uz
Feedback
Yoni Motivation

Yoni Motivation

Kanalga Telegram’da o‘tish

ከማንም አትጠብቅ

Ko'proq ko'rsatish
698
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
«በሕይወት የደስታ ባህር ከመዋኘት ይልቅ በመራራዋ ኩሬ ትንቦጫረቃለህ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ታዲያ የሕይወት ባቡር ጥሎህ ይጓዛል፡፡ ሕይወት ማደርያዋ ዕውቀትን ከሚያደምጡ ሰዎች ዘንድ ነው፡፡ በሕይወት መጨነቃችሁን አቁሙና ዘና በሉ። በውቅያኖስ ዳር ተቀምጠህ የፀሐይ ነፀብራቅ እያየህ ከምትደነቅ ከፀሐይዋ ነፀብራቅ ጋር አብረህ ወደ ውቅያኖሱ ተቀላቀል፡፡» Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት ምክኒያቱም እውነትና እየተፈፀመ ያለ ነገር ስለሆነ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል * በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም *በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ *ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡ *የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ .*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ * በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ። የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!! ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ? ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ አሁን ያለንበት 2014 ዓም + 5500 ዘመን=7514 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ። 8000 – 7514= 486 ዓም ይቀራል። ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ። እና የዘንዶው ሲቆጠር 486 – 400 =86 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ 666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 : 15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡ ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡ ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡ እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡ ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!! ቅዱስ ለ #15 ሰው እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ህይወት ልክ እንደ ሳንቲም ሁለት ገፅታ አላት ። ስኬትና ውድቀት ፣ ማግኘትና ማጣት ፣ ከፍታና ዝቅታ ፣ መራራና ጣፋጭ ፣ ሀዘንና ደስታ ያለባት ምርጥ አስተማሪ ናት ። ህይወት መጀመሪያ ትፈትንሃለች ከዚያ ታስተምርሃለች ። ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

አንዱ ሚዛን ተመዝኖ 35 ኪሎ ሲሆን መዛኙ ምን ቢለው ጥሩ ነው የእድራችሁ ድክመት ነው እንጂ ሞተሃል እኮ😭😭😭😭

ሁሉም ሰው የሚዋሸው ውሸት👆👆👆
ሁሉም ሰው የሚዋሸው ውሸት👆👆👆

#_አንተስ_ምን_አደረክ? #ሲያወሩ አወራህ ? #ሲተቹ ተቸህ ? #ሲያንቋሽሹ አንቋሸሽክ ? #ሲዘልፉ ዘለፍክ ? #ሲሰድቡ ሰደብክ ? ወይስ የተለየ ነገር አደረክ ፤ #ድርሻህን ተወጣህ ፤ ከቃላት ጋጋት በላይ #ሃላፊነትህን ፈፀምክ ? አዎ! ጀግናዬ..! አንተስ ምን አደረክ ? በተቀደደልህ ቦይ #መፍሰስ ጀመርክ ወይስ የእራስህን ቦይ #ቀደድክ ?ብዙዎች ያደረጉትን ደገምክ ወይስ #አዲስ ተግባር ፈፀምክ ? በሌሎች አይን መመልከትን መረጥክ ወይስ የእራስህን #እይታ ማሳደግ ጀመርክ ? አዎ! #ፖለቲካ ሲወራ አንተ አለህ ፤ #እስፖርት ሲተነተን ዋናው አንተ ነህ ፤ #ኢኮኖሚው ሰነገር ቀዳሚው አንተ ነህ ፤ የሚሰራው ሲብጠለጠል አሁንም አንተ አለህ ። አዎ! #ከማውራት ፣ #ከመተቸት ፣ #ከመስደብ ውጪ አንተስ ምን አደረክ ? ማንም ተራ ሰው የሚያደርገው ነገር ቢኖር የሚሰራው ላይ #አስተያየት መስጠት ፣ የሚለፋውንም #መተቸት ነው ። ማንም የሚያደርገውን እያደረክ ደግሞ ማንም የማያገኘውን እንደማትጠብቅ ግልፅ ነው ። ስለሁሉ #ማወቅ አይቻልም ፤ ማውራት ግን ይቻላል ። ስለማንኛውም ነገር እንደ አዋቂ ቁጭ ብሎ #የሚተነትን ሞልቷል ። ትንተናው ተክኖት ተግባሩ ላይ ግን የለበትም ። ማውራት እንደቀለለው ተግባሩ ቢቀል የሰው ልጅ አንድ አይነት ተመሳሳይ ኑሮ ይኖር ነበር ። ነገር ግን እርሱ ሊሆን አይችልም ። አዎ! አብዛኛው #ቢሳሳት ስህተቱ ትክክል ሊሆን አይችልም ። ማንም አላዋቂ የተናገረው ሁሉ ተፈፃሚ አይሆንም ። ጊዜ ሲተርፋቸው #ከሚዘባርቁት ገለል በል ፤ ከማውራት በላይ በአንደኛው ዘርፍ ላይ እርምጃ ውሰድ ፤ #የድርሻህን ተወጣ ። ሰነፎች የሚያደርጉትን እያደረክ አንሰህ ፣ ወድቀህ አትገኝ ። #ከመንጋው ተላቀቅ ፤ የሚጠበቅብህን ድርሻ ተወጣ ፤ አንተን #የሚወክልህን ፣ #የሚገልፅህን ብቻ በሚገባ አድርግ ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ባዶ በርሜል! ___ “ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮኋል፡፡ በዛው ልክ በውሃ የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም። ሲንከባለልም በእርጋታ ነው። የሰው ልጅም እንደዛ ነው። ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ የሚችለው ነገር የለም፡፡ በዕውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮኽን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡ ራሳችንን በዕውቀት እንገንባ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

በሀብታም ወንጀለኛና በተማረ ድሃ ተከበን እንዴት ነው ለመጪው ትውልድ የስኬት ቁልፍ ትምህርት ነው ብለን ምናሳምነው ?
በሀብታም ወንጀለኛና በተማረ ድሃ ተከበን እንዴት ነው ለመጪው ትውልድ የስኬት ቁልፍ ትምህርት ነው ብለን ምናሳምነው ?

መነሻው ዜሮ ነው! 💪💯 የየትኛውም ልዕልና መነሻው አንድ ወይም ሁለት ሳይሆን ዜሮ ነው ። ሁሉም ሰው መነሻው ዜሮ ነው ፤ ምንም ነው ። ብዙ ነገር ከማጣት እልፍ ነገር ወደማግኘት ፤ ተስፋን ከማጣት ትልቁን ተስፋ ወደመሰነቅ ፣ ህልም ካለመኖር የትልቅ ህልም ባለቤት ወደመሆን ፣ ራዕይን ካላማወቅ ግዙፍ ሁሉን አቀፍ ራዕይ ወደማስቀመጥ መሸጋገር ። ቀላል ሊመስል ይችላል ፤ ነገር ግን ክብደቱም ሆነ ቅለቱን ባለቤቱ ያውቀዋል ። ልዩነቱ ማጣትና ማግኘት መሃከል እንዳለው ልዩነት ነው ። ከባዶ መነሳት ከፈራክ አንድ ጋር አትደርስም ፤ ሁለትን አታገኝም ወደ ቀጣዩ ከፍታም መድረስ አትችልም ። ደግነቱ ከዜሮ የምትጀምረው ስራው ወይም ትግሉን እንጂ ወስጥህ ያለውን ሃሳብና ተሰጥኦ አይደለም ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! መነሻው ዜሮ ነው! ከባዶ መነሳት ካስጠላህ ፣ እድገቱንም ሆነ ለውጡን አትፈልገውም ማለት ነው ። ትናንት ምንም ያልነበረው ዛሬ ግን ብዙ ያፈራ አያሌ ሰው አለ ። ምናልባት በአንተነትህ የተሰጠህ ስጦታ ከዜሮ ጀማሪነት ነፃ ሊያወጣህ ይችላል ። ነገር ግን በጥረትህና በልፋትህ የምታገኘው ውጤት ፣ የምታተርፈው አዲስ ግኚት ከምንም ወይም ከዜሮ ወደ አንድ ከአንድም ወደ ሁሉት እያለ በሂደት የሚያድግና የሚጨምር ነው ። 💪💯 አዎ! ዜሮን አትፍራ ፣ በማጣትህ አትሳቀቅ ፣ አትሸማቀቅ ። ማጣትን በማግኘት ፣ ዜሮንም በእልፍ ቁጥሮች የመቀየር አቅም አለህ ። ማመን በሚገባህ እመን ፤ ማድረግ የሚገባህን አድርግ ፤ መውጣት ያለብህን አቀበት ውጣ ፤ መውረድ ያለብህን ቁልቁለት ውረድ ። አጋዠህን ምረጥ ፤ ደጋፊህን አዘጋጅ ። ከምንም ተነስተህ ምን ማድረግ እንደምትችል ፣ የት መድረስ እንደምትችል ፣ ምን ማግኘት ፣ ማስተካከል ፣ መቀየር እንደምትችል ለእራስህም ሆነ ለሚያይህ ሁሉ አሳይ ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

መነሻህ የት ነበር ? ወዶሃልና አዳነህ ፤ አስቦሃልና አሳለፈህ ፤ አዝኖልሃልና አበረታህ ፤ ተረድቶሃልና አሳረፈህ ፤ አውቆሃልና ሰጠህ ፤ እንዳንተ ፍራቻ ፣ እንዳንተ ስጋት ያጣሀው ፣ የደረሰብህ ነገር የለም ። የሰሪው መንፈስ ውስጥህ አለና የፈራሀውን አሳልፎሃል ፤ ከሰጋሀው አሻግሮሃል ፤ በለመለመው መስክ አሰማርቶሃል ፤ ከምቹው ስፍራ አድርሶሃል ። ሃሳብህን በእራሱ መንገድ ፣ በፈቀደው ጎዳና ፈፅሞልሃል ፤ እየፀመልህም ይገኛል ። ትናንት እንደዛሬ አልነበረም ፤ ዛሬም እንደትናንት አይደለም። የፈተነህ ዛሬ የለም ፤ ያደከመህ ፣ ያታገለህ ፣ የተገዳደረህ ዛሬ ተፋቶሃል ፣ ትቶሃል ። ነገር ግን ትቶኛል ፤ አልፌዋለሁ ብለህ እንዳትረሳው ። የዛሬን ብቻ ሳይሆን የትናንት ትዝታዎችህንም አስታውስ ። አዎ! ጀግናዬ..! መነሻህ የት ነበር ? ኬት እዚ መጣህ ? እንዴት እዚህ ደረስክ ? ማን ለዚህ አበቃህ ፣ ማን ደገፈህ ፣ ማንስ አገዘህ ? ምላሽ ላለህ ጥያቄ አትሸበር ። ያለፈው ታሪክህ ላያምር ይችላል ፤ የምትናገረውና በሰው ፊት የማያኮራህ ይሆናል በምትኩ የምታዝንበት ፣ የሚያሳቅቅህ ፣ የሚያሸማቅቅህ ታሪክም ይሆናል ። ነገር ግን ማለፍ ስለነበረበት አለፏል ፤ መተው ስለነበረበት ተትቷል ፤ መቅረት ስለነበረበት ቀርቷል ። የሁሉንም ነገር አላፊነት አይተህበታል ። በሁለት እግርህ መቆም ተስኖህ የነበረ ጊዜ ይኖር ይሆናል ፣ ዛሬ ግን ከእራስህ አልፈህ ለሌሎች ምርጉዝና ድጋፍ ለመሆን በቅተሃል ። አዎ! ጀርባህን አትዘንጋ ፤ ኋላህን አትርሳ ። ከማንነትህ ጀርባ ብዙ ሰዎች ነበሩ ፤ ብዙዎች ሰርተውሃል ፤ ከኋላህ ደጉ ፈጣሪህ አብሮህ ነበር ፤ ሰሪህ ሲያግዝህ ነበር ። ዛሬም ሰዎች ከጎንህ አሉ ፤ በውስጥህ የአምላክ መንፈስ አለ ። ሁሌም ብቻህን አይደለህም ፤ ሁሉም ማለፉን አስታውስ ፤ ሁሉም መረሳቱን ፣ መዘንጋቱን ተረዳ ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

መስጠትና መበተን "አንድ ለማኝ ከመንገድ ዳር እየለመነ ሳለ ከአጠገቡ መኪና ይመለከትና ሄዶ ያስቆመዋል ። ይኽ ለማኝ ለሦስት ቀናት ምግብ አልበላም ነበር እና ባለመኪናው ገንዘብ እንዲሠጠው ይጠይቃል ። ባለመኪናው ሠውዬ የሎተሪ እጣ አሸንፎ ሀብታም ከሆነ ጥቂት ቀናቶችን አስቆጥሯል። ወደ ለማኙ ሲመለከት የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም። የለማኙ ልብስ ምንም እንኳን ያረጀ ቢሆንም ሰውዬው ከደህና ቤተሠብ የመጣ እንደሆነ ደም ግባቱ ያስታውቅ ነበር ፤ ከዚያም በላይ በሚገባ የተማረ ሰው እንደሆነ ንግግሩ ያስታውቃል። " " ባለመኪናው በጊዜው በገንዘብ የተንበሸበሸ ሰው በመሆኑ ባለ መቶ ኖት ሩፒ (ገንዘብ) በማውጣት በለማኙ እጅ ላይ ያስቀምጣል። ይኽን ጊዜ ለመኙ ሠው ባለመኪናው የሠጠውን ገንዘብ ተመልክቶ መሳቅ ጀመረ።" "በሁኔታው ግራ የተጋባው ባለመኪና፦ "ለምን ትስቅብኛለህ ?" ሲል ለማኙን ይጠይቃል ። " "ይኽን ጊዜ ለማኙ ፦ " የምስቀውማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዛሬ እኔ የቆምኩበት ቦታ ቆመህ እንደማይህ ስለታወቀኝ ነው ። እኔም ለማኝ የሆነኩት በዚህ መንገድ ነው ። በአንድ ወቅት የራሴ መኪና ፣ ንብረትና በብዙ ሺ ዎች የሚቆጠር ገንዘብ ነበረኝ ። ነገር ግን እንዳሻኝ ስበትን ኖሬ የምታየኝ ቦታ ለመቆም በቃሁ ። ወዳጄ! መበተንም ሆነ መሰሰት አጥያት ነውና መስጠትን እንጂ መበተንን አትማር ፣አታስተምር " ብሎት ሄደ ። " Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ህይወት አንዴ ነው በሰዎች ህይወት ውስጥ ገብተህ ብዙ ማስተካከያ መስጠት ይቀናህ ይሆናል ግን ሁሌም በማይመለከትህ ነገር ውስጥ የምታውለው ጊዜ ተመልሶ ላይመጣ እየባከነ መሆኑን አትዘንጋ!! ራስህ ላይ አትኩር ኮማች አትሁን አይንህን ጨፊነ ምትገልጥበት ያክል የተረፋ ጊዜ የለህም ንቃ Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ትላት የሞቱት ሰዎች ለዛሬ ጠዎት እቅድ ነበራቸው ዛሬ ጠዋት የሞቱት ሰዎች ደግሞ ለዛሬ ምሽት እቅድ ነበራቸው ህይወትህን እንደቀላል አትውሰድ በሰከንዶች ውስጥ ሁሉም ነገር ሊቀየር ይችላል ስለዚህ ምንጊዜም ይቅር በል በንፁህ ልብህም ለሌሎች ፍቅርን ስጥ ምክንያቱም ይሄንን ዕድል ድጋሚ ላታገኘው ትችላለህ! Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

የማይሆን ላይሆን የሚሆን ላይቀር ምንድ ነው መጨነቅ እዩላቹ እስከዛሬ የማይሆነው ሲሆን አይተናል የሚሆነውም ሲቀር ተመልክተናልና። አንድ ገበሬ ዛሬ ላይ በቆሎ ቢዘራ እና ማሳው ላይ ቁጭ ብሎ ምን እንደሚበቅል አላውቅም ብርቱካን ሊሆን ይችላል ዝንጅብል ሊሆን ይችላል ወይም ፌጦ ብቻ እግዚአብሔር የፈቀደው ይብቀል ቢል ያገበሬ ሞኝ ነው። ምክንያቱም የሚበቅለው እንዲበቅል የተመኘነው እና የፈለግነው ሳይሆን ዛሬ ላይ የዘራ ነው ገነርነው ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ምላጭ ስል ነው ዛፍ አይቆርጥም እንጂ መጥረቢያ ጠንካራ ነው ፀጉር ግን አይቆርጥም ማንነቱን ጠንቅቆ ያላወቀ ሰው ሊናቅ ይችላል ሊገፋ ይችላል ማንንም አትናቅ በተለይ ራስህን ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ሰውነታችን ምንም ነገር መቋቋም ይችላል ትልቁ ጥበብ አእምሮን ማሳመን ነው ። እግርህ በራሱ ፍላጎት ተነስቶ ጎዳና ላይ ሲራመድ አታገኘውም አንተ ማዘዝ አለብህ አንተ መፍቀድ አለብህ ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ስፖርት መስራቴን እወደዋለሁ በል! አእምሮህ ያልከውን ስለሚያምን ከደቂቃዎች በኋላ እጅህ የምትሸከመውን ክብደት ጨብጧል ወይ እግርህ እየሮጠ ነው ወይ ባለህበት ዱብ ዱብ እያልክ ነው ። Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

photo content

#አንተ_አንተ_ነህ #እገሌም_እገሌ_ነው!! " የሆነን ሰው መሆን እየተመኘህ በሄድክ ቁጥር የዛ ሰው ኮፒ ስብእና እንጂ የራስህ የሆነ ማንነትና እውቀት እንዲሁም ተጽዕኖ አይኖርህም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ልትጥለው የሚገባው ነገር እንደ እገሌ መሆን እፈልጋለሁ ወይም እንደ እሱ እሆናለሁ የሚለውን አባዜ ነው ። አንተ ማንንም ለመምሰልም ሆነ ማንንም ለመሆን አልተፈጠርክም ። አንተ አንተ ነህ እገሌም እገሌ ነው ። " Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

#አንዳንድ_ሀሳቦች ✍... አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡ ☮ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡ በነገሮች አትረበሽ፡ ጭንቀትህን አስጨንቀው ፡ "ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡ " ☮አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡ ☯"መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው:" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው የምን ተስፋ መቁረጥ Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ህይወት እስኪያልፍ እሚያልፍ አይመስልም…ሁሉም እስኪሄድ እሚሄድ አይመስልም…ሲመሽ እሚነጋ አይመስልም…ስንጠግብ እሚርበን አይመስለንም… ግን ወዳጄ…ሁሉም ይቀያየረል… ለምን ሆነ አትበል… ከሆነው ጋር መኖርን ግን ተማር… ደስታ ምርጫ ነው… ደስታ እሚስጥህን ነገር ስትመርጥም ተጠንቀቅ…አንዳንዶች ጊዚያዊ ናቸው…እሚወቅስህን አትጥላ… እንዴትም ብትኖር ከወቀሳ አትድንም እና … በህይወትህ ሁሌም ቀጥሎ ያሉት ነገሮች ይከሰታሉ… አልረሳህም ያለህ ሊረሳህ ይችላል… አልተውህም ያለህ ይተውሀል… የመረከው ይረግምሀል… ያሳከው ያስለቅስሀል… ወዳጄ ያልከው ጠላትህን ይሆናል… እናም ተመስገን ብለህ ማለፍን ተማር… ከሚመስሉህ ጋር ጊዜህን አሳልፍ… ከሚቀያየሩ ስሜቶች ጋር አትቀያየር… የተቀረውን ለፈጣሪ ተወው። መልካም ቀን ❤️❤️ Raise Motivate https://youtube.com/channel/UCejbNLF7Cy5AdPRBf6BCBEw ለአነቃቂ ንግግሮች የዩቱብ ቻናላችንን ግብና Subscribe አድርጉ https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600