cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

የኢትዮጵያ ታሪኮች የሚቀርብበትና የሚዳሰስበት ቻናል

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
10 800
Obunachilar
-424 soatlar
+47 kunlar
+6630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
አንጋፋው ጋዜጠኛ መሀመድ አሚን ከ Punjabi የዘር ሀረግ ካላቸው ቤተሰብ በ 1935 ዓ.ም በናይሮቢ ከተማ የተወለደው መሀመድ አሚን፣ ለቤተሰቦቹ ሁለተኛ ልጅ ነው፣ መሀመድ ከልጅነቱ ጀምሮ የፎቶግራፍ ባለሙያ የመሆን ምኞት ነበረው ሲሆን ወደ ሞያው ለመግባት ብዙ ግዜም አልወሰደበትም በ 13 ዓመቱም ይማርበት የነበረው ትምህርት ቤት ለሚያሳትሙት ጋዜጣ ፎቶ ማንሳት ጀመረ ቀስ በቀስም በስራዎቹ እየታወቀ ስለመጣ ለ BBC ፣ ROUTERS ሌሎችም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ፎቶግራፎችን ማንሳቱን ተያያዘው በአለም አቀፍ ደረጃም ስመጥር የፎቶግራፍ ባለሙያ ለመሆን በቅቷል። ➺ መሀመድ ከታላቋ ብሪታኒያ ነፃነቷን ተቀዳጅታ ጆሞ ኬንያታ ወደ ስልጣን ሲመጡ በስፍራው ነበር፣ ያን የማይደበዝዝ ታሪካዊ አጋጣሚ በፎቶ አስቀርቷል። ➺ የሶቪየትና የምስራቅ ጀርመን ወታደሮች ለዛንዚባር ወታደሮች ምስጥራዊ ስልጠና ሲሰጡ በድብቅ በፎቶ አንስቶ ለአለም ይፋ አድርጓል ➺ የዩጋንዳ አራጅ ኢዲያሚን ዳዳ ምስሎች በማስቀረት ለአለም ይፋ በማድረግ የሚያህለው የለም ➺ በ 1960 ዎቹ የፓኪስታን ጦርንና የአፍጋኒስታንን መጃህዲን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፎቶዎች የሱን ያህል ያነሳ አልነበረም። ➺ 1977 ዓ.ም ረሃብ በርካታ በኢትዮጵያውያን ወገኖችን በረሃብ ሲያልቁ የረሀቡን ገፅታ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ በፎቶ በማሳየት "we are the world" እና መሰል እንቅስቃሴዎች መጀመር ምክንያት ከሆኑ ውስጥ አንዱ ነበር። ➺ ግንቦት 27/1983 በጎተራው ፍንዳታ ላይ ፎቶዎች በማንሳት ላይ እያለ በፍንዳታው አንድ እጁን መቆረጡ ይታወቃል። ➺ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን አውሮፕላን ለመጥለፍ ሙከራ በተደረገበት ወቅት አውሮፕላኑ በህንድ ውቅያኖስ በኮሞሮስ ደሴት ላይ በመከስከሱ ህይወቱ አልፏል። #ታሪክን_ወደኋላ
Hammasini ko'rsatish...
👍 14😢 10 3
01:00
Video unavailableShow in Telegram
ግንቦት 27 ቀን 1983 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከዛሬ 33 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ስንቅ እና ትጥቅ እየተባለ የሚጠራው ስፍራ የጎተራው የመሳሪያ ግምጃ ቤት ላይ ከፍተኛ ፍንዳታና ቃጠሎ የደረሰበት ዕለት ነበር። ሙሉውን ቪዲዮ 👇 youtu.be/OsqnCCSl9aw?si=AHJH7YrEhNSHQZ_f
Hammasini ko'rsatish...
21.41 MB
😢 6👍 1
ግንቦት 26 ቀን 1992 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 24 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የፊደል ገበታ አባት አርበኛው ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ያረፉበት ዕለት ነበር። ‹‹ሀ ሁ…እውቀት ይስፋ…ድንቁርና ይጥፋ…ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ…›› ተስፋ ገብረ-ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋሪያ.... ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ፊደል ያላት አገር ናት፡፡ ይህም ከበርካታ የዓለም አገራት ተለይታ እንድትታይ ከሚያደርጓት መገለጫዎቿ መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ፊደል በመላ አገሪቱ ተስፋፍቶ አገራዊ መገለጫነቱ ይዳብርና ብዙዎችም ማንበብና መፃፍ ችለው ከመሃይምነት ያመልጡ ዘንድ የአንድ ኢትዮጵያዊ ጠቢብ ርዕይና ጥረት ያስፈልግ ነበር፡፡ ይህ አርቆ አሳቢ ጠቢብ ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ይባላሉ፡፡ ታኅሣሥ 24 ቀን 1895 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ፣ ቡልጋ ውስጥ አክርሚት በተባለ ስፍራ በመምህር ገብረሥላሴ ቢልልኝ እና ወይዘሮ ሥዕለአብ ወልደሚካኤል ቤት ይችን ዓለም የተቀላቀለው ልጅ ‹‹ተስፋ›› የሚል ስም ተሰጠው፡፡ አራት ዓመት ሲሞላውም ከአባቱ እግር ስር ተቀምጦ ፊደል መቁጠር ጀመረ፡፡ የሕፃኑ ተስፋ ወላጆች አራሽ ገበሬዎችና ከብት አርቢዎች ስለነበሩ፣ ተስፋ እያደገ ሲሄድ ከትምህርቱ ይልቅ ወደ ከብት ጥበቃው እንዲያተኩር ተደረገ፡፡ ተስፋ ከትምህርት ይልቅ ከብት ጥበቃ ላይ እንዲያተኩር መደረጉ ያልተዋጠላቸው የተስፋ አያት መሪጌታ ቢልልኝ ተስፋን እንዲያስተምሩላቸው መምህር ገብረአብ ለተባሉ የቤተ ክህነት ሊቅ ወስደው ሰጧቸው።..... ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/gaamX3BcS4SVtKEV/?mibextid=oFDknk #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@TariknWedehuala11 tiktok.com/@tariknwedehuala
Hammasini ko'rsatish...
👍 21 6👏 3🎄 1
Photo unavailableShow in Telegram
➺ ሻለቃ መንግስቱ ሃይለማርያም ➺ ብ/ጀነራል ተፈሪ በንቲ ➺ ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ነሐሴ -- 1967 ዓ.ም #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@TariknWedehuala11
Hammasini ko'rsatish...
👍 5 2
03:09
Video unavailableShow in Telegram
ፋሺስት የኢጣልያን ወታደሮች በባቡር ተጉዙው ድሬዳዋ የምድር ባቡር ጣቢያ ሲደርሱ በወቅት የጦሩ አዛዥ የነበረው ጄኔራል ናቫራ ለወታደሮቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ አቀባበል ሲያደረግ ፤ #በዛሬዋ_ዕለት ግንቦት 26 ቀን 1928 ዓ.ም ድሬዳዋ #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@TariknWedehuala11
Hammasini ko'rsatish...
72.48 MB
👍 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 7 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አንጋፋው የእግር ኳስ ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ (ፔሌ) በድንገት ከመታጠቢያ ክፍሉ በመውደቁ ምክንያት በተወለደ በ 47 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ዕለት ነበር። www.facebook.com/share/p/8sooaPkCKTtF64Pg/?mibextid=oFDknk ⚽ አሴ ልስልሱ አንጀት አርሱ ⚽ ክብርና ዘላለማዊ እረፍት ለኳሱ ሊቅ አሴ 🙏 #ታሪክን_ወደኋላ
Hammasini ko'rsatish...
🙏 7😭 3
Photo unavailableShow in Telegram
ግንቦት 26 ቀን 1767 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 249 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ መንበር በተወለዱ በ 67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት ዕለት ነበር። የቀብራቸው ስርዓትም በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተክርስቲያን ተከናውኗል። እየተጠናቀቀ ባለው ግንቦት ወር አያሌ ሊታወሱ የሚገባቸው ታሪኮች ተከስተዋል፡፡ የተወሰኑትንም በዚህ የሳምንቱ በታሪክ አምዳችን ይዘን በመቅረብ ታሪካቸውን ልናጋራችሁ ሞክረናል፡፡ ለዛሬ ደግሞ ከታሪካዊ ክስተቶች መካከል አንዱ ወደ ሆነውና በ 18ተኛው መቶ ክ/ዘመን ወደ ተፈጸመው ልንመልሳችሁ ወደናል። ⩩ የ 18ኛው ክ/ዘመን ታላቋ ንግስት እቴጌ ምንትዋብ እቴጌ ምንትዋብ በዙፋን ስሟ ብርሃን ሞገስ በ 1700 ዓ.ም ከአባቷ ደጅአዝማች መንበር እና እናቷ ልዕልት እንኮይ በቋራ፣ ጎንደር ነው የተወለደችው፡፡ እናቷ ልዕልት እንኮይ ከዓፄ ሚናስ ዘር እንደምትወለድ ይጠቀሳል። በታሪክ ፀሐፊዎች እንደሚወሳው እቴጌ ምንትዋብ ‹‹ወለተጊዮርጊስ›› በሚለው የክርስትና ሥማቸው እና ‹‹ብርሃን ሞገሳ›› በሚሉት የክብር ስሞቻቸውም ይታወቃሉ፡፡...... ሙሉውን ታሪክ 👇 www.facebook.com/share/p/G3LVsYPRKh8J4y55/?mibextid=oFDknk #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@TariknWedehuala1
Hammasini ko'rsatish...
👍 14 1🕊 1
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ የነበሩት ሪር አድሚራል እስክንድር ደስታ ፤ የኖርዌይ ንጉስ ሃኮን VII ሰባተኛ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ፤ መስከረም - 1950 ዓ.ም ኦስሎ ፤ ኖርዌይ 👇 ተጫማሪ የቀብራቸው ስነስርዓት ፎቶግራፍ በ Comment ላይ ተቀሞጧል #ታሪክን_ወደኋላ
Hammasini ko'rsatish...
👍 14 1👌 1
ግንቦት 25 ቀን 1953 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 63 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በ 20ኛው ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ "ሪክተር" ሚዛን 6.7 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተበት ዕለት ነበር። በአደጋው አብዛኛውን የማጀቴን ከተማ እያፈረሰ ፣ በጎረቤት ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ 45 መኖሪያ ቤቶች ያወደመ ፣ በካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባ አስመራ መንገድና ድልድዮች ላይ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ምክንያት ትልቅ ውድመት ያደረሰ አደጋ ነበር። #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@TariknWedehuala1 tiktok.com/@tariknwedehuala
Hammasini ko'rsatish...
👍 24😱 3 2🙏 2😁 1😢 1
01:41
Video unavailableShow in Telegram
ለብልሃርዚያ በሽታ አምጪ ለሆነው የቀንድ አውጣ ለሰላሳ አመታት ተመራምረው " እንዶድ 44 " የተባለው ማጥፊያ መድኃኒት ያገኙት ታላቅ የሳይንስ ጠበብት ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ ፤ #ታሪክን_ወደኋላ youtube.com/@tariknwedehuala11
Hammasini ko'rsatish...
21.28 MB
26👍 4