uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Thinking Beings

Thinking Beings

Yopiq kanal

Theology| Philosophy| Science

Ko'proq ko'rsatish
247
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
Bye fam for a few months, “...Human beings are simply more resourceful this way in action, speech, and thought. If someone has a private perception, he immediately starts going around and looking until he finds somebody he can show it to and have it corroborated...” On my rereading of Plato’s Protagoras (Complete works of Plato), page 779. ፕሌቶ በዚህ ጽሑፉ እንደነገረን በግል ለማንበብ ምሞክራቸውንና ጥያቄም ሆነ አግራሞት የፈጠሩብኝን ስለጥፍ ነበር! ቢያንስ ቢያንስ ጽሑፎቹን በማንበብ ስለተባበራችሁኝ አመሰግናለሁ! ርግጥ ሌሎች ቢዚ ሚያደርጉኝ ነገሮች ቢኖሩም ቴሌግራም ላይ የጻፍኩትን ስለጥፍ ደስ እያለኝ ነው! ያው እናንተ የማወራውን አታውቁም ማለት ሳይሆን ከናንተ ጋር ሼር ማድረግ ስለፈለኩ ነው! ዐዳዲስ ዕይታንም ለማግኘት! በድጋሚ አመሰግናለሁ! ለጊዜው አንዳንድ ነገሮች ስለተደራረቡብኝ ሶሻል ሚድያ ለመቀነስና ኖቲፋይ የተደረኩትን ግድ የሆነን ነገር ብቻ ለመመለስና ለመገደብ ወስኛለሁ! Bye bye.

Some comment from my logic teacher about my book... Good Karma,😁 My former logic teacher has got some lesson from her ex stu
Some comment from my logic teacher about my book... Good Karma,😁 My former logic teacher has got some lesson from her ex student😁 This is awesome!

Who said Yes መጽሐፌን ለመገምገምና blurb ለመጻፍ በቀጣዩ መጽሐፍ እስከ አሁን ለግምገማና blurb ለማጻፍ የዐራት ሰዎችን ፈቃድ አግኝቻለሁ! 1) ዐሌክስ ዘጸዓት (የእከይ ጣጣ ጸሐፊ) "...አይደለም የአንድ መጽሐፍ አባሪ መኾን ቀርቶ ሙሉ መጽሐፍ ኾኖ ቢመጣ ራሱ ከጎንኽ ለመቆም ዝግጁ ነኝ!!" 2) ዶ/ር ፋሲል መርዓዊ (የዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ዲፓርትመንት መሪ) "Betam des yilegnal" 3) የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ (phone call በቴሌግራም) 4) ዳዊት በዛብህ (የሕግ ፍልስፍና፣ የማስረዳት ሸክም...ደራሲ)፣ "Its my pleasure" ...ቀጣይ የምጠይቃቸውና በጊዜ ለማግኘት ያሰብኳቸው ሰዎች ዶ/ር ዳኛቸው (የፍልስፍና አስተማሪ) አባ ዳንዔል (ፕሮፌሰር) ዶ/ር ጥላዬ (የጥላዬን ቀደምኩት ደራሲ) ዶ/ር ምሕረት ደበበ ዶ/ር ዳዊት ወ/አገኝ እና ሌሎች ....a matter of time.

የፕላንቲንጋ ሌጋሲ! “...Christianity is on the move, and on the move in philosophy, as well as in other areas of intellectual life... ” Alvin Plantinga, Advice to Christian Philosophers. ዶ/ር ዳኛቸው በፍልስምና መጽሐፍ ላይ በተናገሩት መሠረት ቃል በቃል ባላስታውሰውም የሐይማኖት ሙግት 3 ለ2 እየመራ ነው ብለው ነበር! (የ3 ለ2 አባባል ግልጽ ባይሆንም የቲይዝም ሙግት በፍልስፍናው ዓለም ትልቅ ቦታን አግኞቷል! በተለይ በአንግሎ-አሜሪካን ካልቸር ዙሪያ) ታላቁ ፈላስፋ ፕሮፌሰር አንቶኒ ፍሊው የቲይዝም ሙግቱ ከኤቲዝም ይልቅ እንደሚያሳምን በስተመጨረሻ ገልጸዋል... ታላቁ ኤቲስት ፕሮፌሰር ኩይንተን ስሚዝ ትምህርት በተለይ በፍልስፍናው ዙሪያ ዲሴኩላራይዝ እየተደረገ እንዳለ መስክሯል... በፕላንቲንጋ ፕሮጀክት ሊፈስ የተዘጋጀው ወይም መፍሰስ የጀመረው የፍልስፍና ውሃ ጅረት ክርስትና ለመላለሙ ተስፋ እንደሆነ እና ብቸኛ የመዳኛ (የጤነኛ እውቀት) መንገድ ሆኖ መቅረቡ መታየት ከጀመረ ሰነባብቷል... እዚህ ዐገር ውስጥ የአልን (Plantingaን) ፕሮጀክት ማስተዋወቅ ለብዙ ነገሮች ፈውስን ያደርጋል ብዬ አምናለሁ!

Most religious people and politicians live and walk by Sunk Cost Fallacy!

4 years ago in 2021 I posted this,👇 እኔ ለሃገሬ በብዕሬ!!! Personally I prefer classical apologetics than any other sorts...(as far as I read a book on logic, this method somehow differs me from Dr. Tesfaye Robele ’s reformed( non- inferential belief) approach...😁 Within five years I'll write a book on God's existence. And the book will comprise or I'll discuss these salient features: introduction to logic, philosophers attitude toward God from pre-socratics to post-modern era and their limitations, arguments for God's existence; Cosmological argument, fine-tuning argument, moral argument, argument from the resurrection of Jesus Christ, and ontological argument, criticism on Ethiopian philosophical books, and eventually I'll assess the ramifications of Christian theism and atheistic worldview. Moreover, the book may helps us to think seriously about our faith in God and to show the weaknesses of other worldviews. I need to do something for the kingdom of God and also to set a bit contribution for my dear country, Ethiopia

የኢየሱስ ፍቅር! ለፕሌቶም ለአርስቶትልም ትንግርት የሆነ፣ በዚህ ዓለም ሰዎች ሊኖር አይችልም ብለው የደመደሙት የፍቅር ዐይነት አለ! እሱን ኢየሱስ ኖሮት አሳይቶናል! አጋፔ የሚባል ፍቅር ነው! ደካማውን፣ ጠላትን፣ የታመመን...የሚወደድበት ፍቅር! እነ ፕሌቶ የሚያውቁት ፍቅር እኩያ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚገለጸውን ነው! እንደ ኢየሱስ ዐይነት ፍቅር ለነሱ የማይጠብቁት ነው! በሁሉ ነገር ብቁ የሆነ ተራ ሥጋ ለባሾችንና ደካሞችን (አሕዛብን፣ ሕጻናትን፣ ሴቶችን፣ ሰማሪያውያንን...) የሚወድ! በሕይወት ቢኖሩ exception to the rule ሆኖባቸው አንዳንድ ድርሳኖቻቸውን revise ያደርጉት ነበር ብዬ አስባለሁ! ምክንያቱም ሰዎቹ unexamined life is not worth living በሚለው የታላቁ መሪያቸው ሶቅራጠስ ተከታዮች ናቸውና!

በኔ በኩል ከዚህ በኋላ የሚወጡት መጻሕፍት ሦስት መልክ ነው ያላቸው! 1) ታሪክ፣ 2) የባለ ታሪኮቹ መሠረታዊ ነጥብ፣ እና 3) የእነሱ (ሥራዎቻቸው) ተጽእኖ በታሪክ ውስጥ። ለታሪክ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ሄግል፣ ኮፕለስተን፣ ዎልፍሃርት ፓነንበርግና ባሕሩ ዘውዴ ምሳሌዬ ናቸው! ሌላው ባለታሪኮቹ የጦር ሆነ የአገር መሪዎች ሳይሆኑ የዐሳብ ሰዎች ናቸው! እነሱ በጣም ያስደምሙኛልና! Plantinga, Sophists, Plato, Aristotle, Augustine, Anselm, Descartes, Iguale, ...

አማኝ፣ አማኝ ነኝ ብሎ አእምሮን ዘግቶ መንቀሳቀስ ከማያምነው በላይ ጉዳቱ ብዙ ነው!

Fame ችግር የሚፈጥረው ለ bad or በ bad purpose የመጣ ከሆነ ነው! ሥራችን famous ሊያደርገን ይችላል! ያ ሥራ ግን ጤነኛ መሆን አለበት! አለያም ዝነኝነቱ በተጣመመ መንገድ፣ ለተጣመመ ዓላማ የሚውል ነው የሚሆነው!

Lecture or teaching በዐዲሱ ዓመት በ24/1/2018 ስለ ምክንያትና እምነት አስተምራለሁ! Nice opportunity.

በተስፋ ብሮድካስቲንግ ቲቪና በዩቲዩብ ቻነል ከMy fellow hosts ጋር ያደረኩት ቃለ መጠይቅ በቅርቡ ይለቀቃል!
በተስፋ ብሮድካስቲንግ ቲቪና በዩቲዩብ ቻነል ከMy fellow hosts ጋር ያደረኩት ቃለ መጠይቅ በቅርቡ ይለቀቃል!

Happy new year y’all

2018 ላይ እንደ እርሱ ፈቃድ volume one አንድ መጽሐፍ ይታተማል! ይመረቃል! ፐብሊክ ሌክቸር ይኖራል!

መልካም በሆነ ነገር ሁሉ ከፍ በይ!
መልካም በሆነ ነገር ሁሉ ከፍ በይ!

Imperfect guy, ራሱን ለመለወጥ እየታገለ ያለ ሰው መስማት ትልቅነት ነው! ቲዮሎጂ ልበል እንጂ ገና ለማወቅ እየሞከርኩ ነው...ሎጂክ ስልም ብዙ ስለ ምሳሳት የራሴንም ሕይወት ኦርደር ለማስያዝ ስለምሞክር ነው...ባያዝ ስልም እንደ አብዛኛው ሰው የተሳሰርኩበት ደካማ አስተሳሰብ ስላለኝ እሱንም ለማጥራት ስለምፈልግ ነው...ብቻ አጉል ትሕትና አይደለም ሕይወቴ ብዙ ትግል ያለበት ነው...ሪሊፍ ማገኝበት አንዱ መንገድ ጽሑፍ ስለሆነ ነው...እና አመሰግናለሁ ስል ከዚህም የተነሣ ነው! ከኔ በብዙ ምትሻሉ እዚህ ግሩፕ ውስጥ አላችሁ...

part one, በፒንክ ተለቀለሙት መልስ p.21 ነገሮች መሆን እንደሚገባቸው (how things should n shouldn't be...or ought n ought not be...) ወይም እንዴት መሆን እንደሚገባቸው ያስኬዳል። በዋናነት ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን የምንለይበት መሆኑን ለማሳየት ነው! p.23 ግልጽ አለመሆንን፣ አሻሚነትን፣ ሸዋጅነትን በግልጽ የሚያሳይ ስለሆነ ኢ መደበኛ እንጂ formal የሚመስል እንደሆነ አላይም። p.24 ከላይ እንደተብራራው ይህ ክፍል ስለ ሎጂክ ያሉትን የተዛቡ አመለካከቶች ለማጥራት እየሞከረ ነው። አንዱ የተዛባ አመለካከት ደግሞ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ምክንያታዊ ስላልሆኑ ሎጂክ ሎጂክ እያሉ ማውራት አያስፈልግም የሚል ዐሳብ ያለው ነው። ታዲያ በዚህ ጊዜ እንደ መልስ ምት የተሰጠው ምሳሌ ሥነ ምግባር የሌላቸው ሰዎች ስላሉ ተብሎ እነሱን መገደብ ሆነ መቆጣጠር (በማስተማር፣ በማረም፣ በመቅጣት...) የሚችሉት ተቋማት ይዘጉ ወይ (ልክ እንደ አብያተ ክርስቲያናትና ፖሊስ ጣቢያዎች ያሉ)? ሰዎች ምክንያታዊ አይደሉም ስለተባለ ሎጂካዊ አስተሳሰብና ትምህርት መቆም አለበት የሚል ሙግት አዘል ጥያቄ ነው። p.25 "ለዚህም"ን ያስገባሁት (if...then ዐረፍተ ነገር ስለሆነ ነው፤ የመጀመሪያውን ዐረፍተ ነገር በደንብ ይገልጽልናል። በሌላ ቦታ (አስፈላጊ ሲሆን) "ከዚያ" ብዬ ተክቼዋለሁ).. p.28 የቅራኔ ዐልባ ሕግ ግልጽ አይደለም? I think you defined it right after you pose this Q. So የቱ ወይም ምኑ ነው ግልጽ ያልሆነው? p.29 ሁለት the same የሆኑ ዐረፍተ ነገሮች። በተመሳሳይ ጊዜ፤ በተመሳሳይ ሁኔታ (sense) ቢገለጹ ይጋጫሉ። ለምሳሌ፣ እኔ ሁለት ዐረፍተ ነገር ስሰጥ 1) እኔ አለሁ። 2) እኔ የለሁም። ሁለቱ የሚጋጩ ዐረፍተ ነገሮች ናቸው። p.37 እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ለሰዎች በምናውለው (corporal bodies) የምንልካው Being አይደለም። p.38 ቀድሞ ዐዋቂው እግዚአብሔር ነው። p.41 ላይ ያለውን የቬን ዲያግራም ማብራሪያ ስሕተት አለው (my mistake. And ሌላም አንባቢ በቀላሉ spot አድርጎታል) p.63 የሚያመለክተው syllogism (3 sentences (6 if...then clauses), 3 terms (ሥርዎች) (major, minor, n middle)) መሆኑን ለማሳየት ነው። p.87 O&I የሚቃረኑ particulars ናቸው። so የአንዱ ውሸት መሆኑ የሌላውን እውነት መሆን ሊያሳይ ይችላል። p.106 ሁለቱን ዐረፍተ ነገሮች በእና ካጣመረ ደግሞ አንዱ የአንዱ ተጻራሪ ሊሆን የሚችልን ዐረፍተ ነገር እንዲሁ መግለጽ ከባድ ነው። የእግዚአብሔር መኖር ለተዓምራት መኖርና ለሌሎች ነገሮች ማብራሪያ ይሰጣል። ስለዚህ፣ አንዲ Deist ተነሥቶ እግዚአብሔር አለ እና ተዓምር የለም ቢል በቅርጽም በትርጉምም ትክክል ያልሆነ ዐረፍተ ነገር ነው እንደሰጠን የምንረዳው። በቅርጽ ሲባል በአዎንታ የጀመረውን ዐረፍተ ነገር በአሉታ መዝጋቱ ወይም የመጀመሪያውን ዐረፍተ ነገር የማያሳይ ዐረፍተ ነገር ሊያሳይ በሚችል አያያዥ ቃል መግለጹ ነው። በእውነታው ደግሞ፣ እርሱ ካለ ተዓምር የመኖር probabilityው ሰፊ ነውና የማይመስል (unlikely) ዐዋጅ ነው... p.106 የአጣማሪ የያዘውን ክፍል (not the conjunctions) p. 107 I would say insert the examples in the symbols. p.114 I think the thought of the line would be obvious. እና ከባለቤቱ መሆኑ ተገልጿል። Sorites የመጀመሪያውን ስንቀጥል ባለቤቱ ላይ ነው ጥገኝነታችን... p. 122 ድነዋል እንጂ ድኗል የሚል አይመስለኝም። እሱም የመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ላይ ያለ ነው። p. 148 ያው ከዋናው መጽሐፍ ያገኙሁት ያቺን ምሳሌ ነው። ጥያቄዎች ስላሉት እሱን መሥራት ያግዛል። p. 151 እዚህ ጋር Special Pleading የሚያመለክተው ሰውየው (የውሸት ዐሳብን የሚያቀርበው) የወደደውን ነገር ለማቅረብና ከዋናው ዐሳብ ይልቅ የሚደረድረው (የሚስበው) ዴክ ብቻ እንዲታሰብለት እንደሚፈልግ ለማሳየት ነው። p. 162 የመጀመሪያ Being ስለሆነ የብዙ ነገር መንስኤ ነው። ስለ መጀመሪያ መንስኤ የሚነሱ ነገሮች ደግሞ እርሱ ያለበት category ነው። p. 164 "ሁልጊዜም" የሚለው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሲታሰብ ሊታሰብ የሚገባውን ቀጣዩ ዐረፍተ መሆኑን ነው። ከሱ በፊት ያለውን መልስ አዘል ጥያቄ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚያስቡት ይገልጻልና (ያሳያልና)። ...ይቀጥላል።

https://youtu.be/Ds_I4RisOHM?si=defvtwNVgpApzI9q I like this discussion. Enjoy it.

Such a reader. Big applause.😍👏
+2
Such a reader. Big applause.😍👏

ፖድካስት ነገ በ My Fellow የተስፋ ፖድካስት ፕሮግራም ላይ እቀርባለሁ። ስለ መጽሐፌ፣ የፌሎሺፕ ቆይታ፣ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለውን ፖቴንሻል ትሬትና ኦፖርቹኒቲ፣ እና ሌሎችም ዐሳቦች ላይ እንወያያለን። ቀረጻውም ሲለቀቅ will share በዚህ ቻነል...