cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ቢንት ኢብራሂም

"ወደ አሏህ የሚወስደው መንገድ ረጅም ነው።እኛ በእሱ ላይ እንደ ኤሊ እየተጓዝን ነው።አላማችን መንገዱን መጨረስ አይደለም።ይልቁንም መንገዱ ላይ ሁነን መሞት ነው።" ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁሏህ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
673
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-67 kunlar
-1930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
👉 አስደሳች የቂርኣት ዜና ወቅቱ በሸሪዓ እውቀት በሁሉም ዘርፍ መታጠቅ ወሳኝ የሆነበት ነውና ሌሎችን የእውቀት ዘርፎችን በቀላሉ ለመረዳት ይረዳ ዘንድ የዐረቢኛ ቋንቋ መማሩ ወሳኝ በመሆኑ… እነሆ ከነገ እለተ ጁምዓ ሐምሌ 28 ጀምሮ በሳምንት 2ቀን ሐሙስና ጁምዓ የአጀሩሚያ ኪታብ (ነህው) ቂርኣት በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል እንደሚጀመር ስናበስሮት በታላቅ ደስታ ነው!! 🕰ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ በኡስታዝ አቡ'ል ቡኻሪ ሙባረክ (ሀፊዘሁላህ) ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊትለፊት ባለው ቂያስ ከዱና ዳቦ ጀርባ 2ኛው ቂያስ ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031 የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Hammasini ko'rsatish...
ሁን እንደ ነብር ጣት!!! =========> ወዳጄ! ሲባል አልሰማህም ወጣት ትኩስ ሀይል ለምንም ለማንም ጀግና  ወደ ኋላማይል ሲባል አልሰማህም ወጣት የነብር ጣት ችግሮችን  የሚያልፍ   ያለምንም ስጋት ይህንን ተላበስ ዛሬ ከሆንክ  ወጣት ===///====///====///==///===> ሌት ቀን  የሚለፋ  የተውሂዱ ጀግና የማይደራደር በተውሂድ በሱና በምንም አማራጭ የማይሰጥ ዋስትና ለተውሂድ  ይለፋል  ብዙ ይሰራል ገና እንመልከት  እንጂ  ቆይተን በደህና ===///====///====///==///===> ለቢድዓ ኮተት  አይንበረከክም ለባጢል ባለቤት ልቡ  አይሸበርም ላድስ መጤ  ነገር  አይጨናነቅም የጠፊዎች ብዛት  አያታልለውም ተንኮላቸው ሁሉ ልቡን አይንደውም ===///====///====///==///===> ለግብስብስ  ኢኽዋን ለስልጣን ጥመኛ የሚያግበሰብሱት ለሆኑ የብዛት  ሱሰኛ የማይጨነቅ ነው ለነዚህ  ዋሽቶ በላተኛ ይፋለማቸዋል  ሁል ጊዜ  ለነሱ ሳይተኛ በዚህም በትግል ተግባሩ ሆኗል እዲለኛ ===///====///====///==///===> ለአህባሽ ለሱፍያ ለቀብር አምላኪ የሚንቀሳቀሱት ይዘው ቲርኪሚርኪ የጠንቋይ ጥርቅም የሰይጣን ተላላኪ ለነዚህ  ጉደኞች   ሳይሆን  ተንበርካኪ ይታገላቸዋል ጥሩ በሆነ በሚባል አርኪ ===///====///====///==///===> ማንም ይሁን ማንም ለጥመት አራማጅ ለሚንቀሳቀሱት በስሜት አስገዳጅ ባጢልን አንግበው በከንቱ ተራማጅ ለሚያስፈልጋቸው የተውሂዱ ጋራጅ ይለፋል ያጀግና እነሱን ለማረም ካሉበት በሽታ  በሀዲስ ለማከም ሀቁን ሊያሳያቸው ከንቱውን ሊያጨልም ይደክማል ሳይሰለች ባጢሉን ለማክተም ➶➚➶➶➚➚➶➚➶➚➶ ማንን ይመስልሀል እንዲህ የገለፅኩት ከላይ ባለው መንገድ ላንተ ያብራራሁት አንተን ወጣቱን ነው በል ስማ ወንድሜ አስተውል ከልብህ ልምከርህ ደግሜ ===///====///====///==///===>  ታጥቀህ ተነሳና የህሊና ንቃት ተላብሰህ ቁምና ጥሩ የሆነ ብቃት አጥብቀህ ታንፀህ ጥርት ባለች እውቀት ተውሂድ ሱናን አንግስ ጀግን አንተ ወጣት ቢድዓን ተዋጋ ሁን እንደ ነብር ጣት ሽርክን አንኮታኩት ሁን እንደነብሮ ጣት ሰማኸኝ ወዳጄ!!! ሁን እንደ ነብር ጣት ✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️ ✍ አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን ሀሰን አላህ ይጠብቀው! 📱⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
Hammasini ko'rsatish...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

ሙዚቃ በሰው ልጆች ላይ ➬➬➬➬➬➬➬➬➬ ✅ አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ሙስሊሞች እርካታን፣ መረጋጋትንና እድለኛነትን የሚጎናጸፉበትን ምቹና ቀጥ ያሉ በውስጣቸው በረካ የተሞላባቸውን አቅጣጫዎች የያዘ መመሪያ አውርዷል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሙስሊሞች ከዚህ ቀጥተኛ ጎዳና በማዘንበል ጣፋጭ የሆነ ህይዎት ወይም የልቦና መረጋጋትን እናገኛለን በሚል ስሜት ጎጅና ከባድ ተጽእኖዎችን ወደሚያስከትሉ ተግባራት ፊታቸውን ሲያዞሩ ይስተዋላል፡፡ ዘወትር ሙዚቃ በማዳመጥ ቀልባቸውን የሚያደርቁ በርካታ ወጣቶች አሉ፤ ለምን እንደሚያዳምጡ ሲጠየቁም የቁርኣንና የሐዲስን መረጃዎች መሰረት ያላደረገ ፈትዋ ከአንዳንድ ዑለሞች በመስማታቸው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡በተለይም አሁን ባለንበት ዘመን ቀልብ የሚስቡ የድምጽ ቅላጼዎች በዘመናዊ መሳሪያ እየታጀቡ በመምጣታቸው ወጣቱ ትውልድ ለዱንያውም ይሁን ለአኼራው ጥቅም ከሚያስገኙ ነገሮች ርቆ በማይረቡ ነገሮች ብቻ ተጠምዶ ይስተዋላል፤ በዚህም የነገሩ አስከፊነት እየጨመረ ሄዷል፡፡ እነዚህ ነገሮች መስፋፋታቸው ➩ ዲናቸው እንዲዳከም፣ ➪ ስነ-ምግባራቸው እንዲወርድ፣ ➩  ከከፍተኛና መልካም ከሆኑ ባህሪያት ተርታ ወርደው ወደዘቀጡና ወራዳ ወደሆኑ ባህሪያት ተርታ እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ዘፈኖች ክልክል ለመሆናቸውና በሙእሚኖች ላይ እያሳደረ ያለው ➼ የልቦና፣ ➻ የአዕምሮ፣ ➬ የዲን እና የስነ-ምግባር ተጽእኖ ከባድ መሆኑን የሚያብራሩ ከቁርኣንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን ይዞ የኢስላም ሸሪዓ መጧል፡፡ . . . ➜ ሙዚቃ በሰው ልጆች ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት መካከል በልቦና ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ነው፡፡ በነፍስ ውስጥ ሀራም የሆኑ ስሜቶችን ለመቀስቀስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ብልሹ የሆኑ ፍላጎቶችን ያመጣሉ፤ ከከፍተኛና ምስጉን ባህሪያት ሰዎች እንዲርቁ ያደርጋሉ፡፡ ➼ ሙስሊሞች በዘፈን አማካኝነት አላህን ከማስታወስ፣ ቁርኣን ከመቅራት፣ መልካም ነገሮቸን ከመስማት፣ በመልካም ነገሮች ከመመካከር መታገዳቸውን እንጅ ሌሊት ተነስተው ሶላት እንዲሰግዱ፤ ለወላጆች በጎ እንዲሰሩ፤ ዝምድና እንዲቀጥሉ፤ ሶደቃ እንዲያወጡ አንድም ቀን ተቀስቅሰው እንደማያውቁ ይገልጻሉ፡፡ ➩ አቅለኛ የሆነ ሰው አላህን ከመታዘዝ ከሚያርቁና ሐጢያት ላይ ከሚጥሉ ተግባራት ሊርቅ እና ከመጥፎ ስነምግባርና ከስሜት በሽታዎች በአላህ ሊጠበቅ ይገባዋል፡፡ 📖 ሙዚቃና የሙዚቃ መሳሪያዎች እርምነት ከሚለው ሪሳላህ የተቀነጨበ https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
Hammasini ko'rsatish...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

ያረቢ! ሳንጠይቅህ ውዱን እስልምና ሰጠህን። ጠይቀንህ ደግሞ ውቡን ጀነት አትከልክለን። t.me/bintibrahimm
Hammasini ko'rsatish...
ቢንት ኢብራሂም

"ወደ አሏህ የሚወስደው መንገድ ረጅም ነው።እኛ በእሱ ላይ እንደ ኤሊ እየተጓዝን ነው።አላማችን መንገዱን መጨረስ አይደለም።ይልቁንም መንገዱ ላይ ሁነን መሞት ነው።" ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁሏህ

እኔ ሁለት ሰዎች ይገርሙኛል አቡ ጦለሓ vs ዑመር ከዕለታት በአንዱ ቀን አቡ ጦለሃ ሶላት ላይ ባለበት ሁኔታ የሚያምረው የአትክልት ቦታው ውስጥ ያረፈች አንዲት ወፍ ትኩረቱን ሳባችው ሀሳቡን ከሰላቱ ሰረቀችው ሰላት ውስጥ ሆኖ ዓለማዊ ጉዳይ ሀሳቡን በመስረቁ ለዚህ ክስተት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ የአትክልት ቦታውን ባለበት ሁኔታ ሰደቃ ሰጠው ። በተመሳሳይ ዑመር ረዲአላሁ በአንድ ወቅት ከአስር ሰላታቸው ያዘናጋቸውን ሃያ ዲርሃም የወርቅ ሳንቲም የሚያወጣን የአትክልት ቦታቸውን ሰደቃ ሰጥተውታል ። እውነትም በላጭ ትውልድ !! አላማቸው አኼራ ብቻ የሆኑ ትውልዶች !! ═════ ❁✿❁ ══════ ✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!! https://t.me/Jebrilsultan
Hammasini ko'rsatish...
አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!

Photo unavailableShow in Telegram
💡#የሚስቱን ፎቶ የሚፖስት!   <===============> 📝 የሚስቱ ቆንጆነትም ሆነ የሚስብ አካላቷ እንዲታይለት ከሚስቱ ጋር ፎቶ ተነስቶ የሚያሰራጭ (የሚፖስት) ወንድ “የወንድ አልጫ”፣ እኔ ወንድ አይደለሁም ወንድ የሆናችሁ እይዋት የሚል፣ ሚስቱን የጋራ እቃ ያደረገ ከንቱ ነው። ትክክለኛ ወንድ ግን ማነም እንዳያይበት ሸፍኖ ለግሉ ይጠቀማል። አብዱረህማን ዑመር ሀፊዘሁሏህ 📱⇘⇘⇘⇘⇘ https://t.me/AbuYehyaAselefy https://t.me/AbuYehyaAselefy https://t.me/AbuYehyaAselefy
Hammasini ko'rsatish...
የምን ፕራንክ ነው!? እንዴ!!!መሰልጠን እና መሰይጠን ለዩ        ❪„„„„„„„„„„„„„„„„„❫ ✅ ባለንበት የተደበላለቀ ዘመን የጠራ እውቀት ላይ ሆኖ ዲኑን እና ክብሩን የጠበቀ ታድሏል። ♻️ በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰው busy ካደረጉት የምዕራባውያን ኮተቶች መካከል “ፕራንክ” ❮prank❯ የሚሉት ነው። ➲ Prank ማለት ራሳቸው ምዕራባውያን እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፦ «Prank is a mischievous trick or practical joke.» ፕራንክ ማለት የተሳሳተ ተንኮል ወይም ተግባራዊ ቀልድ ነው።ይህ የተሳሳተ ተንኮል ሰዎች ባለወቁበት መልኩ የሚያስደነግጥ ነገር ይተገበርባቸዋል። ከደነገጡ ብሎም ካለቀሱ በኋላ prank ይባላሉ። በዚህ ተግባር በርካታ አላስፈላጊ ኮተቶች አሉ። ↪️ ሙስሊሞች በዚህ ተግባር መሳተፍ የለባቸውም በፍፁም አንዳንድ ሙስሊሞች ተሳትፈውበታል። የድሮ ፍቅረኛዬ ምናምን እያሉ ወንደላቸውን በሚዲያ የበተኑ ሙስሊም ሴቶችን  አስተውያለሁ። ካፊር ሴት እያቀፈ የሚጃጃል ወንድም ተመልክቻለሁ። ሌሎችም ➪ ስለዚህ ከዚህ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አስፈላጊ ነው። የዚህን መሰል ፈሳድ ካፊሮች ሲያመጡ መከተል እነሱን ከመወዳጀት  ነው። ይህ ደግሞ አደጋ መሆኑ ግለሰፅ ነው። «وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ مِنْكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ» [المائدة: 51] ❝ከእናንተ የተወደጃቸው ሁሉ እኮ እርሱ ከእነርሱ ነው❞ ♻️ ነብዩ ﷺ ይህን አይነት መመሳሰል በግልጽ ማውገዛቸው ከማናችንም የሚሰወር አይመስለኝም። عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ:- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:- "مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ". (صحيح أبي داود) حسنه الألباني (3401) ኢብኑ ዑመር  ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፦ “ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው” [ሶሂህ አቡ ዳውድ]ፕራንክ የምዕራባውያን ፍብርክ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ተግባር መሰለፍ ከእነሱ መመሳሰል ነው። ሲጀመር በውስጡ ያሉ ፈሳዶች ❪ጥፋቶች❫ ፕራንክ መራቅ ካሉብን ተግባራት መሆኑን ይጠቁሙናል። ሌላ አንድ ሀዲስ እንጨምር፦ «عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:- ((لَتَتْبَعُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ شِبْرًا شِبْرًا وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا جُحْرَ ضَبٍّ تَبِعْتُمُوهُمْ)). قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى قَالَ:- ((فَمَنْ)).» رواه البخار ٧٣٢٠ ↪️ አብደላህ ብን ኹድሪይ እንዳስተላለፈው ነብዩ ﷺ የሚከተለውንብለዋል፦ “ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቦጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!”   [ቡኻሪ፡ 7320]ከዚህ ሀዲስ አንፃር የት ነን!? በፕራንክ ጉዳይ busy የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ሀዲስ ልትገሰፁ ይገባል። እስከመቼ ይሁዳ እና ነሷራ ተከትለን እንጓዛለን!? ደግሞ ሙሉዕ የሆነ ዲን እያለን!!! እስልምና ያጓደለው ምንም የለም።  እስልምና ያልስተማረው ካለ ካለና ከሰራነው በትክክል ጥመት ነው። በጥመት ተግባር መሳተፋችንንም ማወቅ አለብን። ነገሮችን ቀለል ማድረግ ትተን ከፕራንክ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አለብን። ↪️ በነገራችን ላይ በዚህ ፕራንክ በሚሉት ኮተት ብዙ ጊዜ የሚከሰቱበት ሁለት ተግባሮች አሉ እነሱም፦ ❶ኛ ሰዎችን ማሸበር ወይም ማስደንገጥ እና ❷ኛ በውሸት ቅንብር ማሳቅ ነው። ☑️ እነዚህ ሁለት ተግባራት ደግሞ በእስልምና የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃዎችንእንመልከት፦የመጀመሪያውን በተመለከተ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ማስጨነቅ ወይም ማሸበር አይፈቅድም፦ عن عبدالرحمن بن أبي ليلى قال:-  قال رسول الله ﷺ "لا يحلُّ لمسلمٍ أن يروِّعَ مسلمًا"        صححه الإمام  الألباني           سنن أبي داود አብዱረህማን ኢብኑ አቢ ሌይላ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሙስሊም ሙስሊምን ማሸበር አይፈቀድለትም" ሱነን አቢ ዳውድ ኢማም አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ✅✅ ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ» "ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!" አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተለውን ሀዲስ እናገኛለን፦ عن أبي أمامة رضي الله عنه قال:- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم:- "أنا زعيم ببيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقا، وببيت في وسط الجنة لمن ترك الكذب وإن كان مازحا، وببيت في أعلى الجنة لمن حسن خلقه".  سنن أبي داود وحسنه الألباني. ♻️ አቡ ኡማማህ ረዲየሏሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡- "እኔ እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን ለተወ ሰው በጀነት ዙሪያ ወይም ዳርቻ ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ስነ ምግባሩ ላማረለት ደግሞ በጀነት የላይኛው ክፍል ውስጥ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።" ሱነን አቢ ዳውድ አል-አልባኒ ሀሰን ብለውታል። ➲ በዚህ ሀዲስ ❸ ነጥቦች ጎልተው ተጠቅሰዋል። ❶ኛ ክርክር ❷ኛ ውሸት ❸ኛ ስነ-ምግባር ✅ ውዱ ነብይ ﷺቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።❞ በማለት በቀልዳችን መዋሸት እንደሌለብን አስረድተዋል። ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞች በፕራንክ ቀልድ የሚደረጉ ውሸቶች ትክክል አይደሉም። እኛም ተጠንቅቀን ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል። 📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
Hammasini ko'rsatish...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

Photo unavailableShow in Telegram
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ "የእድለኝነት ባለቤቶች የተውሒድ ባለቤቶች ናቸው" قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله: “أهل السعادة هم أهل التوحيد..’ مجموع الفتاوى، ٩|٢٩ https://t.me/Abdurhman_oumer/3207
Hammasini ko'rsatish...
00:27
Video unavailableShow in Telegram
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ🌹 اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ🌹 @bintibrahimm
Hammasini ko'rsatish...
1.76 MB
🚫 ከሰጋጆች ስህተቶች ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታል ። ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች ውስጥ : – – በሶላት ውስጥ አለመረጋጋት ይህ የሶላት ሩክን ሆኖ ሳለ ብዙዎች ጋር የሚታይ ስህተት ነው ። ሩኩዕ ላይ ፣ ከሩኩዕ ቀና በሚባልበት ጊዜ ( ኢዕቲዳል ) ላይ ፣ ስጁድ ላይ ፣ በስጁድ መካከል መቀመጥ ላይና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ መረጋጋት ግዴታ ነው ። ካልሆነ ሶላት ያበላሻል ። – እንቅስቃሴ ማብዛት ይህ ኹሹዕ ከማጣት የሚመጣ ከሶላቱ ጋር በሚገናኝ ጉዳይና ሸሪዓዊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በጣም የተጠላ ነው ። – ኢማምን መሽቀዳደም ኢማምን መከተል ግዴታ ሲሆን እሱን መሽቀዳደምና ቀድሞ መነሳት ፣ ሩኩዕ ማድረግ ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ከስጁድ መነሳት የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ሶላት ያበላሻሉ ። – ኢማሙ የሁለተኛውን ተስሊም ሳይጨርስ ያመለጠን ለሞሙላት መነሳት – በንያ ድምፅ አውጥቶ መናገር ንያ ቦታው ቀልብ ስለሆነ ድምፅ አውጥቶ መናገር አያስፈልግም ። – መስጂድ ገብቶ ኢቃም እስከሚባል ቆሞ መጠበቅ አዛን ከተባለ በኋላ መስጂድ የገባ ሰው ወዲያውኑ ሁለት ረካዓ መስገድ ይኖርበታል ። ነብዩ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – በሁለት አዛኖች ( በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት አለ ) ስላሉ ቆሞ መጠበቅ አያስፈልግም ። ቀብልያ ያለው ሶላት ሆነም አልሆነም ለተሒየቲል መስጂድ ለሱነተል ውዱእና ለሱናውም ይሆንለታል ። – መስጂድ ገብቶ ኢማሙ ስጁድ ላይ ወይም ተሸሁድ ላይ ከሆነ ቆሞ መጠበቅ ይህም በጣም ስህተት ነው ። ኢማሙ ባለበት ሁኔታ ተከትሎ ያመለጠውን ኢማሙ ሲጨርስ ሞሙላት ነው ያለበት ። – በስጁድና ሩኩዕ ላይ ቁርኣን መቅራት – አይንን ግራና ቀኝ ወይም ወደ ሰማይ ማድረግ ሶላት በምንስግድበት ጊዜ ወደ ስጁድ ማድረጊያ ቦታ ማየት ነው የሚያስፈልገው ። ሸይጣን ሶላታችንን እንዳይሰርቀን – በሁለት እግሮች ተረከዝ ላይ ቁጭ ብሎ ስጁድ ላይ ሁለት እጆችን እስከ ክርን መሬት ላይ መዘርጋት – በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ ( ሶላት ማቋረጥ ) – ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ደርሶ ተክቢረተል ኢሕራም ሳያደርጉ ጎንበስ ማለት – ሶላት ላይ ዐይኖችን መጨፈን – በስጁድ ላይ የእግር ጣቶችን ማንሳት – ስጁድ ሲያደርግ መሬቱን መሳም – ሶላት ላይ ሲቆም ቀኝ እጅ በግራ ላይ አድርጎ አንገት ስር ማውጣት – ስጁድ ሲወረድና ከስጁድ ቀና ሲል ሁለት እጆችን ማንሳት – በግንባር ፣ በሁለት መዳፎችና ፣ በሁለት ጉልበቶችና በሁለት አውራ ጣቶች ( በሰባት አካላት) ስጁድ አለመውረድ – ሴቶች ሽቶ ተቀብተው መስጂድ መምጣት – ሴቶች በሚሰግዱበት ጊዜ እግራቸውን አለመሸፈነረ እነዚህ ከብዙ ስህተቶች ጥቂቶቹ ናኛቸው ራሴንና አማኞችን ለማስታወስ እነዚህን ጠቀስኩ ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን ። https://t.me/bahruteka
Hammasini ko'rsatish...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.