cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

🇪🇹አዲስ ዜና ከምንጩ

አዲስ ሀገራቀፍና ዓለማቀፍ ዜናዎችን ከምንጩ እዚህ ያገኛሉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
371
Obunachilar
+124 soatlar
+47 kunlar
+930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#OnlineNationalExam ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች እንደሚከናወን የሀገር አቀፍ ትምህርት፣ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ ገልጿል። አንዳንድ ወላጆች " በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንድናቀርብ ተጠይቀናል " ብለዋል። አገልግሎቱ ግን ይህንን በሚመለከት ለትምህርት ቤቶች ያስተላለፈው መልዕክት እንደሌለ እና ወላጆች መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል። የኦንላይን ፈተናው መንግስት በሚያዘጋጀው አቅርቦት እንደሚከናወን አመልክቷል። ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ የሚጠበቅባቸው አንብቦ እና በቂ ዝግጅት አድርጎ የተመዘገቡበትን መታወቂያ ይዞ መምጣት ብቻ ነው ብሏል። ነገር ግን ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ #እንደማይከለከሉ አገልግሎቱ አሳውቋል። ሁሉም ተማሪዎች በኦንላይ እንዳይፈተኑ የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንቅፋት ሊሆን ስለሚችል ዘንድሮ #በተወሰኑ ተማሪዎች ብቻ እንደሚጀመር ገልጿል። በሌላ በኩል ፥ በወረቀት ለሚሰጠው ፈተና የህትመት ስራው ወደ #መጠናቀቅ መቃረቡን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል። ይህ እንዴት ይታያል ? የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና  " ትምህርት ቤቶች ሆኑ ተማሪዎች #የግል_ኮምፒዩተራቸውን ለፈተና መጠቀም አይከለከሉም " ብሏል። ተማሪዎች የራሳቸውን ኮፒዩተሮች ይዘው ሲገቡ በውስጡ ለፈተና ደህንነት የሚያሰጋ ወይም ፈተናውን እንዲሰሩ የሚያግዛቸው የተለያየ ዶክመት ተደብቆበት እንዳልሆነ የሚረጋገጥበት ምን አይነት መንገድ እንዳለ አልተብራራም። ሌላው ተፈታኞች በፈተና ወቅት በኢንተርኔት ድረ ገጾችን በመጎብኘት ጥያቄ የሚሰሩበት መንገድ እንዳይኖር ስለሚወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ የተብራራ ነገር የለም። መሰልና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ችግር ይዘው እንዳይመጡ ከወዲሁ ማሰብና ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሆነው ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የአቪዬሽን ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች። በመድረኩ ላይ ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዱ ተገልጿል፡፡ ኩባንያው ይህን ውሳኔ ያስታወቀው በአፍሪካ ከግዙፍ አየር መንገዶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 65 አውሮፕላኖቹን በቦይንግ እንደሚተካ ማስታወቁን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
Hammasini ko'rsatish...
የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለመንግሥት እንዲያቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ፡፡ ‹‹የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ›› የተሰኘውና ሪፖርተር የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውንም ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማቱ የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን እንደሚኖርበትና የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን እንዳለባቸው ያስረዳል፡፡ አንድ የሃይማኖት ተቋም በራሱ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ፣ ለዚሁ ሥራ የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ እንዳለበት ደንግጓል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት አስቀምጧል፡፡ ሲያሳውቅም የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስምና አድራሻ፣ የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነትና መጠን፣ እንዲሁም ስጦታው ወይም ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት እንዳለበት ተገልጿል፡፡ ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አባል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሃይማኖት ተቋማቱ ኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ያቅርቡ የሚለው የረቂቁ ክፍል ላይ ተቃውሞ የላቸውም፡፡ ከውጭ የሚላክን ገንዘብ አስመልክቶ በረቂቁ ላይ የተቀመጠው ገንዘቡን ማሳወቅ ከሆነም ችግር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ከፋይናንስ ደኅንነት ወይም ከሌላ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ጋር የሚያገናኝ ከሆነ ጣልቃ መግቢያ በር እንዳይሆን ሥጋት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በሦስት ወራት ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንዳለበትና የኦዲተሩን አቋምና የውሳኔ ሐሳብ መያዝ እንዳለበት በረቂቁ ተመላክቷል፡፡ የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንዳለበትም ተደንግጓል፡፡ የአምልኮ ወይም የመቃብር ቦታ አሰጣጥን በተመለከተም ለሃይማኖት ተቋማቱ የመሬት አቅርቦት በመሬት አጠቃቀምና የሊዝ ሕጎች መሠረት እንደሚወሰን ተገልጿል፡፡ ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ በተጠየቀበት አካባቢ ለሃይማኖት ተቋሙ ለተመሳሳይ ዓላማ የተሰጠ ቦታ አለመኖሩ ወይም ተጨማሪ ቦታ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበት፣ እንዲሁም በተለያዩ ቤተ እምነቶች መካከል የሚኖረው ርቀት ቢያንስ 500 ሜትር መሆን እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ ትምህርትና የሃይማኖት ተግባራትን በሚመለከትም በረቂቁ ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ተቀምጠዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ መደበኛ ትምህርት በሚሰጡ የመንግሥት ወይም የግል ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት ሃይማኖታዊ ይዘት የሌለው መሆን እንደሚኖርበት አንዱ ሲሆን፣ በትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስተማር ወይም በቡድን ማምለክ የተከለከለ ነው የሚለው ሌላኛው ነው፡፡ በተጨማሪም ማንነትን ለመለየት የሚያስችሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደማይገባ ተደንግጓል፡፡ ይህን የረቂቁን ክፍል አስመልክቶ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሃይማኖታዊ ምልክቶችን እንደ ቤተ እምነቱ አስገዳጅ ሕግጋቶች ልዩ ሁኔታዎች እንደሚኖሩ መደንገግ ሲገባው፣ ሙሉ ለሙሉ ከትምህርትና ሥራ ገበታ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን መያዙ አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ ለሰላም ሚኒስቴር በላከው አስተያየት፣ ቅሬታና የመፍትሔ ሐሳብ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል የመንግሥት ኃላፊዎች መንግሥትን ወክለው በሃይማኖት በዓላት አከባበር ላይ መገኘት እንደማይችሉ በረቂቁ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት ቤት፣ በመኖሪያ ቤትና በሕክምና ማዕከላት አካባቢ የሚደረግ አምልኮ በአካባቢ ጥበቃ ሕግ የተቀመጠውን የድምፅ መጠን ያከበረ መሆን እንደሚኖርበት፣ ካልተፈቀደ በስተቀር ማስተማርን ጨምሮ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች መፈጸም እንደማይችል ረቂቁ ይደነግጋል፡፡ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በበኩሉ ይህ የረቂቅ አዋጁ ክፍል በልዩ ሁኔታ በወንጌል አማኞች ላይ ጫና የሚፈጥርና ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የሌለው መሆኑን በመግለጽ፣ ሊስተካከል ይገባል በማለት ለሚኒስቴሩ በላከው ደብዳቤ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
"ሙስሊም መስለው ተመሳስለው ኒቃብ ለብሰው እየገቡ ስለሆነ ላይብረሪ ለመግባት ኒቃብ ማውለቅ አለባችሁ"የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሰፈረ ሰላም ካምፖስ የላይብረሪ ሀላፊ (ግንቦት 14/2016፤አዲስ አበባ) … በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰፈር ሰላም ካምፖስ ላይብረሪ ሀላፊ በሆነቸው አልማዝ ተስፋዬ በዛሬው ዕለት በተፃፈ ደብዳቤ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃባቸውን ካላወለቁ ላይብረሪ እንዳይገቡ መከልከሉ ተገለፀ። … በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ በመልበሳቸው ለመለየት እና ሌሎች የሙስሊም እምነት ተከታይ በመምሰል ወደላይብረሪው እየገቡ ስለሆነ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ ካላወለቁ ላይብረሪ እንዳይገቡ መከልከሉን ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል። … ተማሪዎቹ እንደገለፁት ከሆነ ከዚህ በፊትም በቃል ደረጃ ለመከልከል የላይብረሪው ሀላፊዎች መሞከራቸውን እና ሙስሊም ተማሪዎችን ሆን ብለው ከትምህርት ገበታ ለማፈናቀል የተደረገ ሴራ መሆኑን በማንሳት የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በኢትዮጵያ የውጭ የምግብ አቀነባባሪ ሽሮ ወጥን አዘጋጅቶ ለማቅረብ ፍላጎት በማሳየቱ የሽሮ ወጥ ደረጃ መዘጋጀቱ ተገለጸ የውጭ አገር የምግብ አቀናባሪ ኩባንያ ሽሮ ወጥን በኢትዮጵያ ውስጥ በፋብሪካ ደረጃ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ፍላጎት መኖሩን ተከትሎ የሽሮ ወጥ ደረጃ ማዘጋጀት ማስፈለጉን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ ከሽሮ ወጥ በተጨማሪ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩ የተለያዩ “አገር በቀል ምርቶችን” የምግብ ደኅንነት እና የምርትቱን ምንነት እና ይዘት ለማሳወቅ ደረጃዎች እያወጣ መሆኑንም ቢቢሲ አማርኛ በዘገባው አመልክቷል። ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መሠረት በማድረግ የምግብ ይዘታቸው ላይ ጥናት ተደርጎባቸው ደረጃቸው ወጥቷል የተባሉ ምርቶች ሽሮ፣ በርበሬ፣ በሶ እና ጠጅን ያካትታል ተብሏል። ባለፈው ዓመት ደረጃቸው የወጣላቸው የምግብ ምርቶቹ “ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ” ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን፣ ደረጃቸውም አስገዳጅ አለመሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል። የሽሮ ዱቄት ደረጃ ሦስት ክፍሎችን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ የምግብ ይዘቱን እና እርጥበቱን፣ ሲፈጭ እና ሲታሸግ ያለው ንክኪ እንዲሁም በእሽጉ ላይ ምንነቱን እና የመጠቀሚያ ጊዜውን የሚይዝን መግለጫ ያካተተ እንደሆነም ነው የተነገረው።
Hammasini ko'rsatish...
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል። ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል። (የባለሥልጣኑ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን አሳወቀ። በ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 እስከ 21/2016 መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። የአገልግሎት ክፍያ  500.00 ብር በ ' ቴሌ ብር ' ብቻ የሚፈጸም መሆኑ አስገንዝቧል። #ለመጀመሪያ_ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማቸው በኩል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አሳውቋል።
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በኢራን የሂሊኮፕተር አደጋ የሞቱት እነማን ናችው ? - የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ - የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን - የተብሪዝ መስጂድ ኢማም አያቶላህ አልሃሸሚ - የምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አስተዳዳሪ ማሊክ ራህማቲ - የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ማሄዲ ሙሳቪ - የሄሊኮፕተሩ አብራሪ፣ - የሂሌኮፕተሩ ረዳት አብራሪ - ቦዲጋርድ - የበረራ አስተናጋጅ በትላንቱ የሂሊኮፕተር አደጋ ሞተዋል። የፕሬዜዳንት ራይሲን ሞት ተከትሎ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሞሀመድ ሞክበር በ50 ቀናት ውስጥ በምርጫ አዲስ ፕሬዜዳንት እስኪመረጥ ድረስ የፕሬዜዳንቱን ቦታ ተክተው ይሰራሉ።
Hammasini ko'rsatish...
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን አስተዳደር፣ ከቀጣዩ ዓመት በጀቴ ተበድሬ ደመወዝ ላልተከፈላቸው ሠራተኞች ለመክፈል እንቅስቃሴ እያደረግኩ ነው ማለቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። የዞኑ ሠራተኞች ለሦስት ወራት ያልተከፈላቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጭምር ሲጠይቁ እንደነበር አይዘነጋም። ዞኑ የበጀት እጥረት ያጋጠመው፣ በርካታ አዳዲስ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በመፈጠራቸውና የሠራተኞችና የመንግሥት ተሾሚዎች ቁጥር በመጨመሩ እንዲኹም ለዓመታት ሲንከባለል የቆየ የአፈር ማዳበሪያ እዳ በመኖሩ እንደኾነ ተገልጧል።
Hammasini ko'rsatish...
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬል፣ የዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዓቃቤ ሕግ በእስራኤል እና ሐማስ መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው መወሰኑን እንደተቀበሉት ገልጸዋል። ቦሬል፣ ፍርድ ቤቱ ወደፊት የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች ተፈጻሚ ማድረግ የፍርድ ቤቱ አባል አገራት ግዴታ መኾኑን በ"ኤክስ" ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አውስተዋል። የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት፣ የፍርድ ቤቱ መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዎች ናቸው።
Hammasini ko'rsatish...