cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

የነቢ ወዳጆች💖

❖ የቻናሉ አላማ ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
192
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

#አቂዳ #ክፍል_ስድስት #የኢማሙ_መልስ ከዚያ አል አሽአሪይ በእምነት ጉዳዱድ ላይ ስለ አቂዳ መነጋገር አስፈላጊነት ሀሳባቸውን ቀጥለው አቅርበዋል። ምላሾቹን የሰደሯቸው በሶስት አቅጣጫ ነበር። በመጀመሪያው አል አሽአሪይ ያደረጉት ምክንያት አያስፈልግም በሚሉት ላይ ጠረጴዛውን ማዞር ነበር። ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም)በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመጋገሩትን መኮነን/መወገዝ አለባቸው አላሉም። ስለዚህ ሀይማኖታዊ ጉዳዩችን በምክንያታዊነት መነፀር የሚያዬትን የሚኮንኑ ሰዎች ራሳቸው አዲስ ፈጠራ እየፈፀሙ ነው የረሱልን(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ተግባር መከተል አለብን የሚሉ ሰዎች ረሱል (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ያልተገበሩትን መስራት የራስን እጂ እንደመብላት ነው። ሁለተኛው ነብዩ (ሲለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ አካል ተገኝነት ቅስቃሴ እርጋታ ወ.ዘ.ተ ስለማያውቋቸው በመርሱ ላይ በዝርዝር አላወሩም በሚለው ክስ ላይ የነዚህ ጥያቄዎች መሰረታዊ መርህ (ኡሱል) በቅዱስ ቁርአንና በሱና በጥቅሉ ተቀምጧል ብለው መልሰዋል። ከዚያ አል አሽአሪይ መከራከሪያቸውን ለማስረገጥ ከቅዱስ ቁርአንና ከነብዩ ሀዲሶች ማስረጃ አቅርበዋል። በመሆኑም በሀረካህ/ሱኩን/ተውሂድ ወዘተ የቆሙባቸው መርሆዎች በቅዱስ ቁርአንና በሱና ውሰጥ በሀቅነት እንደቀረቡ አሳይተዋል። ሶስተኛ ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እነዚህ ጥያቄዎች በዝርዝር ያውቋቸው ነበር ነገር ግን ጥያቄዎቹ በሳቸው ዘመን አልተነሱም። ስለዚህ እርሳቸው ባላወሩባቸው ነገሮች ላይ ዝምታን እንመርጣለን። በሚለው ላይ የነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደረቦች (ረድየሏሁ አንሁ) ነብዩ ምንም አቅጣጫ ባላሳዩባቸው በርካታ ሀይማኖታዊ ጉዳዩች ላይ ተከራክረው ነበር። በዚህም ምክንያት የተለያዩ አቋሞችን ይዘዋል። ኢማሙ አሽአሪይ በነገረ መለኮት ውይይት ውስጥ የመለኮታዊ ወህይ አስፈላጊነት በዲያሌቲካዊ ዘዴ አስረድተዋል። የኢማሙ ማትሩዲ ህይወትና ስራ #ይቀጥላል..... . .. . . አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የፈጠረው ጌታ አጥብቆ ቢወደው በሰነድ በደሊል አጥብቆ ዘየነው #አቂዳ #ክፍል_አምስት #የአሽአሪይ_አቂዳ_ስነዘዴ አሽአሪይ በአራተኛውና አምስተኛው /አስራ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ የዳበረ ሀይማኖታዊ አስተምሮ ነው። ይህ የአስተሳሰብ ቅስቃሴ "እስልምናን እስላማዊ ካልሆኑ አላባዊያን (አስተሳሰቦች) የማጥራት አላማ ያለው ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ንቃተ ህሊናን ከእስላሚዊ አስተሳሰብ ጋ ለማዋሀድ ይጥራል። ፍፁም ምክንያታዊያኑን ሙእተዚላዎች ነገረ መለኮት (ኢልም አል-ከላም) እና ፅንፈኛ ትውፊታውያንን በመቃወም ትክክለኛውን እስላማዊ ነገረ መለኮት (ከላም) መሰረት ጥሏል።ከሁለቱም ስብስቦች የሚወረወሩባቸው ትቺቶች መመለስ ነበረባቸውና ኢማሙ አሽአሪይ በአንድ ወገን ያሉት ሙእተዚላዎቹ ከወህይ ይልቅ ምክንያታዊነትን የሚመርጡና ለትክክለኛነት እና እውነት ምክንያትን ብቻ እንደ መለኪያ የሚያስቀምጡ ሲሆኑ በዚያ ሂደት ከትክክለኛው ጎዳና አፈንግጠዋል። በሌላው ጫፍ ያሉት እንደ ዛሂሪያ ሙጀሲሞች (ለአሏህ የፍጡር ባህሪ የሚያላብሱ) ሙሀዲሶች (የሀዲስ ሰዎች) እና የህግ ሰዎች ሲሰለፉ ሁሉም ሀይማኖታዊ ቀኖናዎችን ለማብራራት ወይም ከእንግዳ አስተሳሰብ ለመከላከል ምክንያትን ወይም ከላምን መጠቀም የለብንም ከማለታቸው በላይ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ፈጠራ ናቸው ብለው ኮንነዋል። አል አሽዓሪይ ኢስቲህሳን አል ኸውድ የሚለውን መፅሀፋቸውን በዋነኝነት የሇላኞቹን ፅንፈኛ ተቀዋሚዎች ለመሀየስ ፅፈውታል።በሀይማኖት ጉዳዬች ላይ ምክንያታዊነትን መጠቀም የለብንም የሚሉትን አሳማኝ ትችት ተችተዋቸዋል። በዚሁ ስራቸው የተወሰኑ ሰዎች (ዛሂርያዎች እና ሌሎቹ) ድንቁርናቸውን አደልበዋል። ውይይትና ምክንያታዊ ሀሳብ የማይቺሏቸው ሸክም ሆነውባቸዋል። ስለዚህ ወደ ጭፍን እምነትና ቅይድ ተከታይነት (ተቅሊድ) ተዘንብለዋል። ሀይማኖታዊ መርሆችን በምክንያታዊነት ለመተንተን የሚጥሩትን አዲስ ነገር በሚል ይከሷቸዋል። የትውፊታውያኑን ሌላም መከራከሪያ አክለዋል። እነዚህ የአቂዳ ጥያቄዎች ነብዩ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሶሀቦች (ረድየሏሁ አንሁ) መኖራቸውን እያወቁ ዝም ብለዋል ወይም አያውቋቸውም ነበር መኖራቸውን አውቀው በነርሱ ላይ ካላወሩባቸው ዝምታቸውን እንከተላለን ካላወቁም አለማወቃቸውን እንከተላለን በዚህም በዚያ ተባለ በነዚህ ጉዳዩች ላይ መነጋገር ፈጠራ ነወደ ሲሉ ይከራከራሉ ትውፊታውያኑ። በእምነት ጉዳይ ላይ ከላም አል ኢልም መጠቀም ትክክል አይደለም የሚሉት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በጥቅሉ ይህን ይመስላል። ለተከራካሪዎች ኢማሙ ምን አይነት መልስና በምን መንገድ እንደመለሱላቸው በቀጣይ ክፍል ....... #ይቀጥላል..... . . . . አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን የነቢ ወዳጆች💖 ❖ የቻናሉ አላማ ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል https://t.me/mehabetuneby ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
የነቢ ወዳጆች💖

❖ የቻናሉ አላማ ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል

#የሚገርም_ቂሷ_ጀባ_ጊዚያቺንን_በማይረባ_ነገር_እንዳናሳልፍ_ትምርት_ሚሰጠን ነው😢 👳‍♂ኢማም አቡ - ሐኒፋ እና ህፃኑ ልጅ 😭 ---❀-❀--- በእለተ አንድ ቀን አቡ - ሐኒፋ (አላህ ይዘንላቸው) እና ከባልደረቦቻቸው ጋር በአንድ መስጂድ በኩል ሲያልፉ አንድ ሕፃን ልጅ መስጂድ ውስጥ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ አላህን ሲለምን (ዱዓ) ሲያደርግ ተመልክተው ልጁን ለምን እንደሚያለቅስ ይጠይቁታል፡፡ ልጁም:- ‹‹ኢማም ሆይ! እባክዎ ይተዉኝ፡፡›› አላቸው፡፡ እሳቸውም እያግባቡ እንዲነግራቸው የሙጥኝ አሉ፡፡ ልጁም:- ‹‹ያቺ መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የሆነችውን እሳት፤ ለካሐዲዎች ተደግሳለች፡፡›› (አል-በቀራህ፡ 24) የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አንበብዋልን?›› አላቸው፡፡ እሳቸውም:- ‹‹በትከክል አንብቢያለሁ፡፡ ነገር ግን ልጄ ሆይ! አንተ ግን ገና ጨቅላ ነህና ይህ አንቀፅ ባንተ ላይ ተግባራዊ አይሆንም፡፡›› አሉት፡፡ ልጁም:- ‹‹ኢማም ሆይ! እሳት ለማቀጣጠል ስንፈልግ ከትልቅ እንጨት ይልቅ ትንሽ እንጨት አይደለምን የምንመርጠው?›› አላቸው፡ እሳቸውም:- ‹‹እንዴታ!›› አሉት፡፡ ልጁም:- ‹‹ታዲያ ይህ አንቀፅ እንዴት እኔን አይመልከትም!?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜ ኢማም አቡ-ሐኒፋ ወደባልደረቦቻቸው ዞረው :- ‹‹በአላህ እምላለሁ! ይህ ጨቅላ ከእኛ ይበልጥ አላህን ይፈራል፡፡›› አሉ፡፡ እኛ የትና የት ነን ከዚህ ልጅ አንጻር
Hammasini ko'rsatish...
✅እጠቀማለሁ ያለ ነገ በጀነት✅ 💚አቂዳን ይጠብቅ ከሁሉም በፊት💚 ❌ችግር እንዳይዘው መጨናነቅ❌ #ዐቂዳ #ክፍል_አራት የአስተሳሰቡ ለውጥ በየትኛውም ምክንያት ይምጣ ኢማሙ አሽአሪ አስተሳሰባቸውን ሲለውጡ ግን በከፍተኛ ርሀብ ውስጥ ሆነው ነበር። ከለውጡ በሇላ በርካታ መፅሀፍትን የፃፋ ሲሆን ኢብን ፉራቅ እንደሚለው እስከ 300 ይደርሳሉ። ኢብን አሳኪር ደመሽቂ ለ93ቱ ርዕስ የሰጧቸው ቢሆንም ዘመን የተሻገሩት ግን እጂግ ጥቂቶቹ ናቸው። አል ኢባናህ ዓን ኡሱል አል ዲያናህ በሀድርአባድ ዴካን ህንድ በ1321/1903 ሲታተም ሪሳላህ ፊ ኢስቲህሳን አል ኸውድ ፊ አል ከላም የምትባል አነስተኛ በዚያው ሀድርአባድ በ1323/1905 ለመጀመሪያ ጊዜና በ1343/1925 በድጋሜ ታትማለች ። ከአል አሽአሪይ ሌሎች ስራዎቻቸው መሀከል አል መቃላት አል እስላሚዩን (በኢስቱንቡል በ1448/1929 ታትሟል) ኪታብ አል ሸርህ ወል ተፍሲል፣ሙእጃዝ፣ሙእጃዝ፣ለእዳህ አል ቡርሀን እና ታቢኢይን ይታወቃሉ። ከነዚህ ሁሉ መቃላት አል እስላሚዩን ወ ኢኽቲካፍ አል ሙስሊዩን ተለያዩ የሀይማኖቱ ቀኖናዎች እና አስተምሮቶች ላይ የተለያዩ የአስተሳሰብ መስመሮች ያለቸው አቋም በዝርዝር የተነተኑበት ነው። አል መቃለት በጉዳዩ ላይ ከተፃፉት እንደ የሸህረስታኒ ኪታብ አል ሚላህ ወል ኒሃል ወይም የኢብን ሃዝም አል ፊከል አል ሚላህ አህዋል ወል ኒሃል መፅሀፍት በእጂጉ ይቀድማል። ኢብን ቀይምም ስለዚህ የአል አሽአሪይ መፅሀፍ በከፍተኛ አድናቆት ነው የሚያወራው። ሀዚ አል አርዋህ እና ኢጁቲማዕ አል ጃዩስ አል ኢስላሚህ በተባሉ ስራዎቹ ሸህረስታኒ አብዱል ቃድር ባግዳዲ እና ሌሎች በሁዋላ የመጡ ምሁራን የአል አሽአሪን መፅሀፍ ከመገልበጥ ውጭ ሀሳቦቹን አልተነተኑዋቸውም ብሏል። አል አሽአሪይ በርካታ ሊቆችን ያፈሩ ሲሆን ሁሉም ቀኖናዎቹን እና አስተምሮቶቹን አዳብረውታል። ከቀደምት የአል አሽአሪይ ተከታዩች መካከል አቡ ሰህል ሳሉቂ/አቡ ቁፋል/ አቡ ዘይድ ማሩዚ / ዛሂር ኢብን አህመድ / ሀፊዝ አቡበክር ጂርጃኒ / ሸህ አቡ ሙሀመድ ጦበሪ እና አቡ አል ሀሰን ባህሊ ይጠቀሳሉ። የነዚህ ቀደምት ሸሆች ደረሳዎች እንዲሁ ታዋቂ ናቸው። ከነርሱ ውስጥ እጂግ በጣም የሚታወቁት የሚከተሉት ናቸው። ቃዲ አቡበከር ባቂሊ/ አቡበከር ቢነወ ፋራክ / አቡ አል ቃሲም አል ቁረይሺ እና አቡ ኢስሀቅ ኢስፋኒይ እና ደረሳቸው አቡ አል መአሊ አል ጁዋይኒ። #ይቀጥላል..... . . . አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን. ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
እንደሚታወቀው የአቂዳ ትምህርት ከዚህ ቀደም እስከ ክፍል ሁለት አይተናል ያው እጠቀምበታለሁ ያለ አንብቦታል በአላህ ፍቃድ ይጠቀምበታል ❌አደራችሁን አንብበው ሲጨርሱ❌ ያልገባቹሁን በመ ጠየቅ ✅ከገባቹህ ሸር በማረግ ይተባበሩ✅ #ዐቂዳ #ክፍል_ሶስት #የኢማም_አል_አሽዓሪ_ህይወትና_ስራ ኢማሙ አል አሽአሪ የተወለዱት በበስራ ነበር። የትውልድ ዘመናቸውን በተመለከተ የተለያየ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ። ኢብን አል ኻሊካን ስለ ኢማም አል አሽአሪ ህይወት በፃፈበት ስራው በ260 ወይም 270/873 ወይም 883 ተወልደው በ330/941 ወይም ከዚያ ትንሽ በዘለለ አመታት ውስጥ እንደሞቱ ፅፈዋል። እንደ ሺብሊ ኑእማን እና ኢብን አሳኪር (የጠይቢን ኺዝብ አል ሙፍታሪ በየአል አሽአሪ ህይወትና ስራ ላይ መፅሀፍ ደራሲ ነው) አል አሽአሪ የተወለዱት በ270 ሲሆን የሞቱት ደግሞ በ330 ነበር ብለው አስፍረዋል። የተቀበሩት በካርኽ እና ባብ አል በስራዕ (ባበል በስራዕ) መሀከል በሚገኝ ቦታ ሲሆን የረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ታዋቂ ሶሀባ አቡ ሙሳ አል አሽአሪ ዝርያ ነበሩ። አል አሽአሪ በቀደምት ወጣትነት ጊዜያቸው በታላቁ የበስራ ትምህርት ቤት የሙእተዚላ ሊቅ በአቡ አሊ ሙሀመድ ቢን አብዱልወሀብ አል ጁባዓይ እንክብካቤ አድገዋል። የእሳቸው ደረሳ እንደመሆናቸው 40 አመት እስኪሞላቸው የአስተሳሰቡ ቀንደኛ ደጋፊ ሆነው ቆይተዋል። ከዚያ በሁዋላ ድንገተኛ የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተዋል። ከእለታት አንድ ቀን አል አሽአሪ ወደ በስራ መስጂድ ሄደው እኔን የሚያውቀኝ ማንነቴንም እንዲሁ የሚያውቅ እንዲሁም እኔን የማያውቅ እኔ አቡ አል ሀሰን አለከ አሽአሪ እባላለሁ። ቅዱስ ቁርአን ፍጡር እንደነበር የሰዎች አይኖች አሏህን ሊያዬ እንደማይችሉ እና ፍጡሮች ተግባሮቻቸውን እንደሚፈጥሩ አምን ነበር። ተሳስቻለሁ ከሙእተዚላነት ተመልሻለሁ። እነዚህ አስተሳሰቦች ትክክል እንዳልሆኑ አውጃለሁ። ከሙእተዚላዊች ጋርም ለመወያየትና አስከፊነታቸውን እንዲሁም አጥፊነታቸውን አጋልጣለሁ አሉ። ይህን የአል አሽአሪ ድንገተኛ የአስተሳሰብ ለውጥ ምን እንዳመጣው የሚታወቅ ነገር የለም። ሽብሊ በኢልም አል ከላም መፀሀፋ ለውጡ የመጣው በህልማቸው ካዩት የተወሰኑ አቅጣጫዎች ነው ብሎ ፅፏል። ኢብን ኻሊካን ከዚህ ጋ በተያያዘ አል አሽአሪ ከቆየ የሙእተዚላ ሸሀቸው አል ጁቤእይ ጋ የአደባባይ ክርክር ያነሳል። ክርክሩ "የአሏህ ድርጊት ምክንያታዊነትን የተከተለ ነው ወይስ ለፍጡራኑ ምርጥ ያለውን ነው የሚያደርገው" በሚል ፈተና ላይ ያጠነጠነ ነበር። አል አሽአሪ የሶስት ወንድማማቾችን ጉዳይ ይዘው ወደ ሸኻቸው አል ጁቤእይ ይመጣሉ። ሶስት ወንድማማቾች አሉ አንድኛው አሏህን ፈሪ ሲሆን ሌላኛው እምነት የለሽ ነው ሶስተኛው ደሞ በልጂነቱ ሞቷል። በመጪው አለም የነዚህ ወንድማማቾች እጣ ፈንታ ምንድን ነው?? ብለው ጠየቁ አል አል ጁቤእይ ለጥያቄው ትክክለኛ መልስ ሊሰጡ አልቻሉም። ሸኹ በሙእተዚላ የምክንያታዊነት ስርአት በሳላህ ወእል አስላህ ቀኖና ላይ ምላሽ መስጠት ባለመቻላቸው ከሙእተዚላ ካምፕ ኢማም አሽአሪ ይወጣሉ። #ይቀጥላል..... . . . አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን የነቢ ወዳጆች💖 ❖ የቻናሉ አላማ ♠ ሱነተ ነብይ ይማሩበታል ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል https://t.me/mehabetuneby ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
የነቢ ወዳጆች💖

❖ የቻናሉ አላማ ♠ ሱነተ ነብይ ይማሩበታል ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል

በዲንህ ጉዳይ ❌ችላ❌ እንዳትል አደራህን #ዐቂዳ #ክፍል_ሁለት ነገር ግን እንዲህ አይነት በእምነት ላይ የሚያዝ እውር ባህሪ ብዙም እድሜ ሊኖረው አልቻለም። እስልምና እንደ ሁሉን አቀፍነቱና ህያው ሀያልነቱ ለአዳዲስ አስተሳሰቦችና ከባቢዎች ተግዳሮት ተገቢውን ምላሽ መስጠት ነበረበት። በተጨማሪም እነዚህ ተቃራኒ ሀሳቦችና ሊቻቻሉ ያልቻሉ ባህሪያት በሙስሊሙ ውስጥ ቀውስና ረብሻ በመፍጠር የሙስሊሙን አስተሳሰብና ታሪካዊ ሀሳቦችንና እምነቶቹን መናጥ ጀመሩ ። እነዚህ ጫፍ የረገጡ አስተሳሰቦችን የሚያስታርቁና ማህበራዊ ድቀቱን የሚታደጉ ሀሳቦች በታላቅ ጭንቀት ይጠበቁ ነበር። በዚህ ወሳኝና ቁልፍ የሙስሊሙ ታሪካዊ አጋጣሚ ከትክክለኛው የእስልምና አስተምሮቶች ውስጥ እስልምናን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለመጣበት ተግዳሮት ተገቢውን ምላሽ የሚሰጡና በትውፊታውያኑ አስተሳሰብ ደካማነት ምክንያት ወደ ሀይማኖቱ ሰርገው ለመግባት ቀዳዳ ያገኙ እንግዳ አስተሳሰቦችን የሚያፀዱ ስብስቦች ተነሱ። ሙእተዚላዎቹ ያቀረቡትን ዲያሌክቲካል ምክንያታዊነት በማረቅ ትክክለኛውን ነገረ መለኮት በየራሳቸው ስነ ዘዴ አማካኝነት እውን አድርገዋል።እምነታቸውን ለማፅናት ከላምን የተጠቀሙ የነገረ መለኮት ሊሂቃን #ሙተከሊሙን በመባል ይታወቃሉ። ሙተከሊሞቹ በውይይታቸው ፍልስፍና ዘዴዎችን ቢጠቀሙም ዋናውን መሳሪያቸውን ያገኙት ከወህይ ነበር። ወደ ሙእተዚላዎቹ ሜዳ ወርደው የሚያገጥሙበትን የምክንያታዊነት ሳይንስ አዳብረዋል። በመጀመሪያ እነዚህ ትክክለኛ የነገረ መለኮት ቅስቃሴ የተጀመረው በግለሰቦች ደረጃ ነበር በሂደት የመሸርሸርን መንገድ ነበር የተጠቀሙት። በግልፅ መውጣት የህዝብ ተቃውሞ ያመጣል ብለው ፈርተዋል ። ለምሳሌ አል ጁነይድ የአሏህን ብቸኝነት በተመለከተ ሲያደርገቸው የነበሩት ውይይቶች ከቤቱ የወጡ አልነበሩም ። ኢማም አል ሻፊእይ በሌላ በኩል የተወሰኑ የሰለጠኑ የሰዎች ስብስብ ሀይማኖቱን ሊያፀዱትና ሊከላከሉ ይችላሉ ብለው ያስቡ ነበር። ይህም ቢሆን ግን በአደባባይ መሆን የለበትም የሚል አቋም ነበራቸው።አል ሙሲቢ እና ሌሎች በኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል ዘመን የነበሩ አሊሞች ምክንያታዊነት መጠቀማቸው በኢማሙ የመረረ ተቃውሞ አስነቶባቸዋል ሆኖም የሙተከሊሞቹ ቅስቃሴ በሂደት ጉልበት አግኝቶ በተለያዩ የኽሊፋው ግዛቶች በተራራቢ ጊዜ #በሜሶፓታሚያ_በአቡ_አል_ሐሰን_ዓሊ_ቢን_እስማኤል_አል_አሽአሪይ (በ330-334 ዓ.ሒ ያለፉ) #በግብፅ_በአል_ዘህዊ (በ331 ዓ.ሒ ያለፉ) እና #በሰመረልቃንዲ_በአቡ_መንሱር_አል_ማትሩዲይ በአደባባይ መሰበክ ጀመረ። #ይቀጥላል..... . . . አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን https://t.me/mehabetuneby ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
የነቢ ወዳጆች💖

❖ የቻናሉ አላማ ♠ ሱነተ ነብይ ይማሩበታል ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል

Photo unavailableShow in Telegram
🛑🕋 #አሰዳሳች_ዜና የክረምት ኮርስ (ደውራ) #ለደሴ_ከተማ_ሙስሊም_ማህበረሰብ በሙሉ እነሆ የ2014 የት/ት ዘመንን መጠናቀቅ ምክናያት በማድረግ የእረፍት ጊዜዎን ተጠቅመውበትና የዲንን እውቀቶዎን እንዲያዳብሩ ሰፋ ያሉ እድሎችን አመቻችተንለወታል ከእርሰዎ የሚጠበቀው ቦታው ሳይሞላ ፈጥነው መመዝገብ ብቻ ነው #የምንሰጣቸው_የእውቀት_ዘርፎች 1 ቁርአን ማቅራት 2 ዒልመ አት_ተጅዊይድ 3 ፊቂህ ( ሰፊና……) 4ተውሂድ ( አቂደቱ አጥ_ጦሀውያ) እንዲሁም የአርበኛ ቋንቋ ት/ት ስልጠና ይሰጣል። በከተማችን ሴንተር የሚባሉ ቦታዎች ላይ ኮርሱ ስለሚሰጥ የቦታ እርቀት እንዳያሳስብዎ‼ ኮርሱ ( ደውራው ) ፆታ አይገድብም ወንዶችንም ሴቶችንም ያሳትፋል #ለመመዝገብ ቧ/ውሀ፣ ኬላና ተቋም አካባቢ ላላችሁ 0968593431 0913766413 0989959169 ፒያሳና በአካባቢው ላላችሁ 0963612303 0914363246 0914084763 ሰኞ ገበያና በአካባቢው ላላችሁ 0930980318 0904083545 0929516403 ቢለንና ገራዶ አካባቢ ላላችሁ 0948807529 0976565364 0945129577 ሸዋበር አካባቢ ላላችሁ 0988319181 0935393965 ጧኢፍና ዳውዶ አካባቢ ላላችሁ 0975012756 በተጨማሪም በየመድረሳዎች ባሉ አሚሮችና አሳቲዛዎች በኩል መመዝገብ ትችላላችሁ ትምህርት (ደርስ) የሚጀመርበትን ቀን በፔጃችንና በደወል የምናሳውቅ ይሆናል https://t.me/dewura
Hammasini ko'rsatish...
✅እዩሃን ናስ ልብ ብለህ❌ አንብብ ችላ እንዳትል #ዐቂዳ #የአዘጋጁ-ማስታወሻ ወቅቱ እጂግ አሳሳቢ ነበር ከሁለተኛዉ ዓመተ ሂጅራ ጀምሮ፡፡ ለሚቀጥሉት 300 አመታት በእስልምና ሀይማኖት ምሁራኖች ዘንድ እየሰፋ የመጣዉ የአስተሳሰብ ልዩነትና እርሱን ተከትሎ የመጣዉ የሀይል እርምጃዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ ለሁለት ሊከፍለው ዳር ደርሶ ነበር፡፡ አይኑን አፍጦ እየመጣ ካለው አስቀያሚ ነገር የሚገላግላቸው ሀሳብ በጭንቀት ሲያማትሩ ከሶስት ቦታዎች ሶስት ታላላቅ ኢማሞች ብቅ አሉ፡፡ የኢማሞቹ አስተሳሰብ አብዮታዊ ከመሆኑም ባሻገር ሁሉን አቀፍ ነበር፡፡ በሇላም የመጡት የእነዚህ ኢማሞች ተከታይ ምሁራን አስተሰሠሰባቸውን በማዳበርና ከሰፊዉ ማህበረሰብ እስከ ምሁራኑ ድረስ እንዲያናግር አዘጋጂተውታል፡፡ ይህች አነስተኛ መፅሀፍ የተዘጋጀችው እንደኔ ላሉ የሰፊዉ ማህበረሰብ አባላት ነው ፡፡ መጀመሪያ ስለ ኢማሞቹ ኢማም አሽአሪይ እና ኢማም ማትሩዲይ አጭር ታሪክ ይቀርብና ሰለ አስተሳሰባቸው ምንነት አጠር ያለ መሰረታዊ ትውውቅ ይደረጋል ከዚያ አቂዳ ፅንሰ ሀሳብ ጋር ትውውቅ እናደርጋለን አላህንና ረሱልን ሶለሏህ አለይሂ ወሰለለም በተመለከተ የሙስሊሞች አቂዳ ይቀርባል። መፅሀፏ የተዘጋጀቺበት አላማ እንደተጠቆመው ስለ አሽአሪያ እና ማትሩዲይ አቂዳ መሰረታዊ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው።ለሰፊው ማህበረሰብ የአሽአሪያ እና ማትሩዲይ አቂዳ እንግዳ እንዳልሆነ ለማሳየትም ጭምር ነው። መፅሀፏ ከአራት ሸሆች እና ምሁራን የአዝሀሮቹ ሙፍቲህ ሸይኽ አሊ ጁመአህ, ኢማም ሙሀመድ ቢን ኢብራሂም ባጁሪ, ከፓኪስታን ምሁራን ኤም አብዱል ሀይ , ኤኬኤም አዩብ አሊ ስራዎቸደ ተውጣጥታ ለአገራችን አንባቢያን በሚመች መልኩ የተዘጋጀች ነች። መልካም ንባብ አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራቺሁ የአህለል ሱና ወል ጀመአ ሱፍያ ወንድም እህቶች ይህ ቻናል ስለ አሻኢራና ማቱሪድያ ትክክለኛ አስተምህሮት ስለ ሱፍዬች አስተምህሮት እናደርሶታለን 👇👇👇 ሼር ማድረግን እዳይረሱ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
*🍂 ኢማሙ-ሻፊዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ-“በነብዩ ﷺ ላይ በሁሉም ሁኔታ ላይ በብዛት ሶለዋት ማውረድ እወዳለሁ ፤ የጁሙዐ እለት እና በዚያ ምሽት ይበልጥ እወዳለሁ . ትእዛዝ ስለመጣባት በጁምዐ ምሽት እና በእለቷ የከህፍ ምዕራፍን ማንበብ እወዳለሁ. كتاب الأم ٢٣٩/١ የነቢ ወዳጆች💖 ❖ የቻናሉ አላማ ♠ ሱነተ ነብይ ይማሩበታል ♠ የመሻይኾቻችንን አቂዳ ይማሩበታል ♠ ቂሷዎች ( ታሪክ ) ይለቀቅበታል https://t.me/mehabetuneby
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.