cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 የስነ ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን አስተያየት ና ጥቆማ መስጫ ቻናል

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
226
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+17 kunlar
-430 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ዘርፍ ተኮር የሙስና ተጋላጭነት ጥናት በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል፤ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም አ/አ/ስ/ፀ/ሙ/ኮ አዲስ አበባ ዘርፍ ተኮር የሙስና ተጋላጭነት ጥናት በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚቻል የኮሚሽኑ የ9 ወር አፈፃፀም ያሳያል። የአዲስ አበባ ከተማ ሥነ ምግባርና-ፀረ ሙስና ኮሚሽን አንዱ ተልዕኮው የመንግስት ተቋማት የውስጥ አሰራራቸው ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍት አለመሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ባለፉት 9 ወራት በከተማ ደረጃ ካሉ ተቋማትና ቢሮዎች ውስጥ የ40 ተቋማት የሙስና ተጋላጭነትና ደረጃቸውን በመለየት ወደ ሥራ ገብቷል። ተቋማት ሙስና የመከላከል ስልታቸው፣ ተጠያቂነትን የማስፈን ስርዓት፣ ግልጸኝነትን የማስፈን ስርዓት፣ አዋጅንና ድንብን ተከትሎ የመተግበርና አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ የማሻሻል ስልጣን ለተሰጠው አካላ አቅርቦ እንዲሻሻል የመስራት ሁኔታ፣ የንብረት እስተዳደር ስርዓት፣ የግዢ አስተዳደር ስርዓት፣ የሰው ሀብት አስተዳደር ስርዓት እና የኦዲትና ቁጥጥር ስርዓት ምን እንደሚመስል በጥናት ተለይቷል። የሙስና ተጋላጭነት የአሠራር ሥርዓት ጥናት ውጤታማ እንዲሆን በጽሁፍ መጠይቅ፣ በቃልመጠይቅ፣ በሰነድ ምርመራ እና በተቋም ምልከታ አሰባሳብ ዘዴ በመጠቀም የተቋማቱ የሙስና ተጋላጭነት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጥናት ተለይቷል:: የተቋማትን የሙስና ተጋላጭነት መለየት ብቻ ሣይሆን በጥናቱ የተለዩ ችግሮችን አቅዶ መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም ተቋማት Metigation Plan በመስጠት ድጋፍና ግምገማ እየተደረገ ይገኛል። በአመቱ መጨረሻ ላይ በተሰጠው ግብረመልስ መሰረት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ተቋማት እውቅና መስጠት እና ያልፈፀሙ ተቋማት ደግም በሁሉም የተጠያቂነት ሥርዓት እንዲጠየቁ ይደረጋል። “ሙስና ስጋት የማይሆንባት አዲስ አበባን እንፈጥራለን!” ለጥቆማ በነፃ የስልክ መስመር 8887 ፤ ፌስቡክ:- Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና https://www.facebook.com/profile.php?id=100090845517191 ቴሌግራም:- Addis Ababa Ethics Media https://t.me/aaethics2015 ኢሜል ፡- [email protected]
Hammasini ko'rsatish...
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና | Addis Ababa

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና, Addis Ababa, Ethiopia. 8,023 likes · 309 talking about this. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 75/2014...

👍 2
በቀን 05/09/2016 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የሙስና ፅንስ ሀሳብና የመከላከያ ስልቶች እንዲሁም ስነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ላይ በተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ  ጥሪ ተደርጎላቸው ለመጡ  የአዳጋ መከላከል ለመንግሥትና ለግል ተቆማት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኳሚሽን ን/ስ/ላ/ቅ/ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን  የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ብርሀኑ አብረሀም በኩል  ከሰዓት ከ3:00 ጀምሮ ለስልጠና በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሙስና ከሳት አደጋ የማይተናነስ የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ ;ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈጥር ለሀገራችን ሠላም አንድነት እንቅፍት የሆነውን ሙስናን መታገል አለብን በማለት በሙስና ዙርያ እና በስነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙርያ   ሠፋ ያለ ገለፃ በማድረግ ከሰልጣኞች የተነሡትን ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት ስልጠና ተሰጥቷል :: ይህ ስልጠና እንድንሠጥ ትብብር ላደረግሉን  ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ን/ስ/ላ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊን እና አሰልጣኙን ከልብ እናመሠግናለን :: የወረዳ 6 የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል!!!
Hammasini ko'rsatish...
በቀን 01/09/2016 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል የሙስና ፅንስ ሀሳብና የመከላከያ ስልቶች ላይ በተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ  ጥሪ ተደርጎላቸው ለመጡ  የስራና ክሎት ጽ/ቤት ባለድርሻ አካሎች እና የወረዳችን አመራሮችና ሠራተኞች ከወረዳው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር በጋራ በመሆን  የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ብርሀኑ አብረሀም በኩል ከሰዓት ከ3:00 ጀምሮ ለስልጠና በተዘጋጀው ሰነድ ላይ  ስልጠና ተሰጥቷል :: ይህ ስልጠና እንድንሠጥ ትብብር ላደረግሉን ም/ስራ አስፈፃሚና የስራና እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸለመ ተረፈ ከልብ እናመሠግናለን :: የወረዳ 6 የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል!!!
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የዐብይን ፃም ወራት ለሃገር ደህንነት እና ለህዝብ ሰላም በፀሎት እና በተማፅኖ አሳልፈን እንሆ ለበዓለ ስቅለቱ ደርሰናል። ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለበዓለ ስቅለት በሰላም አደረሳችሁ! የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 6 የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ክፍል::
Hammasini ko'rsatish...