cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አቡ ዐብዲላህ ኑርሁሰይን

ተውሂድና ሱናን የበላይ ለማድረግ እና ሽርክና ቢድዓን ለማንኮታኮት መስራት በእኛ ላይ ያለብን የድናችን ሀቅ ነው። https://t.me/nerhussien

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
215
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-27 kunlar
-630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ፍም እሳት እንደመጨበጥ… ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿يأتي على الناسِ زمانٌ، الصابرُ فيهِم على دينِه، كالقابضِ على الجَمْرِ﴾ “ከበስተኋላችሁ ትዕግስትን የሚጠይቅ ዘመን ይመጣል። አንድ ሰው ዲኑ ላይ ፀንቶ (ታግሶ) መቆየት ፍም እሳት እንደመጨበጥ የሚሆንበት።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 8002
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
አቡ ሁረይራ (ረዓ) እንዲህ ይላሉ:- አንድ ቀን ከነብያችን ﷺ ዘንድ ተቀምጠን ሳለ የሆነ ትልቅ ድምፅ ሰማን፤ ድምፁም የትልቅ ድንጋይ ድምፅ ነበር። ከዚያም ነብያችን ﷺ "ይሄ አሁን የሰማችሁት ድምፅ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?" አሉን እኛም "አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ" አልናቸው። ከዚያም ቀጠሉና "ይሄማ ከ 70 አመት በፊት ጀሀነም እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ሲሆን 70 አመት ሙሉ ወደ ውስጥ እየተምዘገዘገ ገና አሁን ውስጥ ላይ እያረፈ ነው" አሉን ይላሉ። ያ አላህህህህ!!!! فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ አላህ ይጠብቀን! "አላሁም ኢና አዑዙ ቢከ ሚን አዛቢል ቀብር ወሚን አዛቢ ጀሀነም!"
Hammasini ko'rsatish...
አቡ ሁረይራ (ረዓ) እንዲህ ይላሉ:- አንድ ቀን ከነብያችን ﷺ ዘንድ ተቀምጠን ሳለ የሆነ ትልቅ ድምፅ ሰማን፤ ድምፁም የትልቅ ድንጋይ ድምፅ ነበር። ከዚያም ነብያችን ﷺ "ይሄ አሁን የሰማችሁት ድምፅ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?" አሉን እኛም "አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ" አልናቸው። ከዚያም ቀጠሉና "ይሄማ ከ 70 አመት በፊት ጀሀነም እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ሲሆን 70 አመት ሙሉ ወደ ውስጥ እየተምዘገዘገ ገና አሁን ውስጥ ላይ እያረፈ ነው" አሉን ይላሉ። ያ አላህህህህ!!!! فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ ያችን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ አላህ ይጠብቀን! "አላሁም ኢና አዑዙ ቢከ ሚን አዛቢል ቀብር ወሚን አዛቢ ጀሀነም!"🤲🤲🤲🤲🤲 ከኢስላም ጥላ ስር-تحت المظلة الإسلام ☂️☂️☂️☂️☂️☂️☂️☂️☂️☂️☂️
Hammasini ko'rsatish...
⭕️ ምንኛ ያማረች ምክር‼ 🛑 አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር! ⭕️ የምትወዴውን ሰው ማሞገስ አታብዛ፣ ⭕️ ጌታውን ከማይታዘዝ ሰው ጋር አትጓዝ፣ ⭕️ ቁጭ ስትል ሰዎችን አትማ፣ ⭕️ በራሱ ጊዜ ከአንተ የራቀን ጓዴኛ ለመቅረብ አትሯሯጥ፣ ⭕️ ራስህን አታቅል፥ አትኩራ፣ ⭕️ እጅግም አትለሳለስ፥ እጅግም አትንጠባረር፣ ⭕️ እውነቱን የሚያወራ ሰው በብዛት አይምልም፥ ታማኝ ሰው ራሱን መልካም አድርጎ አይስልም፣ ⭕️ ሥራውን ለአላህ ብሎ የሚሠራ ሰው ኋላ ላይ አይጸጸትም፣ ⭕️ ቸር ሰው አይመጻደቅም፣ ⭕️ ራስህን ሁን፥ ሌሎች እንዴሚፈልጉት አትሁን፣ ⭕️ ሰዎችን ማክበርህ የሆነ የምትፈልግባቸው ጉዳይ አለ ማለት አይደለም። ስለ ዲንህና አስተዳዴግህ ልታስተምራቸው ጅማሮ እንጅ፣ ⭕️ አክብር → ትከበራለህ! ⭕️ በጸባይህ ውብ ሁን! ⭕️ ባለህ ተብቃቃ፥ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትልቅ ሁን። ⭕️ ከኋላህ ሆኖ ስለአንተ ወዴሚያወራ ሰው አትመልከት። ምክንያቱም እርሱ በመሠረቱ ከኋላህ እንጅ ከፊት ለፊትህ አይዴለም። ⭕️ ከቁርኣን ምን ያክል እንደምትሸመድድና እንዴምትቀራ ለሰዎች አትንገራቸው። ይልቁንም በአንተ ውሰጥ ቁርኣንን እንዲያዩ አድርጋቸው። ⭕️ የተራበን አብላ፣ የተራቆተን አልብስ፣ እርዳታህን የሚሻን አግዝ፣ ለየቲም እዘን፣ የበደለህን እለፈው፣ ለወላጆችህ መልካም ዋል፣ ለሁሉም ፈገግ በል! ⭕️ ቁም ነገሩ ከቁርኣን ምን ያክል ዴርሰሃል ወይንም ሸምዴሃል ሳይሆን፤ ቁርኣን በአንተ ውስጥ የት ዴርሷል የሚለው ነው። https://t.me/
Hammasini ko'rsatish...
ሱበሀን አላህ የመልካምነት እና የክፋት መጨረሻው ሀብታም ባል የነበራት አንዲት ሴት ነበረች። ባሏ ባጣም ሀብታም ቢሆንም ለደሀ እዝነት የሌለው፣ምስኪን ማብላት የሚጠላ ስስታም ባል ነበር።     ሚስቱ ደግሞ ለደሀ የምታዝን፣ምስኪን ማብላት የሚያስደስታት ሴት ነበረች።አንድ ቀን ከባሏ ጋር ምሳ ሊበሉ እያቀራረበች እያለች     ከጊቢው ውጭ ለአላህ ብላቹ የሚበላ ነገር ካለ የሚል፣የለማኝ ድምፅ ሰማች።በዚህ ጊዜ ለሷና ለባሏ ካዘጋጀችው የዶሮ ስጋ ላይ ግማሹን ቀንሳ ግማሹን ለለማኙ ልትሰጠው ሄደች    ሰጥታው ስትመለስ ባሏ ፊቱ ተቀያይሮ ጠበቃት እንዴት እኛ በልተን ሳናበቃ ከላዩ ላይ አንስተሽ ትሰጪያለሽ ከኔ አንድ ለማኝ በለጠብሽ ብሎ በቁጣ ገነፈለ   ለማኙ እየሰማ እንዲሁም ተከትለሽው ሂጅ አላት....እሷም የተራበ ምስኪን ለአላህ ብላቹ ምግብ ስጡኝ ሲል እየሰማን እንዴት ይበላልናል ብዬ ነው እኮ፣ ከአጠፋሁም እባክህ ይቅርታ አደረግልኝ አለችው እሱ ግን ይቅርታ ከማድረግ ይልቅ ፈትቼሻለሁኝ ሂጂ ውጪልኝ ብሎ ከቤቱ አባረራት.....    ይህን የሰማው ለማኝ ጌታ ሆይ የኔ ችግር ከኔ አልፎ የሰው ትዳርም ማፍረስ ደረጃ ከደረሰ እንግዲህ መኖር በቃኝ ያአላህ ግደለኝ እያለ ከአካባቢው ሄደ   ሚስትም ከ ሀብታሙ እና ስስታሙ ሰውጋ ተፋትታ ሙሉ ሀብት ንብረቱ ጥላለት ወጥታ እሩቅ ሀገር ዘመዶቻጋ ሄደች ።ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ግን የተፈታችው ሚስት ሌላ ሀብታም ባል አገባች።    የሚገርመው ነገር አዲሱ ባሏ ለደሀ የሚያዝን ማብላት የሚወደ እሷ ደሀ ስታበላ እጅጉን የሚደሰት ድግ እና አዛኝ ሰው ነበር     ከእለታት አንድ ቀን ባአዲሱ ቤቷ ምግብ እያዘጋጀች ሳለ ከጊቢው ውጭ የሚላስ የሚቀመስ ነገር ካለ ለአላህ ብላቹ አቅምሱኝ እርቦኛል የሚል የለማኝ ድምፅ ሰማች በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፣ ከአሁን በፊት ይሄ ነገር ትዳሬን አፍርሷል አሁንም ተከትሎኝ መጣ አለች ? ቢሆንም ባለቤቴ እስካልከለከለኝ ድረስ ለባሌ  ምግብ እሰራዋለሁ ብላ ለሷና ለባሏ የምታቀርበውን ለለማኙ ልትሰጥ ሄደች።በባሏ አጠገብ ባሏን ከማለፏ በፊት ባሏን ዞር ብላ ስትመለከተው   በፈገግታ ተሞልቶ በረካ ሁኚ ለለማኙ ድረሽለት አላትበዚህ ጊዜ በደስታ ተዋጠች እሷም እሱም ለጋስ በመሆናቸው ለለማኙ የሚበላውን ሰጥታው ስትመለስ ግን ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች ምን ሆንሽ አላት? ከአመታት በፊት ሀብታም ባል አግብታ ትኖር እንደነበር ነገረችው አንድ ቀን ለኔና ለባሌ ምሳ ልንበላ እያቀራረብኩኝ እያለሁ ለአላህ ብላቹ የሚላስ የሚቀመስ ስጡኝ የሚል ልመና ስሰማ ለኛ የማቀርበውን አስቀምጬ ለለማኙ የሚበላና የሚጠጣ ይዤለት ሰጠሁት ስመለስ ባሌ ለማኙ እየሰማ በቁጣ ለማኙ ከኔ በለጠብሽ ለማኙን ተከትለሽ ሂጂ ብሎ ፈታኝ እኔም ሙሉ ሀብት ንብረቱ ትቼለት ወጣሁ አሁን እዚህ የመጣው ለማኝ ያ #ሀብታም የነበረው ባሌ ነው።  ከስቷል፣ጠቁሮዋል፣ተጉሳቁሏል ገላውን እንኳ በቅጡ የማይሸፍን ብቱቶ ለብሶ ፊቴ ቆሞ ሳየው አላስችል ብሎኝ ነው የማለቅሰው አለችው እሱም በጣም ተገርሞ የዛን ቀኑ ለማኝ እኮ እኔ ነበርኩኝ  አዎን አሏህ  ሀብታም የነበረውን ባል ለማኝ አድርጎ አምጥቶ ፊትሽ አቆመው ለማኝ የነበረውን ለማኝም እነሆ ሀብታም ባል አድርጎ አምጥቶ ፊትሽ አቆመው በዛች ቀን በዛች ሰአት ጌታዬን የኔ ችግር ከኔ አልፎ የሰው ትዳር ማፍረስ ላይ ከደረሰ በቃኝ ግደለኝ ብዬ ለምኘው ነበር ሞቴን በተስፋና በደስታ ስጠባበቅ ያልተጠበቀ ሀብት እጄ ገባ ህይወቴ ተለውጦ የመኖር ፍላጎት ቢያድርብኝም ጌታየን ያችን በኔ ምክንያት ትዳሯን ያጣችን ሴት!! ያችን በኔ ምክንያት የተገፋችን ሴት አግኝቼ ከሀብቴ ሳልሰጣት እንዳልቀር እያልኩ አላህን በልቤ እለምን ነበር ከኔ በላይ ለኔ የሚያዝነው ጌታዬ!! ከፈለክ ሀብትህን ብቻ ሳይሆን ሁለመናህን ስጣት ብሎ አንችን ለኔ ሚስት አርጎ አመጣሽ!! አለና በግንባሩ ተደፍቶ የምስጋና ስግደት ለአላህ ሰገደ https://t.me/deawa_selefiya
Hammasini ko'rsatish...
የመቅደላ ማሻ ሰለፍዮች ቻናል

የታላላቅ ዳኢዎችን ፈዋኢድ የሚያገኙበት ቻናል ነው።ይቀላቀሉ።

👍 2
አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ [صلى الله عليه وسلم] እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ ጀነትና ጀሀነምን በፈጠረ ጊዜ ጂብሪልን “ጀነትንና በውስጡ ነዋሪዎ ለሚሆኑት ያዘጋጀሁትን” ተመልከት፡፡ በማለት ላከው፡፡ ከዚያም ወደ ጀነት ሄዶ አላህ ያዘጋጀውን ተመለከተ፡፡ ወደ እሱ (አላህ) ዘንድ በመመለስም፡- “በአንተ ልዕልና እምላለሁ፣ ስለጀነት የሚሰማ ሁሉ እንደሚገባበት (እርግጠኛ) ነኝ” አለ፡፡ ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) ጀነት ዙሪያው በአዳጋች ነገሮቸ እንዲከበብ አዘዘና “ወደ ጀነት ተመልሰህ በውስጡ ነዋሪዎች ለሚሆኑት ያዘጋጀሁትን ተመልከት” አለው፡፡ ዳግም በሚሄድበት ጊዜ ዙሪያው በአዳጋች ነገሮች ተከብቦ አገኘው፡፡ ከዚያም ወደ (አላህ) በመመለስ “በአንተ ልዕልና እምላለሁ፤ አንድም ሰው እንደማይገባበት እሰጋለሁ” አለ፡፡ እሱም “ወደ ጀሀነም እሳት ዘንድ ሂድና እሱንና በውስጡ ነዋሪዎች ለሚሆኑት ያዘጋጀሁትን ተመልከት” አለው፡፡ ጂብሪልም የጀሀነም እሳት አንዱ በሌላው ላይ ተነባብሮ አገኘው፡፡ ከዚያም ወደ እሱ ዘንድ ተመልሶ “በአንተ ልዕልና እምላለሁ፣ ስለእሱ የሚሰማ አንድም አይገባበትም” አለ፡፡ ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) (የጀሀነም) ዙሪያ በሥጋዊ ፍላጎቶች እንዲከበብ አዘዘ፡፡ ከዚያም ጂብሪልን “(ወደ ጀሀነም) ተመለስ” አለው፡፡ እሱም ተመለሰ፡፡ “በአንተ ልዕልና እምላለሁ፤ አንድም ከመግባት እንደማያመልጥ እሰጋለሁ” አለ፡፡ ቲርሚዚይ፣ አቡዳውድና ነሳኢይ ዘግበውታል https://t.me/
Hammasini ko'rsatish...
1
ወደ አሏህ የተቃረብሽ ከሆንሽ......!? በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትኖሪም ደስተኛ ትሆኛለሽ!...ከአሏህ የራቅሽ ከሆንሽ ደግሞ በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኝም እድለቢስ ትሆኛለሽ ። ወደ  አሏህ  በተቃረብሽ  ቁጥር ተስፋ  መቁረጥ  ካንቺ ይርቃል‼️ በልብሽ ውስጥ ተቅዋ ከተረጋገጠች የደስታን ጣዕም እና ሁሉም ጉዳይ ገራገር ሲሆንልሽ ታይዋለሽ ። በውስጡ ሰምጠሽ የምትድኚበት ፍቅር የአሏህ ፍቅር  ብቻ ነው!!ትድኚም ዘንድ ወደ እርሱ አብዝተሽ ተጠጊ‼️ ምናልባት  አሏህ  የምትፈልጊውን ነገር የከለከለሽ የሚያስፈልግሽን ነገር ሊሰጥሽ ይሆናል ። وَعَسَى أَنْ تَكْرَهُوُ شَيْئَاً وَهُوَ خَيْرٌا لَكُمْ وَعَسَيٰ أَنْ تُحِبُّوُا شَيْئَاً وَهُوا شَرٌ لَكُمُ وَاللَّه يَعْلَمُ وَأَنْتُم لَا تَعْلَمُوُنْ" ነቢዩሏህ አዩብ 18 አመት ጠበቀ ነቢዩሏህ ዩሱፍ 13 አመት ጠበቀ ነቢዩሏህ ያዕቁብ 14 አመት ጠበቀ ነቢዩሏህ ሙሳ 40 አመት ጠበቀ‥ ዱኣሽን ይቀበላልና ተስፋ አትቁረጭ‼️ ጉዳይ ኖሮሽ ለማሳካት አቅሙ ከሌለሽ አቅም ኖሮት ጉዳይ የሌለው ጌታ አለሽና ፊትሽን ወደርሱ አዙሪ…! በአሏህ ላይ ተስፋ ማድረግ ትእግስተኞች እንጂ ማንም የማያውቃት ሌላ ህይወት ናት ። እወቂ !! አንች ለነፍስሽ  ከምትፈልጊው ኸይር በላይ  አሏህ ላንች ይፈልጋል ። አሏህ በፈቀደልሽ ነገር ላይ ተብቃቂ በእርሱም ላይ በርቺ ሳትሰላቺ አሏህ ከከለከለሽ ነገሮች ተጠንቀቂ ራቂ! وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبْ..! ጆይን፡‐ https://t.me/deawa_selefiya
Hammasini ko'rsatish...
የመቅደላ ማሻ ሰለፍዮች ቻናል

የታላላቅ ዳኢዎችን ፈዋኢድ የሚያገኙበት ቻናል ነው።ይቀላቀሉ።

👍 2
ልብ እርጥብ ሚያደርግ ቲላዋ ተጋበዙ ➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/deawa_selefiya
Hammasini ko'rsatish...
سورة_الفرقان_كامله_تلاوه_باصوااات_متعدده_من_رواااائع_#شيخ_همام_تاج.m4a17.54 MB
ሀቅ መራራ እንኳን ብትሆን  ተቀበሉ ሀቅ ሆኖ ከማንኛውም ወገን ቢመጣ የመቀበል ግደታ አለብን  ነገር ግን ባጢል የሆነን ነገር ሀቅ አስመስለው ሊጥሉቡን ለሚሞክሩ ሰወች መቸም ቢሆን እጅ አንሰጥም ለዛም ነው ከማንኛውም ግዜ በላይ በዚህ ሰአት  እውቀት ላይ አተኩሩ የሚሉት ሽይኹል አልባኒ አላህ ይዘንላቸው ’ ምክኒያቱም የባጢል ባልተቤቶች ባጢላቸውን ሀቅ ለማስመሰል መረጃ ለመጥቀስ ይሞክራሉ ያኔ ከእውቀት ነፃ ከሆንክ በሹብሀ ጎርፍ ትወሰዳለህ ያቅምህን ያክል እውቀት ለመቅሰም ተፍጨርጨር ትኩረትህ ሁሉ እውቀት ፍለጋ ላይ ይሁን  እውቀት መጨመርን ሁሌም አተኩር አሉቧልታ ውስጥ እየገባህ ግዜህን አትጨርስ የሚጠቅምህን  ከሚጎዳህ  ለይተህ ተንቀሳቀስ #ወሬ የለው ፍሬ ነው እና ነገሩ ወሬ ከማራገብ ራቅ እስኪ አስተውል ስንት አመት አወራን ግን አስኪ ምን አፈራን ድምፃቸውን አጥፍተው የተማሩ ወንድሞችና እህቶች የት ደረሱ ብለህ ጠይቅ ያኔ እራስህር የት እዳለህ ትገመግማለህ ወሬ፣ ሀሜት ፣ነገር  ኪሳራ እንጅ ትርፍ የለውም። https://t.me/nur hussien
Hammasini ko'rsatish...
ለዒልም ተማሪዎች ጉርሻ ኪታብ ከሚቀሩ ተማሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ ለልፋታቸው የሚመጥን በቂ ግንዛቤ አይጨብጡም። ከነዚህ በተቃራኒ ደግሞ በቂራአት ማእድ ላይ ያላቸው ቆይታ አነስተኛ ሆኖ የተሻለ የሚጠቀሙ አሉ። ልዩነቱ ከምን የመነጨ ነው? ለዚህ ልዩነት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ አድምቶ አለመቅራት የሚያመጣው ክፍተት ነው። የብዙ ተማሪዎች አያያዝ የለብ ለብ ነው። አንዱን ኪታብ ጥንቅቅ አድርገን ሳንይዝ ከፍ ወዳለው ለመግባት ያለን ጉጉት ብዙ ቀርተናል የሚል ጉጉታችንን ከማርካት ባለፈ ብስለት እንዳይኖረን ሊያደርገን ይችላል። ይህንን ክፍተታችንን ለመድፈን ከሚያግዙ መንገዶች ውስጥ ሶስቱን ላንሳ፦ 1- ቃላት ለቀማ 2- መልእክቱን መጨበጥ 3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት ላብራራቸው። 1- ቃላት ለቀማ፦ ከምንቀራው ኪታብ ውስጥ አንድ የማናውቀው ቃል መኖር የለበትም። በተቻለ መጠን ሁሉንም ልቅም አድርገን ልንይዝ ይገባል። በዚህ መልኩ ስንሄድ ደርስ በጣም እየቀለለን ነው የሚሄደው። ቃላት በቅጡ ሳንይዝ የምንጓዝ ከሆነ ግን ወደላይ በገፋን ቁጥር ይበልጥ እየከበደን ይሄዳል። በዚያ ላይ ቃላት የማንይዝ ከሆነ አጠቃላይ የደርሱን ጭብጥ የመያዝ እድላችን እያነሰ ነው የሚሄደው። 2- መልእክቱን መጨበጥ:- ከኪታብ ትምህርት ዋናው የሚፈለገው አላማ መልእክቱን መጨበጥ ነው። ቁርኣን የወረደው፣ ሐዲሥ የተላለፈው የቃላት ትርጉም ለማስተማር ሳይሆን ለሰዎች የሚበጃቸውን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። በብዛት በሃገራችን የተለመደው የቃል በቃል ትርጉም የማስተማር ዘዴ በዚህ በኩል ጉልህ ክፍተት አለበት። ስለዚህ ለመልእክት በቂ ትኩረት መስጠት ይገባል። እዚህ ላይ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። "የተማርነውን ኪታብ በበቂ ሁኔታ እንደተገነዘብነው መለኪያው ምንድነው?" የሚል። መለኪያው የተማርነውን ኪታብ ለሌላ ማስተማር በሚያስችል መጠን ይዘነዋል ወይ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ ነው። ለራሳችን እውነተኛ ሆነን እንመልስ። አንዳንዴ አስተማሪዎች ሲሳሳቱ "ማግኘታችን" የራስ ሽንገላ ውስጥ እንዳይከተን ልንጠነቀቅ ይገባል። የእውነት ኪታቡን በስርአት ቁጭ ብለን ማስተማር እንችላለን? ካልሆነ ወደሌላ ኪታብ ለመቀጠል ከመጓጓታችን በፊት አጥርተን እንማር። "ይህንን ኪታብ ቀርተነዋል፤ ሌላ ይሁንልን" ከማለታችን በፊት ራሳችንን እንገምግም። 3- ነጠብጣቦችን ማገናኘት:- በዚህ ክፍል ሁለት ነጥቦችን ነው መጠቆም የፈለግኩት። 1ኛ፦ ማስረጃን ከነጥቡ ጋር፣ በአንድ ባብ (ርእስ) ስር የተደረደሩ የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ከርእሱ ጋር ማገናዘብ። እየነጠሉ መረዳት በቂ አይደለም። ይሄ ሐዲሥ እንዴት ነው ማስረጃ የሚሆነው? ይሄ መልእክት ከርእሱ ጋር እንዴት ነው የሚናኘው? እያልን ማስተዋል ይኖርብናል። 2ኛ፦ ከራሳችንና ከህዝባችን ተጨባጭ ጋር ማገናኘት። ይህም የምንማረው ትምህርት ራስንም ወገንንም ለመለወጥ እንዲያግዘን ይረዳናል። ሀዛ ወላሁ አእለም https://t.me/nerhussien
Hammasini ko'rsatish...
አቡ ዐብዲላህ ኑርሁሰይን

ተውሂድና ሱናን የበላይ ለማድረግ እና ሽርክና ቢድዓን ለማንኮታኮት መስራት በእኛ ላይ ያለብን የድናችን ሀቅ ነው።

https://t.me/nerhussien

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.