ሰዋስው ☘☘☘☘
Kanalga Telegram’da o‘tish
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Ko'proq ko'rsatish1 161
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለቆዝሞስ ወድምያኖስ ወአላንዴዎስ ወአቢሞስ ወአብራንዮስ ወእሞሙ ቴውዳዳ ምልእት መንፈስ"። ትርጉም፦ በመንፈስ የተመላች ለእናታቸው ለቴውዳዳ፣ ለቆዝሞስ ለድምያኖስ ለአላዴዎስ፣ ለአቢሞስና አብራንዮስ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም እብል ለደቂቀ ቴውዳዳ ዘተንዕዱ። በበአስማቲሆሙ ለለአሐዱ። ዘኮነቶሙ ምኅባአ ለእግዚአብሔር በፈቃዱ። ማሕፀነ ምድር አምሳለ ሕፃናት ዘይትወለዱ። ለእሳት ግሩም እስከ ሐልቀ ነዱ"። ትርጉም፦ የሚያስፈራ እሳት ነበልባሉ እስኪያልቅ ድረስ በሚወለዱ ሕፃናት አምሳል የምድር ማሕፀን በእግዚአብሔር ፈቃዱ መሸሸጊያን የኾነቻቸው ለእያንዳንዳቸው የተከበሩ ለኾኑ ለቴውዳዳ ልጆች በየስማቸው ሰላም፡እላለኊ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 22።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 9፥10-18 "ወእንዘ ይረፍቁ ውስተ ቤት" - "በቤቱም፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፥እንሆ፥ብዙ፡ቀራጮችና፡ኀጢአተኛዎች፡መጥተው፡ከኢየሱስና፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ተቀመጡ። ፈሪሳውያንም፡አይተው፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦መምህራችኹ፡ከቀራጮችና፡ከኃጢአተኛዎች፡ጋራ፡ዐብሮ፡ስለ፡ምን፡ይበላል?አሏቸው። ኢየሱስም፡ሰምቶ፦ሕመምተኛዎች፡እንጂ፡ባለጤናዎች፡ባለመድኀኒት፡አያስፈልጋቸውም፤ ነገር፡ግን፥ሄዳችሁ፦ምሕረትን፡እወዳለሁ፡መሥዋዕትንም፡አይደለም፡ያለው፡ምን፡እንደ፡ሆነ፡ተማሩ፤ኀጢአተኛዎችን፡ወደ፡ንስሓ፡እንጂ፡ጻድቃንን፡ልጠራ፡አልመጣሁምና፡አላቸው። በዚያን፡ጊዜ፡የዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ወደ፡እርሱ፡ቀርበው፦እኛና፡ፈሪሳውያን፥ብዙ፡ጊዜ፡
የምንጦመው፥ደቀ፡መዛሙርትህ፡ግን፡የማይጦሙት፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ሚዜዎች፡ሙሽራው፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሳለ፡ሊያዝኑ፡ይችላሉን፧ነገር፡ግን፡ሙሽራው፡ከነርሱ፡የሚወሰድበት፡ወራት፡ይመጣል፥በዚያ፡ጊዜም፡ይጦማሉ። በአረጀ፡ልብስ፡ዐዲስ፡ዕራፊ፡የሚያኖር፡የለም፤መጣፊያው፡ልብሱን፡ይቦጭቀዋልና፥መቀደዱም፡የባሰ፡ይሆናል። በአረጀ፡አቍማዳ፡ዐዲስ፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያኖር፡የለም፤ ቢደረግ፡ግን፥አቍማዳው፡ይፈነዳል፥የወይን፡ጠጁም፡ይፈሳል፡አቍማዳውም፡ይጠፋል፤ነገር፡ግን፥ዐዲሱን፡የወይን፡ጠጅ፡በዐዲስ፡አቍማዳ፡ያኖረዋል፥ሁለቱም፡ይጠባበቃሉ። ይህንም፡ሲነግራቸው፥አንድ፡መኰንን፡መጥቶ፦ልጄ፡አሁን፡ሞተች፤ነገር፡ግን፥መጥተኽ፡እጅህን፡
ጫንባት፥በሕይወትም፡ትኖራለች፡እያለ፡ሰገደለት።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
22/3/2015 ዓ.ም (፳፪/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ።
በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ።
ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን፡፡ መዝ 78:10
🕯 ትርጉም
አሕዛብ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ።
የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል።
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሉቃ. 15:25-30 "ወወልዱሰ ዘይልሕቅ" - "ታላቁ፡ልጁ፡በዕርሻ፡ነበረ፤መጥቶም፡ወደ፡ቤት፡በቀረበ፡ጊዜ፡የመሰንቆና፡የዘፈን፡ድምፅ፡ሰማ፤ ከብላቴናዎችም፡አንዱን፡ጠርቶ፦ይህ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ጠየቀ። እርሱም፦ወንድምህ፡መጥቷልና፥በደኅና፡ስላገኘው፥አባትኽ፡የሰባውን፡ፊሪዳ፡ዐረደለት፡አለው። ተቈጣም፡ሊገባም፡አልወደደም፤አባቱም፡ወጥቶ፡ለመነው። እርሱ፡ግን፡መልሶ፡አባቱን፦እንሆ፥ይህን፡ያኽል፡ዓመት፡እንደ፡ባሪያ፡ተገዝቼልሃለሁ፡ከትእዛዝህም፡ከቶ፡አልተላለፍሁም፤ለኔም፡ከወዳጆቼ፡ጋራ፡ደስ፡እንዲለኝ፡አንድ፡ጥቦት፡ስንኳ፡አልሰጠኸኝም፤ ነገር፡ግን፥ገንዘብህን፡ከጋለሞታዎች፡ጋራ፡በልቶ፡ይህ፡ልጅህ፡በመጣ፡ጊዜ፥የሰባውን፡ፊሪዳ፡ዐረድህለት፡አለው።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
22/3/2015 ዓ.ም (፳፪/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ኢይመውት ዘእንበለ ዘአሐዩ።
ወእነግር ግብሮ ለእግዚአብሔር።
ገሥዖሰ ገሠፀኒ እግዚአብሔር፡፡ መዝ. 117፥17
🕯 ትርጉም
አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ።
የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ በድዮማ ከተማ አረምያ ከምትባል አገር ለሆኑ ለቅዱሳን ለቆዝሞስና ለድምያኖስ ለወንድሞቻቸው ለአላድዮስ ፣ለአቢሞስ ፣ለአብራንዮስና ለእናታቸው ለቅድስት ቴውዳዳ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ቆዝሞስ ማኅበር ሰማዕታት ከሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ወንዶችን፣ ከአርባ ዘጠኝ ሴቶችና ከቀሌምንጦስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ ወንድሞቻቸው አንቲቆስ፣ ዮንዲኖስና አብራንዮስ እናታቸው ቅድስት ቴዌዳዳ፦ እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዌዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ድኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ። ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ።
❤ ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምዕመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም ንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው አጋግዮስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ።
❤ ቆዝሞስና ድምያኖስ በአገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደረሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እነርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበት ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ አስመጣቸውና አምስቱንም በመንኰራኵር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨምሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳቱን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው።
❤ መኰንኑም እነርሱን ማሰቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች። በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብለሸ ጮኸ "የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን?" የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት።
❤ ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 7፥1-5፣ ያዕ 1፥2-17፣ እና የሐዋ ሥራ 1,፥2-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥9-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜና። ለሁላችን ይሁንልን።
❤ የበቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ሊኩን ይጫኑት
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "ውስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ። ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን። ውስተ ኲሐቲሃ ሰቀልነ ዕንዚራቲነ # በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። በአዃያ ዛፎቿ ላይ መሰንቋቻችንን ሰቀልን"። መዝ 136፥1-2። በዘንድሮ ዓመት የኅዳር ጽዮን ማርያም በዓል 21/03/15 ዓ.ም በተፈጠረው ችግር በአኵሱም ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም ማክበር ባንችልም በእግዚአብሔር ፈቃድ በአዲስ ዓለም ርዕሰ አድባራት ዳግማዊ ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ የምዕራብ ኦሞና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርስቲ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፣ በርካታ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ እጅግ በጣም ብዙ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አከበርን ተመስገን። እናታች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከክብር ባለቤት ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አማልዳን ቀአሥራት አገሯን ኢትዮጵያን የተጀመረውን የሰላም ስምንንት ከፍጻሜ አድርሳልን በሚቀጥለው ዓመት በአኵስም ጽዮን ማርያም ለማክበር ሁላችንንም ታብቃን።
https://t.me/Eotcw
1 161
#ታቦተ_ሕጉ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕፅርት ወበመንፈስቅዱስ ክልልት
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር (፪)
የህግ ጽላቱ ለእግዚአብሔር በካህናትየታጠረች በመንፈስ ቅዱስም የተከለለች
ንጉሥሽ ጽዮን አይሸነፍም ለጠላት ሀገሪቱንም አይተዋት(፪)
https://t.me/Eotcw
1 161
#አክሊሎሙ
አክሊሎሙ ለሰማዕት ሲመቶሙ ለካህናት
ነያ ጽዮን መድኃኒት(፪)ኧኸ
የሰማዕታት አክሊላቸው የካህናት ሹመታቸው
ጽዮን ናት መድኃኒታቸው(፪) ኧኸ
https://t.me/Eotcw
1 161
#ሕዝበ_ኢትዮዽያ
ሕዝበ ኢትዮዽያ እለ ተወልዱ
በሕየ እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ልዑል
ሣረራ ውእቱ እግዚአብሔር
#ትርጉም፦
የኢትዮዽያ ሕዝብ ጽዮንን እናታችን ይላል በውስጧ ክርስቶስ ተወለደ የወለደችውም ፈጣሪዋን ነው።
https://t.me/Eotcw
1 161
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ
ማርያም እምነ ናስተበቁዓኪ
እምአርዌ ነዓዊ ተማ ፀነ ብኪ
በእንተ ሐና እምኪ
ወኢያቄም አቡኪ
ማኀበረነ ዮም/3/ ድንግል ባርኪ
ትርጉም
ሰላም ለአንቺ ይሁን ስግደትም ለአንቺ ይሁን
ማርያም እና ችን የመለኮት ዙፋን
ከኃይለኛ አውሬ የምትጠብቂን
ስለቅድስት ሐና ብለሽ ስለኢያቄም ኝህን
ማ በራችንን ድንግል ባርኪልን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
1 161
መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
#አዝ
ይጠሩሻል ካህናቱ
ንዒ ይሉሻል በሳታቱ
ለለመነሽ የማትቀሪ
በልቤ ውስጥ ፀንተሽ ኑሪ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ
መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ
ያዲስ ኪዳን ኪሩ የሆንሽ
ለምኚልን ካንዱ ልጅሽ
ርግብየ ሰናይትየ
ነይ ወደኔ ነይ ወልድየ
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ
#አዝ
ባለም መኖር ሰልችቶኛል
መልካም መስራት አቅቶኛል
እጄን ይዘሽ ድንግል ምሪኝ
አዛኚቷ አትለይኝ
የስጋና የነብስ ፈራጅ 3× ልጅሽ አይደለም ወይ
መሀረኒ ድንግል ወተሰሀለኒ በበዘመኑ
ለእመ መሀርከኒ 3× አንቲ ዘይኩነኒ መኑ
እበላለው ብዬ ማርያም
እመካለው ባንቺ አላፍርም
ካንቺ ወዴት እሄዳለው
ስምሽን ልጥራው እፅናናለው
ኮናኔ ስጋ ወነብስ 3× ወልድኪ ያኮኑ
ማሪኝ ድንግል ማርያም ይቅርም በይኝ በየዘመኑ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ እናቴ ሆይ ከማርሽኝ
ድንግል ሆይ ከማርሽኝ ልጅሽ አይፈርድብኝ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
1 161
#ማርያም ጽዮን
ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ(፪)
እዝራኒ በገዳም (፪)አመ ወዓለ ውዱቁ(፪)
ትርጉም፦የብርሃን የወረቅ መቅረዙ ማርያም
እዝራ በገዳም ወድቆ በዋለ( ገዳም ገብቶ በዋለ)
እንኳን አደረሳችሁ
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ዘካርያስ ርእየ
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኩለንተሃ
ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አእጹቀ ዘይት
ነቢያት ይትፌሥሑ ሐዋርያት ይትሐሰዮ
በውስቴታ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሀ
#ትርጉም፡- በቀኟም በግራዋም የዘይት ጫፍ ያላት የመብራት መቅረዝ
ዘካርያስ አየ ነቢያትና ሐዋርያት
በውስጧ ደስ ይላቸዋል
ዳዊትም በውስጧ ያመሰግናል
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ታቦተ እንተ ውስቴታ
ታቦተ እንተ ውስቴታ ኦሪት እንተ ውስቴታ×2
ውቱረ ይከድንዋ በወርቅ×2 ይከድንዋ×2
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
★ https://t.me/Eotcw
1 161
#ገበዘ አክሱም
ሀሌ ሀሌ ሉያ ወሪድየ ገበዘ አክሱም
ለቤተክርስትያን ርኢክዋ አይመርክዋ አፍቀርዋ ለቤተክርስትያን
ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Eotcw
