጊዜ በኋላ ነው ዛሬም በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚንጸባረቀው ይህ ነው መከራ ችግር ቅጣት ወዘተ ካልገጠመን እግዚአብሔር ያለ አይመስለንም ሁላችንም እግዚአብሔር ሆይ የምንለው የመከራ ቀን ነው ከአህዛብ ነገሥታት አንዱ አቤሜሌክ በመከራ በወደቀ ጊዜ አብርሃምን እባክህ ለእግዚአብሔር ንገርልኝ አስታርቀኝ ብሎአል ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ዓለም በነፈር በኮሮና እንደ በሶ ስትበጠበጥ ዓለም እግዚአብሔር መኖሩን ያወቀው ዓለም ቶማስ ናት የምንለው ለዚህ ነው የትንሣኤው ብርሃን ያሳየን ቸሩ አምላካችን ምስጋና ይድረሰው #አባ_ገብረ_ማርያም
Hammasini ko'rsatish...
ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታት ሰሙነ ፋሲካ ወይም ትንሣኤ እየተባሉ የየራሳቸው ምስጢራዊ ስያሜ አላቸው፡፡ ይኸውም፡- #ሰኞ_ማዕዶት ይባላል ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ጌታችን በሞትና ትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱ መታሰቢያ ሆና «ፀአተ ሲኦል ማዕዶት» ትባላለች፡፡ ዮሐ. 19-18 ሮሜ. 5-10-17 የዳግም ትንሣኤው ማግሥት ያለችው ግን ገበሬው፤ ወንዶቹ እርሻ ቁፋሮውን፣ ንግዱን፣ ተግባረ እዱን ሁሉ ሴቶቹ ወፍጮውን፣ ፈትሉን፣ ስፌቱን የሚጀምሩባት ዕለት ስለሆነች «እጅ ማሟሻ» ሰኞ ትባላለች፡፡ #ማክሰኞ_ቶማስ ይባላል በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችን በዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስ ሐዋርያ አልነበረም ኋላ ከሔደበት ሲመጣ ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት እኔ ሳላይ አላምንም በማለቱ በዚህ ጥያቄው መሠረት በሳምንቱ ጌታችን በድጋሚ ስለተገለጸ ለዚህ መገለጹ መታሰቢያ ሆና ዕለቲቱ «በቶማስ» ተሰየመች፡፡ ዮሐ. 20-24-30 #ረቡዕ_አልዓዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አልዓዛር መታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየት በጌታችን ብዙ ሕዝብ ስላመነበት ቀኒቱ «አልዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡ ዮሐ. 11-38-46 #ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ሉቃ. 24-25-49 #አርብ_ቅድስት_ቤተክርስቲያን ይባላል በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዐርብ «ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡ ማቴ. 26-26-29 የሐ. ሥራ. 20-28 #ቅዳሜ_ቅዱሳት_አንስት ይባላል በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በስተቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበይባት «የቁራ ገበያ» የገበያ ጥፊያ ስትባል በቤተ ክርስቲያን ግን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጉልበታቸው ለአገለገሉት በስቅለቱ ዋይ ዋይ እያሉ እስከ ቀራንዮ ለተከተሉት፣ የትንሣኤው ዕለት ገና ከሌሊቱ ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው በመገሥገሣቸው ትንሣኤው ከሁሉ ቀድሞ ለተገለጸላቸው ቅዱሳት አንስት መልካም መታሰቢያ ሆና «አንስት» ተብላ ትጠራለች፡፡ ሉቃ. 23-27-33፣ 24-1-01፣ ማቴ. 25-1-11 #እሑድ_ዳግም_ትንሳኤ ይባላል በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ #ዳግም_ትንሣኤ በዚች ሰንበት ከላይ እንደተጠቆመው የትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ የጌታችንን መነሣትና እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት «በኋላ እናንተ ዐየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን «ሰምቼአለሁ» ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም» በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላም ለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ» አመነ፡፡ እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ጌታ ሁሉም ተሰብስበዉ በተዘጋ ቤት ስል ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20-24-30   #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ለምን አንጾምም? ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች? ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም? በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/። "የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ 15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው። በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም። መልካም በዓል ይሁንልን።
Hammasini ko'rsatish...
Repost from ጎዶልያስ
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ #ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ #አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ #አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ #ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ #ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo @aklesyazetewahdo
Hammasini ko'rsatish...
ህያውን_ከሙታን_መሀል_ለምን_ፈለጋችሁ_አዲሱ_የሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_መዝሙር_ስሙ_4DVJbJhgzgM.mp3
Hammasini ko'rsatish...
ህያውን_ከሙታን_መሀል_ለምን_ፈለጋችሁ_አዲሱ_የሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_መዝሙር_ስሙ_4DVJbJhgzgM.mp39.44 MB
ተነስቷል ጌታችን | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ @Orthodox_Mezmur_For_All @Orthodox_Mezmur_For_All
Hammasini ko'rsatish...
ተነስቷል_ጌታችን_ዘማሪ_ዲያቆን_አቤል_መክብብ.mp34.48 MB
እንደተናገረ_ተነስቷል_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.mp35.91 MB
እዩና_እመኑ_ሰዎች_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኃይሉ.mp33.35 MB
ተነስቷል_በእውነት_ዘማሪ_ዲያቆን_ሳይዛና_ጌታቸው_እና_ዘማሪ_ዲያቆን_እንዳለ_ደረጀ.mp35.84 MB
የጌታ_ትንሣኤ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ_እና_ዘማሪ_ዲያቆን_ሄኖክ_ሞገስ.mp35.96 MB
ተነሳ_ክርስቶስ_ዘማሪት_ትዕግስት_ስለሺ.mp36.26 MB
ታላቅ_ብርሃን_ወጣ_ዘማሪት_ሳራ_ተስፋዬ.mp36.64 MB
የትንሣኤው_ጌታ_ዘማሪ_ዲያቆን_እንዳለ_ደረጀ.mp36.50 MB
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን። አሰሮ  ለሰይጣን ፤ አግአዞ ለአዳም ። ሰላም፤ እምይእዜሰ። ኮነ፤ ፍሰሀ ወሰላም ።
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.