cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ህይወት ናት መምህሬ 📝

Welcome to my Channal #Best picture🌌 #Music audio🎶 #Couple picture💏 #Birthday pic🎉🎊

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
189
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

🎧🧝‍♀ 👈konjo enda anch🫶 https://t.me/jowiell
Hammasini ko'rsatish...
4.07 KB
Ye afarua konjo♥️ 💥 o💥l💥d 💥m💥u💥s💥i💥c https://t.me/jowiell
Hammasini ko'rsatish...
4.94 KB
Mamen akategn 🥰🥰 yehelemn ngste👸👩‍🦰 yena arekena beru kene meta hiwet letades banch endgena https://t.me/jowiell
Hammasini ko'rsatish...
3.49 KB
ይጠየቅ፣ አንቀባርሬ ነው ያሳደኳቸው፡፡ አሜሪካ ሲሉ፤ አውሮፓ … እንሂድ ሲሉ ልኬ፣ ካለወጉ ከድሬደዋ አሜሪካ ብር እየላኩ ያስተማርኳቸው እኔ ነኝ፡፡ እኔስ እሺ፡ በድያቸው ይሆናል፣ እዚች አንድ ፍሬ ልጅ ላይ ይጨከናል? እንኳን ሥጋው ሁና፣ ይችን ልጅ አያቶ የሚጨከን መገደኛ አለ?"... አነጋገራቸው ያሸብራል ሽማግሌ ፊታቸው ላይ የሚያንዣብበው ሐዘን…ማረፊያ አጥተው ዙሪያ ገባው ላይ የሚንከራተቱት ዓይኖቻቸው፣ አንጀት ይበሉ ነበር፡፡ ከአራት ዓመታት የድሬዳዋ ቆይታ በኋላ፣ ዋናው መሥሪያ ቤት ድንገት ወደ አዲስ አበባ ሲጠራኝ ትንሿ ገነታችን ጨለማ አጠላባት። ይቀጥላል...... Join and share @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire
Hammasini ko'rsatish...
✨✨ ሐኑን ✨✨ ክፍል 6⃣ በጧት እንደ እሳት የሚፋጅ ላሰላሳ ገላዋ፣ የሞቀ አልጋዬ ውስጥ ገብቶ ስትለጠፍብኝ ነበር የነቃሁት፡፡ በእንቅልፍ በሰከረ አእምሮዬ ላይ በሽቶ ባበደ ጠረኗ የታጀበ ሰውነቷ ሲያቅፈኝ፡ ነገሩ ሕልም ይሁን እውነት በወጉ እንኳን ሳይገባኝ፣ የሐኑን የሚንቀጠቀጡ ትኩስና ለስላሳ ከንፈሮች፣ ከንፈሬ ላይ አርፈው ነበር፡፡ ሰውነቴ ከእእምሮዩ ቀድሞ ነቃ፤ ረዥም በሰመመን የተሞሉ ደቂቃዎች ይሁኑ ሰዓታት ከሥሬ ሆና በለስላሳ ቀይ ፊቷ ቆዳ ላይ እንባዋ ኮለል ብሎ ወደ ጆሮዋ ሲወርድና በሕመም ስትቃትት፡ ሥጋዊ ወንድነቴ ከሚሰማው አብሮነት ይልቅ አንዳች የነፍሴ ክፍል ላይ ነፍሷ ለዘላለም ሲነቀስ ይሰማኝ ነበር፡፡ አእምሮዬ በአንድ ጊዜ ሁለት ተቃራኒ ሐሳቦችን እያሰበ ነበር፡፡ "እየተሳሳትኩ ነው" እና "ልክ ነኝ" የሚሉ ሐሳቦች፡፡ እንደዚያ ነበር የማስበው፡፡ አእምሮየ ምንም ያስብ ምን፡ ገና ከጅምሩ ሰውነቴ ለአእምሮዬ መታዘዙን ትቶት ነበር፡፡ ብዙ ሰው የሆንኩ እስኪመስለኝ ድረስ ተከፋፍዬ፣ ተሰነጣጥሬ፣ ሁሉም ስንጣሪ ውስጥ ስጋትና ደስታ እኩል ተሰትኖ ነበር፡፡ የዚያ ቀን፣ አባቷ ከሚያከራዩት ሱቅ አንደኛዉ ዉስጥ ጎርፍ ገባበት ተብለው በጧት የሄዱ፣ ወደምሳ ሰዓት ነበር የተመለሱት፡፡ገና የግቢውን በር እግራቸው እንዳለፈ “ሐኑን አዘጋጅልኝማ!" ብለው ገላቸውን ሊታጠቡ ከቤቱ ኋላ ወዳለው መታጠቢያ ቤት ሲገቡ፣ አላስችለኝ ብሎ ወጣሁና “ደህና ነሽ” አልኳት ዕፍረት ባረበበት ፊት “ደህና ነኝ" አለች፡፡ቀና ብላ አላየችኝም፡አባቷ ጫታቸውን አቅርበው በረንዳቸው ላይ ቁጭ እንዳሉ፣ አላስችለኝ ብሎ እንደገና ብቅ እልኩ፡፡ “ልጅ ሥራም አልሄድክ እንዴ?” አሉኝ፡፡ ስላዩኝ ደስ ብሏቸው ነበር:: “ዛሬ እልገባሁም፣ እቤት ሆኜ የምጨርሰው ነገር ነበር… " "እንኳን ያልሄድክ፣አገር ምድሩ ጎርፍ ሁኗል፡፡ ማረፍ ጥሩ ነው…ዱኒያ እንደሁ እትሞላ! ታዲያ ይችን ነገር ትንሽ ኤልሞክርም አልክ?" ብለው የያዙትን ጫት እጃቸው ላይ መታ መታ እያደረጉ ጋበዙኝ፡፡ የጫት ቅጠሎቹ ጫፋቸው ወደቀይ የሚያደላ ቡና አይነት ነበሩ ልክ እንደ አባባ ፂም ብዙ ጊዜ እንደማደርገው የበረንዳውን ብረት ተደግፌ ፈታቸው ቆምኩና ስለጎርፉ አወራን፡፡ በመሃል፣ “ሐኑን ወንበር አምጭለት የኔ ነገር" አሉ፡፡ “ቆይ ራሴ አመጣለሁ” ብዬ ወደቤት ገባሁ፡፡ ሐኑን ውሃ በፕላስቲክ ጆግ ይዛ ስትወጣ፣ ልክ እንደማይተዋወቅ ሰው በሩ ላይ ተላለፍን፡፡ ስንተላለፍ እስከ ዛሬ ከአእምሮየ ያልጠፋዉ ጠረኗ አውዶኛል፡፡ ልብሷ እንደ መንፈስ በስሱ ዳስሶኝ አልፏል፡፡ የዛን ቀን፣ ከወትሮው ረዘም ላለ ሰዓት ከአባቷ ጋር ተቀምጨ ስናወራ ቆየን በየመሀሉ ሐኑንን በጠሯት ቁጥር እሳቀቅ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድ ጋር የተኛች ሴት፣ እንዲህ ቁጭ ብድግ ስትል፣ ምን የተለየ ነገር ይሰማት ይሆን? የሚል ምርመራዬን በዓይኔ እየተከታተልኩ፡አባቷ ጋር የባጥ የቆጡን እናወራለን። የሚበዛው ወሬ ሱቃቸው ዉስጥ ስለገባው ጎርፍ ነበር፡፡ ሐኑን ማረፍ ባለመቻሏ፣ የሆነ ደስ የማይል ነገር ቢፈጥርብኝም፣ አጠገቧ መሆኔ ግን ምቾት ሰጥቶኝ ነበር፡፡እርሷም ገብቷታል፡፡ አባባ ጎን ተቀምጣ፣ ሳወራ ታየኛለች፡፡ አስተያየቷ ሥጋን ዘልቆ ነፍሴ ድረስ የሚሰማ ሐዘን ይለቅብኝ ነበር፡፡ ዓይኖቻችን ሲጋጩ ዓይኖቿ ማረፊያ ያጣሉ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ፣ ሐኑን የምታደርገው ነገር ሁሉ ያስደነግጠኝ ነበር:: አንድ ቀን ድንገት የሥራ ቦታዬ መጣች፤ ደስታም ድንጋጤም ተቀላቀለብኝ፡፡ሰዎች እንዳይሰሙ ድምፅዋን ቀንሳ "ናፈከኝ!" አለችኝ፤ እንዲያዉ የአባቷ ነገር እያስጨነቀኝ እንጂ፣ እኔም የምይዝ የምጨብጠውን ነገር አላውቅም ነበር፡፡ እንደትኩስ ፍቅር ምን አደገኛ ነገር አለ?…ፍቅራችን በጭንቀትና በጥንቃቄ የተሞላ ደስታ ነበር፡፡ ልክ የተከሰከሰ ጠርሙስ የተዘራበት ወለል ላይ በባዶ እግር እንደሚራመድ ሰው፣ እጅግ በጥንቃቄ፣ ግን ደግሞ ትንፋሽ የሚያሳጣ፣ አብረው ሆነው የሚያነፋፍቅ አንዳች ነገር፡፡ አንዳንዴ ከሐኑን ጋር አንድ ግቢ ውስጥ ከመኖራችን እና ብዙውን ጊዜ አብረን ከማሳለፋችን የተነሳ፣ ግንኙነታቸን ከፍቅረኝነት ይልቅ ትዳር የሚመስል ቅርፅ ይይዝ ነበር፡፡ ልብሶቼን ላውንደሪ ወስዳ ትሰጥልኛለች፣ ምግብ አባባም ቢኖሩ ባይኖሩም ውጭ በልቼ ካልገባሁ እነሱ ጋር ነበር የምበላው። አንዳንድ ቀን አባባን ነግረናቸው ፣አብረን ወደ ገበያ እንሄዳለን፡፡ አባባ ሐኑንን ብቻዋን ከቤት አያስወጧትም፤ ወይ አብረዋት ይወጣሉ፣ አልያም አትወጣም፡፡ እኔ ጋር ግን ስትወጣ "ልጅ መንገድ ላይ እንዳትጠፋፉ እጇን ይዘህ አደራ!" ከማለት ውጭ ምንም ቅሬታ ፊታቸው ላይ አይታይም ነበር፡፡ እንደውም አንዳንዴ :አንች ልጅ ሰው ጋር እንዳታጋጭው” ብለው ለእኔ ያስባሉ፡፡ ከግቢው እንደወጣን ሐኑን “እጇን ያዛት ተብለሃልኮ" ትልና ክንዴን ይዛ በሳቅ እየተፍለቀለቀች፣ በጋሪ ተሳፍረን ቀፊራ ወደሚባለው ገበያ እንሄዳለን፡፡ ንፋሱ ክንብንቧን ሊገፉት ሲታገል፣ ክንዴን ይዛ አንገቴ ስር ትሸጎጣለች፡፡ አብረን እስከሆንን ድረስ ጋሪው የትም ቢወስደን ግድ አልነበረንም፡፡ ቀፊራ ወርደን ከቴምር እስከጭሳጭስ፣ ከዶሮ እስከ ብርቱካን እንገዛለን፤ የሚበዛውን ጊዜ ግን እንዲሁ በመዞር ነበር የምናሳልፈው፡፡ እየተነሳ ፊት ላይ በሚሞጀረው አቧራ ውስጥ፣ በጫጫታውና ግርግሩ ውስጥ፣ በእነዛ ጎሊቶች መሃል ሐኑን ቀይ ሽቲ በቀይ ሻርፕ ለብሳ(ብዙ ጊዜ ስትወጣ እንደዛ ነበር የምትለብሰው) ተያይዘን ስንዞር ውለን የሸመትነውን ጭነን፣ በጋሪ ወደ ቤት ስንመለስ በደመና ሰረገላ ላይ ተጭነን ወደ ሰማየ ሰማያት የምንነጠቅ እስኪመስለኝ፣ደስታዬ ወደር አልነበረውም፡፡ ሁሉም ነገር የተረጋጋ፣ ደሰ የሚልና ሰላም የሰፈነበት፣ ሕልም የሚመስል ሕይወት ነበር፡፡የሐኑን አባት እልፎ አልፎ አልጋ ላይ ከሚጥላቸው ሕመም በስተቀር፣ሁሉ ሰላም ነበረ:: የሰላም ትክክለኛ ትርጉም ረብሻ አለመኖር እይደለም፣ መነሻው ፍቅር የሆነ ረብሻ በነፍስ ውስጥ እንደመዓበል መተራመሱ ነው፡፡ ፍቅር የሌለው ሰላም ውሃው እንደደረቀ ወንዝ ነው፡፡ በሰላም ውስጥ ወንዝ መፍሰስ አለበት ፣ወንዙን ሊሻገሩ የሚታገሉ ነፍሶት መኖር አለባቸው፤ በውሃው ውስጥ የሚጋጩ የሚሳሳሙ ድንጋዮች መኖር አለባቸው፣አሳዎች መኖር አለባቸው፡፡ ሰላም ነበረን እኔና ሐኑን፡፡ አባቷ ህመማቸው ቶሎ ቶሎ ባይነሳባቸውም ሲያማቸው ግን የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ ደግሞ ለከፉቱ ቀድሞ አፋቸውን ነው የሚይዛቸው፡፡ እኔ እዛ ቤት ከተከራየሁ እንኳን ይኸው ሕመም ሁለት ጊዜ ሲያማቸው አጋጥሞኝ ነበር፡፡ ከስኳር ሕመም ጋር የተያያዘ መሆኑን ነግረውኛል፡፡ደግነቱ ብዙ አይቆይባቸውም ነበር፡፡ ሐኑን የአባቷ ነገር አይሆንላትም፡፡ በምድር ላይ ያሏት ብቸኛ ዘመድ እሳቸው ናቸው ፡፡ አባቷ ከወንድሞቿና ከእህቶቿ ጋር እንድትቀራብ ያላደረጉት ጥረት የለም፡፡ ይሄንኑ ነገር አንድ ጊዜ፣ በጣም ከተቀራረብን በኋላ በሐዘን ነግረውኛል “መቼስ! ሰው ይሳሳታል፤ አንዴ እጠፋሁ፣አባት ላይ ይጨከናል? እሷስ እህታቸው እይደለችም? ቤቱ እንደሆነ እንኳን ለነሱ ለባዳውም ይበቃል፡፡ እንዴት እህታቸውን ካለዘመድ ያስቀሯታል? ዕድሜዬም ገፍቷል፡ በሽታውም እየበረታብኝ ነው፡፡ድንገት አላሀ በቃህ ካለኝ እችልጅ ብቻዋን እንዳትቀር ብየ፣ እኔ ቁልቁል ወደ ልጆቼ ታረቁኝ ብዬ ሽማግሌ ብልክክ አከላፍተው መለሷቸው፡፡ መቼስ በእኔ አይጨከኑም ብዬ ራሴዉ ብሄድ፡ የተቀመጥኩበት እየጣሉኝ ወጡ፡፡ ልቤ አዘነ፤ ግን አልረገምኳቸውም ሥጋ ናቸዋ አባት ቢያጠፋስ ይኼ ተገቢ ነው? ድፍን ድሬዳዋ
Hammasini ko'rsatish...
በእያንዳንዱ ብልጭታ፣ የሐኑንን ውብ ፊት አእምሮየ እንደፎቶ እያተመ ያስቀምጣል፡፡ በግራ ትከሻዋ በኩል አልፎ ጡቷ ላይ የሚርመሰመሰዉ ጸጉሯ ግማሽ ፊቷን የከበበ ጥቁር ፍሬም መሰሏል፡፡ እስከ ዛሬ ሐኑንን ሳስብ፣ ያ መልኳ ነው ቀድሞ የሚታወሰኝ፡፡ እንደ ቲማቲም የቀሉ ከንፈሮች ከመቅላቱ ብዛት በወርቃማ ቆዳ የተለበጠ የሚመስል ደረት…ሥዕል፡፡ በየመስኮት መስታዎቶቻችን ላይ የሚንኳለለው የዝናብ ውሃ፣ ነጋችንን አውቆ እርሙን የማያወጣ የዘመን እንባ ይመስል ነበር፡፡ ጡቶቿ ቢጫ የሚበዛበትን ባለብዙ አበባ ሥዕል፣ ስስ የሌሊት ልብሷን ወጥረው፣ ከተደገፈችዉ መስተዋት ጋር ጫፋቸው ተነካክቷል፡፡ ወደ መስተዋቱ ስትጠጋ፣ አፍንጫዋ በመስተዋቱ እየተደፈጠጠ ያስቀኛል፡፡ እኔን በፈገግታ እያየች መስተዋቱን ስትስመው፣ቀያይ ውብ ከንፈሮቿ መስተዋቱ ላይ በክቡ ተለጥፈው፣ ትንፋሽዋ መስተዋቱ ላይ ጭጋግ ይፈጥራል፡፡ በትንፋሽዋ ጉም በተሸፈነው መስተዋት ላይ፣በጣቷ የልብ ቅርጽ ትሥልበታለች ፡፡ትንፋሽዋ መስተዋቱ ላይ በሚፈጥረው ላቦት ምስሏ መደብዘዝ ሲጀምር፣ መስተዋቱን በመዳፏ ትወለውለዋለች፡፡ በዚህ ጊዜ የደበዘዘዉ ምስሏ ቦግ ብሎ ይወጣል፡፡ በቃ እንተያያለን፣ ያለድምፅ ዝም ብለን መተያየት…በምልከት ልተኛ ነው ስላት በእጇ ትንሽ እንድቆይ ትለምነኛለች፡፡ያ ሌሊት በተደጋጋሚ ሕልሜ ይመጣል፡፡ መስተዋት ተደግፌ አድሬ፣ ሊነጋጋ ሲል ድብን ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ጧት የቤቴ በር ሲከፈት እንኳን አልሰማሁም፡፡ በጧት እንደ እሳት የሚፋጅ ላሰላሳ ገላዋ፣ የሞቀ አልጋዬ ውስጥ ገብቶ ስትለጠፍብኝ ነበር የነቃሁት..... ይቀጥላል..... Join and share @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire
Hammasini ko'rsatish...
✨✨ ሐኑን ✨✨ ክፍል 5⃣ አንድ ቀን ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ግን በብዙ ሐሳቦች ዙሪያውን ተወጣጥሬ ቃል መተንፈስ አቃተኝ፡፡ በሁለት ምክንያቶች እንደምወዳት ለመናገር ፈራሁ። አባቷ እንደ ልጃቸው ስለቀረቡኝ፣ ድንገት ይኼ ጉዳይ ጆሯቸው ቢገባና፣ አዲስ አበባ ላሉት አለቆች “የላካችሁት ጎረምሳ ልጄን እያማገጠ ነው!" ብለው ቢናገሩ፣ የሚለው ሐሳብ አስጨነቀኝ፡፡ ለብዙ ነገር ግዴለሽ ናቸው የሚባሉ ሰዎች፣ በማይወላውል ለሰላሳ ማንነት እንደተራራ ረጋ ብለው ቢቀመጡም፤ ድንገት እንደ እሳተገሞራ በውስጣቸው ያለው እሳት ወጥቶ፣ አካባቢያቸውን የሚያቃጥልበት ሽንቁርም አይጠፋቸውም::እኒህም ሰው ለሀብታቸውም ሆነ በዙሪያቸው ላለ ነገር ግዴለሽ ይመስላሉ ማለት፤ ለልጃቸው ግዴለሽ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ዓይናቸው ናት ሐኑን፡፡ዋጋ የከፈሉባት፡፡ ብትመነዘር የስምንት ልጅ ዋጋ ያላት፡፡ ሌላው ጭንቀቴ ሐኑን ራሷ ነበረች፡፡ ገና ለፍቅር ሳስባት የሚጨንቀኝ ነገር አለ፡፡ ዓይኖቿን ስመለከት፣ እርጋታዋን ስታዘብ ፣ተረጋግቶ ሰፊ ቦታ ላይ የተኛ ንጹህ የሐይቅ ውሀ ትመስለኛለች፡፡ወደ ሕይወቷ በፍቅር ሰበብ ብገባ፣ የምትደፈራርስ የምትናወጥ ይመስለኛል፡፡ተፈጥሮን የምረብሽ የማዛባ ዓይነት፡፡እራሴን አላምነውም አንዳንዴ ውሳኔዬ ድንገተኛና እራሴንም የሚያስደነግጥ ነው፡፡ይኼ ድንገተኛና ደፋር ዉሳኔዬ ከዕድል ጋር ተዳምሮ በሕይወቴ ውስጥ ብዙ ቢጠቅመኝም፤ "ሁልጊዜ ፋሲካ የለም" ይለኛል ውስጤ፡፡ ይህ ፍቅር የመሰለኝ ስሜት፡ ውሎ አድሮ ተራ ፍላጎት ሆኖ ቢገኝስ? እላለሁ ለራሴ፡፡ ስልቹ ነኝ፡፡ተንሰፍስፌ የገዛሁት ልብስ ሳምንት ሳይሞላው ሊሰለቸኝ ገና ተማሪ እያለሁ የወደድኳቸው፤ በፍቅራቸው የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ ያልኩላቸው ሴቶች፤ በቀረብኳቸው የወራት ዕድሜ ዓይናቸውን ማየት ሲያስጠላኝ ራሴን ታዝቤዋለሁ፡፡ ምርጫዬን አላምነውም ብቻዬን ብወድቅ ብነሳ የራሴ ጉዳይ ነው ሐኑንን ፣ይችን ንጹህ ነፍስ ምንም የማታውቅ የዋህ ልጅ ይዣት የሕይወት ማዕበል ውስጥ መግባት እፈራለሁ፡፡ ግን እልቻልኩም፡፡ መዓበሉ ራሱ ወደ እሷ ገፋኝ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ፣ ሐኑን እቤቴ መጣችና፣ እያወራን ድንገት(አምልጦኝ መሆን አለበት ) “ሐኑን ላገባሽ እፈልጋለሁም"አልኳት፡፡ እወድሻለሁ አላልኳትም፡፡ አፈቅርሻለሁ አይደለም ያልኳት፡፡ "ላገባሽ እፈልጋለሁ!" አንድም ነገር ሳትናገር ፀጉሯ ላይ ጣል ያደረገችው ክንብንቧ ጫፍ ላይ የተንጠለጠሉ ክሮችን እያፍተለተለች ቆየች፡፡ ጣቶቿን አያቸዋለሁ፡፡ ክንብንቧ ጫፍ ላይ የተንጠለጠሉ ክሮችን እያፍተለተለች ቆየች ጣቶቿን አያቸዋለሁ።ጫፎቻቸው እንደቲማቲም የቀሉ፣ ስትዘቀዝቃቸው የሚንጠባጠቡ የደም ጤዛዎች ይመሳስላሉ ውብ ጣቶች! አስቀይሚያት ይሆን ብዬ ስለፈራሁ፤ ቀረብ አልኳትና በሁለት እጆቼ ጉንጮቿን ይዤ ቀና አደረኳት፡፡ እንባዋ በንጹህ ቀይ ቆዳዋ ላይ ኮለል ብሎ ፈሰሰ።ቃል አልተነፈሰችም አልተነፈሰችም፡፡ በለስላሳ እጇ ጉንጯ ላይ ያረፈ እጄን ያዘችኝ፡፡ትኩስና ለስላሳ መዳፏ ልክ እንደ ከንፈር የልቧን ሐሳብ የሚያወራ ይመስል ነበር፡፡ጥብቅ አድርጋ ያዘችኝ፤ እናም አንድ ነገር ብቻ ተናገረች "እውነትህን ነው? እኔን ታገባኛለህ?” "እዎ” መልሳ አቀረቀረች፡፡ እጇ ግን እጄን እንደያዘ ነበር፡፡ይኼ ቃሌ እስካሁንም እንደ እሳት ጅራፍ ራሴን ይገርፈኛል፡፡ወንዳዊ ማንነቴ በደመነፍስ የፈጠረው ክፉ ማጭበርበር ነበር። ልምዱ ኑሮኝ አልነበረም፡፡ እንዲያው እንዲህና እንዲያ ልበላት ብዬ ቃል ቀምሬም አልነበረም፡፡ከየት እንደመጣ ባላውቀውም እእምሮዬ አጠቃላይ ሁኔታወችን በፍጥነት ደምሮና ቀንሶ ሐኑን ምን እንደምትፈልግ ገብቶት ነበር። አፍቅራ እዚህ መኖር አልነበረም ፍላጎቷ፡፡ ከዚህ በጠቆረ ትዝታ ከጠቆረ ግቢ ብን ብላ መውጣት ነበር መሻቷ ልክ በውሃ በተከበበ ደሴት ላይ ተከባ መውጫ ላጣች ነፍስ፣ራሴን ከዚህ መውጫ ጀልባ ነኝ ብዬ አቀረብኩላት፤ ማቄን ጨርቄን ሳትል ጀልባዋ ላይ ወጣች!! እጇ ትንሽ የተንቀጠቀጠ መሰለኝ... ወይስ የእኔ ነው!? ከዚህ ቀን በኋላ ሐኑንና እኔ በፍቅር ከነፍን፡፡ ግን ፍቅር ነው ወይ እላለሁ፣ ራሴን አላምነውም፡፡ የአባቷ እግር ከቤት ከወጣ የሐኑን እግር እኔ በር ላይ ነው፡፡ ፍቅር እንደ እሳተ ገሞራ ነው- የተረጋጋውን ምድር፣በሰላም ለዘመናት ተኮፍሶ የኖረን የአለት ተራራ ሽቅብ ፈነቃቅሎት ሲወጣ፣ ብናኝና ጭሱ አካባቢውን ይሸፍነዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ገሞራ የፈነዳበት ምድር ወደነበረበት ተፈጥሮው አይመለስም:: እዚያ ግቢ የዚያን ጊዜ የሆነው እንደዚያ ነበር፡፡ የፍቅር ገሞራው ሲፈነዳ፣ ብናኙ የሐኑንን ፊት ሸፈነው፡፡ረጋ ያለችው ልጅ፣ የምትይዝ የምትጨብጠውን አጣች፡፡ ብናኙ ፈገግታ ሆኖ ፊቷን ሸፈነው…ብናኙ የመሻት ነበልባሉን ወደቤቴ ልኮ አለት ብቸኝነቴን አቀለጠው፡፡ የሐዘን ደመና ከውብ ፊቷ ላይ ተገፎ እንደጥዋት ፀሐይ ውብ ፈገግታ ሲረጭ ግቢውን እሳት ሞላው፣ደግሞ ግቢውን ውሃ ሞላው ግቢው በረሃ ሆነ ደግሞም ግቢዉ የኤደን ገነት ሆነ፣ በአንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ሆነ፡፡ በዚህ ፍንዳታ ውስጥ ተረጋግተው ጫታቸውን የሚቅሙት አባቷ፤ "ልጅ ትንሽ አትሞክርም?" ይሉኛል ጫታቸውን እያሳዩኝ፡፡ “በዚህ ላይ ጫት ተጨምሮበት” እላለሁ በውስጤ፡፡ አለመታመንኮ ነው ሰው ግቢ ገብቶ የሰው ሴት ልጅ ያውም ያመኑት የአንድን ትልቅ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ነው፣ ራሱን የገዛ ሰው ነው ያሉትን ሰው … ግን ደግሞ ቦታና ጊዜ፣ ሥራና ደረጃ፣ ፍቅር ፊት ምን ጉልበት አላቸው? ዋናው ጥያቄ ይኼ እብደት ፍቅር ነው ወይ ነው? ራሴን አላምነውም! ሐኑን ጋር ዓይኖቻችን ተንሰፍስፈው ይፈላለጋሉ፡፡ ግድቡን እንደጣሰ ጎርፍ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ነበር፡፡ አንዳንዴ አባቷ እቤት እያሉ ጭምር ድንገት እቤቴ ትመጣለች ፡፡ "ኧረ አባባ" እላለሁ በጭንቀት ድምፄን ቀንሸ፡፡ "እየሰገደ ነው" ትለኛለች፡፡ ከዛ እቅፌ ውስጥ ናት፡፡ "ኧረ አባባ" እላለሁ "የውጭ ስልክ እያወራ ነው" ትላለች፡፡ ይሉኝ ነካክቼ እንደ አልኮል ያስከራትን ፍቅር በምን ላረጋጋው? ዓይኗንም ልቧንም የሠወረው ፍቅር፣ሁለታችንንም አባቷ ዓይን ላይ ሊጥለን እያዳፋ የሚነዳ ደራሽ ጎርፍ ሆነብኝ፡፡ ፈጣን ነበር_ሁሉም ነገር በጣም ፈጣን እየተጨነቅሁ እሰማታለሁ፡፡ እያሰብኩ በደመነፍስ እጓዛለሁ፡፡ አንዳንዴ ሌሊት ትደውልልኛለች፡፡ ፍቅር ከጊዜ ሥርዓት ያፈነገጠ ስሜት መሆኑ የገባኝ ያን ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ከዛ በፊት ያልገባኝ ነገር የገባኝ ያኔ ነበር፤ ብዙ ከዛ በፊት ገብቶኛል ያልኩት ነገር የጠፋብኝም ያኔ ነበር፡፡ የመኝታ ቤቷ መስኮት እና የሳሎኔ መስኮት ትይዩ ስለሆነ መጋረጃችንን ሰብስበን ዝም ብለን እንተያያለን ... እስር ቤት ያሉ ነፍሶች ነበር የምንመስለው፡፡ እነዚያ ሌሊቶች መቼም የሚረሱኝ አይደሉም አንድ ምሽት ደረቅና ሞቃታማዋ ድሬዳዋ፣በድንገተኛ ዶፍ ዝናብ ተጥለቀለቀች፡፡ የድሬደዋ ሰማይ ግፏን አፍና እንደኖረች ሴት፣ ድንገት ነው አስፈሪ ዶፉን እንደ እንባ የሚዘረግፈው፡፡ ዝናቡ ከሰማይ ብቻ ሳይሆን፤ከምድርም ይፈልቅ ይመስል፣ ከምኔው ምድሩ በጎርፍ እንደሚጥለቀለቅ ይገርመኛል፡፡ የዚያን ቀን ዝናቡ ሌሊቱን ሙሉ አላቋረጠም፡፡ በየመኻሉ ሰማዩን ሰንጥቆ አካባቢውን በብርሃን የሚያጥለቀልቅ የመብረቅ ብልጭታ የመስኮቴን መጋረጃ እያለፈ ቤቴን በብርሃን ይሞለዋል፡፡ በተደጋጋሚ ወገግ ይላል፡፡ ምን እንደገፋኝ እንጃ ፣ተነስቼ የመስኮት መጋረጃዬን ሰበሰብኩት፡፡ ሐኑን ልክ የተቀጣጠርን ይመስል መጋረጃዋን ስብስባ ውብ ጉርድ ፎቶ ግራፍ መስላ መስኮቱ ጋ ቆማ ነበር …
Hammasini ko'rsatish...
የሚመስለኝ፡፡አስረኛ ክፍል ላይ የትምህርት ነገር በቃኝ ብላ፣ ቤት ውስጥ ነበር የምትውለው፡፡ አባቷም ከቤት እንድትወጣ አይፈልጉም ፡፡ "አላህ እንዲህ ያለልክ አሳምሮ ኸልቆብኝ በገባች በወጣች ቁጥር ይሄ ባለጌ ወንድ ሁሉ እየተከተለ አስቸገራት፡ አቦ ከዚህ ሁሉ ብትተወውስ ብየ፣ ይኼው እቤት ነው ውሎዋ_አላህ ደጉን ኢማን ያለውን ሰው እስኪወፍቃት” ምከንያታቸው ይኼ ብቻ አልነበረም፡፡ የራሳቸው ልጆች አንድ ነገር ያደርጓታል ብለው ይፈራሉ፡፡ እኔም በኋላ ሳውቃቸው ልጆቹ አያደርጉም የሚባሉ ዓይነት አልነበሩም፡፡ ሐኑን ጋር ቀስ በቀስ ተላመድን፡፡ እንዲያውም ቡና ከማመላለስ ባለፈ፣ አንዳንዴ ኣባቷ ሳይኖሩ እኔ ቤት ትመጣና ስንጫወት ቆይተን ትሄዳለች፡፡ ረጋ ያለ አነጋገሯ አንዳች ጊዜን የማቆም ኃይል ያለው ይመስለኛል፡፡ በተፈጥሮዬ ተኝቼ እንኳን ሐሳቤ የማያርፍ እዚያና እዚህ የምዛብር ሰው ነኝ፡፡ ፊልም እንኳን ከፍቼ አንድ ቀን መጨረሻውን አይቼ አላውቅም የሚያንቀዠቅዥኝ ነገር አለ፡፡ ሐኑን ጋር ስሆን ግን አንዳች የመረጋጋት ስሜት ይሰፍንብኛል፡፡ ጥልቅ ዕረፍት ውስጥ ነፍሴ ትዋኛለች ፡፡ይኼንንም ፍቅር ነው ብየ ነበር:: እሷም ብትሆን እንደወደደችኝ ገብቶኝ ነበር፡፡ በእፍረቷ፣ አንዳንዴ ደግሞ እያመለጣት በምትናገራቸው ቃላት፡፡ ስንቆይ፣ አንዱን የቤቴን ቁልፍ ወስዳ፣ በሌለሁበት ቤቴን አዘጋጅታልኝ ትሄዳለች፡፡ ሁልጊዜ አልጋየ የሚያሰክር ሽቶ ተረጭበት ሳገኘው፣ ነፍሴ ሐሤት ታደርጋለት በድሬዳዋ ቆይታዬ ሐሳቤ ሁሉ ሁለት ነገሮች አይዘልም ሐኑንና ስራዬን ክፉኛ እየወደድኳት ነበር፡፡ ከሥራ ስወጣ ወደ ገነት የምሄድ እስኪመስለኝ ድረስ ልቤ በደስታ ትዘላለች፡፡ ቁልቁለት ላይ እንደሚሮጥ ሰው፣ ራሴን ልቆጣጠርና ልቆም ስታገል፣ ግን ግፊቱ ሲያንደረድረኝ ይሰማኛል ፡፡ አንድ ቀን ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ግን... ይቀጥላል.... ለአስተያየታችሁ @absalattt16 #join_and_share @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire
Hammasini ko'rsatish...
✨✨ ሐኑን ✨✨ ክፍል 4⃣ ባየሁት ቁጥር የዓለም መጨረሻ የደረሰ የሚመስለኝ ችኩል ሥራ አሰኪያጅ ወደ ቢሮው ጠራኝና እንዲህ ሲል መርዶ ይሁን የምሥራች ግራ ያጋባኝን ዱብ ዕዳ አፈረጠው፡፡ "እ..ያው እንደሚታወቀው፣ አዲስ አበባና ወደዚህ ወደ ሰሜኑ ያሉ ቅርንጫፎቻችን ሥራችንን ካሰብነው በላይ እያስኬዱልን ነው፡፡ ይሁንና፣ ድሬዳዋ የከፈትነው ቅርንጫፍ በየዓመቱ ችግር ብቻ ነው የሚያተርፈው፤ ሰውየውም ከሠራተኞቹ ጋር መግባባት አልቻለም፣ እና ማኔጅመንቱ ትላንት በነበረው ስብሰባ፣ ጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግሮበት አንድ ውሳኔ አሳልፏል” ካለ በኋላ የስልኩን እጀታ አንስቶ ወደ እኔ እየተመለከተ፣ “ምን ይምጣልህ?” አለኝ : “ምንም እልፈልግም” አልኩ በአክብሮት፡፡ እኔ እንደሆንኩ ለወሬው ነበር የቸኮልኩት። ኃላፊየ ግን ያልኩትን ወደጎን ትቶ፣ “ሁለት ቡና አምጡልን!” ብሎ አዘዘና ወደጉዳዩ ገባ፡፡በረዥሙ ስለሁኔታው ሲያብራራ ቆይቶ... "እና እንደነገርኩህ ማኔጅመንቱ ድሬደዋ ላለው ቅርንጫፍ ቢሮ መፍትሔ ብሎ ያሰበው፤እዛ ያለውን ሰው በማንሳት፣ ጠንካራና 'ኮሚትድ' የሆነ ሥራ አስኪያጅ መመደብ ነው::ለቦታው የሚመጥን ሰው ስናነሳና ስንጥል ቆይተን ….በመጨረሻ…” ቡና እንድታመጣ የታዘዘችው ልጅ ድንገት በሩን ከፍታ ገባችና ቡናውን በየፊታችን አቅርባልን ወጣች፡፡ "ምንም አልፈልግም" ያልኩት ሰውዬ ኃላፊዬ በግድ ያዘዘልኝን ጥቁር ቡና፣ ገና ከመቅረቡ አንስቼ ፉት አልኩና እያጣጣምኩ ወሬውን እስከሚቀጥል በጉጉት ጠበቅሁ። ጆሮዬ በዚያች ሰዓት፣ ሞያሌ ድንበር ላይ መርፌ ብትወድቅ ይሰማ ነበር፡፡ "እ -ምንም እንኳ ለቦታው አንዳንድ የማታሟላቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ ቀስ በቀስ እንደምታሟላ በማስብ፣በመጨረሻ አንተን እዚያ ብራንች ላይ ሥራ አስኪያጅ አድርገን እንድንመድብህ ወስነናል፡፡ በዚህ አስራ አምስት ቀን ውስጥ ወደቦታው ስለምትንቀሳቀስ፣ አንዳንድ ነገሮችን አመቻች፡፡ ቤት እና ትራንስፖርት እዚያው ያሉ ሰዎች ያመቻቹልሃል፡፡ አንተ በዋናነት ቢቻል በዚህ ስድስት ወር፣ ቢበዛ በቀጣዩ እንድ ዓመት በቢሮው ላይ የሚታይ ለውጥ በማምጣት ላይ ብቻ አተኩር፡፡መልካም ሥራ!" ብሎ እሱው የጀመረውን እራሱ ጨረሰና፤ የሥጋ ድልዳል ያደለበውን ሰፊ መዳፉን ለሰላምታ ዘረጋልኝ ፈቃዴን መጠየቅ የለ፣ ምን የምትለው ነገር አለ ብሎ አስተያየት እንድሰጥ ዕድል መስጠት የለ፤ በቃ ወታደራዊ ትእዛዝ፣ “ተነስና ሂድ !!" መቼስ ወፍራም እንጀራ ጣት ከነሚያስቆረጥም ወጡ፤ ያውም ከአራትና ከአምስት ዓመት በኋላ እንኳን ከማልደርስበት እድገት ጋር ጭነው፣ ቼ ሊሉኝ ሽምጥ ጋልቦ ድሬዳዋ ላይ ከማረፍ ሌላ፣ ምን አማራጭ ነበረኝ? ወደ ኋላ የሚጎትት፣ ሚስት የለኝ ድስት .. ደግ ዘመን! ።።።።።።።።።።።።።።።።። ድሬዳዋ ግሪክ ሰፈር የሚባል ሰፊ የሀብታም ግቢ ውስጥ፣ የራሱ ገላ መታጠቢያ ከፍልና፣ መጸዳጃ ቤት ያለው ባለ ሁለት ክፍል ቤት ከነዕቃው ተዘጋጅቶልኝ ነበር፡፡ ቤቱ የአንድ ባለሀብት ቤት ሲሆን፡ የምሠራበት ባንክ የተከራየው ሕንፃ ጭምር የሰውዬው ነበር፡፡ እንዲሁ ስጠረጥር ባለሀብቱ ቤታቸውን ያከራዩት፣የኪራይ ብር አስጨንቋቸው ሳይሆን ሕንፃቸውን ተከራይቶ በየዓመቱ ጠቀም ያለ ብር የሚከፍላቸውን ባንክ ሥራ አስኪያጅ፣ ቤተኛ ለማድረግ ይመስለኛል፡፡ “ባለቤቱ ይኼ ናቸው” ቢሉኝ ገረመኝ፡፡ ሽርጥ ያገለደሙ ተራ ሰንደል ጫማ ያጠለቁ ከጉያቸው ሥር ምንጊዜም በላስቲክ የተጠቀለለ ጫት የማይጠፉ፣ ጺማቸው በርስሬ መስሎ የቀላ ሽማግሌ፤ የዚያ ሁሉ ሀብት ባለቤት አልመስል ብለውኝ ነበር፡፡ ሰውዬው ለምንም ነገር ግድ የላቸውም፡፡ ሁልጊዜ ከሰዓት በኋላ ጫታቸውን ይዘው በረንዳቸው ላይ ይፈርሹና፤ ጓደኞቻቸው ከመጡ ከጓደኞቻቸው ጋር፣ ከሌሉም ብቻቸውን ቁጭ ብለው፣የምታምር ልጃቸው አንዴ ቡና አንዴ ሻይ እያቀረበችላቸው፣ ሱዳንኛ ዘፈን ከፍተው ጫታቸውን እየቃሙ ይውላሉ፡፡ያንን በሚያክል ግቢ ውስጥ፣ ከአንዲት ቆንጆ ሴት ልጃቸው ጋር ብቻቸውን ነው የሚኖሩት፡፡ መጀመሪያ አካባቢ አብሪያቸው ጫት እንድቅም በተደጋጋሚ ይጋብዙኝ ነበር፡፡ "ልጅ …ጫት አትቅምም ?” ይሉኛል፡፡ “ኤልቅምም አባባ!” “ምነው? በሰላም!?” ሳቄ ይቀድመኛል፡፡በኋላ እንደማልቅም ገብቷቸው፣ ማጨናነቁን ትተው፣እቤት ከዋልኩ ኮካ-ኮላና ለውዝ ይልካልኛል፡፡ ቡናና ሻይ ሲፈላ ደግሞ ልጃቸውን፣ “ሐኑን ነይ ለዚህ ልጅ ውሰጅለት” ይሏታል፡፡ ልጃቸው ሐኑን ከፀጉሯ ላይ እየተንሸራተተ የሚያስቸግራትን መሸፈኛ አሥር ጊዜ ወደፊት፣ወደግንባሯ ሳብ እያደረገች፣ ቡና አልያም ሻይ በሚያምር ሰርቪስ ትሪ ይዛልኝ ትመጣለች፡፡ ቢነኳት የምትፈርጥ የምትመስል ቆንጆ ልጅ ነች፡፡ ገና በር ላይ በአክብሮት ጫማዋን አውልቃ ስትገባ፣ ውብ እግሮቿ ላይ ዓይኔ እያረፈ "ኧረ ጫማሽን አታውልቂ" እላታለሁ፡፡ ምንግዜም ግን ሳታወልቅ አትገባም፡፡ በእርግጥ በዕድሜ ከእኔ ታንሳለች:: በስምንት ወይም በዘጠኝ ዓመት ሳልበልጣት አልቀርም፡፡ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ካየኋት ቀን ጀምሮ ባየኋት ቁጥር፣ ለመቀራረብ የሚገፋኝን ፍላጎቴን መቋቋም አልቻልኩም። ቀስ በቀስ ማውራት ስንጀምር፣ የበለጠ ቀረብኳት፡፡ ብዙ አታወራም ፈገግ ብላ ትልልቅ ዓይኖቿን እያንከባለለች ዝም ትላለች፡፡ ምንም ቃል ሳይወጣት ብዙ ያወራን የሚመስለኝ ነገር ነበር፡፡ ሐኑን፣ ከሌላ ሴት የወለዷት የሰውዬው ዘጠነኛ ልጅ ናት፡፡ ስምንት የወለደችላቸውን ሚሰታቸውን አስቀምጠው፣ያውም እቤታቸው ሠራተኛ ሆና ከተቀጠረች ሴት ነበር ሐኑንን የወለዱት፡፡ ይኼ ነገር በልጆቻቸውም ሆነ በሚስታቸው በቀላሉ የሚታለፍ ነገር አልሆነም፡፡ ትዳራቸውን ሊበትነው ደረሰ፡፡ በመጨረሻ ሠራተኛዋን ከነልጇ ቤት ተከራይተው በድብቅ እስቀመጡ፡፡ ወሬው ግን የሚደበቅ አልሆነም፡፡ ባልና ሚስት ከዚያ በኋላ በሰበብ አስባቡ መጋጨት ሆነ ሥራቸው :: በተለይ ሚስት ከልጆቻቸው ጋር አብረው ሰውዬውን መቆሚያ መቀመጫ አሳጧቸው፡፡ሰውየው ደግሞ ንዝንዝ አይወዱም፡፡ ለአንድ ሰዓት ሰላም በልዋጩ ያላቸውን ሀብት ቢከፍሉ የማይቆጫቸው ዓይነት ሰው ናቸው፡፡ በስልክ እንኳን እያውሩ ትንሽ ንዝንዝ ቢጤ ከሆነባቸው “አቦ! ልቃምበት እንግዲህ አትነጅሱኝ" ብለው ጥርቅም ያደርጉና ስልካቸውን ወዳያ ይወረውሩታል፡፡ሐኑን አንስታ እለመሰበሩን ካረጋገጠች በኋላ እቤት ታስቀምጥላቸዋለች፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ሚስታቸውን ቁጭ አደረጉና፤ "እንግዲህ አጠፋሁ፤ የተተፋ ምራቅ መልሶ አይዋጥም፣ አንቺም ጧት ማታ እያነሳሽ በሰበቡ ከምትነዘንዥኝ፣ ከልጆቼም ጋር ከፉ ደግ ከምነጋገር የወደድሽውን ንብረት ያዥና ከልጆችሽ ጋር ኑሪ፣ በቃ ፈትቼሻለሁ" ብለው ቤቱን ለሚስታቸውና ለልጆቻቸው ትተው ወጡ፡፡ ከቤት ሲወጡ የያዙት ነገር ቢኖር፥ የጀመሯት በላስቲክ የተጠቀለለች ጫት ብቻ ነበር፡፡በሽማግሌ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ቢለመኑ ቢደረጉ እምቢ አሉ፡፡ብዙም አልቆዩም ሐኑን እናት ጋ ጠቅልለው ገቡ ፡፡ የልጆቻቸው እናት ይሄን ሲስሙ፣ ድሮም ጤና አልነበራቸዉም ውሎና አዳራቸው ሆስፒታል ሆነ፡፡በመጨረሻም እንዲቹ እንደተብሰለሰሉ አረፉ፡፡ ልጆቻቸው የእናታቸው ገዳይ የሐኑን እናት እንደሆነች ነው የሚያምኑት፡፡ ጦሱ ምንም ለማታውቀው ሐኑንም ተርፎ ልክ የሌለው ኃይለኛ ጥላቻ ነበር ያለባቸው፤ለዓይናቸው ሊያዩዋት አይፈልጉም፡፡ቃል በቃል "የገረድ ልጅ እናታችንን ያስገደለች" ይሏታል፡፡ የእርሷም እናት እኔ እዚያ ቤት ከመግባቴ ከአምስት ዓመት በፊት ነበር የሞተችው፡፡ ለዚያም ይሆናል ሁሉጊዜም በቆንጆ ፊቷ ላይ እንደ ስስ ደመና የሐዘን ስሜት የማያንዣብብ
Hammasini ko'rsatish...
ለልጅህ ስትል ትዳርህን አታከብርም!? ብላ፣ ቤቱ እስኪናወጥ ጮኸች፡፡ ገና የሁለት ወር ልጅ ምነው ተወልዶ ሰበብ ላደረኩት ብላ በጉጉት የጠበቀችው ነው የሚመስለው፡፡ “ልጅህ” ስትል፣ አቅፋ ጡት የምታጠባውን ልጅ ስለናጠችው፣ መጥባቱን አቁሞ ጭርር ብሎ አለቀሰ: ለማጥባት ሳይሆን አፉን ለማዘጋት በሚመስል ሁኔታ የጡቷን ጫፍ አፉ ውስጥ በእልህ ወተፈችበት ሲያለቅስ ወደውስጥ የሳበውን አየር እንኳን ሳያወጣው አጉረምርሞ ዝም አለ፡፡ አፍና የገደለችው ነበር የመሰለኝ፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ ይኼን የተናገረችው ባለቤቴ ሔራን ናት ብዬ መቀበል ተሳነኝ። ዝም ብዬ አየኋት! ዙሪያዋን የተዝረከረከውን ማቀፊያ ልብስ፣ጡጦ እና ምናምን ሁሉ በቁጣ በታትናው ልጃችንን አቅፋ እያለቀሰች ወደ መኝታ ቤት ገባችና የቤቱ መሠረት እስኪነቃነቅ ቀሩን በእግሯ ወደኋላዋ ወርውራ ዘጋችው፡፡ጓ...ሳሎን መሃል ተገትሬ ቤቱን ቃኘሁት፡ችግር ችግር ሸተተኝ፡፡ አደጋ አደጋ፡፡ ቤታችን ከግድግዳ ሳይሆን ከአራት ቋሚ ችግሮች የተሠራ የመብረቅ ጣሪያ ከላይ የተደፋበት መሰለኝ፡፡ የዘራሁት ኃጢያት ማቆጥቆጥ እንደጀመረ ገባኝ፡፡ ለመሆኑ ሐኑን ብር በባንክ ብልክላትና ሁለተኛ አልመጣም ብላት (አልላትም እንጂ ) ምን ይሰማት ይሆን? ሐኑን…. ሐኑን ሐኑን ሐኑን …የቀጠፍኳት አበባ መዓዛዎ አስክሮኝ ውበቷ አስክሮኝ ጨብጫት ኖሬ ወደቀልቤ ስመለስ እና የጨበጥኩበትን መዳፌን ስዘረጋ፣ እፍኝ ሙሉ እሾህ ተሰከስኮባት፣ ያውም የሚያንገበግብ እና የሚመረቅዝ ቁስል ፈጥሮ አገኘሁት፡፡ አላርፍ ያለ መዳፍ ፡፡ ከስድስት ዓመት በፊት የምሠራበት ባንክ ወደ ድሬደዋ መድቦ ሲልከኝ፡ግማሽ ልቤ አዲስ በተሰጠኝ እድገት እና ደመወዝ ሲደሰት፣ ግማሽ ልቤ ደግሞ ከአዲስ አበባ በመራቄ ደብቶት ነበር፡፡ ባየሁት ቁጥር የዓለም መጨረሻ የደረሰ የሚመስለኝ ችኩል ሥራ አሰኪያጅ ወደ ቢሮው ጠራኝና እንዲህ ሲል መርዶ ይሁን የምሥራች ግራ ያጋባኝን ዱብ ዕዳ አፈረጠው፡፡ ይቀጥላል Join and share @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire @hiwet_nat_memhire
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.